እግዚአብሔር እርሱ መልካም እረኛ ነው:: ሰለዚህ ለእያንዳንዳችን ግድ ሰለሚለው በሰው ሁሉ ዘንድ የተጣልንና የተተውን በሆንንና ብቸኝነት በተሰማን ጊዜ ከጎናችን የሚቆም ካለንበት ሊያወጣን ሊፈውሰንና እደገና ጨለማችንን ሊያበራ ተስፋችንንም ሊያድስ የታመነ ጌታ ነው:: ጨለማው የበራለት እስራቱም የተፈታለትና ተስፋው የታደሰለት እርሱ ኢየሱስ ወደ ህይወቱ ገብቷልና ጌታን ለመከተል አይቸገርም:: ደግሞም ህያው ምስክር ይሆናል:: በዚህ መልዕክት ይህንን በስፋት እንማራለን::