የእግዚአብሔር ቃል ለአማኝ የህይወቱ መርህ ነው:: እለት እለት ለዚህ የህይወቱ መርህ ለሆነው ለእግዚአብሔር ቃል የሚታዘዝ ደግሞም ህይወቱ ያደረገ አማኝ እርሱ ጥልቅ በሆነ መሠረት ላይ ተመስርቷል:: ተስፋውም የፀና ነውው:: *** የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተን መታዘዝ በሆነልን ጊዜ በማንኛውም በሚያናውጥ ነገርና ሁኔታ ፀንተን እንድንቆም ዋነኛ ምክንያት እርሱ ነው::