የእግዚአብሔር ሰዎች መውጣትና መግባታቸው የሚሰሩትና የሚናገሩትም በእግዚአብሔር ፈቃድ ቁጥጥር ውስጥ ራሳቸውን አሰገዝተው ሊሆን የተገባ ነው:: ሰሜትና ሁኔታ የሌሎችም ሰዎች ፈቃድ አይገዛቸውም:: ከፈቃዱ ቁጥጥር በወጣን ጊዜ የሚገዛን የስጋ የአለምና የኃጢአት ሀሳብ ነው:: በዛ ደግሞ ብዙ ኪሳራ ፍርሀትና ድንጋጤ ተሰፋ መቁረጥ ይሆናል:: *** የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይገልጣል:: ሰለዚህ ለቃሉ የተከፈተ ልብ ሊኖረን ይገባል:: ለዚህም ደግሞ የሚረዳ ፀጋ አለ::