አማኝ በህይወት ጉዞው ውስጥ ፍፁም በእግዚአብሔር ሥልጣን ስር መሆኑና መገዛቱ የሚገለጠው በመታዘዝ ነው:: መታዘዝ በሌለበት ህይወት አያልፍም:: የጌታ ኢየሱስ ህይወት ወደ ሚያምኑት ሁሉ ያለፈው ከመታዘዙ የተነሳ ነው እስከ መስቀል ሞት የታዘዘ ሆኗል :: እግዚአብሔር የተናገረው የበረከት ቃሎች ወደ ህይወታችን የሚያልፈው እለት እለት በታዘዝንበት በኩል ነው:: በአለመታዘዝ ምክንያት ወደ ህይወታችን ከመፍሰስ የቆመውን በረከት በፆምና በፀሎት ማግኝት አንችልም:: የእኛን መታዘዝ የሚጠይቁ ናቸውና በአለመታዘዝ ምክንያት እስራኤል በምድረ በዳ እንደቀሩ ሁሉ እኛም በዚህ መንገድ እንዳንሄድ ህያው ቃሉ ይመክረናል:: - ለጌታ የመገዛታችን ፍሬ መታዘዛችን ነው::