ጠላት ብዙዉን ጊዜ ሊያጠምደን የሚሞክረው እውነት ባልሆነ ነገር ግን እውነት በሚመስል ነገር ነው:: ስለዚህ ነው በነገሮች ላይ ወስነን አንድ እርምጃ ከመራመዳችን በፊት ልንመረመር ደግሞም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ ያለብን:: *** ጠላት ይሸነግላል አማኝ ግን የሚመራው በእግዚአብሔር መንፈስ ሰለሆነ አስቀድሞ የመነፈስ ቅዱስን ድምፅ በመስማት ነገሮችን ይመረምራል::