ሰው ፈቃዱና ሀሳቡ ስጋዊ ወደ ሆነውና ወደዚህ አለም አመፅ ባዘነበለ ጊዜ ለክፉው መጠቀሚያ ይሆናል:: በተቃራኒው ደግሞ ሰው ራሱን ቀድሶ እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለማስከበር ቀናውን ነገር ሲያስብ ለእግዚአብሔር የሚጠቅም የክብር ዕቃ ይሆናል:: ዳንኤልም አንዱ የእግዚአብሔር የክብር ዕቃ ነው:: በመሆኑም ከሩቅ ዘመን ሆኖ የዘመንን ፍፃሜ የሚገልጥ ሆኗል:: በዚህ ትምህርት ነገር ሁሉ ወደ ፍፃሜው እየፈጠና አሰቀድሞ የተነገረውም ሁሉ እየተፈፀመ መሆኑን እናያለን:: በዚህ ሁሉ ግን አሁንም ወንጌል የምስራች ነው::