የሰው ህይወቱ በመፈለግ የተሞላ ነው:: መንፈሳዊውንም ሆነ ስጋዊውን እንፈልጋለን:: በህይወታችን ሳንፈልገው ያገኘነው መዳንን ብቻ ነው:: ጌታ ራሱ ፈልጎ አገኘን እንጂ:: ከዳንን በኃላ ግን ብዙ የምንፈልጋቸው ነገሮች አሉ:: የእግዚአብሔርም ቃል ፈልጉ ታገኛላችሁ ሲል መፈለግ አንዱ የህይወታችን ክፍል እንደሆነ ይጠቁማል:: *** የምንፈልገውን ሁሉ እንደምናገኝ ወይም እንደምንቀበል ዋስትና አልተሰጠንም ነገር ግን እግዚአብሔር እነደ ወደደ ለእርሱ ክብር የሚያመጣውን ለእኛም ደግሞ የሚጠቅመንን ይሰጠናል እንጂ::