እግዚአብሔር ፈቃዱን ደግሞም ክብሩን በቃሉ ይገልጣል::የእግዚአብሔር ቃል ለመምከር ለመገሰፀ ደግሞም ለመባረክ ወደ ሰው ይመጣል:: ከወረድንበት ጥልቅ ጉድጓድ ከተስፋ መቁረጥ ያወጣናል:: ለቃሉ በህይወታችን ሰፍራ እየሰጠን በመጣን መጠን የጌታ ብርሃን ወደ ህይወታችን ይበራል አማኝ በቦታው ሲገኝ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጉብኝት ይሆናል:: የእርሱ ጉብኝት ደግሞ ወደ ክብር ያወጣል: የህይወት መታደስ ይሆናል:: ጨለማው በብርሃን ይሞላል:: ልምላሜና በረከትም ይሆናል::