እግዚአብሔር ለላቀ ክብር የለያቸው ሌዋውያን በምድረ ርስት የተካፈሉት ርስታችን የሚሉት መሬት አልነበረም:: እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ርስታችሁ እኔ ነኝ::ብሏቸዋልና ለጌታ ለመሆን ከወሰንበት ቀንና ሰአት ጀምሮ የእኛ እድል ፈንታ ርስታችን አርሱ ራሱ ጌታ ነው:: በዚህ ምድር ተስፋ የምናደርገውና የምንናፍቀው ነገር የለንም:: ይሁን እንጂ ይሄና ያ ጎደለብኝ ብለን የምናማርር የምናንጎራጉርም ከሆነ የርስታችንን ክብርና ታላቅነት አጥርተን እንዳላየን ያመለክታል:: አማኝ በዚህ ምድር እንደ መፃተኛ ሊኖር ደግሞም ተስፋው የከበና የታመነ እንደሆነ በቃልና በኑሮ እየመሰከረ ሊኖር የተገባ ነው::