ሰው ትክክለኛ ማንነቱን ሊያይና ራሱን ሊያዋርድ የክርሽቶስን ህይወት እንዳይኖር መሰናክል የሆነውን በውስጡ ያለውን እርም ማስወገድ የሚችለው የእግዚአብሔር ብርሃን በበራለት መጠንና በብርሃኑ ውስጥ ራሱን ባየበት ልክ ነው:: ይህ ሲሆን ከማይበቃ ማንነታችን ውስጥ በእርሱ ፀጋ የሚበቃውን አዲሱ ማንነታችን ይወጣል:: አዲሱ ሰው የሚታዘዝ ነው:: አካሄዱ ከእግዚአብሔር ጋር ነውና:: የእርሱ ክብር ሞገስና በረከትም ያለው በመታዘዝ ውስጥ ነወ:: እንደ እግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው አዲሱ ሰው የጌታ ብርሃን የበራለት እርሱ ስጋን ይከለክላል:: ሰራውንና ሀሳቡን ይቃወማል:: የመግዛት ሀቅሙም የጨምራል:: በመከራ ውስጥም ለማለፍ በዚህም ውስጥ እንኳ ለመታዘዝ የሚበረታ ነው