አባትነት የጀመረው የሁሉ አባ ከሆነው ከእግዚአብሔር ነው:: አባት ተብሎ ሲጠራም ቸርነቱን ለጋስነቱን ተንከባካቢነቱንና ደራሽነቱን ይገልፃል:: ሰውም አባት ሲሆን ይህን በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው የአባትነት ባህርይ በጥቂቱም ቢሆን እንዲገለጥበት ነው:: አባት ለቤቱ መሪ ራስ ልጆቹም ደግሞ አባት ነው:: ስለዚህ የአንድ ቤት የመንፈሳዊነት ጣሪያው አባት ቤቱን ይዞ በእግዚአብሔርፊት በጸሎት በአምልኮ የመገኘቱን ያህል ነው:: እንዲሁም የቤቱ ሰላም ደግሞ የሚጠበቀው በነገሮች ሁሉ አባት ከሚኖረው የልብ ስፋት መጠንና ራሱነም ለመለወጥ ዝግጁና ፈቃደኛ የሆነው ያህል ነው:: *** በዚህ ትምህርት የአባትን በቤቱ ላይ ያለውን ድርሻና ከልጆቹም ጋር ሊኖረው የሚገባውን ግንኙነት በጥልቀት እንማራለን::