የመንፈሳዊ ህይወታችን የአድማስ ስፋት ሰውን ሁሉ በክርስቶስ ፍቅር የማየታችንና የመቀበላችን መጠን ህሊናችን ኀፁህ የሆነውን ያህል ነው:: ነፃ ባልወጣንበትና ባልተፈታንበት በዛ የክርስቶስ ህይወት ወደ ሌሎች አያልፍም:: በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ያዘንበት አልፎም የተጎዳንበት ህሊናችንም ያልነፃበት ጊዜዎች ሁኔታዎችና ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ:: ይሁን እንጀ በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር የተቀበልነው ፀጋ ይህን ሁሉ ልናልፍ በወጥመዱም እንዳንያዝ እንድናሸንፍ የሚያበቃ ፀጋ ነው:: - ህሊናው ንፁህ የሆነና የተፈታ እርሱ እጆቹን ወደ እግዚአብሔር ለማንሳት ደግሞም ለመፀለይና ለማምለክ ነፃ ነው::