አማኝ እግዚአብሔርን ለመምሰል ደግሞም እግዚአብሔርን እንደ ቃሉ ወደ ማወቅ ማንነት ያድግ ዘንድ የሚሰራበት መንገድ አንዱ የእግዚአብሔር መዘግየት ነው:: በእግዚአብሔር መዘግየት ውስጥ ትክክለኛው ማንነትችን ደግሞም ያለን መንፈሳዊ ደረጃና መረዳት ደገለጣል:: በእግዚአብሔር መዘግየት ውስጥ ትዕግስትንና ትህትናን ዝቅ ማለትን እንማራለን:: *** በእግዚአብሔር መዘግየት ውስጥ በምስጋና ሆነው በትዕግስት የሚጠብቁ እነርሱ በፀጋው ውስጥ ናቸው:: ነገር ግን ከምስጋና ርቀው በማጉረምረም ያሉ እነርሱ ከፀጋው የወጡ ናቸው::