የእግዚአብሔርን ኤልሻዳይነት መመስከር መናገር የምንችለው አይናችን ተከፍቶ እርሱን ያየነውን ያህል ነው:: የልብን አይን የሚከፍት እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነው:: በስጋ አይን የምናየው የምንጠይቀውም ምድራዊ የሆኑ ለጊዜው የሆኑ ደግሞም የሚያልቁና የሚጠፉ ናቸው:: የልብ አይን ሲከፈት ግን ለአሁኑ ደግሞም ለወደፊት ለዘለአለም የሆነውን ሁሉ ነው:: እርምጃችንም በመሰለኝና በተሰማኝ ሳይሆን ተረድተንና አይተን እንራመዳለን:: *** የመጨረሻው ዘመን ትልቁ ችግር በጸሎት ያለመፅናት ነው:: በመቆየት በፀሎት ፀንቶ በመቆም የእግዚአብሔር ጉብኝት ይመጣል:: ማየት ይሆናል:: ወዳዘጋጀውም ህይወትና በረከት መግባት ይሆናል::