ሰው ይብዛም ይነስ የኔ የሚለው የሚቆጥረው የሚኮራበት ልቡንም የሚጥልበት ደግሞም የሚመካበት ነገር አለው:: እውቀት ሀብትና ውበት እንዲሁም ዘመድ የቅርብ የምንለው ሰው ወዘተ... በአንድም በሌላ ሰው ከሚመካባቸው ጥቂቶቹ ናቸው:: እነዚህ ሁሉ ግን እንድ ቀን የሚክዱን ደግሞም ተስፋ የማይደረግባቸው ይሆናሉ:: በጊዜውም አለጊዜውም የማየከዳና የማያሳፍር ፅኑ መመኪያ ግን እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ብቻ ነው:: እግዚአብሔርን በተመካንበት በዛ ሰላም ይኖረናል:: ተስፋችንም እውን ይሆናል::መፅናናት ሀይልና ብርታትም ይሆንልናል::