የፅድቅና የህይወት ጉዳይ ጌታ በመስቀል ላይ ራሱን የሰጠበት ጉዳይ ስለሆነ በዚህ መደራደር ወይንም ይህን ተክቶ በህይወታችን ስፍራን የሚይዝ ሊኖር ፈፅሞ አይገባም:: እግዚአብሔር በፀጋው የሚገልፀው ወይም የሚሰራው የእኛን ህይወት ሳይሆን የሚያሳየው የፀጋውን ነገር የእግዚአብሔርን ሉዐላዊነትና ምህረት ነው የሚያሳየው:: *** በዘመናችን ደግሞም በዙሪያችን ያለውን ክፋት አሰራሩንም እያሰተዋልን በፅድቅ ልንነቃ ከኃጢአትና በደልም ልንርቅ ጊዜው ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው::