የእግዚአብሔር ድምፅ ህይወት ነው:: የሚቀድስ የሚያጠራ ደግሞም የሚፈውስ ድምፅ:: ብዙ ግራ የሚያጋቡ የሚያውኩና የሚያስቱ ድምፆች እጅግ በበዙበት በዚህ ዘመን የጠራውን የጌታን ድምፅ ማግኘት መስማትም ዋና ነገር ነው:: እግዚአብሔር በአንድም በሌላ ነገር ይናገራል::የተናገረውም ደግሞ ይሆናል:: የሚከለክልም የለም:: ጌታ በእኛ ሁኔታ ሲናገር ምንም እንኳ በብዙ ፈተና ውስጥ ብንሆንም እንኳ ድምፁ ለህይወት ለፈውስና ለበረከት ነፃ ለማውጣት ይመጣል::