ከአብርሃም እስከ ዳዊት አስራ አራት ትውልድ አለ፣ ከዚያም እስከ እየሱስ ድርስ ሄዷል፣ አሁንም ሰዎችን ሁሉ በክርስቶስ የማዳን ስራ፣ የመንግስቱ ስራ እየሄደ ነው። ይህ የእግዚአብሔር ሃሳብ ከትውልድ ወደትውልድ እየተላለፈ የመጣው፣ የእለቱን ሳይሆን የዘላለሙን በተመለከቱ ስዎች ነው። ነገሮችን በራሳችን እይታ ማየት ከጀመርን፣ የመለኮትን ሃሳብ አናሳልፍም፣ እየተራመደ ያለውን የእግዚአብሔርን ስራ ያስቆማል። ማለትም፣ ጌታ በራሱ መንገድ ስራውን ይቀጥላል ግን በኛ አልፎ አይሄድም፣ የጌታንም ስራ በትውልዳችን አናይም ይህ ደግሞ ትልቅ ጉዳት ነው።