በኢየሱስ ክርስቶስ በማዳኑና በፀጋው የተካፈልነው ህይወትና ኑሮ ታላቅ ብድራት ያለው በእውነትና በፅድቅ ደግሞም በጥንቃቄ ልንኖረው ልንጠብቀውም የሚገባ ነው:: በክርስትና እምነት ውስጥ ካሉት ታላላቅ እውነቶች አምስቱን በዚህ ትምህርት እንማራለን:-- - መዳናችን እጅግ ታላቅ ነው:: ከሞት ወደ ህይወት ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የመጣንበት:: - የጌታ እረኝነት:: ነፍሱን ሰለ በጎቹ አሳልፎ የሰጠ መልከምና ታላቅ እረኛ:: - የጌታ የሊቀ ካህንነት ሥራ:: ፍፁም የሆነ የዘላለም ሊቀካህን:: - ታላቅ ብድራት:: ጌታን በማመን የምናገኘው ብድራት እጅግ ታላቅ ነው:: - ታላቅ መጋደል:: በነፃ የተቀበልነው የክርስትና ህይወት ታላቅ መጋደል ያለበት መፅናትንም የሚጠይቅ ነው:: ክርስቶስ የሰራውና እኛም የእርሱ የሆንበት ነገረ እጅግ ታላቅ ነውና ከዚህ ሌላ ተመክህት አይኖረንም:: ሰለዚህ ትምክህታችንን አንጥልም ብድራቱ እጅግ የላቀ ነውና::