የአማኝ መንፈሳዊ ሕይወት ከሚሰፋባቸው መንገዶች አንዱ ፀሎት ነው::ፀሎትም በእግዚአብሔር ቃል ነው:: የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ የእግዚአብሔርን ሀሳብ ፈቃዱንም ይገልፃል:: የእግዚአብሔር ቃል እነደሚያሳየንና ሸክም አድርጎ እንደሚሰጠን የማንፀልይ ከሆነ በዙሪያችን ካለው ከምንሰማውና ከምናየው ተነስተን ብቻ እነጨነቃለን:: ችግሮች የሚመሩን እንሆናለን:: በፀሎት ሕይወት እያደግን ስንሄድ በእግዚአብሔር በሆነው ፅድቅ ደግሞም እኛም መሆን ባለብን ግድ ወደሚለን ደረጃ እንመጣለን::