የአንድ መንፈሳዊ ሰው ጥንካሬ ወደፊት ሄዶ የእግዚአብሔርን ፀጋ መቀበሉ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የተቀበለውን መጠበቁ በተቀበለውም መገኘቱና መቆሙ ነው:: የተቀበለውን ፀጋ ለማሰጠበቅ ደግሞ ዋጋ ማስከፈሉ ግድ ነው:: በህይወታችን ምንም ያህል እናድርግ ምንም ያህል ፀጋ በህይወታችን ይገለጥ ህይወታችንን የመጠበቅ አቅማችን ያለው ራሳችንን ለእግዚአብሔር የሰጠነውን ያህል ነው:: ሰለዚህ ዕለት ዕለት ህይወታችንን እየመረመርን ለእግዚአብሔር ያልተሰጠውን ማንነታችንን ልናስገዛ ልንቀድስ ያስፈልጋል::