አግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ከራሱ ጋር አሰታርቆናል:: ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋው መቆረስ የጥሉን ግድግዳ ስላፈረሰ እዳችንም ሰለተከፈለ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አድርገናል:: ይህም የህይወት ሰላም በእኛ ዘንድ የሚጠበቀው በክርስቶስ ውስጥ በመሆን ነው:: *** ሰላም ህይወት ነው ሰላም ኑሮም ነው:: በክርስቶስ ውስጥ እስከሆን ደግሞም የምናከናውነውን ሁሉ በጌታ ፍቅር ወስጥ ሆነን እስካደረግን ድረስ:: በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ ጌታ ሰላማችን ነው::