አማኝ በዚህ ምድር የሚኖረው ራሱን ላሰገዛለት ለጌታ ነው:: ለእግዚአብሔር መንግስት የመኖራችንም ፍሬ ከራሳችን ወጥተን ለሌላ ስንሆን ነው:: ለሌላው ለመሆንና የመንፈስን ፍሬ ለማፍራት ደግሞ ዋናውና ቀዳሚው የራስ ሸክም የሆነውን በጌታ ላይ መጣልና ከጭንቀት ከፍርሀት ነፃ መሆን ነው:: *** ለሌሎች መሆን አንዱ በእግዚአብሔር ፀጋ ታግዘን ዋጋ የምንከፍልበተና ጌታን የምናሳይበት ከራሳችንም ወጥተን ለተፈጠርንበት የእግዚአብሔር አላማ የምንኖርበትነው::