እግዚአብሔር ያሰበልንን የአሁኑንም ሆነ ዘላለማዊውን እርስት ለመውረስ ቀዳሚው እኛ በጌታ ልንወረስ ያስፈልጋል:: በጌታ ያልተወረሰ ለእርሱ ያልተገዛ ማንነታችን ከጌታ ለምንቀበለው ማንኛውም ነገር እንቅፋት ይሆናል:: በአመታት መካከል እስራኤልን በድንቅ የመራ የረዳ ዛሬም ለህዝቡ ጌታ ታማኝ ነው:: ይመራል: ሞገስ ይሆናል: ይባርካል: ብርታትና ጉልበትም ይሆናል:: ከእኛ የሚጠበቀው ሙሉ በሙሉ ራስን ለፈቃዱ ማስገዛት ደግሞም ጌታ ለእኛ ያሰበልንን ማየት ነው::