ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌንና አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ከእስር ለመፈታት የግንቦት ሰባት አባል መሆናቸውን አምነው የይቅርታ ፎርም ላይ እንዲፈርሙ መጠየቃቸውንና ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። የአቶ ክንፈሚካኤል ደበበ እናት ወ/ሮ ብዕዓት ኃይለጊዮርጊስ፤ "እኛም ቤተሰቦቹ ሆነ እርሱ ብዙ መሰዋትነት ከፍለናል። ስለዚህ ይቅርታ ባለመጠየቃቸው በጣም ደስ ብሎኛል።" ብለዋል።
ከመንግሥት ሰራተኞችና ከሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች እያገኙት ያለው ድጋፍ የሕዝቡ ትግል አንድ እርምጃ ወደ ፊት መሄዱን እንደሚያሳይ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ተናግረዋል፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
በባሌ ዞን በመዳ ወላቡ ወረዳ "መዳ" በተባለች ቀበሌ የገበያ ቦታ ላይ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በተፈጠረ ግጭት የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ከሟቾቹ ውስጥም አንዲት የስምንት ልጆች እና አንዲት የሰባት ልጆች እናት ወተት በመሸጥ ላይ እያሉ በመከላከያ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባርና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ለሦስት ቀናት ይቆያል የተባለ ውይይት ትናንት ዕሁድ ተጀምሯል። በኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና በኦብነግ መካከል ንግግሩ የተጀመረው ተለይቶ ባልተገለፀ የኬንያ ከተማ ነው።