ከዚህ ቀጥሎ የምታደምጡት ዝግጅት በኮንሶ ምሁራን የመወያያ መድረክ የቀረበ ሲሆን "ትምህርት፣ ቴክኖሎጂና የማህበረሰብ ንቃተ ህሊና" በሚል ርዕስ የተደረጉ ውይይቶች ሁለተኛውና የውይይት ርዕሱ የመግቢያ አሳብ የሚቀርብበት ነው:: በዚህ ክፍልና በሌሎች ቀጣይ ሁለት የፕሮግራሙ ክፍሎች "ኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂና ትምህርት" በሚል ንዑስ ርዕስ ውይይቶችን ወደ እናንተ እናደርሳለን:: በዚህም መሠረት ይህ ክፍል የውይይቱ መግቢያ አሳብ የሚቀርብበት ነው::