የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ስንፈልግ የሚይስፈልገን ነገር ሁሉ ይጨመርልናል። እግዚአብሔር ልጆቹን የሚባርክበት የተለያዩ ቁልፎች አሉ፣ ከብዙ የበረከት ቁልፎች አንዱ፣ የእግዚአብሔር የአምላካችንን ስራ በመተባበር እርሱ በሚፈልገው ሁኔታ መስራት ሲሆን፣ ለዚህ ስራ ስንነሳሳ፣ ልባችንን ከመንገዳችን እንድናነሳና የእግዚአብሔርን ስራ ለማደናቀፍ፣ ሰይጣን መካሪ ይገዛብናል፣ በሌለንበት ነገር ክስ ያዘጋጅብናል፣ ሌሎችም ብዙ የተለያዩ ፈተናዎችን በመንገዳችን ያቆማል። በዚህ ሁሉ ግን እኛ ለእግዚአብሔር ስራ ጨክነን ስንቆም፣ እግዚአብሔር፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ የሚል ድምጹን ያሰማናል።