ከእግዚአብሔር ጋር ትክክል ካልሆንን የእግዚአብሔር ፊት ይሰወርብናል፣ ምህረቱ ብዙ ርህሩህና መልካም አባት በመሆኑ ለክፉዎች እንኳን ጸሃይን ያወጣል ሆኖም ግን እንደልባችን ማንንነት የሚገናኘን አምላክ ነው፣ እግዚአብሔር ቃሉና መንፈሱ ባለበት ቦታ ሁሉ ይገኛል ደግሞም ይናገራል፣ መኖሩን ግን ለማወቅና ድምጹን ለመስማት የልባችን ማንነት ይወስነዋል፣ መንገዳችን ግራ ከሆነ እንደመንገዳችን በግራ ሆኖ እናገኘዋለን፣ ልባችን ከቀና ደግሞ መልካምና ቸር ሆኖልን እናገኘዋለን::