ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ ሲመላለስ የመስቀል ጉዞ ነበር የተጓዘው:: የመስቀል ጉዞ ደግሞ በመጀመሪያ ራስን ዝቅ ማድረግን ይጠይቃል:: ራሱን ባዶ አድርጎ በስጋው ወራት የተመላለሰበት የጌታ ህይወትና ኑሮ ዛሬ እኛ የእርሱ ተከታዮች ልንኖረው የሚገባውን ኑሮ ያሳያል:: እውነተኛ ደቀመዝሙር ኢየስሱን በቃልና በስራ በህይወቱ የሚያሳይ ሲሆን የመስቀሉንም ጉዞ ሲጓዝ ብቻውን ሳይሆን ነገር ግን ታላቅ ተስፋን ከሰጠው አሸናፊ ከሆነው ጌታ ጋር በመሆን ሌሎችን ደቀመዝሙር ለማድረግ የሚተጋ ነው::