ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብና ከእግዚአብሔር ጋር ስንሆን ሁልጊዜ አሜንና ሐሌሉያ የምንልበትን መልስ ብቻ ላንቀበል እንችላለን። ሊሆን የሚገባው ባይሆን፣ በጥያቄያችን ላይ ጥያቄ ቢደራረብብን፣ ጌታ ከባሕሪው ተካፋዮች ሊያደርገንና ዕይታችንን ከእግዚአብሔር ዕይታ ጋር ሊያስማማ ነውና፣ እኛ ግን እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ እንዳለና እውነተኛ ፈራጅ መሆኑን ተረድተን፣ እግዚአብሔር በኛ የጀመረውን ስራ እንዲጨርስ፣ በፊቱ ዝም ብለን እርሱን ብቻ ከምስጋና ጋር መጠበቅ ይኖርብናል።