ትዳር ማለት መውሰድ እንዲሁም ደግሞ መወሰድ ማለት ነው:: ከፈጥረት መጀመሪያ አዳም ሄዋንን ከእግዚአብሔር እጅ ተቀብሎ እንደወሰዳት እነዲሁ ዛሬም አንዳችንን ለአንዳችን የሚሰጥ ትዳርን የሚሠራ እርሱ እግዚአብሔር ነው:: ሰለዚህ የተወሰደ አይመለስም:: ምክንያቱም ሁለቱ ተጣብቀዋልና:: አንድ ስጋ ሆነዋልና:: ትዳርን የሚጠብቀው ሁለቱም በመንፈሳዊ ህይወታቸው በሁለት እግራቸው የቆሙና በብርሃን ውስጥ መሆናቸው ነው:: *** - በግል ህይወቴ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት በፅድቅና በአውነት አለሁ ወይ ? - አልሆነችልኝም ወይም አልሆነልኝም ሳይሆን እኔ ሆኜለታለሁ ወይ ? ወይም ሆኜላታለሁ ወይ ? ብሎ መጠየቅ ከሁለቱ የትዳር አጋሮች ይጠበቃል: