Voice of Truth and Life: Recent Episodes

Donatist

Being a light in this world.

View Details

አንዳንዱ የጸሎት መልስ መፍትሄ የሚመጣው ሳይታክቱ የእግዚአብሔርን ፊት በመፈለግ በጾም ጸንቶና ተግቶ በጌታ ፊት በመሆን በትግስት በእምነት እስከመጨረሻው ጌታን በመጠባበቅ የሚገኝ ድል ጉብኝት አለ

View Details

እግዚአብሔር የታደገን ሊመራን ቢሆንም፣ እኛ አማኞች ደግሞ በእርሱ ዓላማና ሐሳብ የተያዝንና እርሱን ለመከተል ፈቃደኛ መሆን አለብን፣ እግዚአብሔር ያለን ሰዎች ሆነን ግን ብዙ ጊዜ በራሳችን መንገድ እንሄዳለን በራሳችን ደግሞ ሁሉን ለማድረግ እንሞክራለን ሆኖም በአንድ ቦታ መዞር መጥመልመልና ድካምን ነው የምናተርፈው፣ ተስፋ የሚጣልበት እውነተኛው አምላክ እግዚአብሔር ሲመራን ግን እርሱ መንገድ በሌለበት መንገድ በጨለማ ውስጥ ደግሞ ብርሀን ይሆንልናል፣

View Details

መልአክና ሰው የተፈጠረው ለአምልኮ ስለሆነ ወንጌልም ወደ ሕይወት ካመጣን በኃላ ወደ አምልኮ ነው የሚያደርሰን፣ በትክክለኛ አምልኮ ከአምላካችን ጋር ስንገናኝ የእግዚአብሔርን ትልቅነት እያየንና እግዚአብሔር በስራው ጻድቅ መሆኑን እየተረዳን በምናልፍበት ሁሉ እርሱን ማመስገን እንጀምራለን፣ መርገማችንን ሽሮ የመንግስቱ ወራሾች ያደረገን አምላካችን እዚህ ምድር ላይ ያስቀመጠን ለመንግስቱ ስራ መሆኑ ሲገባን ዛሬ የምለምናቸው ነገሮች ያንሱብንና በምስጋና እንሞላለን፣ በምስጋና ደግሞ ብዙ ቀንበራችን ይሰበራል ብዙ ድልንም እንቀዳጃለን፣

View Details

እግዚአብሔርን በታሪክ ውስጥ ስናየው እምነታችን ይጨምራል፣ መንፈሳዊ ሰው የሚኖረው በእምነቱ ስለሆነ እምነታችን ሲያድግ አንዳንዴ እግዚአብሔር እየተናገረ ያለው ባዶ በሆነ ነገር ላይና ለሰው በማይመስል ነገር ላይ የእግዚአብሔርን ሐሳብ ለማስተናገድ አንቸገርም፣ የእግዚአብሔርን ሐሳብ ለመበጥበጥ በሚመጣው ማንኛውም ነገር ባለመታወክ ፍቅሩንና ምህረቱን እያሰብን እግዚአብሔር የማያሳፍር አምላክ መሆኑንም በመረዳት፣ የሚታየውን የሚሰማውንና የምናስበውን ሳይሆን ጌታን ማየትና መስማት እንጀምራለን

View Details

ያደገ ሰው ወደ ውስጥ የሚያስገባውን እና ከውስጡ የሚያውጣውን በቃሉ እና በመንፍስ ቅዱስ ይመዝናል 1ኛ ቆሮ 2:13 2ኛ ነገ 13 ሐዋ 17:11-28

View Details

በንስሐ ወደ እግዚአብሔር እንደርሳለን፣ ጌታን እንደግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበልና በሐጢያታችን ስንናዘዝ ጌታ ይቅር ይለንና ልጆቹ ያደርገናል፣ ዳግመኛ በእውነት ቃል ከማይጠፋው ዘር እንወለዳለን፣ ጌታን ካወቅን በኋላ ንስሐ ያልገባንበት ሐጢያት ካለ የእግዚአብሔር ለሆነው ነገር ጠንካሮች እንዳንሆንና በጉስቁልና እንድንኖር ያደርገናል፣ እግዚአብሔር ከሐጢያት ጋር ሕብረት ስለሌለው ከጌታ ጋር ህብረት እንዳይኖረንም ያደርጋል፣ ስለዚህ እራሳችንን ሁልጊዜ አየመረመርን በንስሐ የእግዚአብሔርን ፊት ልንፈልግ ይገባናል፣

View Details

በመንፍሳዊ ህይወታችን ሰናድግ ፈረሃት አይገዛንም ዕብ 2:14-15 1ዮሐ 4:18 ኢሳ 8:13 መሳ 6:10 ራዕ 21:8

View Details

ሰይጣን ደካማ ጎናችንን ያውቃል ነገር ግን ከዛ ውስጥ ጠንካራ ነገር ይወጣል። ይህ ጠንካራ ጎን የሚወጣው በሞትንበት ነው።

View Details

በህይወቱ ያደገ ሰው የሰማውን ቃል የመጠበቅ ብቃት አለው በአንጻሩ ያላደገው ሰምቶ የመጠበቅ ብቃት የለወም ሕዝ 3:10 ሉቃ 8:13-15 2ኛ ጢሞ1:14 ራዕ 3:3 ኢዮ 20

View Details

ሰው እግዚያብሔርን ተስፍ ካደረገበት በላይ የህይወት አቅም የለውም ሮሜ 8፡24 ሮሜ 8:12 ዘፍ 13:10

View Details

ጠላት ይከሳል ነገር ግን የሚሰምርለት ከውስጥ ከአካል ተባባሪ ካገኘ ብቻ ነው። ምክንያቱም ጌታ የቅዱሳን ክስ ስለማይሰማ። ይህም ፀጋን ብቻ እንድንመለከት ነው።

View Details

የእግዚአብሔር የሆነው ሁሉ መንፈሳዊ ነው፣ አኛ አማኞች ቃሉን ሆነን የምንገኘው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው፣ ያለመንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን ሙላት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለስዎች ማድረስ አንችልም፣ ይህንን መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ካልታዘዝን፣ ህሊናችን ንጹህ ካልሆነና ካልተጠማን መሞላት አንችልም፣ ጌታችን እየሱስ እራሱ ከመታዘዝ ጋር አያይዞታል፣ ትዕዛዛቱን ሁሉ ጥለን መንፈሱን መፈለግ አንችልም፣ ትዕዛዛቱን መጣል ማለት እታድርጉ የተባልነውን ማድረግና አድርጉ የተባልነውን ደግሞ አለማድረግ ነው፣

View Details

ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፣ ክርስቶስን የሚያውቅና የእርሱ ተከታይ የሆነ እማኝ ዋነኛው የባህሪው መገለጫ ፍቅር ሊሆን ይገባል፣ ጌታ እየሱስ እንኳን አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው ከሕግ የትኛይቱ ትእዛዝ ታላቅ እንደሆነች ሲጠይቀው የመለሰው መልስ፣ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍሥህም በፍጹም አሳብህም ውደድ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም ባልንጀራህን እንደ ነፍሥህ ውደድ የምትለው ናት ብሎ ነው፣ እንግዲህ በዚህ ፍቅር ለማደግ የመጀመሪያው ይቅር ማለት ሲሆን በመቀጠል ፍቅርን መከታተልና ከቅዱሳን ጋር ጤነኛ ህብረትን በመፍጠር ልንገለጽ ይገባናል፣ ክርስቶስ በምን ያህል ፍቅር እንደወደደን ሲገባን ሌሎችን ለመውደድ አንቸገርም፣

View Details

ሰው እግዚያብሔርን ተስፍ ካደረገበት በላይ የህይወት አቅም የለውም ሮሜ 8፡24 ሮሜ 8:12 ዘፍ 13:10

View Details

ያደገ ሰው በጽጋ ይኖራል ሮሜ 7 ሮሜ 6:14 ሮሜ 6:11 ራዕ 12:10

View Details

እግዚአብሔር መልካም ስለሆነ ለህዝቡ ለመልካም ቀን ይቀጥራል። እኛ ግን በመታመን መጠበቅ አለብን። እግዚአብሔር ካለን ይልቅ ሁኔታን አይተን መናወጥ የላብንም። እስራኤል እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ ጠላት የሚላቸውን ይሰሙ ስለነበር በምድረብዳ ቀርተዋል። እኛም ከጥርጠና ፍርሀት ሀሳባችንን መጋረድ እለብን። በዚህ ክፍል ውስጥ ይህንን በስፍት እንማራለን።

View Details

ለሰዎች መሆን ክርስቶስን መምሰል ሲሆን ዋጋ ያስከፍላል ዘኍ 16:45 ኢያ 3፡13 ዘኍ 16፡41

View Details

ያደገ ሰው ጦር እቃው ምንድን ነው? ያላደገስ? 2ኛ ቆሮ 10 1ኛ ጵጥ 3

View Details

ባደገ ሰው ውስጥ ከሚታዮት ባህሪዎች ውስጥ ለሌሎችህ መስጠት ለራስ ከማድርግ በላይ ያስደስተዋል ዕብ 13:16 ሉቃ 6:38

View Details

በእኛ መልካምን ስራ የጀመረው ልኡል እግዚአብሔር ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በህይወታችን የሚሰራው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው የታመነ አምለክእ ነው

View Details

የቤርያ ሰዎች ልበ ሰፊዎች ነበሩና ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እንደመረመሩ እንደ እግዚአብሔር ቃል ሆኖ ሲያገኙት ደግሞ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ እንደተቀበሉ አማኝ ከቃሉ ጋር የሚንሰማውን ሁልጊዜ ማመሳከር አለበት

View Details

የዛሬ ጥያቂዎች 1. ነፃ የወጣ ሰው ነው ለእግዚአብሔር የሚሆነው ይህ ደግሞ እድገት ነው የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 2. ጌታን ስንቀበል በመንፈስ ቅዱስ ታትመናል ልጅ ለመሆን ግን ገና መንፈስ ቅዱስ አልተሞላንም የሚለው ሀሳብ አብራራልን። 3. የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚሄደው ከመታዘዝ ጋር ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 4. በመዳን ውስጥ ትልቅ ትንሽ የለም ወደ መንፈስ ቅዱስ ሙላት ስንመጣ ለእያንዳንዱ የተለያየ መለእክት አለው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 5. በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ የአሸናፊነት አቅም የሚኖረው ህይወታችን ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን።

View Details

ክርስትያን የሚያድገው የፈርሰውን ያህል ነው ያደገ ሰው ይሰማል ምሳ 1:32-33 ሮሜ 10:10

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ሳምሶን የተቀባ አመንዝራ ነው የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። እግዚአብሔር የቀባው ሰው እንደ ሳምሶን ዐይነት ህይወት ነው የሚባለው ምን አይነት ሲሆን ነው? 2. የቃሉ ሙላት የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 3. የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከሌለ ለልጆቻችን ወንጌል ማድረስ አንችልም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። ወንጌል ሰምተው ሰዎች ወደ መዳን የማይመጡት ለዚህ ነው ማለት ነው? 4. ጌታ እየሱስ 30 ዓመት ለማገልገል መንፈስ ቅዱስ ስላልተሞላ ነው ወይስ ግዜው ስላልደረሰ? 5. ቃሉ ክርስቶስ ስለሆነ ቃሉ የሌለው ሰው ደስታ የለውም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን።

View Details

ወዳጅነታችን እንደ ክርስቶስ ባህሪ የሆነ የማይለዋወጥ መሆኑ ማደጋችንን ያሳያል ምሳ 11:17

View Details

ሐዋርያት አንድ ላይ በመሆን ይተናነጹ ነበር፣ ዛሬም በዘመናችን ቤተ ክርስቲያን እንድትናነጽ አንዳችን ለአንዳችን መጸለይ የወንድማችን ወይም የእህታችን ነገር ተስምቶን ልንሸካከም ይገባናል፣ እንዲሁም የእግዚኣብሔርን እውነት እየገለጽን በመካከላችን ያለ እውቀት ያሉትን በቃሉ እግዚአብሔርን ወደማወቅ እንዲደርሱ ማስተማር፣ እርስ በእርስ በመዋደድና በመከባበር አብረን የሰማዩን መንግስት እንደምንወርስ ሁልጊዜ ማሰብ ያስፈልገናል

View Details

ያደገ ማንነታችን ክርስቶስን በመምሰል ሲገለጥ ባላደገው ማንነታችን ደግሞ ስጋችን ይገለጣል ምሳ 20:22 1ኛ ጵጥ 3

View Details

እግዚአብሔር ለቃሉ የታመነ ነው፣ እርሱ እስራኤላውያንን ሊያድን ሲመጣ ለአባቶቻቸው የገባውን ቃል ነበር የሚያመለክታቸው፣ የእምነት አባቶችም የተስፋይቱን ምድር እንደሚወርሱ የተናገራቸው አምላክ እግዚአብሔር ታማኝ መሆኑን ተቀብለው ምድሪቱን እንደሚወርሱ አምነው ነው የሞቱት፣ አንዳንድ ጊዜ መከራው በዝቶብን አልፈን ማየት ቢከብደን እንኳን እግዚአብሔር አደርጋለሁ ያለውን የሚያደርግን ምንም የማያቆመው ታላቅ አምላክ መሆኑን ልናምን ያስፈልገናል፣

Activity

View Details

ያደገ ሰው ለሚወስነው ውሳኔ ሁሉ የእግዚያብሔርን ሃሳብ የሚጠይቅ ሰው ነው ያላደገ ስው ግን ስዎች የሚሉትን ብቻ ይሰማል 1ኛ ሳሙ 14:36 ሮሜ 8:14 መሳ18:5-

View Details

ኃጢያት ወደ ዓለም ሲመጣ ውርደት ይዞ ነው የመጣው፣ አዳምና ሕዋን ኃጢአትን በሰሩ ጊዜ ከእግዚአብሔር መንግሥት ጎሎዋል፣ውርደትን ለብሰዋል፣ መንፈሳዊ ውድቀት የሆነው በሰው ሕሊና፣ በሰው ልብ፣ በሰው አስተሳሰብ፣ በሰው አመለካከት ውስጥ ነው፥ ጌታ ኢየሱስ ስጋ ለብሶ ወደ ምድር የመጣው በኃጢያያት ምክያት ከአግዚአብሔር መንሥት የተለየውን የሰው ልጅ ወደ ክብሩ ለመመለስ ነው፤ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ ብሎ በቃሉ እንደ ተናገረ አምነው ለተከተሉት የሕይወት ተድሶ ለማድረግ ነው

View Details

ክርስትና በጨለማ ላለው ሕዝብ የሚመሰከው በመኖር ነው፥ ጌታ በቃሉ ስያስተምር፤ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ ብሎዋል፣ ጌታ ሐዋርያትን በአፍ ከመመስከራቸውና ከመስበካቸው በፍት ክርስትናን ነረው እንድያሳዩ ነው የፈለገው፥ ክርስትና ኖረን በሕይወታችን የሚታይ መሆን አለበት፣ የጌታም ክብር ጎልቶ የሚታየው ያኔ ነው

View Details

ያደገ ሰው የውስጡን ንጽህና ግድ ይለዋል ያላደገ ሰው ደግሞ ስው የሚያየው የውጭው ማንነቱ ግድ ይለዋል መዝ 51:10 ዘፍ 6:5 ዘፍ 8:21 ማቴ 5:8

View Details

አማኝ ከሁሉ በላይ የሚያስመካው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አብሮነትና መገኝት ብቻ ነው እግዚአብሔር በምህረቱና በቸርነቱ በህይወታችን ከሚያደርገው በጎነቱ የተነሳ የጊዜውን ነገር ብቻ እየተመለስ የምንኖር ሳይሆን በእምነት እንድናድግ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው

View Details

እምነት ማለት በእግዚአብሔር ዘንድ የሚደረግልንን አይናችን ሳያይ ጌታ በተናገረን ውስጥ ሆነን ሁሉን ለርሱ በመተው እንደሆነልን እንደተደረገልን አምነን በሰላሙ ውስጥ ማረፍ ነው

View Details

በጌታ ያደገ ማንነት እና ያላደገ ማንነት ገላ 4 ሉቃ 11:5-13 ዕብ 4:16

View Details

ያደገ ሰው ፀሎት እና ያላደገ ሰው ፀሎት መዝ 32:6 ኤር 2:27 ሉቃ 22:46 መዝ 11

View Details

እግዚአብሔር ያለውን የምንሆነው በመለኮት ጥበቃ ውስጥ እንዳለን አይናችን ሲበራ ብቻ ነው፣ ያለዚያ እንታወካለን፣ ለፈቃዱ ወይም ለተጠራንበትም መኖር አንችልም፣ አይናችን ሲበራ ግን እራሳችንን ከሐጢያት የምንጠብቅበት ወይም ክፉውን የምንጸየፍበትና እግዚአብሔርን በመፍራት የምንኖርበትን ማስተዋልና ጥብብን የተቀበልነው ከመለኮት መሆኑን እንረዳለን፣ በእርሱም አርፈን እንኖራለን

View Details

ሰማያዊ ዜግነትን ሰው የሚያገኝው ወንጌልን ሰምቶ ሲያምን ብቻ ነው ወንጌል ሁሉም አካል የሚሰራው ስራ ሲሆን አንዱ በመሄድ ሌላው በጸሎት በገንዘብ በሚያስፈልገው ሁሉ ይህን የምስራች በማድረስ ሰዎች ሲድኑ ደስ መሰኝት ለተቸገሩ መድረስ ነው

View Details

የውስጥ ጥማት ካለ ለኔ አይሆንም የምንለው ምንም ነገር የለም፣ እግዚአብሔር ዘኪዮስን በጊዜው እንደጎበኘው፣ እኛ ክርስቶስን ለማግኘት ፍላጎትና ጥማት ይኑረን እንጂ ጌታ ማንንም አያሳፍርም፣ እርሱን ለማየት ብዙ ነገሮች በዙሪያችን ቢጋርዱን እንኳን የልባችንን መሻት የሚያውቅ አምላክ እግዚአብሔር በጊዜው በዙሪያችን ከጋረዱን ነገሮች አልፎ ወደእኛ ይመጣል

View Details

እግዚአብሔር በማእበል በወጀብ ውስጥ መንገድ አለው ክብሩን ለመግለጥ እምነታችንን ለመጨመር እንባችንን ለመጥረግ የጎበጠ ነገራችንን ቀና ለማድረግ ለማስጣል ለማዳን ለመባረክ መንገድ አለው

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ምሳሌ 31፡11 መንፈስ ቅዱስን የሚያሳዝን ሰው ይለፋል ፍሬ የለውም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 2. መዝሙር 53፡1 የሚጸጸት ህይወት ከሌለን የንስሀ ፍሬ የለንም የሚለው ሀሳብ አብራራልን። 3. ምሳሌ 16 ለትውልድ የምናተርፈው ነገር ምንድን ነው? 4. ምሳሌ 31፡17 የውሳኔ ሰው መሆን ያስፈልገናል የውሳኔ ሰው ያልሆነ ግን ህይወት አደጋ ላይ ነው ያለው ለእርሱ ብቻ ሳይሆን በአካባቢው ላሉ ጭምር መሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 5. ወደ እግዚአብሔር ስቀርብ እንደ ማይገባው ሰው መኦን አለበት የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 6. ምሳሌ 31፡18 አመስጋኝ ሰው መብራቱ አይጠፋም የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 7. የአንዳንድ ሰው መብራት የሚታየው በቀን ብቻ ነው የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። ይህ ብርሀን በቀን ብቻ እንደሚበራልን በማታ እንደማይበራ እንዴት ነው የምናውቀው? 8. 2ኛ ነገሥት 8 እግዚአብሔር የሚያየን ቃሉን እንዴት እንደ ተቀበልን ነው እንጂ ምን እንዳደረግን አይደለም የሚለው ሀሳብ ይብራራልን።

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. የጌታ ወዳጆች ሀጢያተዮች ነበሩ የእኛስ ወዳጆች እነማን ናቸው? 2. እግዚአብሔር በተለያየ ጎዳና ሊያገኘን ይችላል። ጸሎታችንንም ሊመልስ ይችላል ነገር ግን ያልተገኘ የህይወት ክፍል ሊኖረን ይችላል የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 3. ማቲዮስ 3፡16-17፤ 4፡1 ለእግዚአብሔር ለመገኘት ከጥምቀት በሗሏ በመስቀል ህይወት ማለፍ አለብን ወይ? 4. መኋልየ መኋልይ 4፡12 ምንጩን የምንደፍነው ራሳችን ነን ነገር ግን እግዚአብሔር ይከፍተዋል የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 5. በህይወታችን ቅጣት ሲመጣ እንዴት ነው የምናውቀው? ይህንን እኛ ነን ወይስ ሌሎች ናቸው የሚይውቁት? ቅጣትስ ለምንድን ነው የሚመጣው? 6. 1ኛ ጥሞቴዎስ 2፡15 ይብራራልን። ምሳሌ 31፡15 ማለዳ የሚለው ግዜን ነው ወይ የሚያመለክተው? 7. ምግብ አብልታ ወደ ተግባር ታሰማራቸዋለች የሚለው ሀሳብ ቢብራራልን? 8. ኤፌሶን 2፡5 በአደገ ማንነታችን ጸጋን የምንፈልገው ከሀጢያት ለመላቀቅ ነው ይላደገው ማንነታችን ግን ጸጋን ለመሸፈን እንፈልገዋለን ይህንን ወደ እኛ ህይወት አምጥተ አብራራልን።

View Details

የጥሞና ሕይወት የተለማመዱ ስዎች የእግዚአብሔርን ቅድስና ይለማመዳሉ የቅድስናውን ሕይወት ይካፈላሉ ከብዙ ነገር እራሳቸውን ይጠብቃሉ። ቅድስና ከእግዚአብሔር የምንካፈለው ነው በራሳችን ይምናመጣው አይድለም፤ መጽደቅ አንድ ግዜ ነው፡ ቅድስና ግን እለት እለት ይምንለማመደው ነገር ነው፤ ጽድቅ የተገለጠው በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ነው።

View Details

እግዚአብሔር ያለውን የሚያደርግ ሉአላዊ አምላክ ነው ቅንነት ፊቱን ታየዋለች እግዚአብሔር መግቢያው የቀና ልብ ነው በረከቱ ወደ እኛ የሚመጣው በመታዘዝ ነው

View Details

ከሰማይ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ህይወታችንን ኑሮአችንን ዛሬንና ነገአችንን ያቀናል ጌታ አስቀድሞ በህይወታችን በተናገረው ውስጥ እናልፋለን መልካሙን ገድል እንጋደላለን

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ጌታ የሰጠን ፍቅር እሱን ብቻ እንድንወድ ሳይሆን የእርሱ የሆኑትን ጭምር እንጂ የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 2. የእርሱ የሆኑትን መውደድ የምንቸገረው ለምንድን ነው? 3. 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡4 ያደገ ሰው በሞተ ፍቅር ላይ ህይወትን ይዘራር የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 4. የእግዚአብሔር እረፍት በእኛ የሚሆነው እሱ በአለን ውስጥ ስንገኝ ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 5. ራሳችንን እግዚአብሔር በተናገረን ካላየን መስኮት እንደሌለው ቤት ነው የምንሆነው የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 6. ዮሐንስ 5፡5 መንፈሳዊ ነገር ስንሆን አስመስለን የምንለው ነገር አለ እና ይህ ይብራራልን። 7. መኋልየ መኋልይ ዘሰለሞን 4፡12-16 የመከራ እና የድርቀት ንፋስ ካለመጣ ነገራችን አይከፈትም ወይ?

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ምሳሌ 30፡11-12 በወላጆቻቸው የተጎዱ ልጆች የእግዚአብሔር በረከት እንዲያገኛቸው እንዴት ነው እንደዚህ ዐይነት ልጆችን ማገልገል የምንችለው? 2. በግልፅ የሚደረግ ፀሎትና በስውር የሚደረግ ፀሎት ብታብራራልን? እንዴት ነው እንደዚህ ዐይነቶች ፀሎት መፀለይ የምንችለው? 3. ምሳሌ 31፡1-5 ልጅን በማሳደግ ውስጥ ልጆች በሚያልፉበት መንገድ የወላጆች ድርሻ በተመለከተ ምን ትመክረናለህ? 4. ከውጪ ያየነውንወደ ቤተ ክርስትያን ስላመጣነው ምን ትመክረናለህ? 5. ምሳሌ 31፡13 በማጉረምረም እና በማረም ላይ ልጅን በማሳደግ ላይ ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

View Details

የቤተክርስቲያን ዋና ተልዕኮ የእግዚአብሔርን በጎነት መናገር፣ መንፈሳዊ ቤት ሆኖ መሰራትና መንፈሳዊ መስዋዕትን ማቅረብ ነው፣ ታላቁ ትዕዛዝ ደግሞ አምላካችንን በፍጹም ልባችን ነፍሳችንና ሃሳባችን መውደድና ባልንጀራችንን ደግሞ እንደራሳችን መውደድ ነው፣ ጌታን መውደዳችንን የመንገልጸው ከአላማው ጋር በመተባበርና ለቃሉ በመታዘዝ ሲሆን በምድር ሲያስቀምጠን ትልቁ አላማው ደግሞ ወንጌልን ለፍጥረት ማድረስ ነው፣ ባልንጀራችንን እንደራሳችን እድርገን መውደዳችንን የምንገልፀው ለባልንጀራችን መልካም ነገርን በማድረግ ሲሆን ሰውን ሁሉ ወደ ዘለአለም ህይወት ከመምራት የበለጠ ደግሞ ምንም መልካም ነገር የለም፣ አማኞች ለዚህ ታላቅ ተልዕኮ ሁልጊዜ የተጋን እንድንሆን ጌታ ይርዳን፣

View Details

የጥሞና ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ የማረፍ ህይወት ነው የጥሞና ጊዜ የለመዱ ሰዎች ፊቱን ይናፍቃሉ በእግሩ ስር መሆን ይወዳሉ ደስታና እረፍት በመንገዳቸው ነው አይናወጡም ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ስር ናቸው

View Details

የአንድ አማኝ መንፈሳዊ ሀብቱ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ራስን በእግዚአብሔር ቃል ተስፋ በመለኮት ሀሳብ ውስጥ ማግኘቱ ነው

View Details

ጌታን በጽድቅ እየተከተልን ስንሄድ በህይወታችንበብልዩ ልዩ ፈተና አና መከራ እናልፋለን። በዚህ የህይወት ጉዞ ውስጠ እግዚአብሔር ለምን የሚል ጥያቄ ይፈጠርብናል። በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እንደተፃፈው፣ ብዙ የእግዚአብሔር ሰዎችም ጠይቀዋል። እግዚአብሔር ዝም ሲል በህይውታችንን ሊከብር እና ለእኛም የበለጠ እና የተሻለን ነገር ስላየልን ነው። በዚህ ትምህርት ውስጥ ይህንን በጥልቀት እንማራለን።

View Details

ሰው እየሱስ ክርስቶስን እንድ ግል መድሀኒቱ እድርጎ ሲቀበል ከኩነኔና ከእር ግማን ነፃ ወጥቶአል። ነገር ግን በህይወት ጉዞ ውስጥ ደግሞ በጌታ ለማደግ የግዚአብሔር ፀጋ ያስፈልገውል።ምክንያቱም ከጌታ በፊት የነበሩንን የሀጥያት ልምምዶች የምንጥለው ፣ ባህርያችን የሚለወጠው ፣ ከእስራታችን የምንፈታው በፀጋው ነው። እንዲሁም በመከራና በአስጨናቂው አለም ውስጥ ስናልፍ የጌታ ሰላም እንጠበቃለን። በዚህ ክፍል ውስጥ ይህንን ብዝርዝር እንማራለን።

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ምሳሌ 30፡32 በዚህ ዘመን መጠየቅ ያለብን ምን በላን ሳይሆን በሰው ህይወት ውስጥ ምን ሠራን መሆን አለበት የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 2. በህይወታችን ውስጥ ማዕበል ጸጥ የማይለው እንዴት ነው? 3. እየሱስ ክርስቶስ ብቻ ካለን እለት እለት የሚያስፈልገንን ፀጋ ላንቀበል እንችላለን ወይ? 4. በተለያየ ነገር አድገን ጌታን ካልመሰልን እነዚህ ነገሮች በህይወታችን ምን ሊመስሉ ይችላሉ? 5. ያደገ ሰው ሰውን ያስተካልክላል ስለሚል አገልጋዮችን ሳናስቀይም እንዴት ነው ማስተካከል የምንችለው? 6. ቃሉን እንደ ቃል መውሰድ የምንችለው እንዴት ነው?

View Details

እውነተኛ ባለጸግነት ያለው በክርስቶስ ውስጥ ነው ይህም የሚገኘው በእምነት ነው፤ በክርስቶስ ውስጥ ያለውን ባለጸግነት ለማግኘት መክሰር የግድ ያስፈልጋል መጣል የግድ ያስፈልጋል፤ በክርስቶስ የተሰጠን ብለጸግነት መጠን የለውም፤ ይህ ጸጋ የሚለቀቀው ግን ስለ ክርስቶስ ስንከስር ነው፤ ለዚህ ምድር የምንጠቅመው አማኝ ስለሆንን አይደለም፡ በክርስቶስ ባለጸግነት ውስጥ ካለን ለዚህ ምድር እናስፈልገዋለን። 2 ቆሮንቶስ 6:10

View Details

የተስፋን ቃል የሰጠን የታመነ ነው፣ ተስፋን የተቀበልን አማኞች ቃሉን የህይወታችን መመሪያ በማድረግ በምናልፍበት ውጣ ውረድ ሁሉ በዚህ ታማኝ አምላክ መደገፍ ይገባናል፣ በተስፋችን ጸንተን አስከፍጻሜ እንዳንሄድ ከሚያደርጉን ነገሮች አንዱ ፍርሐት ሲሆን፣ እኛ ግን አይምሮአችን ወይም ሁኔታዎችን ሳይሆን ቃሉ የሚለንን በመስማት እና በመቀበል ተስፋ የሰጠን ጌታችን ደግሞ ተመልሶ እንደሚመጣና ወደ ራሱ አንደሚወስደን በማመን በትጋት እስከፍጻሜ መጽናት ይኖርብናል፣

View Details

ዛሬ ምን ሰምታችኃል? ዛሬ የሰማነው ነገር እንዳያወርደን አብዝተን ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል፤ የሰማነው ነገር ወደ እግዚአብሔር የማያቀርበን ከሆነ ያለመስማት ይመረጣል፤ ነገራችን ነጋችን በእግዚአብሔር እጅ ነው መራራው ይቀየራል ያስፈራራን ይለወጣል እርሱ ፍጻሚያችን ያውቃል

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በደማቸው እንዲናገሩ የማይሰወሩ ነቢያት አሉ የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። ይህንንስ እንዴት ነው የምናውቀው? 2. ሰውን ይቅር ማለት ፈጽሞ ነገርን መተው ማለት ነው ወይ? 3. እግዚአብሔር በችግር ግዜ አዚሁ ተቀመጡ ቢለል ድምፁን እንዴት ነው የምንለይው? 4. አድርጉልን የምንል ከሆነ አላደግንም ማለት ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 5. ጠባዬ ነው ብለን የምናደርገውን ነገር እንዴት ነው ማስተካከል የምንችለው? 6. በአላፊነት ያለ ሰው በበቂ ምክንያት ሀላፊነቱን መወጣት እንደማይችል ቢናገር ይህ እድገት ሊሆን ይችላል? 7. በተቸገርን ሰዓት ብቻ ሳይሆን በተሳካልን ግዜ የተከፈተ ዐይን ሊኖረን ይገባል ማለት ነው? 8. እግዚአብሔርን መታዘዝ ማለት መሰወር ማለት ነው?

View Details

የአንድ አማኝ ዕድገት ትልቅ ከፍታ እኔ የጌታ ነኝ ማለት መቻሉ ነው፣ የተፈጠርነው የእግዚአብሔር ለመሆን እንደሆነ ሲገባን የመከራና የችግሮች መደራረብ ከክርስቶስ ፍቅር እየነጠሉን ሳይሆን የእርሱ መሆናችንን እያስረገጡልን ነው የሚሄዱት፣ እግዚአብሔርም ከጥንት ከመጀመሪያው የእርሱ ስላደረገን ባለቀቅነው ማንነታችን ወይም የእርሱ ሆንን ባልተገኘንበት የእርሱ ሆነን እስክንገለጥ ወደ እርሱ የሚይስጠጋንን የህይወት ማዕበልና ወጀብ ይፈቅዳል፣

View Details

አማኝ እግዚአብሔርን ሲከተል መስቀሉን ሊሸከም ይገባዋል። በዚህ የክርስትና ጉዞ ውስጥ በእምነት እና በደስታ፣ በመጽናት፣ ራስን በመካድ ልንከትለው ያስፈልጋል። በዚህ ትምህርት ውስጥ እንዴት መስቀላችንን ተሸክመን እስከመጨረሻው ጌታን እንደምንከተል እንማራለን።

View Details

ጌታ ኢየሱስ የሰጠን ሰላም የማይናወጥ አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ ሀሳባችንን የሚጠብቅ ሰላም ነው፤፤ አእምሮአችንን የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብ በማሰላሰል እለት እለት ማስለመድ አለብን

View Details

እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነው በሙሉ ሀይላችን እርሱን ስንታመን ደስ ይለዋል ምንም የለኝም አንተ አለኃኝ እሚያየኝ የለም አንተ ታየኛለህ የሚሰማኝ የለም አንተ ግን ትሰማኛለህ እንድንለው ይወዳል፤፤ አይኖቻችን በእግዚአብሔር ላይ ብቻ ሲሆኑ እግሮቻችን ለመናወጥ አይሰጡም

View Details

ሁሉን ለጌታ የሚተው ትግስተኛ ሰው ነው፣ የመታገስ አቅም ያለው ሰው ነገርን ሁሉ ለጌታ የተወ ነው፣ ሰው እንደመሆናችን ነገርን መለወጥም ሆን መሸከም እንደማንችል በመረዳት ለመንፈስ ቅዱስ እውቅናን በመስጠት ፈቃዳችንን ለጌታ ስናስገዛና አለን የምንለው ጌታ ብቻ ሲሆን ነገራችንን ለጌታ ለመተው ብዙ አንቸገርም፣

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. 1ኛ ሳሙኤል 9፡7 ሳዖል አህይ ፍለጋ ወጥቶ እግዚአብሔር በሚገኝበት ሥፍራ እንዲገኝ አድርጎታል ይህ መንፈስ ቅዱስ በሚመራበት ወቅት በህይወታችን ሊከናወን ይችላል? 2. የተለየን ቀን ልንስተው እንችላለን ወይ? ከሳትንስ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? 3. ችግር ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ማቅረቢይ ነው? 4. በዚህ ዘመን በልጆቻችን ላይ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? 5. ደካማ ሰው ሁልግዜ ተበቃይ ነው ጥበበኛ ሰው ግን ነገሩን ይንቃል በዚህ ውስጥ የበቀል ምኞት፣ የበቀል ጸሎት አለ የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 6. ትጋትና ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት እንዴት ነው ወደ ህይወታችን ማምጣት የምንችለው? 7. 2ኛ ተሰሎንቄ 3፡3 “ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው።” የሚለውን ሀሳብ አብራራልን።

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በመንፈሳዊ ነገር ያደገ ሰው ያለውን ነገር ሙሉ በሙሉ ለጌታ የሰጠ ሰው አንዳንዴ ወጣ ገባ ሊል ይችላል ወይ? 2. በመንፈስ ካልታመንኩ ሰው የነገረኝን ሚስጥር መሰወር አልችልም ወይ? 3. የራስ ሸክም መንፈስ ቅዱስ ከሚሰጠው ሸክም ምንድን ነው ልዩነቱ? 4. ያደገ ሰው የእግዚአብሔር እውነት የእርሱ የሆነ ሰው ነው። የእኔ የእድገት ደረጃ እውነት ከሆነልኝ ነገር ነው የሚወሰነው ማለት ነው? ይህስ መረዳት ስለ ጌታ መረዳት ነው ወይ? በህይወቴ በሚሆነው መረዳት ይቻላል ወይ? 5. ወላጆች ሳይሆኑ ልጆችን የሚየሳድጉትን ምን ማድረግ እንዳለብን ብትመክረን?

View Details

የክርስትና ህይወት የውትድርና ህይወት ነው፣ ሁልጊዜ እራሳችንን በፊቱ እየመረመርን መንገዳችንን ልናነጻ ይጠበቅብናል፣ በንጽህናና በቅድስና ለመኖር ስንወስን ደግሞ ፈተና የለብንም ማለት ሳይሆን ነገር ግን እኛ ሃጢያተኛ እንደሆንን እና እርሱ ጌታ ብቻ ጻድቅ እንደሆነ በማመን በሙላት ህይወታችንን እንዲመራ ስንፈቅድለት ምድራዊው ፈተና በፊታችን እነደ ትቢይ ይሆናል፣

View Details

በጊዚያዊ መከራዎች ውስጥ ስናልፍ መታከት የለብንም። ምንም የውጭው ሰውነታችን በብዙ መከራ ቢጎዳ የውስጥ ሰውንታችን ግን ዕለት ዕለት ይታደሳል። በዚህ ክፍል ውስጥ በህይወታችን እንዳንታክትና ክርስቶስ በህይውታችን እንዲገለጥ ምን መሆን እንዳለብን በሰፊው ያስተምረናል።

View Details

በእግዚአብሔር መንገድ ላይ ስንሆን፣ እርሱ እኛን በሚያገኝበት እኛም ለእርሱ በምንገኝበት ያደርገናል።በመንገዱ ስንሆን በምንም አንታለፍም።ከእኛ ያልሆነ ጥንካሬና ጉልበት ይሰጠናል።በመንገዱ ላይ መሆን ማለት በጉብኝት ቀናችን ላይ መሆን ማለት ነው።የመዳን ቀን ማለት እርሱ በሚያልፍበት ቀን የተገኝንበት ቀን ነው። በዚህ ትምህርት ውስጥ ይህንን በጥልቀት ያስተምረናል።

View Details

ዳዊትና ሌሎችም በመጽሀፍ ቅዱሳችን ውስጥ ብዙ የእግዚአብሔር ሰዎች በጭንቅ በመከራና በማይወጡበ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ግን እግዚአብሔርን በመታመን እንዴት ከነበሩበት ያለቀና የተቆረጠ ነገር ውስጥ ጌታ ደርሶ እንደታደጋቸው ተጠቅሷል፣ ዛሬም እኛ የክርስቶስ ተከታዮች የምንሰማውና የምናየው ደስ ባያሰኝ የታመንነው ቢከዳን ዙሪያችን በሚሆነው ሳንወሰድ ባለመታወክ ጸንተን ጌታን መጠበቅና ልባችንን ጌታ ፊት ማፍሰስ ይገባናል ምክኒያቱም ረድኤታችንና መታመኛችን እርሱ እግዚእብሔር ብቻ በመሆኑ፣

View Details

እግዚአብሔር ብቻውን አምላክ እንደሆነና እውነተኛ አምላክ መሆኑ እንዲታወቅ ስለሚፈልግ ክብሩን በተለያዩ ስዎች ገልጧል፣ ዮሴፍም ከነዚህ ስዎች መካከል አንዱ ሲሆን ዛሬም እግዚአብሔር እንደ ዮሴፍ ራዕይን የተሸከሙ ሰዎች አሉት፣ ይህንን ራዕይ የተሸከሙ ሰዎች በተለያየ እንቆቅልሽ ውስጥ ያልፋሉ፣ ጌታ ስሙን ለማስከበር አንዳንዴ የራሱ የሆኑትን እንደንዚህ አይነት ሰዎችን በመከራ እንዲያልፉ ይፈቅዳል ግን በመከራቸው ክብሩ ይገለጣል፣

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. 1ኛ ቆሮንቶስ 14፡34-37 የሴቶችን አገግሎት በተመለከተ ይህ ክፍል እንዴት ነው የሚገለጠው? 2. ኤፌሶን 6፡18 “ በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ” ይህ ክፍል ይብራራልን። 3. ምሳሌ 29፡25 ሰውን በመፍራት እና በማክበር ያለው ልዩነት ምንድን ነው? 4. ሰው በሚያልፍበት ነገር ማንነቱ ይገለጣል የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 5. በምንሰማውና በምናየው ነገር ስንፈራ እንገኛለን ያ ማለት የእግዚአብሔር ፍርሀት የለንም ማለት ነው? 6. ኢዮብ 23፡10 የአማኝ እረፍቱ እሱ ያውቃል ማለቱ ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 7. 1ኛ ዮሐንስ 3፡21-24 የተጨበጠ መረዳት ከሌለን ስንቆሽሽ አናውቀውም ስለዚህ የእምነታችን መለኪያ ስሜታችን ነው የሚሆነው የሚለውን ሀሳብ ግልፅ አድርግልን። 8. 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡8 ለችግሮቻችን አጥብቀን እንፀልያለን እንጂ እግዚአብሔርን ለመስማት ብቁ አይደለንም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን።

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ምሳሌ 29፡20 የሚቸኩል ሰው መንፈሳዊ ፍሬ ሊያፈራ አይችልም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 2. ምሳሌ 30፡1-5 በዚህ ዘመን ብዙዎቻችን ጌታን እናመልከዋለን እንጂ እናምነውም የሚለውን ሀሳብ ግልፅ አድርግልን። 3. መዝሙር 23፡24 ነገሬን ከሰው ጋር የማያይዝ ከሆነ በመንፈሳዊ ነገሬ እያደኩ አይደለም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 4. ክፉ ነገር ሁሉ ከሰይጣን አይደለም ወይ የሚመጣው? ታድያ እንዴት ነው ነገሬን ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር የማያይዘው? 5. እቅድ አውጥተን ባናደርገው እንደ ስለት ሊቆጠር ይችላል? 6. 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡1-5 ኤጴስ ቆጶስ መሆን የሚፈልግ ህይወቱ ምን ዐይነት መሆን እንዳለበት ተገልጣል ግን አሁን ያለች ቤተ ክርስትያን ይህንን አትጠቀምም እንዴት ነው? 7. ራዕይ 22፡17 በዚህ ዘመን ለምንድን ነው አማኞች ማራናታ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና የማይሉት?

View Details

እኛ በጌታ ውስጥ ጌታም በእኛ ውስጥ መሆኑን ማወቅ 1ኛ ዮሐ 3:21-24

View Details

እግዚአብሔር ባለበት በለቅሶ ሸለቆ ስፍራ በረከት በዚያ አለ፤፤ ኢዮሳፍጥ እግዚአብሔርን ሰምቶ አምኖአልና መከራውን ወደ ክብር ሸለቆ ለወጠለት፤፤ ዳዊት እግዚአብሔርን ታምኖአልና የስብራቱን ቀን ወደ በረከት ቀየረለት፤፤ ያቤጽም ጸልዪአልና እግዚአብሔር የመርገም ታሪኩን ወደክብር ቀየረለት፤፤ እግዚአብሔር ስለወደደን እርግማናችንን ወደበረከት ቀየረልን፤፤

View Details

ያደገ ማንነት በጌታ ስለሚታመን ስለ ነገ አይጨነቅም ማቴ 6:34 ማቴ 7:24 ሉቃ 12

View Details

እረፍት ኢየሱስ ነው:: ለእረፍት ተጠርተናል: እረፍት ከመዳናችን ጋር የተያያዘ ነው እንጂ ከሁኔታዎች መለዋወጥ ጋር የተያያዘ አይደለም:: እረፍት ውስጥ አለን ማለት ልባችን አይምሮአችን ሀሰባችን በክርስቶስ የተጠበቀ ነው ማለት ነው:: ማሳረፍ የእግዚአብሔር ባሃሪ ነው: እኛ ራሳችንን ማሳረፍ አንችልም::

View Details

ነገሮቻችንን ወደ ጌታ ማምጣት ጌታን ወደ ነገሩ ያመጣዋል ማቴ 11:27 ማቴ 17:17 ማቴ 8:7

View Details

በጽሎት ማደግ ማቴ 16:21 ኢሳ 43 መዝ 22 1ኛ ነገ 17 ሰቆ.ኤር 3

View Details

የጌታን ድምጽ በግል መስማት ዮሐ 5:25 ዮሐ 10:4

View Details

ጌታ ይቅር እንዳለን የበደሉንን ሁሉ ይቅር ማለት አለብን። በዚህ ክፍል ውስጥ የምንማርው ቂምና ጥላቻ ካለብን የእኛም ሀጥያት ይቅር እንድማይባልና ፀሎታችንም እንደማይመላስ ነው። ይህም ደግሞ ደስታችንን አና በረከታችንን ይይዛል። ስለዚህ ሁልጊዜ እራሳችንን እየመረመርን ከእንደዚህ እይነት ሀጥያት ልንመለስ ይገባል። ይቅር ማድረግ ፣ሰውን ሁሉ መውደድ ጌታን ደስ ማሰኘት ይገባናል።

View Details

ከእግዚአብሔርና ከቅዱሳን ጋር ያለን ህብረት ጤናማ እንዲሆን ያስፈልገናል። በዚህ ክፍል የምንማረው ለዚህ ጤናማ ህብረት የሚያስፈልጉንን ነገሮች እና እደራረጉን ነው።ይህም፣አለምዊ ምኞትን፣ የስጋ ምኞትን የአይን አምሮትን እና ስለ ገንዘብ መመካትን ማስወገድ ነው። ይህንን ስናደርግ ህብረታችንን በሁሉም አቅጣጫ ጤናማ ይሆናል።

View Details

ከተቀበልነው ጸጋ አንዱ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፣እግዚአብሔርን መፍራታችን የመቀደሳችን ምልክት ነው፣ አካሄዳችን የተስተካከለ መሆኑ የሚታወቀው ቃሉን ከመዳፈርና መንፈሱን ከማቃለል ወጥተን ጌታን ስንፈራ ነው፣ እግዚአብሔርን እያወቅን ባደግን ቁጥር የእግዚአብሔር ፍርሃት በህይወታችን እየጨመረ ይሄዳል የሚያስፈራንና የሚይስደነግጠንም እርሱ ብቻ ይሆናል፣ ፣ አይምሮአችን በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር ካልሆነ ግን ሌላው ቅዱስ ያልሆነው ፍርሃት አይምሮአችንን ይቆጣጠረዋል በዚህ አይነቱ ፍርሃት ውስጥ ስንሆን ደግሞ እግዚአብሔር የተናገረንን በጎ ነገር ሁሉ ከጃችን ያስጥለናል እግዚአብሔርንም የመስማት አቅም እንዳይኖረን ያደርጋል፣

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ምሳሌ 29፣24 የእኛ ያልሆነውን ነገር መውሰድ ሌብነው ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 2. ለአገልጋዮች ማድረግ ያለብን በጎ አድራጎት ምን ድረስ ነው? 3. ወደ ፊት እንዳንሄድ ህይወታችንን የያዚ ነገሮች አሉ ስለዚህ ብዙዎች ያላመለጡ ክነገሮች ጋር ያልተፋቱ ብዙዎች ናቸው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 4. ምሳሌ 29፣27 ሰዎች መልካም ሲያወሩልን እንጠንቀቅ የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 5. ጸጋን መቅመስና ተቀባይ መሆን የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 6. ያነበብነው ቃሉን መያዝ ካልቻልን እንዴት ነው ትንቢትን በቃሉ መመርመር የምንችለው? 7. ከሌላ ቤተ ክርስትያን መጥተው ትንቢትን ሲናገሩ ሀሰት መሆኑን እንዴት ነው የምናውቀው?

View Details

እግዚአብሔር ካልቀ ከተቆረጠ ምን እንሆናለን ካልንበት ነገር ውስጥ አዲስ ምዕርፍ አለው፤ በምናልፍበት ችግር ነው በምንለው ውስጥ እግዚአብሔር አለ እርሱ የሌለበት ችግር አልፈን አናውቅም፤ በሰው ልብ የሌለ በሰው ሃሳብ ውስጥ ያልታሰበ ነገር ግን ሁልጊዜ ባለቀ ነገራችን የሚያደርገውን የሚያውቅ የሰራዊት ጌታ ድንቅ ሠሪው በመካከላችን ከእኛ ጋር አለ፤ የእኛ ነገር ያለቀው እየሱስ ባለበት ነው። ዮሐንስ - 2:1-10

View Details

እድገት እራስን መለወጥ እና ለሀላፊነት መብቃት ነው 1ኛ ቆሮ 13:11 አሞ 6

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ምሳሌ 29፣ 24 ከሰዎች ሁሉ የራሳችን ያልሆነውን ለመቀበል መጠንቀቅ አለብን ወይ? 2. ምሳሌ 29፤25 ሰውን ማክበር እና መፍራት ልዩነቱ ምንድን ነው? 3. ሮሜ 15፤3 ዕብራውያን 3፤16 ክርስቶስን ወደ መምሰል መምጣት የምንችለው እንዴት ነው? 4. ሰዎች ያደረጉትን መልካም ነገር ስንለወጥ እንዴት ነው በህይወታችን ማለፍ የምንችለው? 5. እንዴት ነው በህይወታችን የእግዚአብሔር ቃል የሚመራን? 6. ሰው ራሱን ለበግዛት በመንፈስ ቅዱስ መሞላት አለበት ወይ? 7. የማያምን የትዳር ጓደኛ ቢኖረኝ የሚያደርገው ነገር ከህይወቴ ጋር ይደባለቃል ወይ? 8. በመንፈሳዊ ህይወት ማሸነፍ ያለው ከመሸነፍ ህይወት ውስጥ ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 9. ምሳሌ 29፤20 ችኩል ሰው መንገሳዊ ፍሬ ሊያፈራ አይችልም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን።

View Details

ያወቅነውን የጌታን ቃል ምን ያህል እንኖረዎለን? ሉቃ 5:9

View Details

አይንን የፈጠር አምላክ ያያል በጨነቀን ግዜ ያያል፡ እግዜአብሔር ፍርድን አደላዳይ የሚያይ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር ያያል የሚለው እውቀትና መገለጥ በጥንቃቄ እንድንመላለስ፥ በጨነቀን ጊዜ አጉረምራሚ እንዳንሆን፥ ውለታውን እንዳንረሳ፥ እግዚአብሔርን እንዳንከስ፥ ባልተመቸ ቀን ያስጥለናል እንድንቆም ያድርገናል።

View Details

ራስን መግዛት እና እግዚያብሔርን ለመምሰል ራስን ማለማመድ ገላ 5:22 ምሳ 25:28 1ኛጵጥ1:5 1ኛ ጢሞ4:8 መኃ2:4 ኤር 4:6

View Details

ጌታን የምናገኘው በተውነው ልክ ነው፣ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሆኖ ሳለ ከእግዚአብሔር ጋራ መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጥረውም፣ እራሱን ዝቅ ባደረገ ክብሩን በተወው ልክ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፣ ሙሴም ካደገ በኃላ ባደገበት ቤት ያደገበት ነገር ሳይሆን የወረሰው የተወለደበት አላማ ነው፣ ዛሬም እኛ በሰማነው ልክ ሳይሆን ስለ ክርስቶስ በተውነው ልክ የእግዚአብሔር ክብር በኛ ይገለጣል ደግሞም በተውነው ልክ ብድራት ይከፈለናል

View Details

ተሸንፎ ማሸነፍ የመንፈሳዊ ሰው እድገት ውጤት ነው ማቴ 5:3-12 ዮሐ 10

View Details

ስልቹነት ያለማደግ ምልክት ነው 1ኛ ጴጥ 2:3 1ኛ ነገ 19 2ኛ ነገ 2:10-12

View Details

በላይ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን የመጥራቱን ሃሳብ ለመያዝ ስንገሰግስ አሉ የሚባሉ ችግሮች ሁሉ የምናልፋቸው ናቸው፤ ነገር ግን ወደዛ የማንገሰግስ ከሆነ እነዛ ችግሮች የሚያልፉ አይመስለንም፤ ይህም መከራ ያልፋል ማለት የምንችለው ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን ሃሳብ ማየት ስንችል ነው

View Details

ጾምን አወጅን ስንል በመጀመሪያ ከክፉ ሀሳባችንና መንገዳችን በእውነተኛ ንሰሃ መመለስ ፤ ከምግብና ከሚጠጣ ብቻ ሳይሆን ከሚያዝናኑ ነገሮች ጭምት ሆነን በሁለንተናችን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን በማዋረድ ፤ የምንፈልገው አንተንና ከአንተ ብቻ ነው በማለት አለመቻላችንን አውቀን ፤ እውቅናን ለልኡል እግዚአብሔር በመስጠት ትችላለህ እያልን ከእርሱ ብቻ ለመስማት ራሳችንን በፊቱ ማዋረዳችን ነው

View Details

የእግዚአብሔር ሕዝብ የተሰጠው የክህነት አገልግሎት ስለሆነ የህዝብን ህጥያት ለብሶ በእግዚአብሔር ፊት ይጮሃል። በዚህ ትምህርት ውስጥ የብሉይ ኪዳን አገልጋዮች፣ ሙሴ፣ኤርሚያስ እንዴት ለህዝብ እንደማለዱ እንዲሁም ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን እንዴት ባለ ብርቱ ጩሀት ምህረትን ፣ ፈውስን እና ይቅርታን ከአባቱ ዘንድ እንዳስገኘን በስፊው እንማራለን።

View Details

በሰላም ወቅት የተደረገውን መልካምነት በክፉ ቀን የማየርሳ ማንነት መዝ 103 ሮሜ 16 ዕብ 6

View Details

የእግዚአብሔር ቃል የፀና ነው። በዚህ ትምህርት ውስጥ የቃሉን ወተት ሁልጊዜ ልንጠጣና፣ ልናድግ እንድሚገባን እንማራለን። ጴጥሮስ ወደ ጌታ መሄጃው ጊዜ እንደደረሰ አውቆ አምኞችን በእግዚአብሔር ቃል እንዲተከሉና እንዲያድጉ እየመከራቸውና እያሳሰባቸው፣ የእግዜብሔር ቃል ከየትኛውም ትንቢት የፀና እንደሆነ ይነግራቸዋል። ለእኛም በዚህ ብዙ አይነት የስህተት ትንቢትና ትምህርት በበዛት ዘመን ላለን የሚመክረንና የሚያሳስበን ይህንኑ ነው።

View Details

ያደገ ሰው በተቀርፀበት ማንነት የሚገለጥ ነው ሮሜ 15:3 ዕብ 13:16

View Details

ነገሮችን ሁሉ በእግዝያብሔር ቃል የሚመርምር ማንነት 1ኛ ተሰ 5:20-21 ፊሊ4:8

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ኢየሱስ ያልበቃው ሰው ምንም ነገር የማያረካው ሰው ነው እንዲህ አይነቱ ሰው በህይወቱ እድገት የለውም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 2. ኤፊሶን 2፡6-7 ማርቆስ 5፡36-39 ጌታ የሚሰጠንን ነገር ቁጭ በሉ በማለት ነው የጀመረው የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 3. ዘፀ 14፡13 ቁጭ ያለ ሰው በመጨረሻ ቆሞ ይገኛል የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 4. ዮሐንስ 20፡23፣ ማቴ16፡19 18፡18 የሚሉት ይብራራልን። 5. ጌታን ከመከተል ወደ ጌታን አለማወቅ ልንገባ እንችላለን ወይ? 6. ወንድሞችን ማስቀደም ጌታን ከማስቀደም ጋር ያለው ልዩነት ምንድን ነው? 7. በጌታ የሚቀድሙንን እስከ ምን ድረስ ነው ማስቀደም ያለብን?

View Details

የእግዜአብሔርን ጸጋ መቀበያ መጠን፣ እግዚአብሔርን መስማት መጠን ነው፤ እግዚአብሔር እኛን ባገኘበት መጠን እኛ ድግሞ እራሳችን በሰጠንበት መጠን ነው እግዚአብሔር የሚናገረው። በእግዚአብሔር ከታቀደልን ከዘላለም ሃሳብ ጋር የምንገናኘው እነሆኝ እኔ ምን እንዳደርግ ትወዳለህ ብለን እግዚአብሔር ሲናገረን እኛ በሰማነው በኩል ነው። ከእግዚአብሔር የሰማ ሰው የሄደበትን ደግሞ አይሄድም የኖረውን ደግሞ አይኖርም። ሙሴ እግዚአብሔር ከተናገረው በኃላ አንድ በትር ይዞ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ ሊያወጣ ተነሳ።

View Details

አንድ እውነተኛ ክርስቲያን የተጠራው ክርስቶስን ለመምሰል ነው። ስለዚህ ጳውሎስ ያለውን ሁል ስለክርስቶስ እንደ ጉድፍ ቆጥሮ እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ እንዳለ እኛም ስለክርስቶስ መተው ያለብንን ነገር እየተውን ለሌሎች ምሳሌ በመሆን ክርስቶስን እየመሰልን የእግዜአብሔርን ፍቃድ ምን እንደሆነ አውቀን፣ በፍቅር የተሞላ ህይወት ሊኖረን የገባል። 1ኛ ቆሮንቶስ 11:1

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ኢዮብ 19፡25-27 እኛ የምናልፍበት ችግር ወይም መከራ የእግዚአብሔር ክብር መግለጫ እንደሆነ የማውቅበት መንገድ ምንድን ነው? 2. ትዕግስት የሌለን ሰው ከሆንን እግዚአብሔር አያገኘንም ማለት ነው? 3. ዮሐንስ 3፡13 ያለንን ጥበብ እና ማስተዋል የምናሳይበት መንገድ አለ ወይስ ቃሉን ማንበባችና መጸለያችን ነው? 4. ሰዎች በሰማያዊ ጥበብ ይናገሩን ወይም የራሳቸውን ጉድለት መሸፈን ይህን እንዴት ነው የምንለየው? 5. ብዙ አማኞች አሉ ነገር ግን ለተቀደሰ ሰልፍ ግን ብቁ አይደሉም የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 6. ምሳሌ 29፡9 ጠቢብ ይጣላል ወይ? ጠቢብ የሚጣላው ከሀጢያት ጋር ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 7. በህይወታችን የሚይልፈው መፍራትና መታወክ መሆኑን እንዴት ነው የምናውቀው?

View Details

የሰው ትክክለኛ ማንነት ሁሉ በሞላና በተደላደለ ጊዜ እና በጨነቀው ጊዜ ይገለጣል ዘፍ 22 መዝ 118:5-6 ያቆ 1:1 1ኛ ጵጥ 5:10 ዘዳ 32:15

View Details

የማይርካ ማንነት እና መንፈሳዊ እድገት ጢሞ 6:6 ፊሊ 4:11 መዝ 73:25

View Details

ያረፈ የተረጋጋ እና የተቀመጠ ማንነት ዘጸ 14:13 ቆላ 3:3 ኤፊ 2 ሮሜ 14

View Details

ህይወት የሆነው ክርስቶስ እና በህይወት ውስጥ መኖር ኤፊ 1:13 ማቴ 18:8-9 1ኛ ዮሐ 5:12 ዮሐ 15:7 ሉቃ 2:49 ዮሐ 6:26

View Details

መንፈሳዊ ሰልፍ የሌለበት መንፈሳዊ ጉዞ ውርስ የሌለው ነው ሐዋ 14 ሉቃ 9፡62 2ኛ ዜና 25:7-10

View Details

ቤተክርስቲያን ህያው የሆነች የእግዚአብሔር ተቁዋም ነች፤ ወደ ክርስቶስ የፈለሱ አዲስ ፍጥረት የሆኑ ዳግመኛ የተወለዱ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ህይወት ያገኑ የዳኑ የቅዱሳን ስብስብ ነች ቤተክርስቲያን።

View Details

እኛ የተጠራነው ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሀንን ሲሆን ለሌሎች እንድናበራና ሌሎች ለእግዚአብሔር ምስጋናን እንዲያቀርቡ ነው፣ የተጠራንበት ጥሪ የልጅነት ጥሪ ነው ደግሞም በሰውና በእግዚአብሔር መሀል ገብተን ለማስታረቅ ካህን ለመሆን ነው፣ እንግዲህ የተጠራነው እንደወደድን እንድንኖር ሳይሆን በብርሃን እንዳሉ በእግዚእብሔር እንደተወደዱ ልጆች ዕለት ዕለት እግዚአብሔርን ለመከተልና ለቃሉ ክብርን እየሰጠን ሳንፈራ ለክህነት ስራችን እንድንተጋ ነው፣

View Details

ትልቁ የአምላካችን የእግዚአብሔርን ድምጽ የምንሰማበት መንገድ ቃሉ ነው: ይሄ ህያውና ክቡር ቃሉ አይሻርም መዶሻ ነው እሳት ነው ዘላለማዊ ነው የሚሰራ ሁለት አፍ ካለው ስይፍ ይልቅ የተሳለ ነው::

View Details

እግዚአብሔርን ማንም አላየውም ነገር ግን አንድያ ልጁ ተረከው አንደሚል ቃሉ፣ እግዚአብሔርን በሚገባ የገለጠው ጌታ እየሱስ ነው። እንዲሁም ሐዋርያቱ አብረው ከጌታ ጋር ስለነበሩ ያዩትንና ከእርሱ የሰሙትን መስክረዋል። በዚህ ክፍል እኛም በክርስቶስ የሆንን የባህርይው ተካፍዮች ከሆንን ምስክሮቹ እንደሆንን እንማራለን። ይህም እግዚአብሔር ብርሀን እንደሆነ ጨለማም በእርሱ ዘንድ እንደሌለ ፤እኛም በብርሀን ልንመላለስ እንደሚገባንና ደግሞም ጨለማ በእኛ ዘንድ ካለ ንሰሀ መግባትና መመለስ እንዳለብን እንጂ በዚህ ዘመን እንደሚያስተምሩት በስጋ የሚደረግ ሀጢያት ምንም አይደለም ብለን እንዳንጠፋ ያስጠነቅቀናል።

View Details

እግዚአብሔር የስጠንን ደስታ የሚስርቁብን ነገሮች ምን እንደሆኑ ጠንቅቀን ተረድተን ከህይወታችን እንዴት ልናስወግዳቸው እንደምንችል ያስተምረናል። ደስታችንን የሚሰርቁብን ነገሮች ብዙ ናቸው። ነገር ግን በዚህ ትምህርት ውስጥ ፍርሀትን፤ገንዘብን መውደድና፤ ጭንቀትን እንመለከታልን። መፍትሄያቸውም፣ሁኔታን ስይሆን ጌታን መፍራት፤ ገንዘብን ሳይሆን ጌታን መውደድ፣ መጨነቅ ሳይሆን ጌታን ማመን እንደሆነ በሰፊው ያስረዳናል ።

View Details

የእግዚያብሔር እውቀት የእድገታችን መሰርት ነው ዘፍ 12 ዮሐ 10 1ዮሐ 5:20 ዮሐ 4 ዮሐ 9 ማቴ 16

View Details

የተወደደ ቀን እንዳለ ሁሉ የክፉ ቀንም እንዳለ ልንገነዘብ ያስፈልጋል። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደሆነ ፣እንደማይተወን ፣ያለ እርሱ ፈቃድ በህይወታችን ምንም እንደማያገኝን ልናውቅና ልንረዳ ያስፈልጋል። በስይጣን ሽንገላ እንዳንታለል አዕምሮእችንን ልንጠብቅ ይገባናል። የመጀመሪያና ትልቁ ነገር በዚህ እውነት ውስጥ ሆነን ምሽጋችንን መጠበቅ ነው። በዚህ እውነት ከቆምን ውጊያው የጌታ ስለሚሆን አሸናፊዎች ነን። ይህንን እውነት ጥለን ግን አዎ፣ ጥሎኛል፣ትቶኛል፤ ከእኔ ጋር የለም ካልን በሰይጣን ውሸትና ሽንገላ ተታለን እንወድቃለን።ሰይጣን ሸንጋይና ውሸታም ነው።

View Details

እግዚአብሔር ሲመጣ ያልጠበቅነውን የክብሩን ስራ ሊያደርግ ነው፣ እግዚአብሔር ስውን ድንገት አይጎበኝም ነገር ግን ሰው ለጉብኝቱ የበቃ እንዲሆን የሚጎበኘውን ሰው ያበጃል ይሰራል ይመክራል ደግሞም ያስተምራል፣

View Details

ያደገ ሰው እግዚያብሔርን ያስቀድማል ማቴ19:4 ዘፀ 12:15 ዘሌ 23:5 ዘፀ 4:23 1ኛ ሳሙ 14

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ምሳሌ 29፡5 ከወዳጆቻችን ጋር ስህተትን ስህተት ካላልን የራሳችንን ፅድቅ የለንም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 2. ለወንድሙ መብራት መሆን ያልቻለ ጽድቅ የለውም የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 3. ከምስጋና ህይወት እንዴት ነው ወደ ማጉረምረም ህይወት የምንመጣው? 4. እግዚአብሔር የደበቀውን አንዳንድ ግዜ እኛ ልናወጣው እንፈልጋለን ይህ ደግሞ ዋጋ ያስከፍለናል የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 5. ለእስላም ወንጌልን ለመንገር ቁራን ማንበብ ጥሩ ሀሳብ አይደለም ወይ? 6. ሰማያዊ ጥበብን ከምድራዊ ጥበብ እንዴት ነው የምንለየው? 7. ሰማያዊ ጥበብ በህይወታችን የማይገለጠው በምን የተነሳ ነው?

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. እግዚአብሔር ሰውን እንዲያነሳ ሰው በመጀመሪያ መጣል አለበት ወይ? 2. ከሁሉ መጣል በሗላ ነው መነሳት ያለው ወይስ ሌላ መታል አለ? 3. በሩን የዘጋሁት እኔ ልሁን እግዚአብሔር መሆኑን እዴት ነው እንዴት ነው የምናውቀው? 4. ሰው ባለፈበት ባልተፅናናበት ለሌላውን ሰው ማጽናናት ይችላል ወይ? 5. እግዚአብሔርን በመጠበቅ እንዴት ነው ህይወታችንን የምንመራው? 6. ሰው እግዚአብሔርን ከመፈለግ ሰደ አለመፈለግ መሄድ ይችላል ወይ?

View Details

እድገት ጥበብ እና እውቀት በአንድ ላይ መጨመር ማለት ነው ማቴ 10 ያቆ 3:13 2ኛዜና 9:22 መክ 2:3 መክ 1:18 ቆላ 4:5

View Details

እንዳደግን አንዱ ትልቁ ምልክቱ መጽናኛችን መንፈስ ቅዱስ ሲሆን ነው ዘፍ 16 ሮሜ 14:17 ሐዋ 9:31 2ኛ ቆሮ 12

View Details

እራሳችንን በጌታ ብርሃን ማወቃችን እና ይህ ብርሃን እየጨመር ሲመጣ እየለወጠን እየጠራን እያስጠጋን ሲመጣ ማደጋችን ይታውቃል ኢሳ 6:1 ዮሃ 13:37 1ኛ ቆሮ 15 ቲቶ 3:4-6

View Details

ጌታ ተመልሶ እንደሚመጣ በብዙ የመጽሐፍ ቅድስ ክፍሎች እንደተናገረን ሁሉ ተዘጋጅተን እንድንጠብቀውም መክሮናል:: መንፈሱና ሙሽራው ና ይላሉ ምክንያቱም የሁሉ ጥያቄ መልስ ያለው ዳግም በመምጣቱ ውስጥ ነውና፣ ያቀን በድንገት እንደሌባ ይመጣልና ነቅተን በንፅህና እንጠባበቅ::

View Details

ያደገ እውነት የበራለት ስው ለይቅርታ የማይቸገር እና በመንፍሳዊ ህይወቱ የሚተጋ ይሆናል ሉቃ 19:1-10

View Details

ሕዝቅያስ በእግዚአብሔር በመታመን በታላቁ በአሶር ንጉስ የመጣውን ታላቅ መከራ በድል እንደተወጣ ሁሉ፣ የእግዚአብሔር ልጆችም በእርሱ በመታመን ፣ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ(በፀሎት) እንዲሁም እግዚአብሔርን በመጠበቅ በሚገጥማቸው የህይወት ፈተና በድል መወጣት ይችላሉ። ሁሉም ቅዱሳን አባቶች የመከራን ቀን ድል የነሱት እግዚአብሔርን በመታመን ነውና ።

View Details

ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው በጌታ ላይ ነው ደግሞ ራስ የሆናትም ጌታ ነው፤ ቤተ ክርስቲያን ህያው በሆነው ክርስቶስ የተጠራች፣ የእርሱ የሆነች፣ የእኔ የሚላት፣ የሚመግባት፣ የሚንከባከባት፣ የሚያስውባት፣ የሚያሳድጋት፣ አካሉ ናት፤ እኛ ደግሞ በእርሱ ያምናምን ወደዚህ አካል ነው የገባነው፣ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፣ አንዳችን የአንዳችን ጉዳይ ይሰማናል ስለዚህ በማንፈስ አንድነትና በፍቅር ይህን አካል ላማነጽ እንትጋ፤

View Details

ለማደግ የእግዚያብሔርን ነገር ማስተዋልና የእግዚያብሔርን ውለታ መስብስብ ወይም መያዝ ያስፈልጋል መዝ 103 ኢያ 1 መዝ 50:23

View Details

የማደግ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ለእግዚያብሔር እራስን እየሰጠን መምጣት ሲሆን ሌላው ደግሞ የራሳችንን ሸክም ለመሸከም የበቃን ሆኖ መግኝት እና የመንፍስ ፍሬን ማፍራት ናቸው 1ሳሙ 1:24-28

View Details

ወደ ከበረው የእግዚአብሔር መዝገብ የምንገባው ፈቅደን ከተዋረድንበት ከተጣልንበት ነው፤፤ ከተዋረድንበት በጊዜው ያከብረናል ከተጣልንበት በጊዜው ያነሳናል ዝቅ ካልንበት በጊዜው ከፍ ያደርገናል፤፤ በምድር ላይ ጸንቶ የሚኖረው ክብር እግዚአብሔር ያነሳው ክብር ብቻ ነው፤፤

View Details

እግዚአብሔርን ስንጠብቅ ኪስራ የለም። አለመጠበቅ ግን አመጽ ነው። እርሱን ጠብቆ ማፈር የለም።እግዚአብሔርን ከሁኔታ፣ ከእድሜ፣ከእድልፈንታ ጋር ሳናስተያይ ብንጠብቅ እንጠቀማለን።የምንጥብቅበትን ጸጋ አየሰጠ፣ አይዞህ አይዞሽ እያለ ወደ ጠበቅንበት መልሳችን ያደርሰናል።

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. እግዚአብሔር የሚያደርግልን ስለ ስሙ እንጂ ስለ ፆምን እና ስለ ፀለይን አይደለም የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 2. በህይወታችን በሚያልፈው ነገር እንዴት ነው ወደ ማጉረምረም ህይወት ልንገባ የምንችለው? 3. ምለን የገባንበት ነገር ስንነካ እግዚአብሔር እኛን ይነካል የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 4. መስቀል በተለያየ ምክንያት የምናልፈው ችግር ነው ወይስ ስለ ክርስቶስ የምንቀበለው መከራ? 5. ሰው እንዴት ነው በአገልግሎት አድጎ በህይወት ላያድግ የሚችለው? 6. በመጠበቅ ውስጥ እንዴት ነው የእግዚአብሔርን ፍቃድ ልናውቅ የምንችለው?

View Details

ለማደግ በስፍራ መገኝት 1ኛ ጵጥ 3 1ኛጢሞ 5:22 1ኛጢሞ 6:20 2ኛጢሞ 1:14 1ጢሞ 6:30 ገላ 6:1

View Details

ለእድገት የሚያስፈልጉን ነገሮችና ለማደግ የሚጠቅመን ነገሮች ምንድን ናቸው? 2ኛ ጢሞ 4 2ኛ ጢሞ 2:1-2 ቆላ 1:28 ሮሜ 1

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ጌታን እንድንቀበል መንፈስ ቅዱስ እንዲያበራልን ያስፈልጋል የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 2. መንፈስ ቅዱስ የማይመራው አማኝ ህይወቱ አደጋ ላይ ነው የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 3. እግዚአብሔር እጃችንን ይዞ መንገዳችን ግን ለጠላት ሊሰጥ ይችላል የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 4. በልጆቻችን ላይ እንዲሆን የምንፈልገው የእግዚአብሔር ፍቃድ ይሁን አይሁን እንዴት ነው የምናው ቀው? 5. እንደ አማኝ ህልም ስናይ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? እግዚአብሔር ህልም ይሰጣል ወይ? 6. በእምነት ለማደግ ከእኛ የሚጠበቀው ምንድን ነው?

View Details

እግዚአብሔር የልቡን ሀሳብ በእኛ በባሪያዎቹ ያየውን አስደናቂውን ነገር አይችልምን ይችላል አይሆንምን ይሆናል እያደረገ አምጥቶ ክእኛ ህይወት ጋር የሚያገጣጥመው ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤፤

View Details

በጌታ ሆኖ ለሌሎች መታወቅ ሮሜ 16፡10 ዕብ 4፡15 ፊሊ 2:19-22 ማቲ 10:25

View Details

የጥሞና ጊዜ እግሂአብሔር ፊት ያለምንም ጥያቄ መሆን ነው። ቅድስና እና ንጽህና ባለበት ህይውት ጌታን የምንንገናኝበት ነው። የጥሞና ጊዜ, እግዚአብሄር ፊት ሆነን ፈቃዱን የምንሰማበት ነው እንጂ የአንድ ጊዜ ሁኔታን ፈጽመን ብዙ የጸሎት ርዕሶቻችንን ይዝን የምንንቀርብበት አይደለም።ነገር ግን እርሱን የምንሰማበት ጊዜ ነው።

View Details

እግዚአብሔር ስለ ስሙ የሚሰራ አምላክ ነው። ጌታ ስለ ስሙ ሲሰራ ጸሎቴ ነው ልመናዬ ነው ብለን ልንመካ አንችልም፣ ካልንም ትዕቢት ነው። እግዚአብሔር ማንኛውንም ነገር በህይወታችን የሚሰራው ስለተቀደሰ እና ስለ ታላቅ ስሙ ነው። በእኛ ላይ ስለተጠራው ስሙ ሲል ይባርከናል የሚያስፈልገንን ይሰጠናል።ስለዚህ ልመናችንና ጸሎታችን ምስክርነታችን እንጂ ትምክህታችን ሊሆን አይገባም።ስሙ ከስሞች ሁሉ በላይ ነው። አጋንንትን ያንቅጠቅጣል ፣ ያስወጣል፣በሽታንም ይፈውሳል።

View Details

ሰው ለመንፈሳዊ እድገት ምን ያስፈልገዋል? ዕብ 11:6-7 ዕብ11:1 ሉቃ 24 ኤፌ 1:13 ሮሜ 5:1-6 ኤፌ2:8 ሮሜ 12

View Details

እያደግን እንደሆን በምን እናውቃለን? 1ኛ ጢሞ 6 ቆላ 3-17 1ቆሮ 10-31 1ኛቆሮ 12-13

View Details

በህይወት ለማደግ እንድንችል የሚርዱን ነገሮች ዕብ 5:11-14 1ኛ ጴጥ 2:2-3

View Details

እግዚአብሔር የራሱን የልቡን ሀሳብ ነው እንዲናገረን የምንፈልግው ወይስ የእኛን የልባችንን ሀሳብ ነው እንዲነገርልን የምንፈልግው!! በዚ ስብከት ራሳችንን እንመረምራለን፤ እግዚአብሔር የራሱን የልቡን ሀሳብ ሲናገረን ግን ታሪካችን ይለወጣል፤፤

View Details

በአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ጉባኤ ነች የጌታን አጀንዳ በምድር የምታስፈጽም፤ የኢየሱስ ሙሽራ ነች ዳግም ምጽአቱን የምትጠባበቅ፤ እግዚአብሔር ለአንድነት በአንድነት ቤተክርስቲያንን ጠራ፤ ቤቱ የእውነት አምድና መሰረት ነው

View Details

በህይወት ለማደግ እንድንችል ልናስተውላቸው የሚገቡ ነገሮች መክ 7:25 መክ 10:1

View Details

ወንጌል መንግስትን ያህል ትልቅ ነገር ከጀርባው ያዘለ ታላቅ ሐይል ነው፣ ይህቺ መንግስት ደግሞ በሰማይ ሆና በዚህ ምድር ግዛትዋን የምታሰፋ ስትሆን በመጨራሻው ዘመን የዚች መንግስት መቅረብ ለአለም ሁሉ ይነገራል፣ መንግስቱ ከዚህ አለም ስለአይደለች ማንም የማይጋራት ሁሉን የምትገዛ መንግስትና ዋስትና ያለበት የዘለአለም አምላክ ገዢዋ የሆነ በመልካም ዕንቁ የተመሰለች መንግስት ናት፣ ሃጢያታችንን በመናዘዝ በወንጌሉ አምነን የእግዚአብሔር ልጆች የሆንን ሁሉ የላይኛው መንግስት ወራሾች ስለሆንን በምድራዊ ነገር ላለመያዝ መትጋት አለብን፣

View Details

በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ፊልጵስዩስ መልእክት መቼ ማንና የት እንደተጻፈ እንማራለን፣ መልእክቱ የሚያተኩረው ደስተኛ ስለመሆን ነው፣ እውነተኛ ደስታ የሚገኘውና ለሁሉ ደግሞ መፍትሔ የሆነው ሁኔታ ወይም በምድር የምናገኛቸው ነገሮች ሳይሆኑ የምስራቹ ወንጌል መሆኑን ለማስርገጥ ዻውሎስ በሁሉ ደስ ይበላችሁ እያለ መልክቱን ሲያስተላልፍ በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ ነበር፣

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. 2ኛ ነገ5፡3 የደረስንበት የፈውሳችን መቀበያ በሩ እንደሆነ የምናውቀው እንዴት ነው? 2. አልፎ ማየት ያልቻለ አማኝ በር ከፍቶ ሰይጣንን እንደማስገባት ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 3. በጠዋት የምናደርገው ነገር ጣዖት ይሆንብናል እና በረከታችንን ይይዛል ብለን ተምረናል ግን አንዳንድ ሰዎች በጠዋት ተነስተን ቃሉን አንብበን ፀልየን በረከታችን ትይዞብናል ይላሉ ይህ የሚሆነው እንዴት ነው? 4. መንፈስ ቅዱስ እየመራን እንደሆነ እንዴት ነው የምናውቀው? 5. ሰውነታችንና መንፈሳችን የሚያረክሱ ነገሮች ምንድን ናቸው? 6. ጌታን ማወቅና ከጌታ ጋር መገኘት እንድነት አላቸው ወይ? 7. ቅንነትና ጽድቅ ይገናኛል ወይ? ቅንነት ባህሪ ነው ወይ?

View Details

እራስን እና የራስን ህይወት መጠበቅ ምሳ 1:33 1ኛ ጢሞ 4:13-16 2ኛ ነገ 9 ማቴ 25:1-25

View Details

እግዚያብሔር እይታ ውስጥ መሆንን ማየት. ዘፍ 16:13 ዘፍ 39:2-3 ዘፍ32

View Details

-የዛሬ ጥያቄዎች 1. አማኝ ሁሉ በልሳን መፀለይ ይችላል ወይ? 2. ምሳሌ 28፡17 ሰውን መጥላት መግደል ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 3. ነፍስን መንካት እግዚአብሔርን መንካት ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 4. ፀልየን ላልተመለሰ ፀሎት ለምን ብለን ለመጠየቅ ጊዜ አለው ወይ? 5. እግዚአብሔር በጸሎት ሲናገረን ባለማስተዋል ካለፍነው በህይወታችን ሊያስከትል የሚችለው ነገር ምንድን ነው? 6. የአባት ሀጢያት በልጅ ላይ ደግሞ ለማድረግ ተያያዥነት አለው ወይ? 7. በአባት ሀጢያት ምክንያት ወደ ልጅ እንዳይመጣ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? 8. ፊሊ1፡9-11 ቅንነት ጌታን ስናገኝ የምንቀበለው ነው ወይስ በፀሎት የምናመጣው ነው? 9. ቅን ያልሆነ ብልጥ ሰው ከጌታ ሰላም የለውም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 10. ፀሎት የሚያቅተን ለምንድን ነው? 11. አማኝ ስኬት ተብሎ የሚጠራው መክሰኑ ነው ወይ?

View Details

አንድ መንፈሳዊ ሰው አልኝ የሚለው ትልቅ ሃብት/ስኬት የሚመጣው በመንፈስ ቅዱስ ለመመራት ከበቃበት ነው። ሰው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው በመንፈስ ቅድስ ቁጥጥር ሲሆን ነው። እግዜአብሔር ሲመራን በመንፈስ ሃሴት እናደርጋለን።ምሪት እግዚአብሔር ወደ ሚከብርበት የሚያገናኝ መንገድ ነው። ለእኛም እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት የሚያስኬድ መንገድ ነው።

View Details

የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እኛ ነን፣ እንድ ቤት ሊከብር ካስፈለገ ባለቤት ሊኖረው ይስፈልጋል፣ በዋጋ ተገዝተናልና የራሳችን ስላልሆንን ለእኛ ለአማኞች ህይወት ባለቤት ሊሆንና ሊከብር የሚገባው ደግሞ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ነው፣ የከፍታችንና የሰላማችን ምንጭ እርሱ ነው፣ ስለዚህ ከማንነታችን ወጥተን ክርስቶስ በእኛ እንዲከብር በሚረዳን መንፈስ ቅዱስ ስር ዕለት ዕለት ራሳችንን በማስገዛት በቅድስና ልንኖር ይገባናል፣

View Details

የጥሞና ጊዜ ማለት በእግዚአብሔር ፊት መገኘት፣ እኛና እግዚአብሔር በትክክል የምንገናኝበት ስፍራና ሰዓት ነው፣ በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ የሆን ሰው የራሱ መሆን አይችልም፣ እንደቀድሞው አይነት ሰው አይሆንም፣ በዚህ ትምህርት ውስጥ ለጥሞና ጊዜ የሚያስፈልጉንን ነገሮች፣ ልናደርግ የሚገቡንና የጥሞና ጊዜ ለአንድ አማኝ ለምን እንደሚያስፈልግ በዝርዝር እንመለከታለን፣

View Details

ሰው ሸምግሎ አርጅቶ በስራው ሁሉ በእግዚአብሔር ከመባረክ የበለጠ ምንም ነገር የለም፣ ወደዚህ በረከት ለመምጣት ሚስጥሩ መታዘዝ ሲሆን ለመታዘዝ ማመን ያስፈልጋል ለማመን ደግሞ መስማት ያስፈልጋል፣ ከዘለአለም ጥፋት ያዳነንና በክርስቶስ እየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ያስቀመጠን እምላካችን የከፍታውን ስፍራ እንድንይዝ ይወዳል፣ ምንም እንኳን በምድር ብንኖር በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሾች ነንና በላይ ያለውን ለመሻት መትጋት አንዳለብን መፅሐፍ ቅዱሳችን በተደጋጋሚ ያሳስበናል፣ በህይወታችን የምንበረታውና የሰማዩን መንግስት በትጋት የምንጠብቀው ልባችን የተዘጋጀውን ያህል ነው፣

View Details

እግዚአብሔርን የሚፈራ ከሁሉ ይወጣል፣ እግዚአብሔር ታማኝና እንደቃሉ የሆን አምላክ ነው፣ በእርሱ የሚታመኑትንና በፍርሃት የሚያከብሩትን ያውቃል፣ እግዚአብሔርን በመፍራት የሚኖር ሰው ጠግቦ ይኖራል ከመልካም ነገር አይጎድልም፣ እግዚአብሔርን መፍራት አሁን ላለንበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለትውልድ የሚሆን በረከትን ማከማቸት ነው፣ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የጊዜው መነጋገሪያ ሊሆን ይችላል መጎብኘቱ ግን የበዛ ነው፣

View Details

ጌታን ስንከተል መከራ አለብን። በዚህም ደስ ልንስኝ ይገባል።ይህ መከራ በእኛ ብቻ የሚደርስ ሳይሆን በወንድሞች ሁሉ ላይ እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል። መጠንቀቅ ያለብን ክፉ አድርገን መከራ ብንቀበል ከጌታ ዘንድ ምንም ምስጋና እንደሌለን ነው።በምናልፍበት መከራ ውስጥ እግዜብሔር አይጥለንም።በተስፍ ይጠብቀናል፥ ከመከራውም ያወጣናል። ስለዚህ ጌታን ተስፍ እያደረግንና እያመንን በመከራ ውስጥ እንጽና ጌታንም እንጥብቅ፡፡

View Details

በጸሎት ውስጥ ያለ ማስተዋል ቆላ 2:2 ዳን 5

View Details

በንስሐ ከሐጢያቱ የተመለሰ ደግሞም ከውሀና ከመንፈስ የተወለደ አማኝ የእግዚአብሔር መንግስት ወራሽ ኔው፣ አማኞች የሆንን ሁላችን የዚህ መንግስት ወራሽ መሆናችን እጅግ በጣም ሊይስደስተን ይገባል ምክኒያቱም የምንወርሰው የእግዚአብሔር መንግስት ሁሉን የምትገዛ የዘለአለም መንግስት ፍርድ አደላዳይ ጌታ ንጉስ የሆነባት መንግስት ናትና፣ የሰማይ መንግስት ወኪል የሆነ አንድ አማኝ ለምድራዊው መንግስት ብቻ ቢያስብና ቢለፋ ምንም ትርፍ የለውም፣

View Details

ተቀድሰን እንድንኖር የስላሴ ሐሳብ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ይቀድሰናል፣ የእግዚአብሔር ቃል የማንጻትና የመቀደስ ሀይል ስለአለው የሚቀድሰን እግዚአብሔር ቢሆንም ፍላጎቱና ፈቃደኝነቱ ከእኛ ይጠበቃል፣ የጠራን ቅዱስ ስለሆን ስጋና መንፈስን ከሚያረክስ ማንኛውም ነገር ነጽተንና ተቀድሰን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደሚጠብቅ አማኝ በትጋት በእርሱ ውስጥ እንድንኖር ይጠበቅብናል፣ ስንቀደስ እግዚአብሔር በመካከላችን ድንቅ ነገርን ያደርጋል፣

View Details

በእምነት በጸለይነው ጽሎት ውስጥ መቆየት ሉቃ 1 1ኛ ሳሙ 14 ዘፍ- 26 መዝ 90:89 ዮሐ 16:30

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. አገልጋዮችን እንዴት ነው ማረም ያለብን? 2. ሰቆ ኤር 3፡27-29 “ሰው በታናሽነቱ ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው። እርሱ አሸክሞታልና ዝም ብሎ ለብቻው ይቀመጥ። ተስፋ የሆነው እንደ ሆነ አፉን በአፈር ውስጥ ያኑር።” የሚለውን አብራራልን። 3. “በእርሱ መኖን” የሚለውን ሀሳብ ግልጽ አድርግልን። 4. እውነታኛውን ህመም ጠላት ሊፈትነን ካመጣው ህመም እንዴት ነው የምንለየው? 5. ክርስቶስ የተነሳው በአካል ነው ወይስ በስብከት? 6. የሚያምን ልብ ክብሩ እንዲገለጥ ያዘጋጅለታል የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 7. አትስከር እንጂ አትጠጣ ነው የሚሉ ሰዎች አሉና ብታብራራልን? 8. አብርሃም ባልታመነበት ነገር የራሱን መንገድ እንዳዘጋጀ አይተናልና ብታብራራልን?

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. 1ሳሙ 13፡8-9 እግዚአብሔር ተናግሮን በመጠበቅ ፈንታ እርምጃን እንወስዳለን የሚለውን ሀሳብ ግልፅ ብታደርግልን? 2. እግዚአብሔርን መቅደም ማለት የራስን ጸሐይ ማውጣት ነው ይህ ደግሞ አይቻልም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 3. ምሳ 28፡8 በሥራ ቦታ አድሎ ሲደረግብን እርምጃ መውሰድ አለብን ወይስ እግዚአብሔር ጣልቃ እስኪገባ ድረስ መጠበቅ አለብን? 4. ስጋ ደሙን መውሰድ የሚችል ማን ነው? የሚከለከለውስ ምን ቢሆን ነው? 5. የአሳማ ሥጋ መብላት ተፈቅዳል ወይ? 6. ሲፀለይ እጅ ለእጅ በመያያዝ ፀጋ ይተላለፋል ወይ? 7. ህይወታችን ከክርስቶስ ጋር ተሰውራል የሚለውን አብራራልን። 8. ንስሀ መግባት ያለብን የጌታ ራት ስንወድ ብቻ ነው ወይስ ሁሌም ማድረግ አለብን?

View Details

ሰዎች በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ ስለ ተናገሩት ተቃራኒ ነገር ተባብረን ውድቀታቸውን ማውራት የተገባ አይደለም፣ ከመፍረድ በፊት የምንናገረውን ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል እየመረመርን ነው ማየት ያለብን፣ በዚህ መልክት ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል ስለ የሃሰተኛ አስተማሪዎችና ነቢያቶችን ባህሪይ ምን አንደሚል እንማራለን፣

View Details

የጸሎት ፈተናዎች ዮሐ17:11 ዮሐ 18 ማቴ 17 ማቴ 26 ሉቃ 8

View Details

መንፈሳዊ ነገርን በምድራዊ መስፈሪያ መስፈር አንችልም ብዙ ስዎች በመጽሐፍ ቅዱስ በምድራዊ ነገር ለሰው የከሰሩ በመሰሉበት አትርፈው እግዚአብሔርም ከብሮ እስከዛሬ ለብዙዎቻችን መልካም ምሳሌ ሆንውናል፣ የሰማዩን ስኬት የሚያመጣው የምድሩ ኪሳራ ነው፣ የምድሩን ኪሳራና አለመሳካት እንደበረከት አድርገን ካልቆጠርነው የእግዚአብሔር ቸርነትና በጎነት የሚገለጥበትን መንገድ ማየት አንችልም፣ እንዚህ ኪሳራዎች ወደ እግዚአብሔር ሐሳብ የሚያደርሱን ናቸው፣ ለኪሳራችን መወጣጫ በራሳችን መንገድ የምናዘጋጃቸው ዘዴዎች ከኪሳራ ወደ ሌላ ኪሳራ እኛን ከመክተት ሌላ መፍትሔ አይሆኑንም፣ መፍትሔው እግዚአብሔር ያየው እስኪመጣ ድረስ በስፍራችን ሆንን እርሱን መጠበቅ ነው::

View Details

የእግዚአብሔር ፈውስ ወደ እኛ የሚመጣውና የሚባርከን ክርስቶስን በምንመስልበት ነው፣ ጸሎት መልካም ነው ግን የምንጸልየው ለፈውስ ብቻ ሳይሆን ወደ ምሪት እንድንደርስ ነው፣ እንዳንዴ እግዚአብሔር እቅጣጫችንን ሲያሳየን በህይወታችን ያስቀደምነው ከርሱ ያስበለጥነውን ነገር ገልጦ ሊያሳየን ይችላል፣ ጌታ ሳይቀድም በረከትን መቀበል ስለማንችል ይህንን ከጌታ ያስበለጥነውን ነገር ካልጣልንና እግዚአብሔር በሰጠን አቅጣጫ ካልተመራን ከፈውሳችንና ከበረከታችን ጋር እንተላለፋለን::

View Details

ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ሲሞላ ፈሪ የነበሩ እንኳን በልዩ ብርታትና ሀይል ይቆማሉ፣ የተጠራነው ምስክር እንድንሆን ነውና በድፍረት ክርስቶስን ይመሰክራሉ፣ ደግሞም በልሳን ሲጸልዩ ሌሎች ሰዎች ይሰሟቸዋል፣ በሰላም የተሞሉ ናቸው፣ ሌሎች ሰምተው እንኪደነቁ የሚያመሰግኑ ደግሞ ናቸው፣

View Details

ችግር ወደ ጸሎት ያቀርባል ዮሐ 9

View Details

መንፈሳዊ ዕድገት ያለው በመቆየት ውስጥ ነው፣ እግዚአብሔር የሚያደርገውን ሁሉ ከክብሩ አኳያ ስለሚያደርግ ለአንዳንድ መልሶች ጌታ ለጥቅማችን ያቆየናል፣ ዘግይቶ የሚመጣበት ምክኒያት የመሸከም አቅም እንዲኖረን ነው፣ ደህንነታችንን የመያዝ አቅም በሚኖረን ጊዜ ሁሉን በጊዜው ያደርጋል፣ እኛም እግዚአብሔርን እንደ እግዚአብሔርለቱ ማክበር የምንችለው በቆየንበት ነው፣

View Details

ጸሎትን መከተል አስ 4:13-17 አስ 5 ማቴ 11:28

View Details

አለም ስጋና ሰይጣን አንዱ የመዋጊያ መንገዳቸው እኛን ከቅንነታችን እንድንጎድል ማድረግ ነው፣ ቅንነት ሲጎድለን በሰማነው መቆም ያቅተናል፣ እግዚአብሔር ጻድቅና በስራው ፍጹም የማይሳሳት አምላክ ስለሆን ቅን ለመሆን በገባንም ባልገባንም ነገር ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት ነው፣ አንድ አማኝ በቅንነት ለመኖር ሲወስን ብዙ የማይመቹና ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ይኖራሉ ሆኖም ግን ለአማኞች የተመረጠልን መንገድ ይህ ነው፣

View Details

ከጸሎት መራቅ ማለት ከእግዚአብሔር መራቅ ማለት ነው፣ እምነታችን በእግዚአብሔር ላይ ሲሆን በጸሎትም እየበረታን እንሄዳለን፣ ለብዙዎች እግዚአብሔርን ለሚያውቁ ሰዎች የህይወት ክንዋኔ አንደኛው መክኒያት ከእግዚአብሔር ጋር ግኑኝነትን ማድረግ ሲሆን የእግዚአብሔርን ጉብኝት እስኪመጣ ድረስ በጸሎት መትጋታቸው ነው፣ ዛሬም እኛ አማኞች ሃይልን ለመቀበለና የእግዚአብሔርም ጥሪ እንዲበራልን በጸሎት ልንተጋ ያስፈልገናል

View Details

እምነት በሌለበት ጥርጣሬና ፍርሃት አለ፣ አማኝ በእምነት እንጂ በማየት ስለማይመላለስ እግዚአብሔር ታማኝና በስሙ የተጠሩትን ለመጠበቅ የሚተጋ አምላክ መሆኑን በመረዳት እኛም ለተቀበልነው የህይወት አደራ ጸንተን መጋደል አለብን፣ አንዱ የመንፈድሳዊ መዋጊያ መሳሪይችን የጽድቅ ጥሩር ሲሆን ከእኛ የሆን ምንም ጽድቅ እንደሌለን ደግሞ መረዳት አለብን፣ ሰይጣን በሚከሰን በማንኛውም ሁኔታ ልናሸንፈው የምንችለው በክርስቶስ እየሱስ ጽድቅ ስንገለጥ ነው፣

View Details

እግዚአብሔር ብቻውን ሁሉን ሊያደርግ የሚችል አምላክ ስለሆን እርሱ አሻግራለሁ ካለ ለማሻገር የማናችንንም ድጋፍ አይፈልግም፣ በህይወት ማዕበልና ወጀብ ብዛት እምነታችን እየተፈተነ ሊሆን ይችላል ግን በድካማችንም ቢሆን ወደ እርሱ ስንጮህ ነፋሳት ማዕበሉና ውጀቡ ለቃሉ የሚታዘዙለት ጌታ ማዕበልና ወጀቡን ጸጥ ያደርገዋል፣ የጠራን አምላክ የሚያደርስ እንጂ መንገድ ላይ የሚተው እባት ስላልሆነ እርሱ ከያዘን በምንም አይነት ማዕበል ውስጥ ካለመናወጥ እናልፋለን፣ እምነታችንን በእርሱ ላይ ካደረግን ደግሞ ምንም የሚጥለን ነገር አይኖርም፣

View Details

ጸሎት እና ምፀዋት ሐዋ.10:1-4 ኢሳ 58 ዮሐ 13

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. አንድ ክርስትያን ድግምት ቢደገምበት በሽታ ላይ ሊወድቅ ይችላል ወይ? 2. አንድ ክርስትያን የጸሎት ህይወቱ ደካማ ከሆነ እንዴት ነው ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኘው?

View Details

ክርስትና በመናገር ብቻ ሳይሆን በአኗኗር የምናሳየው እምነት ነው፣ እራስን ሙሉ ለሙሉ ለጌት በመስጠት ሲጀምር፣ የሚጠሉንን በመውደድ፣ በእውነተኛ ትሕትና ከራስ ይልቅ ሌሎችን በማስቀደምና እግዚአብሔርን በጊዜውም ያለጊዜውም በማምለክ እንደሚገለጡ ይህ መልዕክት በሰፊው ያስተምረናል፣

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በዚህ ዘመን አንድ አማኝ ሀጢያትን ሀጢያት ለማለት ምንድን ነው ማድረግ ያለበት? 2. ፀሎታችን ወደ እግዚአብሔር ሀሳብ መለወጥ የለበትም ወይ? እንዴት ነው ወደዚህ ሀሳብ ማዘንበል የምንችለው? 3. በፀሎት መቆየት ማለት በአካል መቆየት ማለት ነው? ስንጸልይ ብዙ የጸሎት ርዕሶች ይመጣልናልና ይህን ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? 4. አንዳንዴ ነገር የሚከብደን ጸልየን በትዕግስት ስለምንጠብቅ ነው የሚሆንብን? 5. ሰው ሊያምን ግን ላይጸልይ ወይም ሊጸልይ ግን ላያምን ይችላል ወይ? 6. ደጋግመን ከመጸለይ ወደ እግዚአብሔር ሀሳብ መግባት የምንችለው እንዴት ነው?

View Details

በክርስቶስ ውስጥ መሰወር ቆላ 3:2-3 2ኛ ተሰ 3:3 ሮሜ 12፡12 ሮሜ 8:28

View Details

በእግዚአብሔር ፊት የሚታይ ማንነት ሲኖረን ጌታ ከማንኛውም ክፉ ነገር ይታደገናል፣ ጸሎታችንም የሚሰማው በእግዚአብሔር ስንታይ ነው፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚታይ ማንነት እንዲኖረን ቅንነትና እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ለቃሉ የምንታዘዝ መሆን አለብን፣ ያለ ቅንነት በእግዚአብሔር ፊት የሚታይ ማንነት የለንም፣ ዛሬ ከብዙዎቻችን ቅንነት ጠፍቶ እንኳን አንገነዘበውም፣ ግን ሲጎድልብን እናያለን፣ ነገሮች ሲከብዱብን ጸሎታችን አልሰማ ሲል መውደድ ሲያቅተን መራራትና ምህረት ማድረግ ሲያቅተን፣ ይህን ሁሉ በዘመናችን እያየን ስለሆነ፣ ከመቼውም በበለጠ በፊቱ ሞገስ የምናገኝበትን ጸጋ መለመን አለብን፣

View Details

አንዳንድ ጊዜ የማንወጣው የሚመስለን ችግርና መከራ ውስጥ ስንሆን መፍትሄ ወደምናገኝበት ልንሄድ እንችላለን ብዙ ጊዜ ግን እንዲደረግልን የምንጠብቀው ከሌለን ነገር እንደሚመጣ ነው፣ ጌታ ግን በእጃችን ያለውን ተስፋ የተቆረጠበትን አይጠቅምም አይበዛም ያልነውን ሊያበዛ የሚችል አምላክ ነው፣

View Details

ጸሎት ከተሰጠን ጸጋ ጋር መገናኘት ነው

View Details

የሚያስፈልገን ነገርና ጸሎት

View Details

ጌታ ሲጠራን በምንም እንዳንጨነቅ ነው፣ ምክኒያቱም እርሱ የሚያስፈልገንን ሁሉ ስለሚያውቅና በጊዜው የሚያስፈልገንን ሁሉ ስልሚያደርግልን ነው፣ የተጠራነው የመንግስቱ ሚስጥር ተገልጦልን የመንግስቱ ወራሾች ለመሆን ነውና ይሄ ሚስጥር ገብቶን አንዳች ነገር ሳይስፈራን የምንከተለውን አውቀን መንግስቱን በትጋትና በጽድቅ መጠበቅ አለብን::

View Details

ትልቁ እምላካችንና አባታችን እየሱስ ክርስቶስ እንኳን መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ነው ተአምራትን ማድረግ የጀመረው፣ እኛም ይህንን መንፈስ ዕለት ዕለት መሞላት ያስፈልገናል፣ በዚህ መንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር ስንሆን በመንፈስ መመላለስ እንጀምራለን፣ በእምነት በጽድቅና በቅድስና እንድንኖር ያግዘናል፣ ለአካሉም የምንመች እንሆናለን፣ በደልን የማንቆጥር ደግና ሩህሩህ ስለሚያደርገን ለአካሉም የምንመች እንሆናለን::

View Details

ሰው ባልነቃበት እግዚአብሔር አያልፍም፣እግዚአብሔር ለጽድቅ የሚያነቃቃን ከአመፅ ነፃ ስንሆንና ከራሳችን ፈቃድ ወጥተን ለእግዚአብሔር ፈቃድ እራሳችንን ስናስገዛ ነው፣ እግዚአብሔርን መፈለግ አንዱ የመነቃቃት ምልክት ሲሆን ይህ በትጋት የፈለግነው ቃል በመንፈስ ቅዱስ ለጽድቅ ለቅድስናና እግዚአብሔርን በመፍራት እንድንነቃ ያደርገናል፣ ፍሬያማም የምንሆነው ለህይወት የነቃነውን ያህል ነው፣ በመንፈሳዊ ማንነት ስንመላለስ ስጋን እንንቀዋለን ሃጢያትንም እንጠየፈዋለን፣

View Details

እግዚአብሔር ጸሎትን ይሰማል

View Details

ሰው ዛሬ ብዙ ነገር ከቤተሰቡ ሊወርስ ይችላል ግን ያ ሁሉ ያልፋል፣ የማያልፍ ዘለአለማዊ መንግስትና ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔር መንግስት ነው፣ ይህ መንግስት ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጆች ለሆኑ ለቅዱሳን ሁሉ ተሰጥቷል፣ ይህንን መንግስት በትጋት ስንጠብቅ ለሚገጥሙን ችግሮች የምልፍበትን ጸጋ ከጌታ ብንቀበልም ክዚህ ዘለአለማዊ መንግስት ሊያጎድሉን ከሚችሉ ነገሮች ልንጠበቅ ይገባናል፣ እነዚህም መዳናችንን ቸል ማለት፣ የማይምን ክፉ ልብ፣ ክሕደት፣ ወደን የሐጢያት ባሪይ መሆንና ለጊዜው በሐጢያት የሚገኝ ደስታ ናቸው፣

View Details

በጸሎት መቆየት

View Details

ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን፣ የእርሱ ልጆች ለመሆንና ለጽድቅ ለመኖር ከወሰንበት ቀን ጀምሮ እኛን ወደኋላ የሚስብ የሚያዘናጋና ከእግዚአብሔር ክብር እንድንጎል የሚተጋ መንግስት እንዳለ በማወቅ መንፈሳዊ ውጊያ ሁልጊዜ እንዳለ ልንረዳና የጦርነቱን አቅጣጫ ልናውቅ ይገባናል፣ ስለዚህም አንደ ትጉ ወታደር መዘናጋትን ከኛ አስወግደን ሁልጊዜ ቃሉን ታጥቀን ለጽድቅ ነቅተን እንኑር፣

View Details

እግዚአብሔር እጅ ትንሽ የምትመስል ግን ትልቁ የእግዚአብሔር በር ናት፣ የእግዚአብሔር አብሮነት በኛ የሚገለጠው ከአንድ ነገር ወደ ሌላ የምንሸጋገረው አቅጣጫችንንና እይታችንን የምትቀይረው በተዘጋ በር አዲስ ምዕራፍ የምትከፍተውና መከናወንን የምትሰጠው የእግዚአብሔር እጅ ስትመጣ ነው፣ ይህቺን የእግዚአብሔርን እጅ ከመቼውም በላይ በጸሎት በእግዚአብሔር በመታመንና ሰው ባለው ሳይሆን እግዚአብሔር ባለው መንገድ እየተራመድን በትጋት ልንሻት ይገባናል፣

View Details

የነቢያትና አስተማሪ የመሆን ጸጋ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ስጦት ሲሆን ጥሪውም የሚመጣው ከጌታ ነው፣ እግዚአብሔር አንድን ሰው ለዚህ ስራ ሲጠራ ጸጋውን የሚሰጠው በወሰነው ስፍራና ጊዜ ለፈቀደው ሰው ነው፣ እንዱ የሐሰተኞች ነቢያትና አስተማሪዎች መለያ በጥሪ ሳይሆን እራሳችውን ነቢያትና አስተማሪዎችዎች ብለው መሾም ሲሆን በዚህ ትምህርት ውስጥ ሌሎች ባህሪያችውንና የሚጠብቃችውን ፍርድ እንማራለን፣

View Details

ያመጣነውን ለጌታ መተው

View Details

እግዚአብሔር ላይ የታመነ ሰው ራሱን የጣለ ነው፣ እግዚአብሔርን በታመንነው መጠን ነው የአርሱ ማንነት በእኛ የሚገለጠው፣ እግዚአብሔርን ከመታመን ጋር አብረን ልናስኬድ የምንሞክራቸው የራሳችን የችግር መወጣጫ ዘዴና መላዎች መፍትሔ ሳይሆኑ ለጠላት መግቢያ ቀዳዳዎች ናቸው፣ የራሳችን ብልሃት ሁልጊዜ አደጋ ነው እንፈተንበታለን ደግመን ደግመን እንወድቅበታለን፣

View Details

የሰው ንጽሀናው ራሱን በእግዚአብሔር ላይ የጣለውን ያህል ነው፣ የትኛውም አማኝ በአግዚአብሔር ላይ ከተጣለበት በላይ ሃይልም አቅምም የለውም፣ በችሎቱ የበረታ የማንንም እርዳት የማይፈልገው ጌታ በራሳችን ማስተዋል መደገፋችን አያስደስተውም፣ እግዚአብሔር አቅም የሚሆንን ከራሳችን አቅም ሰንወጣና በእርሱ ሀይል ችሎት የበረታን ስንሆን ነው፣ ስልዚህ ከራሳችን ብርታትና ማንነት ወጥተን በጌታ ታምነንና በጸጋው ተደግፈን ልንኖር ያስፈልገናል፣

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ህይወቱን የማይጠብቅ ሰው አጥር እንደሌለው ነው። የሚጠበቅበት ቃሉና ጸሎት ነው የሚለውን ሀሳብ ግልፅ ብታደርገው። 2. ጠንቃቃ ሰው ለመንፈሳዊ ህይወቱም ጠንቃቃ ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 3. አንድነት ከሌለ መንፈሱ አያልፍም የሚለውን አብራራልን። 4. ለክርስቶስ ለመታዘዝ አህምሮን ሁሉ እንማርካለን የሚለው ምን ማለት ነው? 5. ስንፍናም ትጋትም ማንነት ነው የሚለውን አብራራልን። 6. አንድ አማኝ ሁለት ማንነት ሊኖረው ይችላል የሚለውን ሀሳብ አብራራልን።

View Details

እውነት ሲገለጥልን ያለው እምነት

View Details

እንዴት እንጸልይ ክፍል 20 እምንት እና ፈተና ነህ 9:8 1ኛ ጴጥ 5:6-11

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ያለግዜው የአለም ብርሃን መሆን ካልተቻለ እንዴት ነው የአለም ብርሃን መሆን የሚቻለው? 2. የእምነት ሰው ልንሆን እንችላለን ነገር ግን ከጌታ ሀሳን ልንጎድል እንዴት ነው የምንችለው? 3. አዳም ለሰራው ሀጢአት ምህረት አግኝቷል ነገር ግን ይሁዳ ምህረት ያላገኘው ለምንድን ነው? 4. በምድር ላይ እያለ የጌታ የሆነ ሰው አድጎ ይጨርሳል ወይ? 5. የምንሰማውን የእግዚአብሔር ቃል ለመያዝ ማድረግ ያለብን ምንድን ነው? 6. እድገት የማይቆም ከሆነ ባላደግንበት ስህተት አለ ማለት ነው? ስህተት ካለ እንዴት ነው ሚዛናዊ ህይወት ሊኖረን የሚችለው?

View Details

የእምንት መሰርት ሮሜ 10:17 ዮሐ4:4-29

View Details

የኋለኛው ቤተ መቅደስ ክርስቶስ ነው ደግሞም ቃሉ እንደሚል የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እኛ አማኞች በደሙ ነጽተን በክርስቶስ እየሱስ ልጆች የሆንን ሁላችን ነን፣ ይህንን ቤተ መቅደስ የሚበልጥ ያደረገው በሰው የተሰራ ሳይሆን አግዚአብሔር የሰራውና ህያው በመሆኑ ነው፣ ይህ ህያው ጌታ በመንፈሱ ለእርሱ በተሰጡ አማኞች ውስጥ ይኖራል፣ ከውጪ ሳይሆን በውስጥ ሆኖ ልጆቹን ይመራል፣

View Details

ለአንድ አማኝ ትልቅ በረከት በጌታ መገኘት ውስጥ ራሱን ማግኘት ነው፣ እምነት በእግዚአብሐር መገኘት ውስጥ እንድንገኝ ያደርገናል፣ ለቃሉ ታማኝ ስንሆን አንደ ቃልህ ወይም እንደፈቃድህ ይሁን ብለን ስንፈቅድ ለጌታ እንመቻለን፣ የምንኖረው ለህይወት እንጂ ኑሮአችን በህይወታችን ላይ ተፅእኖ እንዲያደርግ መፍቀድ የለብንም፣ የምናስበውን ለእግዚአብሔር ክብር ስናስብና በርሱ መገኘት ውስጥ ስንሆን ኑሮ ላይመቸን ይችላል ህይወት ግን ይመቸናል፣

View Details

መንፈስ ቅዱስ በሙላት የሚሰራብን እራሳችንን የሰጠነውንና የተጠማነውን ያህል ነው፣ የሰዎች ቋንቋ የተደበላለቀው ለክፉ ስራ ስለተባበሩ ሲሆን ይህንን የተለያየውን ቋንቋ ወደ አንድነት መንፈስ ለማምጣት ጌታ ለቤተ ክርስቲያን ይህንን የልሳን ስጦታ ሰጠ፣ ይህ ልሳን በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሰረተ እውነት ለመሆኑ ምስክር አንዲሆን ሰው በሚሰማውና በሚረዳው ቋንቋ ይነገራል፣ አማኝ ከእግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት የሚስጥር ቋንቋ ነው ደግሞም በሌሎች ሰዎች የሚተረጎምና ራሳችንን የምናንጽበት ነው፣ ይሀን ልሳን ለመቀበል ሰው ወደ እምነት መምጣት አለበት፣

View Details

እንዴት እንጸልይ ያዕ 2:14-26 ዕብ 10:38 ሮሜ 1:17 ገላ 3:11 ክፍል 18

View Details

ለዳንኤል የስኬት ምክንያቶች ለእግዚአብሔር በመቀደስ በጽድቅ ከመኖሩ ጋር በተጨማሪ የእምነት አጋሮችን ማግኘቱ ነው፣ ዛሬም እኛ በአካል ውስጥ እንዳሉ ብልቶች ከእግዚአብሔር በታች አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን፣ በተከፈተው በር ሁሉ በመግባት ህብረት ማድረግ ሳይሆን በእውነት ጌታን ከሚወዱ በጽድቅ መንገድ ከሚሄዱ ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር ህብረት ማድረግ ያስፈልገናል፣ ቃሉም እንደሚያስተምረን በአንድነት ተስማምተን የምንጸልየው ጸሎት በእግዚአብሔር ይሰማል::

View Details

እራስን መመርመር 1ኛ ቆሮ 11:31 2ኛ ቆሮ 13:5

View Details

ህይወትን የተቀበልነው በነጻ ቢሆንም ይህን ህይወት ለመጠበቅ ግን ዋጋ ያስከፍላል፣ በጥንቃቄ ያልተጠበቀ ህይወት አጥር እንደሌለው ቤት ነው፣ ህይወትን በጥንቃቄ ለመጠበቅ ዕለት ዕለት ስጋችንን እየጎሸምን አይናችንንና ጆሮእችንን ከክፉ በመጠበቅ መንገዳችንን በቃሉና በጸሎት ማንጻት ይኖርብናል፣ በተጨማሪ በአንድ አማኝ በረከት ሌላው አማኝ ሁሉ ስለሚባረክ ለራሳችን ህይወት መጠንቀቅ ማለት ለህብረትም መጠንቀቅ ነው::

View Details

ወደ ትክክለኛ ምሪት የሚያደርስ ጸሎት ሉቃ 4:3-8 መዝ 90

View Details

አምኖ መጸለይ 11:24 ማቴ 21:22 ዕብ4:16

View Details

እግዚአብሔር የሚሰራው በጊዜ ውስጥ ነው፣ መንፈሳዊነት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጊዜ ጋር መራመድና ጊዜውን ማስተዋል ነው፣ ለእያንዳንዱ ነገር ተወስኖ የተሰጠ ጊዜ አለ፣ ሁሉም ከጊዜው አያልፍም፣ ሁሉ በጊዜ የተወሰነ ነው፣ ሰው ግን በራሱ ጉዳይ ሲያዝ ዘመንን ለመዋጀት የእግዚአብሔርን ነገር የሚሰማበት ጆሮ የለውም፣ ጊዜን የሚሰማ ጆሮ ደግሞ ከሌለን የጊዜው ጸሎት የለንም የጊዜው ጸሎት ከሌለን ደግሞ የጊዜው መልስ የለንም፣ ከእግዚአብሔር ጊዜ ጋር ስንራመድ ጠቃሚዎች ለዘመኑ መልስና ለእግዚአብሔርም መልክተኞች እንሆናለን፣

View Details

የእግዚአብሔርን ሞገስ በህይወት ለማየት የመጀመሪያው ነገር ለእግዚአብሔር መቀደስ ነው፣ ለጌታ ለመቀደስ ደግሞ ማንነትን ማወቅ አስፈላጊ ነው፣ በክርስቶስ እየሱስ ደም ተዋጅተን ለእርሱ የተለየንና በእርሱ ደግሞ የተቀደስን መሆናችንን በማሰብ ህሊናችንን ከሚያቆሽሽ ማናቸውም ርኩሰት እራሳችንን መጠበቅ ይኖርብናል ደግሞም የጠራን ቅዱስ እንደሆነ በኑሮአችን ሁሉ ተቀድሰን እንድንኖር ይጠበቅብናል፣

View Details

መንፈሰ ቀና መሆን ለእግዚአብሔር በረከት መንገድን ይከፍታል፣ ከጌታ ጋር ለመራመድ የምንችለውና የበረከቱ ተካፋዮች የምንሆነው ልባችን የቀናውን ያህል ነው፣ ልባችንን ደግሞ የሚያቀናው ቃሉ ነው፣ የእግዚአብሔር ቃል ሲገለጥልን ህይወታችንን ይቀርጽና የቀና መንፈስ እንዲኖረን ያደርጋል መንፈሳችን በቀና ቁጥር ደግሞ ለእግዚአብሔር እሺ ባዮች ገርና ቅን ባህሪይ ይኖረናል ደግሞም ከሌሎች የእግዚአብሔር ሰዎች ጋር በቀና መንፈስ ለመራመድ አንቸገርም፣

View Details

ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ከሞተ ህይወት ትንሣኤን ያገኘ ደግሞም ዳግም የተወለደ ሰው በእርሱ ውስጥ የጌታ መንፈስ አለ:: ስለዚህ ሁልጊዜ ናፍቆቱና መሻቱ ጌታን ነው:: ህይወታችን ከክርስቶስ ጋር ተሰውሯልና ከምድር በሆነው ከአመፀኝነት ከክፋትና ከትዕቢት ጋር አንተባበርም:: የትንሤኤ ልጆች ነንና በመንፈስ ቅዱስ እገዛ ከሁሉ የላቀውንና የከበረውን በላይ ያለውን ጌታ እየናፈቅን በትጋት እንኑር::

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ፀሎት መናገር ብቻ ሳይሆን የሚሰማ ጆሮ ያሰፈልጋል የሚለውን ሀሳብ አብራራልን? 2. ያለ ግዜው እንዳንፈርድ ቃሉ ይለናል የሚለውን ሀሳብ ግልፅ አድርግልን። 3. ወደ ፀንቶ ደጅ መጥናት መድረስ የምንችለው እንዴት ነው?

View Details

ጸሎት በእግዚያብሔር እይታ

View Details

ልብን ማፍሰስ ሉቃ 18፡35-43 ሮሜ 8:26-27 ኤር 33:3

View Details

በዘመናት ሁሉ ብዙ ፈልገን ያላገኘናቸው ነገሮች አሉ፣ እግዚአብሔር ግን ከፈለግነው ይገኝልናል፣ እርሱን ፈልገን ካገኝነው ደግም ከመልካም ነገር ሁሉ አንጎድልም፣ ታሪካችንን ይቀይራል እውነተኛ እርካታ ወደ ህይወታችን ይመጣል ለራሳችን እንኖር የነበርን ያለንን ለሌሎች ማካፈል እንጀምርለን፣ እግዚአብሔር ባለበት በዚያ በረከት አለ፣ እድሳትና እርካታ አለ፣ ምርኴችን ይመለሳል ቜጠሯችን ሁሉ ይፈታል፣

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ስለ ፍቃዳችን ስንኖር የምንኖረው ኑሮ ልክ እንደ አለማዊ ሰው ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 2. መንፈሳዊ ህይወት ዘመኑን አውቆ መዋጀት ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 3. ቅዱሳን የሚለያዩት ስል ዘመኑ ሲነጋገሩ ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 4. ምን ዐይነት ፀጋ ሲኖረን ነው ዘመኑን መርምረን ከህይወታችን ጋር የምናወህደው? 5. ሰውን ለማቅናት ሰውን መውደድ አለብን የሚለው ሀሳብ ቤተሰብንም ይጨምራል ወይ? እኛም ደካማ ሰለሆንን ወደ ታች ወርደን ነው ሰውን ማቅናት ያለብን ማለት ነው? 6. ሰው እንዳይፈተን ሰውን ምን ያህል ነው ማመሰገን የምንችለው?

View Details

በልማድ ያልሆነ ጸሎት መዝ 46:1-11

View Details

እግዚአብሔር ሰውን የሚጎበኘው በራሱ ጊዜ ሲሆን በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ የሆነ ሰው ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር ጉብኝት የነቃ ነው፣ ዘወትር በመንፈሱ ውስጥ ስንሆን ከሐጢያት እየሸሸን በምናየውና በምንሰማው ስፍራችንን ሳንለቅ ተረጋግተን በንቃት እንኖራለን፣ በጌታ ከመጎብኘት የሚያጎድለን አንዱ አለመዘጋጀት ነው፣ ብዙዎቻችን እንጸልያለን እናመልካለን ደግሞም እናገለግላለን ለጌታ መገኝት ግን የነቃን አይደለንም ይህ ከአርሱ ጉብኝት ውጪ ያለው አደራረጋችን ይለመድና እርሱ ሊጎበኘን በመካከላችን ሲመላለስ አንረዳውም፣

View Details

በመንፈስ ቅዱስ እሳት የሚያጠምቀው እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ሲሆን በዚህ መንፈስ ቅዱስ እስት ለመጠመቅ ሰው ንስሐ መግባትና በክርስቶስ እየሱስ ደም መዋጀት አለበት፣ በመንፈስ ቅዱስ እሳት ከተጠመቅን በኌላ ደግሞ እሳቱ እንዳይጠፋ በቃሉ በጸሎትና በቅዱሳን ህብረት እየተጋን ይህንን እሳት ማቀጣጠል የእያንዳንዳችን አማኞች ድርሻ ነው፣

View Details

አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ የጌታን መንገድ የተከተለ ሰው ነው፣ አካሄዳችንን ከእግዚአብሔር ጋር ስናደርግ በእግዚኣብሔር ፊት ቅኖች በሰውም ፊት በደል የማይገኝብን እንሆናለን፣ አካሄዳችን ከእግዚአብሔር ጋር ሲሆን የምናዝን የምንምር የዋሆች ጽድቅን የምንራብ ልበ ንጹሀንና የምናስተራርቅ እንሆናለን፣ አካሄዳችን ከእግዚአብሔር ጋር ሲሆን የእምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ እስከ መጨረሻው እንድንዘልቅ ይረዳናል፣

View Details

በየዘመናቱ ወደኋላ እንድናይ የሚይደርጉን ብዙ ነገሮች አሉ፣ ጌታ ግን ያለፈውን በደላችንንና ሐጢያታችንን ላያስብ የእዳችንን ፅህፈት ደምስሶታል፣ ስለዚህ ያለፈውን በደል ማሰብ የአሮጌው ሰው ባህሪ ስለሆነ ወደፊት ለመሄድና ከፊታችን ያለውን ለመያዝ በትጋት ቃሉን ማጥናት መጸለይና ህብረትን ማድረግ ይጠቅመናል፣

View Details

ጸሎት እና ምስጋና መዝ 50:3፣ 65:1 ኤፌ5:20 1ኛ ተሰ 5:17-18 ፊል 4:6

View Details

በጸሎት መናገር እና ማዳመጥ

View Details

ሳትታክቱ ጸልዮ መዝ 40:1-3, ሉቃ 18

View Details

ይቅርታ ማለት የጎዱንን ሰዎች መልሶ ለመጉዳት የሚቻለውን መብት መተው መብትን አለመጠቀም ማለት ነው፣ ይቅር አለማለት ጸሎታችን እንዳይሰማ ያደርጋል በእግዚአብሔር ፍቅር እንዳንመላለስና መራራ ህይወት እንዲኖረን ከማድረጉም በላይ በጤናችን ላይ ቀውስን ያመጣል፣ ጌታ እኛን ይቅር ሲለንና ሲወደን እንዲቀበለን የሚያደርግ አንዳች በጎነት ተገኝቶበን አይደለም፣ ይህንን የተካፈልነውን የይቅርታ ህይወት ለሌሎች ማካፈል ይጠበቅብናል::

View Details

እግዚአብሔር የሚጎበኝ አምላክ ነወ፣ እግዚአብሔር ሲጎበኝ ተስፋን ይፈጽማል፣ የሰጠንን የምንጠብቀውን ተስፋ እንድንጨብጠው ያደርጋል፣ ጸሎታችንን ይሰማል፣ እግዚአብሔር ሲጎበኘን እንጸናለን፣ ከመከራ የሚያወጡንን ሰዎች ያዘጋጅልናል፣ ጠላቶቻችንን ያዋርዳል ደግሞም እንጀራን ይሰጠናል::

View Details

የእውነተኛ ትንቢት ምንጩ እርሱ እግዚአብሔር ነው:: አገልጋዩም ይህንኑ በመንፈሱ ከእግዚአብሔር የሰማውን መልዕክት ከራሱ ስሜትና ፈቃድ ጋር ሳይቀላቅል ይናገራል:: ከእግዚአብሔር የሆነው ትንቢትም ሊፈፀም የግድ ነውና መልዕክቱ የመጣለትም እንዲሁ ከራሱ ወይንም ከሁኔታዎች ጋር ሳያስተያይ በእምነት ሊቀበል ደግሞም በጥንቃቄ ሊጠባበቀው ይገባል:: ይህን ሀሳብ በተመለከተ በዚህ መልዕክት በስፋት እንማራለን::

View Details

እግዚአብሔርን ብቁ ማድረግ ማለት ሁሉን ከእርሱ መጠበቅ ማለት ነው፣ አግዚአብሔርን የተጠጋ ሰው ብቁ ነው ብቃቱ የራሱ ሳይሆን አግዚአብሔር ራሱ ስለሆነ ነው፣ አንዳንድ ጊዜ ጌታን እየተከተልን በፈቃዳችን እርሱን በቂ ሳናደርግ ስንቀር በጎደለን ነገር እንጋለጣለን፣ የእውነትና የጽድቅ ጌታ እንዲሁም ለሁሉ በቂ ለሆነው አምላክ የነቀፌታ ምክኒያቶች እንሆናለን

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. መንፈሳዊነት እግዚአብሔርን የቀደምንበትን እና ያልቀደምንበትን ማወቅ ነው የሚለው ቢብራራልን። 2. ለሰላም አብሮ ለመኖር ተብሎ ሰው ሲያጠፋ እየታየ ዝም ይባላል ይህ እንዴት ነው ሊሆን የሚችለው? 3. ፍቅር ስለሌለ ነው ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው የሚለው? 4. ለበጎ ነገር የሚነሳሳ ልብ ከሌለን ህይወታችን ትርጉም ሊኖረው አይችልም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 5. ሰዎችን ስህተታቸውን ስንነግራቸው የሚቆጡ አሉ ለእንደዚህ ላሉት እንዴት ነው ስህተታቸውን መንገር የምንችለው? 6. ሰው ጌታን ወደ ቤቱ አስገብቶ ጌታን ግን ወደ ልቡ ላያስገባ ይችላል የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 7. ስንፀልይ አንዳንድ ጌዜ ሀሳባችንን የምናሳይ ይመስለናል የሚለውን አብራራልን።

View Details

በባለፈው እያመሰገኑ መጸለይ መዝ 16:13, 78:14 ማቴ 16:5 ማር 8:14

View Details

ብዙ ነገር ከሰው መሰወር እንችላለን ከጌታ ግን ለንሰውር የምንችለው ምንም ነገር የለም፣ እንዳንድ ጊዜ የአስተሳሰብ ውድቀት በህይወታችን ሲኖር ወይም ጥላቻ ቂምና በቀል በውስጣችን ሲኖር ከእግዚአብሔር ልንሰወር እንሞክራለን፣ ግን እግዚአብሔር በነገራችን ላይ የሚገለጠው ነገራችንን ለእርሱ በገለጥንበት ነው፣ ከእግዚአብሔር የደበቅነው የመሰለን ነገር ገዳያችን ሲሆን ለእርሱ የገለጥነው ነገራችን ደግሞ ፈውሳችን ነው፣ በተገለጠ ነገር ላይ ጌታ በክብር የገለጣል፣

View Details

የጸሎት ምንጭ ያዕ4:3

View Details

በፈተና ብቁ ሆኖ መገኝት ሉቃ 4:1-13

View Details

በደሙ ታጥበው ንስሐ በገቡ ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ እንደሚኖርና አንድ ሰው ከዚህ መንፈስ ቅዱስ ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ለዘለአለም ይህ መንፈስ አብሮት እንደሚሆን የመከረን ያለውን የሚያደርግና የተናገረውን የሚፈጽም እውነተኛ አምላክ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ነው፣ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ከኛ ጋር እንደሌለ አይምሮአችን እንዲያስብ መፍቀድ የለብንም፣

View Details

ለብዙዎቻችን በምንወደው መደሰት ቀላል ነው፣ በጌታ ፈቃድ መደሰትን የተለማመዱ ክርስቲያኖች ግን ጥቂቶች ናቸው፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ አለመደሰት ማለት ለእግዚአብሔር አለመታዘዝ ማለት ነው፣ እኛ የማናየው ጌታ ግን የሚያየው ማንነት በውስጣችን ስላለ፣ አንዳንዴ በራሳችን ፈቃድ ስንሄድና የማንወጣው መከራ ውስጥ ስንገባ እርሱ ቸርና የፍቅር አምላክ በመሆኑ እጃችንን ይዞ ያወጣንና ከርሱ ፈቃድ ጋር ያገናኘናል፣

View Details

ኑሮ 1ኛ ጢሞ 6:3-11

View Details

ጸም እና ጸሎት ዘጸ 24, ዘጸ 33:3 , ት.ኤር 52, ዘኍ14:27, 2ነገ 25

View Details

ዕለት ዕለት ለመኖራችን ዋስትና የእግዚአብሔር ምህረት ነው፣ ይህንን የተካፈልነውን ሕይወት ደግሞ ለሌሎች ማካፈልን አምላካችን ስለሚጠብቅብን ሁልጊዜ ሰዎችን ሁሉ ለመማር የተዘጋጀ ልብ ሊኖረን ይገባል::

View Details

እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ይናገራል ደግሞም ይፈውሳል፣ በወደደው መንገድ ወደ ወደደው ሰው ይደርሳል፣ በዘመናት ሁሉ ሰውን ከእርሱ ጋር ለማነካካት ምክኒያት የሚሆኑ ስዎች እግዚአብሔር አሉት እኛ እያንዳንዳችን ግን ከእርሱ በረከትና ፈውስ ጋር የምንነካካው ስንታዘዝና እርሱ የሚለንን ስናደርግ ነው::

View Details

ለእግዚአብሔር አደራ መስጠት እና ጸሎት 1ሳሙ 12:23

View Details

የመዳናችን መንገድ የወንጌል እውነትና ስለ እግዚአብሔር ያለን እይታ ነው፣ የመዳናችን መንገድ በበራልን መጠን ህይወታችን ትክክለኛውን አቅጣጫ እየያዘ የሄዳል፣ እይታችን ከእግዚአብሔር ጋር ሲበላሽ እጃችን ላይ ያለው ክቡር የሆነው ነገር ሁሉ ይበላሻል፣ እይናችን ተከፍቶ የአምላክ እውቀት ሲገባብን ግን እርሱ የሚያየውን የሚያስፈልገንን በትክክት ማየት እንችላለን፣

View Details

ለእግዚአብሔር አደራ መስጠት እና ማመስገን ዕዝራ 8:21-23

View Details

ይህ ለኛ የደረሰንና ለሚመጣውም ትውልድ የሚተላለፈው የእግዚአብሔር ቃል ስዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት በአይናቸው ያዩትና በእጃቸው የዳሰሱት እንዲሁም ከሰማይ የሰሙት የእውነት ድምጽ ነው፣ ስለዚህ ነው ክርስትናን ልዩ የሚይደርገው ተረት ሳይሆን የተገለጠ ህይወት በመሆኑ ነው፣ አማኝ ወደ ከርስቶስ ከመጣ በኌላ ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያኖር እውቀት ያስፈልገዋል፣

View Details

ለእግዚአብሔር አደራ መስጠት መዝ102:17

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ሰዎች ጌታ አለን በማለት ዶክተር ያዘዘላቸውን መድሐኒት ባለመውሰዳቸው የሞቱ ሰዎች አሉ እዚህ ጋር ምኑ ጋር ነው ስህተት ያለው? 2. እግዚአብሔር ከፊታችን ካላየነው ነጋችን ጨለማ ነው የሚሆነው የሚለው ይብራራልን? 3. እግዚአብሔር ያላስቀደመ የውድድር አቅሙ ደካማ ነው የሚለው ይብራራልን? 4. ጠንካራ አህምሮ ያለው ሰው ራሱን ደብቆ ለሌላ ሰው ሌላ ባህሪ ሊያሳይ ይችላል የሚለውን ወደ አማኝ ህይወት ስናመጣው እንዴት ነው? 5. የተጠላ ሰው ምንድን ነው ማድረግ ያለበት? 6. የምናልፍበትን ህይወቴ ነው ብለን እንደ ጳውሎስ መቀበል የሚያቅተን ለምንድን ነው?

View Details

ንፅህና አንዱ የጌታ ባህርይ ነው:: ይህ የእርሱ ባህርይ በእርሱ ውስጥ ሆነን በተገኘንበት ለእኛ ሆኗል:: አማኝ በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ ያለና የክርስቶስን ህይወት እየኖረ መሆኑ የሚታወቀው በንፅህናው ነው:: ይህ ንፅህና የአይን የልብና የመንፈስ ንፅህና ነው:: ንፅህናችንን እንዳናቃልል ደግሞም እነዳንጥል ከንፅህና የጎደለም መመለስ አንዲሆን የዚህ መልዕክት ዋና ምክር ነው::

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ሳምሶን የእግዚአብሔር ቅባት አለው ነገር ግን ቤተሰቦቹ የሚሉትን አይሰማም ነበር ይህ ደግሞ አለማዊ ክርስትያንን ይመስላል የሚለው ይብራራልን። 2. እግዚአብሔርን መናፈቅ እና መጠማት ቃሉን ከተለያየ ቦታ እየሰሙ መሰብስብ ነው ወይ? 3. ፆምን እንዴት ነው የምንፆመው? 4. እንደ ቀልድ አድርገን በተናገርነው ነገር የተጎዱትን ልጆች እንዴት ነው መመለስ የምንችለው?

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 47 ቆላ. ከምዕራፍ 1:28-29

View Details

የጌታን ምጽአት ከዘመን ጋራ እንድናስተውል መጽሃፍ ቅዱስ ይነግረናል፣ ጸሎትም መጸለይ የሚቻለው እግዚአብሔር ዘመኑን ከገለጠበት ከበራልን ነው፣ ዘመኑን ካልተረዳን ጸሎትም አይኖረንም፣ እግዚአብሔር ለህዝቡ ሳይናገር ምንም የሚሆን ነገር ስለሌለ እርሱን ብቻ ከሰማን ሳንናወጥ እግዚአብሔር ያለው እንደሚሆን አውቀን መደረግ የሚገባውን ነገር እያደረግን መሆን የሚገባንን እየሆንን የመጣው ዘመን ሳያሰናክለን ጸንተን መኖር እንችላለን፣ ዘመንን ደግሞ ከእግዚአብሔር ካልሰማን እንዴትና ስለምን እንደምንጸልይ አንረዳም ከእግዚአብሔር ለሰሙ ሰዎች ደግሞ እንቅፋት እንሆናለን

View Details

የዛሬው ማንነታችን ነገ በህይወታችን ለሚሆነውና ሊገለጥ ላለው ደግሞም ለምንሆነው ዋናና ወሳኝ ነገር ነው:: የእግዚአብሔር ክብር በነገው ህይወታችን እንዲገለጥ በእኛም ደግሞ እንዲሰራ ዛሬ ትሁት ሆነን ፅድቅንም በመምረጥና እርሱን በመስማት በፊቱ ልንሆንያስፈልጋል::

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 46 ቆላ. ከምዕራፍ 4:7-8

View Details

የጸለይንበት ማለት እግዚአብሔር እንካችሁ ብሎ የሰጠን ነገር ማለት ነው፣ የእግዚአብሔር ስጦታ ፍጹም በረከትና መርገም የሌለበት ሲሆን በባህሪው ደግሞ ደግ አባት በመሆኑ የሰጠንን መልሶ አይወስድብንም፣ ልጅን የሚያክል ውብ ነገር ከምጥ በሗላ እንደሚገኝ አንዳንዴ ከውስጣችን የሚወለድ ነገር ካለ እግዚአብሔር እንድናምጥ ያደርገናል፣ በምጥና በስቃይ ውስጥ ስናልፍ በእግዚአብሔር ፊት ጥሩ ባልሆነው ነገር እንዳንያዝ በጥንቃቄ የእግዚአብሔርን ጥሩ ለማወቅ መጸለይና የእርሱን ጥሩ ለማድረግም ሆን ለመቀበል ዝግጁ መሆን አለብን፣

View Details

የእግዚአብሔር ቃል በዋጋ ተገዝታችኍልና የራሳችሁ አይደላችሁም ስለሚል አካሉን ለመጥቀም በምንችልበት ሁሉ የምንቆምና ለበጎ ስራ ሁልጊዜ የተዘጋጀን ልንሆን ይገባናል፣ ለራስ መኖር ትልቅ ውድቀት ነው፣ እግዚአብሔርን መበደል መንፈስ ቅዱስን ማሳዘንና የሙላቱ መገለጫ የሆነችውን ቤተክርስቲያንን ማጎሳቆል ነው፣

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 45 ቆላ. ከምዕራፍ 1:24-25

View Details

እግዚአብሔር ካልተናገረ የመለኮት ሃሳብ ወደ ሰው የሚደርስበት መንገድ ስለሌለ በዘመናት ሁሉ እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን አስኪገባን ይናገረናል፣ ቃሉ እንደሚል ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፣ በክርስቶስ የእውነት ልጆች ሆነን ተወደናልና እውንትን ለመስማት ልባችን ሁልጊዜ የተዘጋጀ ሊሆን ይገባል፣

View Details

መንፈሳዊ ስኬት ማለት እግዚአብሔርን ከፊት ማየት ነው፣ ዛሬ እያለፍንበት ያለነው ወይም ነገ በህይወታችን ለሚመጣው ማንኛውም ፈተና የመወጣጫ አቅም የሚኖረን ጌታን ከፊታችን ባየነው መጠን ነው፣ እግዚአብሔርን ከፊታችን ስናይ በማንኛውም የህይወት ማዕበልና ወጀብ ውስጥ ሳንታወክ ተረጋግተን እንኖራለን፣ እግዚአብሔርን ከፊት ማየት ሲጠፋብን ግን የሚያስጨንቀንንና ተስፋ የሚይስቆርጠንን የጠላት ድምጽ አስተናጋጆች እንሆናለን፣

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 44 ቆላ. ከምዕራፍ1-4

View Details

የሰማነው የሕይወት ቃል ማንናታችን ሊሆን ይገባል፣ ክርስትናችን ደግሞ ሕይወት ብለን የያዝነው በጊዚያዊ መነካት የሚለካ ነገር ሳይሆን በመሆን የሚለካ ነው፣ በተለያየ ፈተና በመጠላት በመገፋት ስናልፍ እግዚአብሔርን በመፍራት በንጹህ ህሊና በገርነት በእውነትና በጽድቅ ማንነታችን ሊገለጽ ይገባል፣

View Details

አንዳንድ ጊዜ የማንወጣው የሚመስለን ችግርና መከራ ውስጥ ስንሆን መፍትሄ ወደምናገኝበት ልንሄድ እንችላለን ብዙ ጊዜ ግን እንዲደረግልን የምንጠብቀው ከሌለን ነገር እንደሚመጣ ነው፣ ጌታ ግን በእጃችን ያለውን ተስፋ የተቆረጠበትን አይጠቅምም አይበዛም ያልነውን ሊያበዛ የሚችል አምላክ ነው፣

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 43 ቆላ.ምዕራፍ 4:12-18

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 42 ቆላ.ምዕራፍ 4:10-12

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ኤፊሶን 4፡17 “...በአህምሮ ከንቱነት ከእንግዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ።” በአህምሮ ከንቱነት የሚለው ይብራራልን። 2. ታካች የሆኑትን ልጆች እንዴት ነው መመልስ የምንችለው? 3. ትንቢት ተነግሮላቸው ለህብረተሰቡ ሸክም እየሆኑ ያሉታን ልጆች እንዴት ነው ልንመራቸው የምንችለው? 4. ስልጣናችንን ካልተጠቀምን ልጆቻችን ሊታዘዙልን አይችሉም የሚለው ይብራራልን። 5. ትዕግስት ስናጣ የእግዚአብሔር ወደ ሚመስል ነገር ፈቀቅ እንላለን የሚለውን ብታብራራልን። 6. የምንሰብከው ህይወታችንን ይሁን እምነታችንን መሆኑን እንዴት ነው የምናውቀው? 7. ክርስቶስን ከሰበክን በመከራ ቀን እሱን ማሳየት ቀላል ነው ነገር ግን እምነታችንን ከሰበክን በችግር ጊዜ መቆም አንችልም የሚለው ይብራራልን።

View Details

ጌታ እያንዳንዳችንን ብቻችንን ይፈልገናል፣ ብቻውን ለእግዚአብሔር ያልተገኘ ሰው እግዚአብሔር በህይወቱ ስፍራ ያላገኘ ሰው ነው፣ ጌታ ብቻችንን ሲያገኘን ከእርሱ ጋር ጥሩ ህብረት ይኖረናል ደግሞም ባህሪውን እየተላበስን እንመጣለን፣ የባህሪው ተካፋዮች ስንሆን ለሌሎች መገኘት ወይም መትረፍ እንችላለን፣

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 41 ቆላ.ምዕራፍ 4:7-9

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 40 ቆላ.ምዕራፍ 4:1-5

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. መንፈሱን የማይከለክል ሰው ቅጥር እንደሌለው ሰው ነው የሚለው ግልፅ ቢሆንልን። 2. ጌታን የሚከተል የህይወት ብርሃን ይሆንለታል ይላል ግን ለምንድን ነው ጌታን ተከትለን ብርሃን የማይበራበት የህይወት ክፍል የሚኖረን? 3. ስንፍ እና ባህሪ ማንነት ከሆነ እንኚህ ባህሪያት የሚታዩት ባልዳኑ ሰዎች ከሆነ በጌታ የሆንን እነኚህ ባህሪያት ካሉን እንዴት ነው ወደ አዲስ ፍጥረት መምጣት የምንችለው? 4. ወላጆች በልጆች ህይወት ምንድረስ ነው ጣልቃ መግባት የሚችሉት? 5. ከጌታ ጋር እየሄድን ያለን ነገር ሌላ ስለሚሆን ነው ወይ ለሰዎች ጌታን መስጠት የሚያቅተን?

View Details

እኛ ብርቱዎች ሆነን ሳይሆን እግዚአብሔር ግን ርህሩህ አባትና የታመነ አምላክ ስለሆንና የማንንም ጥፋት ስለማይፈቅድ ለሁላችን አስቀድሞ መንገዳችንን ይነግረናል፣ ሊታለፍ በማይቻልና ምርጫ በሌለበት ሁኔታ የእግዚአብሔር ድምጽ መጥቶ ወደ ፊት እንዲሄዱ ወይ ወደ ኋላ እንዲመለሱ የተናገራቸውና ድምጹን ሰምተው ከክፉ ያመለጡ ከሞትም የተረፉ ብዙ ስዎች አሉ፣ የልቡን ሃሳብ ለልጆቹ የሚነግር አምላክ ነውና እኛ ቀርበን ከጠየቅነው አይደብቀንም፣

View Details

የተጠራነው እግዚአብሔርን ለመከተልና የጌታን ነገር ከጌታ ጋር ለማድረግ ነው፣ እግዚአብሔርን መከተል ማለት ደግሞ ምህረትን ፍርድንና ጽድቅን መከተል፣ ትምህርቱን መቀበልና በትምህርቱ ውስጥ መገኘት ማለት ነው፣ በእግዚኣብሔር ትምህርት ውስጥ መሆን በእግዚአብሔር ፍጹም በረከት ውስጥ መሆን ነው፣

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 39 ቆላ.ምዕራፍ 3:18-25

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 38 ቆላ.ምዕራፍ 3:12-17

View Details

ከእግዚአብሔር ጋር ትክክል ካልሆንን የእግዚአብሔር ፊት ይሰወርብናል፣ ምህረቱ ብዙ ርህሩህና መልካም አባት በመሆኑ ለክፉዎች እንኳን ጸሃይን ያወጣል ሆኖም ግን እንደልባችን ማንንነት የሚገናኘን አምላክ ነው፣ እግዚአብሔር ቃሉና መንፈሱ ባለበት ቦታ ሁሉ ይገኛል ደግሞም ይናገራል፣ መኖሩን ግን ለማወቅና ድምጹን ለመስማት የልባችን ማንነት ይወስነዋል፣ መንገዳችን ግራ ከሆነ እንደመንገዳችን በግራ ሆኖ እናገኘዋለን፣ ልባችን ከቀና ደግሞ መልካምና ቸር ሆኖልን እናገኘዋለን::

View Details

እግዚአብሔር በኛ ጊዜ ላይገኝ ይችላል ነገር ግን ለኛ የዘገየ በመሰለን ሁሉ እርሱ ጻድቅ ነው፣ የእግዚአብሔር መዘግየት ምን ያህል እርሱን ተስፋ እንዳደረግነው አንዱ የሕይወታችን መፈተሻ መንገድ ነው፣ ነፍሳችንን የሚይዝ የእግዚአብሔር የባህሪው እውቀት ከሌለን መታገስ ያቅተናል በእርሱ ባህሪይ ውስጥ ስንሆን ግን ተረጋግተን እርሱን አንጠብቃለን፣

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 37 ቆላ.ምዕራፍ 3:6-13

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 36 ቆላ.ምዕራፍ 3:1-4

View Details

እኛ ሁላችን ሃጢያተኞችና ፍርድ የሚገባን ሆነን ሳለን እግዚአብሔር በክርስቶስ እየሱስ ይቅር ብሎን በምህረቱ ልጆቹ ስላደረገን እንደተወደዱ ልጆች የእግዚአብሔር የአባታችንን ባህሪይ ልናንጸባርቅ ይገባናል፣ ምህረት ከእግዚአብሔር የተካፈልነው የህይወት ፍሬ ነው፣ ስለዚህ እንደ ምህረት ልጆቹ ለሌሎች መገለጥ የምንችለው በምህረት ነው::

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 35 ቆላ.ምዕራፍ 2:16-23

View Details

ከታማኝነት አንዱ እገዚአብሔርን መጠበቅ ነው፣ የሚታየውና የምናልፍበት ሁኔታ የማይመችና ተስፋ የሚያስቆርጥ ሊሆን ይችላል፣ በዚህ ሁሉ ግን የጠራን አምላክ ታማኝ ነውና በሚሆነው ሁሉ ከእምነት የሚያጎድለንን የሰይጣንን ድምጽ ሳይሆን ታማኝ የሆነውን የእግዚአብሔር የአምላካችንን ቃል ተስፋ አድርገን በስፍራችን እገዚአብሔርን መጠበቅ ይገባናል፣

View Details

በእግዚአብሔር መታሰብ ውስጥ ያሉ ሶስት ነገሮች ቦታ ሁኔታና ሰዓት ናቸው፣ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሊያገናኘንና በበለጠ ወደ እርሱ ሊያስጠጋን፣ በወሰነው ስፍራ በተለያዩ ሁኔታዎች እንድናልፍ ይፈቅዳል፣ እነኚህ ሁኔታዎች የመታሰቢያችን ምክኒያቶች ናቸው፣ ሁኔታዎችን ለመቀየር መታገል ለውድቀት እራስን ማጋለጥና መከራችንን ማብዛት ነው፣ የሚሻለን ሁኔታዎችን በእግዚአብሔር እይታ እያየናችው በራሱ ጊዜ በማዳን የሚገለጠውን ጌታን ብቻ ተስፋ በማድረግ እርሱን መጠበቅ ነው፣

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በአሁኑ ግዜ ቤተ ክርስትያን የማይስማሙትን የክርስቶስ አካል ስላልሆኑ ነው የሚለው ይብራራልን። 2. የክርስቶስ መከራ በህይወታችን ካላላፈ ለስዎች መፅናናት መሆን አንችልም ማለት ነው? 3. በወንጌል አላፍርም የሚለውን ብታብራራልን። 4. በሀጢያት ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነታችንን እናጣላን ወይ? 5. ሰዎች ጌታን ከማወቅ ይልቅ ትክክል መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ይፈልጋሉ ይህን ማወቅ ጥቅም አለው ወይ? 6. ልጆች ወ ተሳሳተ ትምህርት እንዳይሄዱ ወላጆች ምን ማድረግ ነው ያለባቸው? 7. ወገኖችን ለማፅናናት ሀዘን ቤት ስንሄድ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? 8. መጨቃጨቅ ማለት ማድረግ ያለባቸውን ስላላደረጉ ያንን ደጋግሞ መናገር ማለት ነው?

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 34 ቆላ.ምዕራፍ 2:12-15

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 33 ቆላ.ምዕራፍ 2:7-19

View Details

የምናመልከው አምላክ እርሱ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው:: ሰለሆነም በእኛ አይን ምን ከባድና የማይቻል ሆኖ ቢታየን እግዚአብሔር ግን እንዴት ይሆናል አይባልም:: ያልነበረውን ወደ መኖር ባመጣ በእርሱ ዘንድ ቀላል ነው:: ድንቅና ተአምራት የምታደርግ የእግዚአብሔር እጅ ዛሬም ለመርዳት ለማገዝ ለማዳንም የተዘረጋች ነች:: አላጠረቸ::

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ክርክራችን ከታላላቆቻችን ጋር ቢሆን ምን ማድረግ ነው ያለብን? 2. ከሰዎች ጋር ያለንን ክርክር ለሰዎቹ ሳንናገር ወደ ፀሎት ማምጣት እንችላለን ወይ? 3. ለበደለን ሰው መልካም ስናደርግ እግዚአብሔር ብድራቱን ይመልስበታል በሚል መንፈስ መሆን አለበት ወይ? 4. ሰው በጌታ ከሆን በሗሏ በህሊናው ባይወቀስ ርሱን መጠየቅ የለበትም ወይ? 5. ሰው ጌታ ካወቀ በሗሏ ቀድመው አብረው ከነበሩ ሰዎች ጋር ያደርግ የነበረውን ላለማድረግ መለየት አለበት ወይ? 6. ከእግዚአብሔር ሀሳብ ውጪ የሚያስተምሩትን እንዴት ነው መለየት የምንችለው? 7. ወንጌልን ለመናገር ድፍረት እስከማጣት የምንደርሰው ለምንድን ነው

View Details

አማኝ መንፈሳዊ ህይወቱ ጤነኛ ለመሆኑ መገለጫው ጌታን መጠማቱና መራቡ ነው:: ጌታን መራብና መጠማት ባለበት በዛ ተስፋ አለ:: መፅናናትም አለ:: አስቀድሞ በእርሱ የሚሆንልንን ሳይሆን እርሱን ራሱን ጌታን መጠማትና መራብ ለህይወት መታነፅና እድገት የሆንልናል:: ከእርሱም የሆነው በጎነትና በረከት ይጨመርልናል:: በዚህ መልዕክት ጌታን መፈለግና ከጌታ የሆነውን የመፈለግ ልዩነት እንማራለን::

View Details

መንፈሳዊ ህይወታችን ጤናማ መሆኑ የሚታወቅበት አንዱ መንገድ መንፈሳዊ ነገርን የሚራብና የሚጠማ ማንነት ሲኖረን ነው፣ ተፈጥሯዊ ማንነታችን መንፈሳዊውን ነገር አይፈልግም ጌታ ግን ፍቅር ስለሆነ በወደደው መንገድ አሳልፎ እርሱን ፈላጊዎች ያደርገናል፣

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 32 ቆላ.ምዕራፍ 2:6-15

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 31 ቆላ.ምዕራፍ 2:1-9

View Details

የቤተ ክርስቲያን መብዛት ማለት የአዳዲስ ሰዎች መጨመር ማለት ነው፣ መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደሚያስተምረን በስደት የተበተኑት የክርስቶስ ተከታዮች ወንጌልን ለማብሰር ስደታቸው አላቆማቸውም፣ እንዲያውም በደረሱበት ሁሉ የምስራቹን ቃል ያበስሩ ስለነበረ ስደታቸው ለመብዛታቸው ምክኒያት ሆኖላቸዋል፣ ዛሬም እኛ ይህን ደህንነት ያገኘን ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት ሀላፊነት እንዳለብን በመረዳት በግልም ሆነ በሕብረት እግዚአብሔር ባዘጋጀልን ስፍራና በከፈተልን በር ሁሉ የክርስቶስን አዳኝነት ለሰዎች ሁሉ ልንመሰክር ይገባናል፣

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 30 ቆላ.ምዕራፍ 2:1-5

View Details

አሸናፊ ሕይወት እንድንኖር የሚረዳንና መንፈሳዊ ሰው የሚያስብለን እግዚአብሔር ያየውን ስናይና ያወቀልንን ስናውቅ ነው፣እግዚአብሔር ያየውን ካየን በዙሪያችን ያለ ማንኛውም ሁኔታ አያናውጠንም፣ እርሱ ያየውን ካላየን ግን ከእምነታችን እንጎድላለን ተስፋችን የሆነው እየሱስ ይደበዝዝና በምናየውና በምንሰማው እውነት ባልሆነው ሁሉ የምንናወጥ፣ ጭንቀትንና ፍርሃትን ብቻ የምናስተናግድ እንሆናለን፣ እግዚአብሔር ግን ለአምላክነቱ እውቅናን እየሰጠን ቃሉን ተደግፈን በአረፍት እንድንኖር ይፈልጋል፣

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 29 ቆላ.ምዕራፍ1:24-29

View Details

እግዚአብሔር ወደእኛ የሚመጣው በሕብረት በአንድነትና በፍቅር ስንቆም ለእርሱ ስንታዘዝና የሚለንን ስናደርግ ነው፣ ጌታ ደግሞ አንድ ነገርን አድርጉ ብሎ ካዘዘን ክብሩን ለመግለጽ ክብሩን ለማየት ተካፋዮች ሊያደርገንና ጎዶሎ የሆነው ነገራችንን ሊሞላ ነው፣ የሚያደርገውን የሚያውቅ ይህ ትልቅ ጌታ አድርጉ የሚለንን ሰምተን ከታዘዝን የበረከቱ ተካፋዮች እንሆናለን የሚለንን ደግሞ ካላደረግን ክብሩን ከማየት እንጎድላለን፣

View Details

በህይወት ጉዞ ውስጥ መልካምና በጎ የሀሴትና የደስታ ጊዜዎች እንዳሉ እንዲሁ ደግሞ የምናልፋቸው ብዙ አስጨናቂና አስፈሪ ሁኔታዎች ይኖራሉ:: አናልፍም ያልናቸውን አልፈንና ተሻግረን ዛሬን መድረሳችን ከሚመራንና ካሳለፈን ከእግዚአብሔር የተነሳ ብቻ ነው:: የእግዚአብሔር እኛን የመምራቱ ችሎት ከሚያስጨንቀን ከወጀቡ በማሳለፍ ይገለጣል:: በልጆቹ ላይ ክፉው የክፉውም ማስጨነቅ ስልጣን የለውምና:: ይሁ ደግሞ ለስሙ ክብር ይሆናል::

View Details

አማኝ የተጠራበት ጥሪ የከበረ እንደሆነና ያገኘውንም የክብር ታላቅነት አጥርቶ ማየትና ማወቅ ዋነኛና አስፈላጊ ነገር ነው:: የጠራንን አምላክ ልጁንም ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ በተጠራንበትም መጠራት እንደሚገባ ልንመላለስ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድና ደሰ የሚያሰኘውም ነው:: የዚህም መልዕክት ትኩረት በዚሁ ሀሳብ ላይ ነው:: እንዴት እንደሚገባ መመላለስ እንዳለብን በስፋት ይዘረዝራል::

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 28 ቆላ.ምዕራፍ1:21-29

View Details

እግዚአብሔር እርሱ የቃል ኪዳን አምላክ ነው:: ስለዚህ የቃል ኪዳኑን ህዝብ ያስባል:: የምናልፍበት ማንኛውም ሁኔታ በፊቱ ነው:: በጊዜው ጉብኝት ይሆናል:: በእግዚአብሔር መታሰባችንም በተለየ ሁኔታ ይገለጣል:: የአስበኝ የፀሎት መልስ እውን ይሆናል:: ጨለማው በብርሃን ይለወጣል:: ከውድቀት መነሳት ይሆንል:: ከድካም መበርታት ይሆናል:: ተስፋም ይሞላል:: በህይወታችን ያለው አንዱ ተስፋ እርሱም በእግዚአብሔር የምንታሰብ ሰው መሆናችን ነው::

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 27 ቆላ.ምዕራፍ1:13-23

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ሰው ቢበድለን ለራሱ እንንገር እንጂ ለሌላ ሰው መንገር የለብንም የሚለው ይብራራልን። 2. ታዘን እሺ ካልን በሗሏ ባናደርገው ይህ ወደ መንፈሳዊ ህይወት አያመጣንም የሚለው ይብራራልን። 3. ለሰዎች ታማኝ ባልሆንበት ነገር ሰውን እናሳዝናለን ይህ ደግሞ ለመንፈሳዊ ህይወታችህ ጥሩ አይደለም የሚለውን ብታብራራልን። 4. ትዕግስት ማለት ምን ማለት ነው? 5. ትዕግስት ማለት ሽንፈት ማለት ነው? 6. ሰው ተስፋ አላደረገም ማለት የጌታ ፍቅር የለውም ማለት ነው? 7. ታማኝነት ማገልገል ብቻ ሳይሆን መሆን ነው የሚለው ቢብራራልን። 8. ለሎሎች የንስሀ እድል ሲሰጥ ለምንድን ነው ለአዳምና ለሄዋን ያልተሰጠው?

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 26 ቆላ.ምዕራፍ1:8-12

View Details

እግዚአብሔር በሐይሉ ችሎት የበረታና ለታላቅነቱ ወሰን የሌለው አምላክ ነው፣ አንዳንድ ጊዜ ግን በተለያየ መከራ ውስጥ ስናልፍ፣ ከዚህ እውነት ጎድለን፣ አይናችንን ከእግዚአብሔር ላይ አንስተን፣ እምነታችን ላልቶ እናገኘዋለን፣ አይናችንን ከእግዚአብሔር ላይ ማንሳትና በምናልፍበት ሁሉ እርሱን አላማመናችን፣ የእግዚአብሔርን ችሉት ያጠፋብናል፣ እርሱን ውስን ያደርገዋል፣ እግዚአብሔርን መወስን ደግሞ ሐጢያት ነው፣ እግዚአብሔር አይናችንን እንዲከፍትልንና የእግዚአብሔርን ትልቅነት ዘወትር እንድናስብ እንዲረዳን መጸለይ አለብን

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ለጣኦት የተሰዋውን አትብሉ የሚለው ቢብራራልን። 2. ወንድም ለመከራ ቢዜ ይወለዳል ሲል ማን ማለት ነው? 3. ምሳሌ 17፡17 “ወዳጅ በዘመን ሁሉ ይወዳል” ምን ማለት ነው? 4. ምሳሌ 24፡26 የምንናገረው ቃል ሀይል አለው ሲል ክፉ ነገር ብንናገር ይሠራል ማለት ነው? 5. ምሳሌ 25፡6 እና 17 ሁሉን ነገር በመጠን መኖር አለብን የሚለው ሀሳብ መንፈሳዊ ነገራችንንም እንዲህ መሆን አለበት ማለት ነው? 6. ሰው ከህይወታችን አጣ ማለት እግዚአብሔር ወደ ህይወታችን የሚመጣበት መንገድ አጣን ማለት ነው የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 7. በአህምሮአችን ያለው ትክክል ነው ብሎ ሰው ካሰበ ወደ መንፈሳዊ ነገር መምጣት አይችልም የሚለው ይብራራልን። 8. በመንፈሳዊ ህይወታችን የአህምሮ መታደስፍ የሚመጣው እንዴት ነው? 9. ጌታ በትክክል በህይወታችን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 25 ቆላ.ምዕራፍ 1:7-12

View Details

የእግዚአብሔር ከብዙዎቹ የአምላክነቱ መገለጫው አንዱ፣ ሰውን በስፍራው መመልከት፣ ማወቅና መድረስ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ፈውሶች በእየሱስ ተከናውነዋል ብዙ በረከቶችም ከጌታ ለስዎች ተሰጥተዋል። ይህንን ፈውስና በረከት የተቀበሉ ሰዎች ሁሉ፣ ያልተቅበዘበዙና በስፍራቸው የተገኙ ሰዎች ናቸው። ከበረከታችን ጋር እንድንተላለፍ ሰይጣን የሚጠቀምበት አንዱ ትልቁ መሳሪያው፣ እኛን በማቅበዝበዝ፣ ስፍራችንን አንድንለቅና መገኘት በማይገባን ስፍራ እንድንገኝ በማድረግ ነው። እኛ ግን ያለንበት ስፍራ ምንም የማይመች ቢሆንም፣ ስፍራችንን ላለመልቀቅ በመጨከን፣ የሚለቀቅልንን ጸጋ በመደገፍ በእምነት መጽናት ይገባናል።

View Details

እግዚአብሔር ባዶ ወደሆነው ህይወታችን ሲመጣ ለክብሩ ምስጋና ሊያደርገን ታሪካችንንም ሊለውጥ ነው:: በጉድለታችንና በባዶነታችን ጊዜ አጠገባችን ሊቆም የሚወድ ችግራችንንም የሚካፈል ማግኘት ጭንቅ ነው:: ቢገኝም አብሮን የመቆም ችግራችንንም የመካፈል ሀቅሙ ጥቂት ነው:: ክፉውም ይህን ሁኔታችንን ምክንያት አድርጎ ተስፋ ሊያስቆርጠን የሚጠቀምበት ይሆናል:: ጌታ ግን ጉድለታችንን ሊሞላ ሊያቆመንም ተችሎታል:: ስለዚህ ሰው ሁልጊዜም የሚመስለው የተሞላውን ነው:: በዚህ መልዕክት ባዶነታችን በምን ሊምላ እንደሚገባው እንዴት እንደሚሞላም እንማራለን::

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 24 ቆላ.ምዕራፍ 1:1-8

View Details

የተቀበልነው የጸጋ ስጦታ የተለያየ ሆኖ በሁላችን ውስጥ ያለው የጌታ መንፈስ ግን አንድ ነው፣ ይህ የጸጋ ስጦታ እራሳችንን የምናስተዋውቅበት ሳይሆን ክርስቶስን ከፍ የምናደርግበትና ለአካሉ ጥቅም የተሰጠ መሆኑን ልንረዳ ይገባል፣ በዚህ ትምህርት ውስጥ እነዚህን የተለያዩ የጸጋ ስጦታዎችንና ለአካሉ የሚሰጡትን ጥቅሞች በዝርዝር እንማራለን

View Details

በህይወት ዘመናችን ሁሉ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው:: ነገር ግን ደግሞ በህይወታችን ሊያደርግ ሊፈፅም የሚፈልገውን የሚያደረገው በራሱ ጊዜ ነው:: ስለዚህ በምናየው በምንሰማውና ደግሞም በምንሰራው ውስጥ የጌታን አብሮነት መፈተሽ ፈቃዱንም መመርመር ያስፈልጋል:: አግዚአብሔረ እንዳያልፈን ከቸርነቱና ከበጎነቱ እንዳንጎድል ያጀርጋልና:: በዚህ መልዕክት ለትምህርታችን ደግሞም ለህይወታችን መቃናት ይሆን ዘንድ በህይወታችን ሰለምን ምክንያት ጌታ እንደሚያልፈን በዝርዝር እንማራለን::

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 23 1ኛ ዮሐ2:15,16 ገላ 1:4 ሐዋ 2:40

View Details

ዛሬ የፍላጎታችንን ትልቁን ስፍራ የያዘው ምን ይሆን? መጽሐፍ ቅዱሳችን ግን፣ በማንንኛውም ችግርና መከራ ወይም በተመቻቸ ሁኔት ውስጥ ብንሆን፣ ሁልጊዜ ይህንን ትልቁን ጌታ እንድንፈልግ ያስተምረናል፣ ስንፈልገው ደግሞ እርሱ ፈጥኖ የሚገኝና፣ ከማንኛውም የመከራ አይነት የሚታደገን አምላክ ነው። እግዚአብሔርን በመፈለግ ብዙ ከምናተርፍባቸው ዝርዝሮች ጥቂቶቹ፣ እንጸናለን፣ ሁሉን ወደ ማስተዋል እንደርሳለን፣ ሌሎችን የሚይስጨንቅ ምድራዊው ነገር አያስጨንቀንም፣ ደግሞም እግዚአብሔርን ስንፈልግም በህይወት እንኖራለን።

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 22 ሮሜ ምዕራፍ 7:4-12

View Details

የእግዚአብሔር ቃል ምን ያህል አቅምና ጉልበት እንዳለው የተረዳው ፣የእምነት ምሳሌ አባታችን አብርሃም ልጁን ለመሰዋት አልራራም። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር የተናገረን ቃልና እኛ የምናልፍበት መንገድ ፈጽሞ ላይገጣጠም ይችላል ሆኖም ግን የተናገረን እግዚአብሔር ይሁን እንጂ፣ የሌለን ነገር ወደ መኖር የሚያመጣ፣ ቃሉን የማያጥፍ ጌታ፣ በቃሉ ይገኛል፣ ከኛ ጋርም ሆኖ የሚያናውጠንን ወጀብ ጸጥ ያደግልናል። ቃል ካለን፣ ባዶ አንሆንም፣ አንወድቅም፣ አንጠፋም፣የማንሻገረውም ማዕበል አይኖርም።

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 21 ቲቶ ምዕራፍ 3:5 እና ማቴ ምዕራፍ 1:21

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ቆላ.ምዕራፍ 1:13-14 ክፍል 20

View Details

ጌታ ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ ስለአለና ስጋ ደግሞ ደካማ በመሆኑ መትጋት የምንችለው በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር ስንሆን ብቻ መሆኑን ሊነግረን ነው፣ ሰይጣን በብርቱ የሚዋጋን መንፈስ ከሆነው አባታችን ጋር የጠበቀ ግኑኝነት እንዳይኖረን በማድረግ ነው ይህን መንፈሳዊ የሆነውን የጠላት አሰራር መዋጋትና ማሸነፍ የምንችለው በመንፈስ ስንሆን ነው፣ በመንፈስ መሆን የሚያስገኘውን ውጤት በዚህ ትምህርት በዝርዝር እናያለን፣

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በምናልፈው ነገር እንዴት ነው እግዚአብሔርን ማፅደቅ የምንችለው? እንዴትስ ነው ከእግዚአብሔር ጋር የምንወግነው? 2. እንዴት ነው የከበበንን ጠላታችንን ድል የምንነሳው? 3. በምናየውና በምንሰማው ነገር የምንሰናከለው ከራሳችን ፅድቅ ጋር ስለምናያይዘው ነው ወይ?

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ዮሐንስ ምዕራፍ 12፡20-29 ላይ ጌታ እየሱስን የጠየቁት ሊያዩት ሆኖ የመለሰላቸው ግን ሌላ ነው። ይህ ክፍል ቢብራራልን። 2. እድሜአችን ከገፋ በሗሏ ጌታን አወቅን ታድያ ጌታን በምንድን ነው የምናገለግለው? 3. መታዘዛችን የሚፈጸመው መቼ ነው? አለመታዘዝን የምንበቀለው መቼ ነው? 4. የበቀል ቅባት ተቀባው ይባላል ቢብራራልን። 5. እግዚአብሔር የእጁን ይስጠው የምንለው ይህ የበቀል መንፈስ ነው ወይ ሌላ? 6. በተፈጥሮ ማንነታችን ስርአት ከሌለን መንፈሳዊ ህይወታችን ስርአት የለውም የሚለው ይብራራልን። 7. አስቀድመን የሠራነው ከሌለን ለጌታ አንጠቅመውም የሚለውን ግልፅ ቢሆንንል።

View Details

ከውድቀት በኃላ በሰው ልጅ ላይ መጀመሪያ የተገለጠው የሰው ጠላት ፍርሀት በሰው ላይ ሰልጥኖ ይኖራል:: በውስጥ ፍርሀት በውጭ ፍርሀት በማግኘት ፍርሀት በማጣትም ፍርሀት:: ከዚህ የፍርሀት ባርነት ነፃ መውጫ መንገዱ አንድ ነው:: እርሱም እግዚአብሔርን መፍራት ነው:: እግዚአብሔርን የሚፈራ እርሱ እንደ ቃሉ ይኖራልና በእግዚአብሔር ላይ ያለው መታመን የበረታ ነው::ሰለዚህ የክፉው ስራና ማስፈራራቱ በእርሱ ላይ ሀቅም አይኖረውም::

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 19 ቆላስይስ ምዕራፍ 2:3

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ጠላት የሚፈትነን ሰዓት አለው ወይ? በምን ዐይነት ሁኔታ ስንሆን ነው ጠላት የሚፈትነኝ? 2. በመንፈስ የሚመሩ በውስጣዊ ማንነት ብቻ ነው ወይስ በውጫዊ ማንነት መገለጥ አለባቸው ወይ? 3. ማንነታችንን (የጌታ ልጅ መሆናችንን) መንገር ያለበት ማን ነው? 4. በውስጣችን የተቀመጠውን የጥበብ እውቀት ወደ ህይወታችን እንዲመጣ ምን ማድረግ አለብን?

View Details

ጌታ እየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ፣ የአባቱን ፊት በመፈለግ፣ ለሁሉ መልስን ይሰጥ ነበር፣ የጸሎት ስው ነበር። እኛማ ዛሬ በዚህ እጅግ አስቸጋሪ በሆን አለም የምንኖር፣ ምን ያህል ፊቱን መፈለግ ይገባናል? ጸሎት በእምነት ጌታን እንድናውቅ ከማድረጉ በላይ፣ ትሁቱን ጌታ በመምሰል ወደ እግዚአብሔር መቅረብን ያስተምረናል፣ ደግሞም አንዱ የእግዚአብሔርን ቅርብነት የምንመለከትበት መንገድ ነው። እግዚአብሔር ጸሎትን ይሰማል ግን በኛ ጊዜ ሳይሆን፣ በራሱ ጊዜ ይመልሳል። በዚህ ትምህርት ውስጥ፣ ስለ ጥቂት የተለያዩ የጸሎት ሰዎች መልስ እንማራለን።

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 18 1ኛ ጢሞቴዎስ - ምዕራፍ 1:8-11

View Details

የሰው ልብ እጅግ አስቸጋሪ ነው፣ ልባችን ለራሳችን እንኳን አይታዘዝልንም ምክኒያቱም የሰው ልብ ያለው በእግዚአብሔር እጅ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ፈቃደኞች ስንሆን ግን፣ እግዚአብሔር ልባችንን ይከፍትልናል፣ ንፁህ ልብን ይሰጠናል፣ እራሳችንን እንድናይና ነገራችንን እንድናስተካክል ይረዳናል ያንጊዜ ከእግዚአብሔር ስዎች ጋር ህብረት ማድረግ አንቸገርም፣ ለመንፈስ ቅዱስ ደግሞ የተመቸን እንሆናለን።

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 17 ሮሜ ምዕራፍ 8:9-11

View Details

እግዚአብሔር ሰውን የወደደበት ፍቅር ከመታወቅ የሚያልፍ መንፈስ ቅዱስ ብቻ የሚያበራልንና የሚገልፅልን እውነት ነው:: ይህ ፍቅር የበራለት አማኝ ታላቅ ለውጥ በህይወቱ ይሆናል:: በአስተሳሰብና በእይታው ሁሉ ይለወጣል:: መንፈሳዊ ድፍረትም ይኖረዋል:: በእግዚአብሔር የተወደድንበት ፍቅር ሲበራልን በእግዚአብሔር ላይ ያለን ትምክህት ደግሞም ለፍቅሩ የሚኖረን ምላሽ እለት እለት በምንኖረው ኑሮ ይገለጣል:: የምንምር የምንራራ ደግሞም እኛም የምንወድ እንሆናለን::

View Details

የቀደመችው ቤተክርስቲያን አንዱ መታወቂያዋ እግዚአብሔርን መፍራት ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ስዎች እግዚአብሔርን በመፍራት እንደከበሩና ብዙዎች ደግሞ እርሱን ባለመፍራት ፍርድን እንደተቀበሉ ያስተምረናል። እግዚአብሔርን በመፍራት የምንኖረውን ኑሮ እውን ለማድረግ፣ ለአባትነቱ የሚገባውን አክብሮት ፣ ልጌትነቱ የሚገባውን ክብር፣ በመስጠትና እንዱሁም ለእርሱ ሀሳብና ትዕዛዝ ምላሽ በመስጠት እንገልጻለን። እግዚአብሔርን በመፍራት ስንኖር ጌታ ይከብራል፣ እኛም ከተለያየ የሀጢያት ክፋት እንጠበቃለን፣ እግዚአብሔርን በመፍራት የሚኖሩትን ወገኖች ልብ ደግሞ እናሳርፋለን።

View Details

እየሱስ ማን ነው? ሉቃ.4:1-13 ክፍል 15

View Details

የሐዋርያት ሥራ.26:19-32 ክፍል 93

View Details

ደቀመዛሙርቶቹ እርሱን ሲያዩት፣ ሁሉን ትተው ተከተሉት። መንፈሳዊ አይኖቻችን ተከፍተው፣ ጌታን ካላየን፣ የምንፈልጋቸው ጊዚያዊ ነገሮች፣ ክጌታ እኩል ይሆኑብናል፣ አንዳንዴም ከጌታ በልጠውብን እናገኛቸዋለን። ለአንድ መንፈሳዊ ስው ትልቁ ስጦታው የአይን መከፈት ነው። አይናችን ሲከፈት፣ ሁሉን ለመተውና፣ ጌታችን የሆነውን ክርስቶስን እስከመጨረሻ ለመከተል፣ የሚከፈለውንም ዋጋ ሁሉ ለመክፈል የተዘጋጀን እንሆናለን።

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 16 ሮሜ ምዕራፍ 7:4-6

View Details

እየሱስ ማን ነው? 2ቆሮ.10:1-6 ክፍል 14

View Details

የዲያብሎስን ሽንገላ ለመቃወም ፣ የጌታ እየሱስን ስልጣንና ሃይል፣ እንዲሁም የተሰጠንን መሳሪያ አጠቃቀም ማወቅ አለብን። ይኸውም፣ ወገባችንን በእውነት መታጠቅ፥ የጽድቅን ጥሩር መልበስ፥ የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልናጠፉ የምንችልበትን የእምነትን ጋሻ ማንሳት፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ መያዝ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ እየጸለይን፤ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመነን በመጽናት ሁሉ መትጋት የገባናል።

View Details

አማኝ የጌታን ራት በሚወስድበት ጊዜ ሊያስተውለውና ሊረዳው የሚገባውን ዋና ነገር በዚህ መልዕክት ውስጥ እናገኛለን::

View Details

ጸጋንና ምህረትን ከጌታ የተቀበልን፣ በምህረቱ ውስጥ ያለን አማኞች ሁሉ፣ ልንኖር የሚጠበቅብን፣ ምህረትን እንዳገኘ ሰው ነው። ምህረትን ያገኘ ሰው ደግሞ፣ አይዝም፣ አይቆጥርም ደግሞም አይፈርድም። ነገርን ከእግዚአብሔር ጋር ብናያያዝ በምህረት እየኖርን ነው፣ ነገርን ከስው ጋር ብናያያዝ ግን በምህረት እየኖረን አይደለም፣ ሰይጣን ከህይወት መንገድ እያወጣን ነው። በክርስቶስ ምህረትን ያገኘን ሁላችን ዛሬ ህይወታችንና አኗኗራችን ማንን ይመስላል? የሚጠሉንን እየወደድን፣ የሚረግሙንን እየመረቅን፣ ? ለሚያሳድዱን እየጸለይን፣ በክፉውስ ፋንታ፣ መልካምን እያደረግን ነው?

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 13 ዮሐ.ምዕራፍ 14:8-11

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በዮሐንስ ምዕራፍ 9 ላይ ዐይኑ የተፈወሰው ሰው ጌታን ከተፈወሰ በሗሏ ከማግኘቱ በፊት ምስክርነቱ ትክክል አልነበረም የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 2. ጌታን አግኝተውም ሆነ ሳያገኙ ጌታን የተከተሉ ሰዎች አሉ የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 3. ቤተክርስትያም በመከራ ካላለፈች ለጌታ መሆን አትችልም ወይ? 4. “ፊተኛው አዳም ህያው ነፍስ ሆነ ሗለኛው አዳም ህይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ” የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 5. አማሊቅ የማን ዘር ነው? 6. ሰይጣን ሀጢአት ሲሰራ ይህ አለም ቀውስ ውስጥ አልወደቀም ሰው ግን ሀጢያት ሲሰራ ፍጥረት ሁሉ ወድቃል ለምንድን ነው? 7. ብዙ ተምረን ወደ ተማርነው የማንደርሰው ለምንድን ነው

View Details

አጋር በአግዚአብሔር አይን ለመታየት፣ ለሰው አይምሮ እጅግ በሚከብድ ሁኔታ ውስጥ አለፈች። እንዳንድ ጊዜ የተመቻቸና ትክክለኛ ቦታ ያለን እየመሰለን፣ ግን በእግዚአብሔር አይን ውስጥ ላንሆን እንችላለን። ያንጊዜ፣ አግዚአብሔር በእርሱ አይን መታየታችንን ስለሚፈልገው ፣ በመራራ ነገር ውስጥ እንድናልፍ ይፈቅዳል ግን ይሄ የጊዜው መራራ ጉዞ፣ ከዘለአለም ደስታችን ጋር አንደሚያገናኘን አውቀን የመራራውን ጉዞ፣ ከሰው ጋር ሳናያይዝ፣ እግዚአብሔር በአይኑ ለመታየት ሊያበቃን፣ የዘለአለም ባለታሪክ ሊያደርገንና ከተራ ማንነት ሊያወጣን መሆኑን በመረዳት፣ ደስተኞች ልንሆን ይገባናል።

View Details

እየሱስ ማን ነው? 1 ጢሞ.1:5 ክፍል 11

View Details

ከአብርሃም እስከ ዳዊት አስራ አራት ትውልድ አለ፣ ከዚያም እስከ እየሱስ ድርስ ሄዷል፣ አሁንም ሰዎችን ሁሉ በክርስቶስ የማዳን ስራ፣ የመንግስቱ ስራ እየሄደ ነው። ይህ የእግዚአብሔር ሃሳብ ከትውልድ ወደትውልድ እየተላለፈ የመጣው፣ የእለቱን ሳይሆን የዘላለሙን በተመለከቱ ስዎች ነው። ነገሮችን በራሳችን እይታ ማየት ከጀመርን፣ የመለኮትን ሃሳብ አናሳልፍም፣ እየተራመደ ያለውን የእግዚአብሔርን ስራ ያስቆማል። ማለትም፣ ጌታ በራሱ መንገድ ስራውን ይቀጥላል ግን በኛ አልፎ አይሄድም፣ የጌታንም ስራ በትውልዳችን አናይም ይህ ደግሞ ትልቅ ጉዳት ነው።

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ክፍል 12 ሮሜ ምዕራፍ 12:3

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ጌታ ባደረገልን ነገር ጌታን ማወቅ አንችልም የሚለው ይብራራልን። 2. ሰዎች ፅድቅን ለማድረግ ከኢየሱስ ጋር የሆኑ እመመሰላቸው ከቴታ ጋር ላይሆኑ ይችላሉ የሚለው ይብራራልን። 3. ለሀጢያት መሞት ማለት ምን ማለት ነው? 4. የማላ የተትረፈረፈ በለከት ምንድን ነው? 5. የተቀበልነው ወንጌል ኢየሱስ ማን እንደሆነ ለእኛ ይወስነዋል የሚለው ይብራራልን።

View Details

እየሱስ ማን ነው? ሉቃ.15:11-24 ክፍል 6

View Details

እግዚአብሔር የሰውን ዋና ነገር ይፈልጋል:: ልባችንን:: የሰው ሁለንተና በልቡ ካለው ሀሳብና ፈቃድ ጋር የተያያዘ ነው:: ስለዚህ በፊቱመልካም እንዲሆንልን እንታዘዘውና እንገዛለት ዘንድ ጌታ ልባችንን እንድንከፍት ፈቃዱንም ከቃሉ ምክር እንድንቀበል ይጠይቀናል:: ሰምቶ ለሚከፍት ከጥፋት መዳን ይሆንለታል:: የተራቆትንበት ጉድለታችንም ይሞላል:: በረከትም ወደ ህይወታችነ ይመጣል:: * ለወዳጃችን ለጌታ ኢየሱስ ልባችንን ላለመክፈት ምክንያት አይኑረን::

View Details

ማርያም መልአኩ የነገራት መልእክት ምንም እንኳን ለሰው አይምሮ ከባድ ቢሆን፣ እርሷ ግን የእግዚአብሔርን ነገር በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር። መንፈሳዊ ህይወታችን ትክክል አለመሆኑ አንዱ መገለጫው መጠበቅ ሲያቅተን ነው። የምንጠብቀው የእግዚአብሔር እውነት ግን በውስጣችን ካለ፣ ለጠበቅነው ነገር ለመለየትና ዋጋ ለመክፈል አቅም ይሆነናል፣ የሰይጣን ፈተናም ሲመጣብን፣ የጠበቅነው እውነት ራሱ ጋሻ ይሆንልናል። ይህ በውስጣችን ያለው እውነት ደግሞ ተዳፍኖ መቅረት ሳይሆን በጸጋው በእኛ ውስጥ አልፎ ለትውልድ እንዲደርስ ያስፈልጋል።

View Details

እግዚአብሔር እንደፈቀደ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በማመን ልጆቹ የሆንን ሁላችን በእኛ ካደረው ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ መንፈሳውያን እንባላለን:: መንፈሳዊነታችንም እንደ ጌታ ፈቃድና ሀሳብ በመመላለስ በተግባር ይገለጣል:: ክርስቶስንም እንመስል ዘንድ እለት እለት በቃሉና በመንፈሱ እንሰራለን:: እኛም ለመሰራት እራሳችንን እናቀርባለን በምድር ላይ በተሰጠን አጭር የእድሜ ዘመን በቅድስና በፅድቅ አና በእውነት ልንመላለስ በጨለማውም አለም የወንጌልን ብርሃን በቃልና በህይወት ልናበራ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው::

View Details

በዘመናችን እጅግ ብዙ የዕውቀት መገብያ ድርጅቶች ተከፍተዋል ነገር ግን እነዚህ ሁሉ የዕውቀት ስፍራዎች እግዚአብሔርን ወደማወቅ አያደርሱንም። ለኛ ግን በክርስቶስ እውነተኛ የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቦና ተስጥቶናል። እርሱም እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። እግዚአብሔርን ከማወቅ አንዱ ይህን አለም ለኛ እንዳልተገባ አድርጎ መቁጠር ነው።

View Details

የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ተስፋ፣ በክርስቶስ ደም ታጥበን የእግዚአብሔር ልጆች ለሆንን ሁሉ የተሰጠ ተስፋ ነው። መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል፣ አዲስ ስውና ትሁት ያደርገናል፣ ሀይላችንና ሰላማችን፣ አፅናኛችን፣ አስተማሪያችን፣ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያሳስበን ነው። በዚህ ነውጥ በበዛበት አለም ውስጥ፣ ከመቼውም በበለጠ ይህ መንፈስ በሚይስፈልገን ጊዜ፣ ከዚህ ተስፋ ውጪ ብንሆን እጅግ በጣም እንጎዳለን።

View Details

የቀደመችው ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ቃል እውነት የምትመላለስ በፀና መሠረት ላይ የታነፀች ነች:: ይህ ደግሞ ከቃሉ የተነሳ በጌታ ላይ የፀና ህይወት መኖርን ያመለክታል:: በእግዚአብሔር ቃል ሥር የሰደደና የፀና ህይወት ከየአቅጣጫው በሚነፍሰው የአመፅና የክፋት ንፋስ አይናወጥም:: ስለዚህም ነው ወንጌል በብዙ ፈተናና መከራ አልፎ ወደእኛ የደረሰው:: በዚህ መልዕክት ቅዱሱ የእግዚአብሔር ቃል እለት እለት በህይወታችን ደግሞም በቤተክርስቲያን ያለውን ስፍራና ፋይዳ እንዲሁም ከእኛ የሚጠበቀው ምን እንደሆነ እንማርበታለን::

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ሉቃ.5:27-39 ክፍል 9

View Details

በመለኮት እቅድ የተጠራ ስው፣ ገና በማህጸን ሳለ፣ በጌታ የታወቀና የተጠበቀ ነው። በእምነት እራሳችንን በእርሱ ጥበቃ ውስጥ ማስቀመጥን እንድንለምድ እግዚአብሔር ይፈልጋል። ጌታ ትልቁ የሚፈልገው፣ የታመነ መሆኑን እንድናውቅና በቃሉ የሚገኝ ታላቅ አምላክ መሆኑን እንድንረዳ ነው። እግዚአብሔር እራሱን ለኛ የገለጸው፣ በታማኝነቱ ነው፣ ይህንን ስንረዳ፣ በእርሱ ላይ ተደግፈንና አርፈን መኖር እንችላለን።

View Details

ሰው ለሚያውቀው ምህረትን ሊያደርግ ይችላል ያም ቢሆን እንኳን ምህረቱ ውስን ነው። የእግዚአብሔር የአምላካችን ምህረት ግን ለዘለአለም ነው። ደግሞም ምህረቱ በሁኔታዎች ወይም በስሜት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፣ ቸርነትና ምህረት ባህሪው ነው። በእግዚአብሔር ቤት ለመኖራችን ዋስትና ምህረቱ ነው፣ በዚህ ብዙ ውጣ ውረድና መከራ በበዛበት አለም፣ ወደ ፊት ለመራመድ አቅም የሚሆነን የእርሱን ፍቅር፣ ምህረቱንና በጎነቱን ሁልጊዜ ስናስብ ነው።

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ሉቃ.5:27-39 ክፍል 8

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? መኃልይ.5:2-9 ክፍል 7

View Details

መጠበቅ ቀላል ነገር አይደለም፣ ሕይወትን ወደ ብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ የሚከት፣ ብዙዎች አባቶቻችን ተፈትነው የወደቁበትና ጥቂቶች ያለፉበት ደግሞ በረከታቸውን የተቀበሉበት ነገር ነው። በዚህ ትምህርት ውስጥ፣ በተለየ አገላለፅ፣ የእግዚአብሔርን ታላቅ ፈዋሽነት፣ ፈውስን የተቀበለው የሠላሳ ስምንት አመት ታማሚ በመጠበቅ ውስጥ ያለፈባቸው ሁኔታዎችንና አንዲሁም በአካባቢው ያሉትን ሰዎች ባህሪ እናያለን።

View Details

እግዚአብሔር በልጁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ወደ መንግሥቱ ሲያስገባን ሁለንተናችንን ለራሱ ሊያደርግ ነው:: ለእርሱ ልንሆን ነው:: የአማኝ ደስታና እረፍት ለጌታ መሆኑ ነው:: ነገር ግን ለእርሱ ባልሆንበት በግል ደረጃም ሆነ እንደ ቤተክርስቲያን ከክብሩና ከሰላሙ የጎደልን እንሆናለን:: ስለዚህ በጊዜውም አለጊዜውም በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ለጌታ ልንሆን ፈቃዱም በእኛ ሊፈፀም ቤተክርስቲያንም የበረከት የሰላምና የመፅናኛ ስፍራ ልትሆን ይገባታል::

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ሉቃ.19:1-9 ክፍል 6

View Details

በዚህ ትምህርት ውስጥ፣ ከሰይጣን መጠበቅ የምንችልባቸውን አስፈላጊ ዝርዝሮችን ስንማር፣ ከዝርዝሮቹ አንዱ እግዚአብሔርን መፍራት ነው። እግዚአብሔርን በመፍራት ስንኖር፣ የእግዚአብሔር መላእክቶች በዙሪያችን ይሆናሉ የሚያስፈራንና የሚያስደነግጠን ከእርሱ በቀር ምንም አይኖርም ክፉ ነገርም አያገኘንም። በተጨማሪም፣ እግዚአብሔርን ስንፈራ ከሐጢያት ለመራቅ ጉልበት እናገኛለን የአሸናፊነትንም ሕይወት እንለማመዳለን።

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ለጽድቅ ሊሞቱ የተጠሩ ሰዎች አሉ የሚለውን ብታብራራልን። 2. ችግር ሲገጥመን ዝም ብለን ጌታን እያየን መጠበቅ አለብን የሚለው ይብራራልን። 3. ወደ ቅድስና ህይወት ለመምጣት መንገዱ ምንድን ነው? 4. በሰውነታችን ለሀጢአት ህግ መገዛት እና በአህምሮአችን ለእግዚአብሔር ህግ መገዛት ምን ማለት ነው? 5. ለሀጢአት የሞታችሁ ለጽድቅ ህያዋን ናችሁ የሚለው ይብራራልን። 6. ለሰራነው ሀጢአት የህሊና እና የብርሃን ወቀሳ ልዩነት ምንድን ነው? 7. የምንወቀሰውን በክርስቶስ ካላየነው ሀጢአት ይሆንብናል የሚለውን ብታብራራልን።

View Details

እግዚአብሔር በሰው አይምሮ የማይቻል፣ በስርአትና በሕግ የማይንካ ነገርን አልፎ ይነካል ። በመፅሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ብዙ ምሳሌ የሚሆኑን በእግዚአብሔር የተነኩና ከቀድሞ ማንንነታቸው የተለወጡ ሰዎች ተጠቅሰውልናል። ሰው ከመለኮት ጋር ከተነካካ የቀድሞውን ማንነቱን መሆን አይችለም። ምህረትን፣ ፍቅርንና ፅድቅን የተለማመደ፣ በብርሀን የሚመላለስና፣ የአሸናፊነት ህይወት ያለው ይሆናል። ዛሬ የእግዚአብሔርን ቃል እየሰማን፣ እያመለክንና እያገለገልን፣ የደከምንበት ወይም ያልተነካንበት ነገር ካለ፣ ይህንን ታላቅ ጌታ እንጠይቀው፦ በመራራት፣ እጁን በድን ወደሆነው ነገራችን ላይ ይዘረጋል።

View Details

ኢየሱስ ማን ነው?ዮሐ.4:10 እና 4:39-45 ክፍል 5

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ሊሰራን ወደ እኛ የሚመጣውን የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት ነው በምን መንገድ እንደሚሰራን የምናውቀው? 2. ሰማያዊ ጥበብ ለቤታችን የሚጠቅመን ምንድን ነው? 3. ለጌታ ፍቅራችንን የምንገልጥበት ቃል ነው የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 4. የተገለጠልን፣ የተሰጠን እና የሆነልን ነገሮች ምንድን ናቸው? 5. በእኛ ስለሚበዛው ህይወት ብታብራራልን። 6. ዐይናችን ወደ ጌታ እንዳናነሳ ችግራችን ምንድን ነው?

View Details

አንዳንድ ጊዜ ተስፋ አድርገን በድፍረት የተናገርንበት፣ ነገራችንን ሁሉ የጣልንለትና የምናልፍበት ሁኔታ በጣም የተራራቀና ልብን ዝቅ የሚያደርግ፣ መነጋገሪያም አድርጎን ሊሆን ይችላል። ነገር ግን፣ እግዚአብሔር ተስፋ የሚይደርጉትን፣ ልባቸውንና አይናቸውን እርሱ ላይ ያደረጉትን አሳፍሮ አያውቅም። በምናልፍበት ሁሉ፣ እርሱን በመተማመን አንጠብቀው። በታገስንበትና እርሱን በጠበቅንበት መጥቶ ሀይላችንን ያድሳል፣ ቀና ያደርገናል፣ ለቅሶአችንን ወደ ደስታ ይለውጣል።

View Details

በራሳችን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ብዙ ነገሮችን ለማድረግ እየጣርን፣ እየወጣንና እየወረድን ብዙ እየደከምን፣ ይሄ ሁሉ ድካማችን ግን ከእርሱ ደስታ ጋር አላገናኘን ይሆን። ኢዮሣፍጥ የተባለ የይሁዳ ንጉሥ አንድ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር እንደተገኘበት መፅሐፍ ቅዱሳችን የነግረናል። ይህም ነገር እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን ማዘግጀቱ ነው። እግዚአብሔርን የሚያስደስተው፣ የኛ ልጅ መሆን ነው። እኛም ልጅ መሆናችን ከገባን፣ ልጅነታችንን፣ ከአባታችን ጋር ህብረት በማድረግ፣ እርሱን በመውደድና በመታዘዝ፣ በልጅነት ስፍራችን ልንገኝ ይገባናል።

View Details

የአማኝ አንዱ የደህንነት ትሩፋት ቅዱሱን ጌታ እግዚአብሔርን ማገልገል ነው:: ነገር ግን የምናገለግለውን ጌታ እንደሚገባ ልናውቀው የተገባ መሆኑ ዋና ነገር:: የነገሮቻችን ሁሉ መፍቻ ቁልፍ እርሱን ማወቅ ነውና:: እግዚአብሔር ራሱን የሰወረ አምላክ አይደለም:: ነገር ግን እኛ እርሱን ለማወቅ ያለን ፈቃድ ደግሞም አካሄዳችን ወሳኝ ነገር ነው:: በዚህ መልዕክት እንደ ቃሉ እግዚአብሔርን እንደሚገባ የምናውቅባቸውን መንገዶች በስፋት እንማራለን::

View Details

ኢየሱስ ማን ነው ዮሐ. 4:10 እና 4:39-45 ክፍል 3

View Details

ኢየሱስ ማን ነው?ዮሐ.4:10 እና 4:39-45 ክፍል 4

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ዮሐ. 4:10 እና 4:39-45 ክፍል 2

View Details

መንፈስ ቅዱስ ስለ ኃጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድም የሚነግረን አውነተኛ የሕይወት መሪ ነው። ይህ ከክርስቶስ ጋር አብሮ ይስራ የነበረው መንፈስ፣ የእየሱስ የሆነውን ሁሉ የሚነግረንና፣ ይህንን ታላቅ ጌታ በሕይወታችን እንድናከብር የሚረዳን መንፈስ ነው። ካለዚህ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ወደ እውነት መድረስ ስለማንችል አጥብቀን ይህንንን መንፈስ መፈለግና ለመቀበል ደግሞ ልባችንን ማዘጋጀት ይኖርብናል።

View Details

የክርስቶስ ወገን የሆንበት አንዱ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ስላለብን ነው። መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ስላለ፣ መንፈሳዊ ሰዎች ለመባል አያበቃንም ነገር ግን መንፈሳዊ ሰዎች የሚያሰኘን፣ ለዚህ መንፈስ ቅዱስ ዕውቅናን በመስጠት፣ ስናከብረውና ሀሳባችንንም ፈቃዳችንንም እንዲገዛ ስንፈቅድለት፣ በሕይወታችን ደግሞ ተገልጦ ፍሬው ሲታይ ነው።

View Details

የቤተክርስቲያን መልክ በውስጥና በውጭ የሚገለጥ ነው:: በውስጥ በሰላም የተሞላች ነበረች:: በውጭ ደግሞ መፈራትና ሞገስ ነበራት:: የቤተክርስቲያን ሰላም ከጌታ የተቀወለችው በውጭ ባለው ሁኔታ የማይወሰን በበመከራና በፈተና ውስጥ እንኳ የማይደፈርስ የፀና ሰላም ነው:: ጌተ የሰጠን ሰላም አለም እንደሚሰጥ ሳይሆን በሁኔታዎች የማይደፈርስ የውስጥ ሰላም ነው:: እያንዳዳችን በዚህ ሰላም ከተሞላን ደግሞም ከጠበቅነው ቤተክርስቲያንም በዚሁ ሰላም የተሞላች ትሆናለች:: ስለዚህ በቤታችን በስራ ቦታ በስፍራው ሁሉ ራስን በመግዛት ጌታንም በመታመን የሰላም ሰው ሆነን ልንመላለስ ያስፈልጋል::

View Details

መታዘዝ ማለት ራስን በጌታ ፈቃድ ውስጥ በገባን በተረዳንና በተገለጠልን ማግኘት ማለት ነው:: ለአማኝ በህይወት ለመኖር ለመጠበቅና ለማደግ አስተማማኝ ስፍራ እርሱ ለመታዘዝ ህይወቱን የሰጠበት ስፍራ ነው:: መታዘዝ እነደ ደረስንበት መረዳት መጠን ዋጋ ያስከፍላል:: ይሁን እንጂ የመታዘዛችን ፍሬው የህይወት መብዛት ነው:: ከእኛ አልፈን ለሌሎችም በረከት ሰላምና መፅናናት እንሆናለን:: በአሸናፊነትም ህይወት ይቀጥላል::

View Details

እግዚአብሔር ሂዱ ባለን መንገድ ላይ ከሆንን፣ በተለያየ እቅጣጫ ብዙ የሚያናውጥ ሁኔታ በዙሪያችን ቢከስት እንኳን፣ ፍጥረት ሁሉ የሚታዘዝለት ይሄ ታላቅ ጌታ ብቻችንን እይተወንም። ሂዱ ያለን አምላክ እንደማይተወን በማመን፣ በስልጣኑ ሁሉን ማድረግ የሚችለው አምላካችን፣ የሚናገረንን ቃል ብቻ እየሰማን፣ በዙሪያችን ያለውን ወጀብ ሳይሆን፣ አይኖቻችንን ብርቱ በሆነው አምላክ ላይ ልናደርግ ይገባናል።

View Details

የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ስንፈልግ የሚይስፈልገን ነገር ሁሉ ይጨመርልናል። እግዚአብሔር ልጆቹን የሚባርክበት የተለያዩ ቁልፎች አሉ፣ ከብዙ የበረከት ቁልፎች አንዱ፣ የእግዚአብሔር የአምላካችንን ስራ በመተባበር እርሱ በሚፈልገው ሁኔታ መስራት ሲሆን፣ ለዚህ ስራ ስንነሳሳ፣ ልባችንን ከመንገዳችን እንድናነሳና የእግዚአብሔርን ስራ ለማደናቀፍ፣ ሰይጣን መካሪ ይገዛብናል፣ በሌለንበት ነገር ክስ ያዘጋጅብናል፣ ሌሎችም ብዙ የተለያዩ ፈተናዎችን በመንገዳችን ያቆማል። በዚህ ሁሉ ግን እኛ ለእግዚአብሔር ስራ ጨክነን ስንቆም፣ እግዚአብሔር፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ የሚል ድምጹን ያሰማናል።

View Details

ኢየሱስ ማን ነው? ዮሐ. 4:10 እና 4:39-45 ክፍል 1

View Details

የሐዋርያት ሥራ.28:23-31 ክፍል 106

View Details

የሐዋርያት ሥራ.1:8 ክፍል 107

View Details

እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክ ሆኖ ሳለ፣ አንድ የማይችለውና የማይተባበረው ክሃጢያት ጋር ነው። እንዱ ትልቁ የጸሎት እንቅፋት ንስሀ ያልገባንበት ሃጢያት ሲሆን፣ ሌሎችም እንቅፋቶች በዝርዝር በዚህ ትምህርት ውስጥ ተጠቅሰዋል። እንዲሁም እነዚህን የተዘረዘሩትን የጸሎት እንቅፋቶች ካላስወገድን፣ የሚደርሱብንን ጉዳቶችና፣ እነዚህን እንቅፋቶች ለማስወገድ ደግሞ መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች እንማራለን።

View Details

እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ የስው ልጆችን ለልባቸው ፈቃድ ይሰጣል። ሰው ደግሞ ለልቡ ፈቃድ ሲሰጥ፣ ክንዱን አምላክ ያደርጋል፣ ስለሚፈልገው ነገር የሚያደርገው ሁሉ ትክክል ይመስለዋል፣ የመጨረሻ ጥበቡንና ብርታቱን ይገልጣል ነገር ግን ሰው የእግዚአብሔርን ፅድቅና ዕውነት ማዛባት ሲጀምር፣ ፃድቁና ፍርድ አደላዳዩ አምላክ እግዚአብሔር ይነሳል፣ ጣልቃ ይገባል። እግዚአብሔር ሲነሳ ደግሞ የሰው ኩራትና ትእቢት ሁሉ ከንቱ ይሆናል፣ ትልቅ ነኝ ያለው ትንሽ ይሆናል።

View Details

ዳዊት እግዚአብሔርን የለመነውና ሁልጊዜ የሚሻው አንድ ነገር ነበር ይኸውም፤ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት መኖርና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ማየት ነበር፣ ይህ ደግሞ ዳግመኛ ከማይጠፋ ዘር የተወለድን ሁላችን ልንመኘው የሚገባ ነገር ነው። ብዙ የጌታን ፍቅርና ምህረት ከመለማመዳችን የተነሳ፣ የእግዚአብሔርን ክብር እንዳንዳፈር፣ ነቅተን፣ ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን ክብር ባለማጛደል ለመኖር ስንወስን፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ይረዳናል።

View Details

የሐዋርያት ሥራ.28:17-22 ክፍል 105

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በህይወታችን ላይ ያለውን መንትያ ሀሳብ ለመጣል ስንሞክር ወድቀን እንቀራለን የሚለውን ግልፅ ብታደርግልን? 2. ፍሬ እንድናፈራ የሚያደርገንና ፍሬ እንዳናፈራ የሚያደርገን ወንጌል አለ የሚለውን ግልፅ ብታደርግልን። 3. በወጀብ ውስጥ ስናልፍ ጌታ አጠገባችን እያለ የለሌለ ይመስለናል የሚለውን ቢብራራልን። 4. ሰዎችን ማፅናናት የምንችለው ጌታ ሲናገረን ብቻ ነው ወይስ እኛም ማፅናናት እንችላለን ወይ? 5. ጌታ ጳውሎስን “አብረሁ ያሉትን ሰጥቼአለሁ” ያለው በሥጋ ነው ወይስ መንፈሳቸውንም ጭምር ነው? 6. የአህምሮ እና የልብ ጠቢብነት የሚለው ቢብራራልንና የልብ ጠቢብነት ቀድሞ የአህምሮ ጠቢብነት ሊከተል ይችላል ወይ?

View Details

በዚህ በክፉው በተያዘ ደግሞም ወደ ጥፋቱ እየፈጠነ ባለው አለም ያለን የእግዚአብሔር ልጆች በሁሉ ነገር ንቁ ልንሆን ያስፈልጋል:: ንቁ ያልሆነ ከሚታየው አልፎ ከመንፈስ ቅዱስ የሆነውን ዘልቆ የማያይ እርሱ ለዘመኑ ባዳ ነው:: ይህ መልዕክት በህይወታችን ንቁ እንድንሆን ደግሞም በፊታችን ከቆመው ከሚያስፈራራንና ከሚያስጨንቀን ችግራችን ይልቅ የምናመልከው አምላክ እርሱ ትልቅ እንደሆነ እናይ ዘንድ ያነቃቃናል::

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. የእግዚአብሔር ሀሳብ አውቀን መውጣት ማለት ከራሳችን ያለፈ ለሌሎች በረከት ያደርገናል ማለት ነው ወይ? 2. በህይወታችን እድገት የማናየውና ወደ ደስታ የማንመጣ ከሆነ ችግሩ አለመለወጣችን ነው ወይስ አለመዳናችን ነው? 3. ለእግዚአብሔር ቀንተን ሰውን ልናስዝን እንችላለን ወይ? 4. አልኮል መጠጥ መጠጣት ተፈቅዳል ወይ? ከተፈቀደስ መጠን አለ ወይ? 5. መጠጥ የሚለው አልኮል ያለው ሳይሆን ሌሎች የሚያሰክሩ ነገሮች አሉ የሚለውን ብታብራራልን። 6. ዳዊት “አንተን ብች በደልኩ” ሊል የቻለው በምን መረዳት ውስጥ ሆኖ ነው? 7. ሀጢያትን እግዚአብሔር እንደምንበድል ሲገባን ለሀጢአት የሚኖረን ክብደት ይጨምራል ማለት ነው?

View Details

የነቃ መንፈሳዊ ነገራችን ያያል፣ ያስባል፣ ይለያል። ንቁዎችን እግዚአብሔር አያልፋቸውም፣ እንቁዎቻቸውን ይጠብቃሉ ከአጉል መንገድም ይጠበቃሉ። በኛ ላይ ያለውን ፀጋ የመጠበቅ ሃይላችን የነቃነውን ያህል ነው። ሰይጣን በርኩሰት፣ የብርሃን መልአክ መስሎ በመገለጥ እንዲሁም በጥበብ ተመስሎ ሁልጊዜ የሚያደባው ባልነቃንበት የህይወት ክፍል ነው። ወደ ህይወታችን ገብተው ዛሬ መውጫ ያጡ ነገሮቻችን ሁሉ፣ ባልነቃንበት ቀን የገባንበት ወይም የገባብን ነገር ነው። ስለዚህ፣ ክዚህ በኋላ ሁልጊዜ በነቃ መንፈስና በትጋት እንድንኖር መንፈስ ቅዱስ ይርዳን።

View Details

የሐዋረያት ሥራ.28:10-16 ክፍል 104

View Details

መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ በወረደ ጊዜና የመጀመሪያውን የወንጌል ምስክርነት አሰምተው ሰዎች በኢየሱስ ባመኑ ጊዜ የቤተክርስቲያን ውበት መገለጥ ጀመረ:: በአመታት መካከል በቁጥር እየበዛችና እያደገች ደግሞም እየተገለጠች መጣች:: መከራ እየጨመረ በመጣ መጠንም በቤተክርስቲያን አብዝቶ ድንቅና ተአምራት ይሆን ነበር:: ፀጋም ይገለጥ ነበር:: በጉዞ ውስጥ ድካም ሲኖር ዝለት ሲመጣ ጌታ ደግሞ ተሃድሶን ያደርጋል:: ጉብኝት ይሆናል:: ሀይል ይታደሳል:: እንደ ቀድሞ የእግዚአብሔር ሀይል ይገለጣል:: በዚህን ጊዜ ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከእርሱ ጋር ያለው የሰው ግንኙነት እንዲታደስ ይፈልጋል::

View Details

የሐዋረያት ሥራ.28:7-10 ክፍል 103

View Details

ትልቁ አምላካችንና ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ሲመላለስ የሁሉ ነገር ምንጩ አባቱ ነው። ሁሉን የተቀበለውና ለሁሉ ነገር መልስ የሰጠን ወደላይ እያየ ነው። እኛም ዛሬ ከአመጻ የተነሳ ፍቅር በቀዘቀዘበት፣ ርህራሄና መተማመን በጠፋበት በዚህ አለም ስንኖር፣ አይናችንን ልናነሳ የሚገባን ወደላይ ወደ ጌታ ነው። አንዱ የታማኝነት መገለጫ አይናችንን በርሱ ላይ ማድረግ ሲሆን፣ አይናችንን ከርሱ ላይ ማንሳት ደግሞ ዋጋ ያስከፍላል።

View Details

የሐዋርያት ሥራ.28:1-6 ክፍል 102

View Details

ተለክቶ በተሰጠን በዚህ ዘመናችን በእኛ ህይወት እግዚአብሔር ሊያደርግ ካቀደው ከወሰነው ማንኛውም ነገር ከማድረግ ከመፈፀም የሚያግደው አንዳችም ነገር የለም:: የሚያገኘን ክፋት ደግሞም የምናልፍበት ሁኔታ በእኛ ላይ ያለውን የጌታን ጥበቃ ሊያልፍ ማዴኑንም ሊከለክል አይችልም:: ለትምህርታችን ተፅፏልና በቀደሙት የእምነት አባቶች ህይወት የተገለጠውን የጌታን ማዳን ጥበቃውንም በዚህ መልዕክት በስፋት እንማራለን:: ዛሬም ጌታ የሚታደግ የሚያስመልጥ እንደሆነ እናይበታለን::

View Details

ያለ መንፈስ ቅዱስ ህይወትም ሆነ አገልግሎት ድካም ነው። በመንፈስ ቅዱስ የተነገረለትና፣ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የተወለደው ትልቁ አምላካችንና ጌታችን ወንጌልን መስበክ የጀመረው፣ በሽተኞችን ይፈውስና አጋንንትን ያስወጣ የነበረው በእግዚአብሔር መንፈስ ነው: በሚያደርገው ነገር ሁሉ ይህ መንፈስ አብሮት ነበር ። ትልቁ ጌታችን በመንፈስ ይህን ካደረገ፣ ለኛ ለደካሞቹ ምን ያህል ይህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚያስፈልገን ማሰብ አያዳግተንም። ይህ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የሚሠጠው ፈቃደኛ ለሆኑና ለሚፈልጉት ስለሆነ፣ ዕለት ዕለት ከምንም ነገር በላይ አጥብቀን ልንፈልገውና ልንሞላው የተገባ ነው።

View Details

የሐዋርያት ሥራ.27:39-44 ክፍል 101

View Details

የእግዚአብሔር ቃል ሰው ከታናሽነቱ ጀምሮ ሀጢአተኛና ከእግዚአብሔር ክብር የጎደለ ደግሞም ከሀጢአት የተነሳ በእግዚአብሔር ፊት ሊቆም የማይችል እንደሆነ ይናገራል:: ይሁን እንጂ ግዚአብሔር ሰውን ከመውደዱ የተነሳ በራሱ ምረጫ እንደገና በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ወደ ክብር ሊያመጣው ወደደ:: በዚህ መልዕክት ድንቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን ምህረት ደግሞም የእኛን የአማኞችን ማንነት በምድር ላይ ባለ አጭር ዘመናችንም ሊኖረን የሚገባውን ኑሮና እንዲሁም ደግሞ የህይወት መዳረሻችንንም በስፋት እንማራለን::

View Details

በየዘመናቱ እግዚአብሔር ሀያላን የሚላቸውን ሰዎች በህዝቡ መካከል ያስነሳል:: የእርሱን ፈቃድ የሚፈፅሙ ሀሳቡም የሚከናወንባቸው:: ስለዚህ ሀያላን በመካከላችን እንዲበዙ ደግሞም ሀይላቸው እንዳይደክም የእግዚአብሔርንም ፈቃድ ከመፈፀም እንዳይዝሉ ልንፀልይ ያስፈልጋል:: በዚህም መልዕክት ሰለሀያላን መነሳት በፀሎት እንተጋ ዘንድ ሰለምን እንደሚዝሉ ደግሞም ስለምን እንደሚወደቁ በስፋት እንማራለን::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.27:33-38 ክፍል 100

View Details

በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለን፣ እግዚአብሔር በክርስቶስ እየሱስ ሕይወትን ሰጠን፣ በጸጋም አዳነን፣ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ሆኖም ግን ይህንን ደህንነታችንን የማይወድ ሰይጣን፣ ሊያዘናጋን ሁልጊዜ ይተጋልና፣ ሃሳቡን ላለመሳት፣ ክፉ ስራዎቹን ልናውቅ ይገባናል። በዚህ ትምሕርት ውስጥ በሰፊው የነዚህን ክፉ መናፍስቶች ስራ ተዘርዝረው እናያለን።

View Details

ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብና ከእግዚአብሔር ጋር ስንሆን ሁልጊዜ አሜንና ሐሌሉያ የምንልበትን መልስ ብቻ ላንቀበል እንችላለን። ሊሆን የሚገባው ባይሆን፣ በጥያቄያችን ላይ ጥያቄ ቢደራረብብን፣ ጌታ ከባሕሪው ተካፋዮች ሊያደርገንና ዕይታችንን ከእግዚአብሔር ዕይታ ጋር ሊያስማማ ነውና፣ እኛ ግን እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ እንዳለና እውነተኛ ፈራጅ መሆኑን ተረድተን፣ እግዚአብሔር በኛ የጀመረውን ስራ እንዲጨርስ፣ በፊቱ ዝም ብለን እርሱን ብቻ ከምስጋና ጋር መጠበቅ ይኖርብናል።

View Details

የሐዋርያት ሥራ.27:27-32 ክፍል 99

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ከጌታ የሆነውንና ከሌላ የሆነውን መከራ እንዴት ነው የምንለየው? 2. እኛ የጌታ ባርያ ነን የሚለው ይብራራልን። 3. “በዋጋ ተገስታችኋልና የሰው ባርያ አትሁኑ” የሚለው ምን ማለት ነው? 4. ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ ከፍታ የሚያወጣንን መከራ እንዴት ነው መለየት የምንችለው? 5. ጌታ ከተናገረን ተቃራኒ ነገር ሲገጥመን ምን ማድረግ ነው ያለብን? 6. የዳነ ሰው ችግር ሲገጥመው እርግማን ነው ይባላል እና የዳነ ሰው እርግማን ያጋጥመዋል ወይ?

View Details

የሐዋርያት ሥራ.27:15-32 ክፍል 98

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. መንፈሳዊ ህይወታችንን ጠብቀን አጉል ቦታ ላሉት ወንጌልን እንዴት ነው ማድረስ የምንችለው? 2. የማይሆን ነገር መስማት ሀጢያት ነው የሚለው ይብራራልን። 3. በታማኝነት ያደረግነው ነገር የተረሳ የሚመስለን ግዜ አለ የሚለው ይብራራልን። 4. በእግዚአብሔር ፊት ባዶ ለመሆን ማደረግ ያለብን ነገር ምንድን ነው? 5. የጴጥሮስ ዋና ጠላቱ አውቃለው ማለቱ ነው የሚለው ይብራራልን? 6. ጌታን እናገለግላለን የምንል ሰዎች እንዴት ነው ወደ ባዶነት መምጣት የምንችለው?

View Details

ጌታን መከተል ማለት ለእግዚአብሔር ፈቃድ መኖር ለሀሳቡም መገዛትና በመንገዱ መሔድ ማለት ነው:: በእርሱ ፈቃድና ሀሳቡ ለመኖር የሚያስፈልገው የሰው እውቀትና ችሎታ ሳይሆን የሰማያዊው ጥሪ ተካፋይ መሆን ደግሞም በፀጋው መቆም ነው:: እግዚአብሔርን መከተል የእኛን ፈቃድ ይጠይቃል:: ደግሞም ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀን ልንሆን ያሰፈልጋል:: በመረጥንበትና በወሰንበትም ልክ የሚያበቃንን ፀጋ እንቀበላለን::

Activity

View Details

የሐዋርያት ሥራ.27:9-12 ክፍል 96

View Details

የሐዋርያት ሥራ.27:13-20 ክፍል 97

View Details

በምድር ሥህተት የሌለበት የከበረ ሕይወት፣ ሰው እግዚአብሔርን አስቀድሞ የሚኖረው ሕይወት ነው። የነገር ሁሉ መነሻና መድረሻ የሆነውን ትልቁን እግዚአብሔርን መውደዳችንን የምንገልጥበት መንገድ እርሱን በማስቀደም ሲሆን፣ ማስቀደማችንን ደግሞ የምናሳየው፣ የራሳችንን ፈቃድ በመተው፣ ከሐጢያት በመራቅ፣ ያለ ሁከት፣ በሰላምና በእርጋታ፣ ነገራችንን ሁሉ በርሱ ላይ ጥለን በእረፍት በመኖር ነው።

View Details

በመከራና በስደት ወይም በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ማለፍ ደስ የሚያሰኙ ሁኔታዎች አየደሉም ሆኖም ግን እንዚህ ሁኔታዎች የእግዚአብሔርን አብሮነት ማሳያ መንገዶች ናቸው። እግዚአብሔር አብሮን ሲሆን፣ በጊዜው ከመጣብን የሕይወት ነውጥ ይታደገናል፣ የሚታየውን ብቻ ሳይሆን የውስጣችንን ነውጥ ሁሉ ወደ መረጋጋት ይለውጠዋል። እግዚአብሔር አብሮን ሲሆን፣ ሰልፍ የለም ማለት አይደለም፣ ነገር ግን በሰልፍ ውስጥ ድል አለ።

View Details

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ዳግመኛ በተወለድን ጊዜ የእርሱን መንፈስ ተካፍለናልና መንፈሳውያን ተብለናል:: መንፈሳዊ ስንባል መነፈስ ሆነናል ማለት ሳይሆን ነገር ግን ከተካፈልነው የክርስቶስ ቅዱሱ መንፈስ የተነሳ በእኛ ላይ ሰልጥኖ የነበረውን የሥጋን ሥራ በመግደል ለእግዚአብሔር ፈቃድና ሀሳብ ሁለንተናችንን በማስገዛት መመላለስ ነው:: * መንፈሳዊነታችን በልባችን ውስጥ ከሚመላለሰው ሀሳብ ጀምሮ በውጭ እስከሚሰማና እስከሚታይ እንቅስቃሴያችን ድረስ እለት እለት በኑሮአችን የሚገለጥ ነው::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.27:1-12 ክፍል 95

View Details

መንፈስ ቅዱስ ህያውና የሚሰራ፣ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራንና እረፍትን የሚሰጠን መንፈስ ነው። ይሕ መንፈስ በአማኝ ሕይወት በጣም ብዙ ስራዎችን ይሰራል፣ የእግዚአብሔርም ክብር በመካከላችን እንዲታይ ያደርጋል ሆኖም ግን ይህ ህያው የሆነው መንፈስ በሙላት በህይወታችን አንዳይሰራ የሚያደርጉ ነገሮች አሉ። አስራ አራት የሚሆኑ የመንፈስ ቅዱስ ስራ እንቅፋቶችን በዚህ ትምህርት ውስጥ ተጠቅሰው እናያለን።

View Details

አማኝ ህይወቱ ጌታን የሚከተል ተልዕኮ ያለው በዚህ ምድር በአላማ የሚኖር ነው:: ተልዕኮውም የኢየሱስን ሞትና ትነሣኤ በቃልና በስራ በኑሮ የመስከር ሰውንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መንስት ማፍለስ ነው:: ስለዚህ አማኝ ሁሉ በደቀመዝሙርነት ህይወት ሊመላለስ ደግሞም ለአማኝ ሁሉ በተሰጠው ስልጣን ስሙን ሊጠራና በእምነትም ስልጣኑን ሊጠቀምና ሊመላለስ የጌታ ፈቃድ ነው:: በዚህ መልዕክት የደቀመዝሙርን ህይወት ከስልጣንና ከእምነት ጋር በተገናኘ በስፋት እንማራለን::

View Details

እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ እንደተፃፈ ቅዱሳን ልንሆን ተጠርተናል:: ለዚህ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደመምሰል ህይወት እንድንመጣ እለት እለት መንፈስ ቅዱስ ያዘጋጀናል:: መንፈስ ቅዱስ ካዘጋጀው በላይ በእግዚአብሔር ፊት የበቃ ወይም ቅዱስ ሆኖ መታየት አይቻልም:: መንፈስ ቀዱስ ከፊት ሊሆን ያለውን የሚያውቅ ስለሆነ ከወዲሁ ያዘጋጀናል::ሰለዚህ የምናልፍበት ምንም አስቸጋሪ እና አስፈሪ ቢሆን እንኳ በእርሱ ችሎት እናልፈዋለን::አስቀድሞ ለችግሩ ለፈተናው አዘጋጅቶናልና:: ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ የሚለው ቃል እንዲሀ አይደለም:: ነገር ግን የሚያዘጋጀን መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቶን ነው እንጂ::

View Details

የክብርን ወንጌል ሰዎች ሰምተው ወደ ጌታ እንዳይመጡ ከሚዋጋበት መንገድ አንዱ የሰዎችን መንፈሳዊ አይን በማሳወር ጆሮንም በማደንቆር ነው:: በአማኞችም አዕምሮ ክፉ ሀሳብን በመላክ ደግሞም አይኖቻችን በአለም ውበት እንዲሳቡ በማድረግ ይዋጋል:: ይሁን እንጂ በክርስቶስ በስሙ ስልጣንና በፀጋው ጉልበት አሸናፊዎች ነን:: ለጨለማው ገዢ እምቢ እያልን ለጌታ ግን በመገዛትና በመታዘዝ ፈቃዳችንንም ሁሉ ለእርሱ ፈቃድ በማስገዛት ልንመላለስ ያስፈልጋል

View Details

ጊዝያትና ዘመናት ይለዋወጣሉ፣ ነገስታቶች ወደ ስልጣን የወጣሉ ደግሞም ከስልጣን ይወርዳሉ። ጥበብና ሀይልን የተሞላው አምላካችን እግዚእብሔር ግን ዙፋኑ የማይናወጥ የሁሉ ገዢና ጌታ ነው። እኛም የማይናወጥ መንግስት የሚጠብቀን ሰዎች መሆናችንን ተረድተን፣ አንድ ቀን በፊቱ እንደምንቆም በማመን፣ በመፅናት እርሱን አምላካችንን መጠባበቅ ይኖርብናል።

View Details

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ በተለያየ ጊዜ፣ በተለያዩ ቦታዎች ለብዙዎች ደርሳ ያደረችውን ድንቅ ነገሮች በዚህ ትምህርት ውስጥ እናያለን። እጁ ለሚፈሩት ትታወቃለችና፣ የአግዚአብሔር እጅ ወደ እኛ እንድትመጣ፣ አግዚአብሔርን መጠየቅና አሱን በመፍራት በፅድቅና ከበደል ነፃ የሆነ ኑሮን ልንኖር የተገባ ነው። በተጨማሪም፣ እግዚአብሔር አምላካችንን ከፍ ከፍ አያደረግን፣ ከምስጋና ጋር ለእግዚአብሔር ስራ መነሳሳት አለብን።

View Details

የሐዋርያት ሥራ.26:19-32 ክፍል 94

View Details

ጌታ እየሱስ የድል አምላክና ለሁሉ መልስ ነው። ለጥያቂያችን ሁሉ መልስ የሚሆነው ግን የህይወታችንን ዋና ክፍል በሰንጥነው መጠን ነው። ዛሬ ጌታ ስጡኝ ሲለን ያልለቀቅንለት፣ በብዙ ነገር እያለፍን ጌታን ወደዳር ያስቀመጥንበት፣ ወደላይና ወደታች የምንልበት፣ ተሸክመን የምንደክምበት ነገር ምን ይሆን? ለከበደን ነገር ሁሉ መፍትሄ ለማግኘት፣ ጌታ እየሱስ የህይወታችን ሁለንተና እንዲሆን እንፍቀድለት።

View Details

የሐዋርያት ሥራ.26:1-19 ክፍል 92

View Details

አማኝ የተጠራው በራሱ ትግል ትክክለኛ ሰው እንዲሆን አይደለም:: ነገር ግን እግዚአብሔርን በመምሰል በፀጋው ጉልበት በሚሄድበት ሁሉ ብርሃን ለመሆን ኢየሱስን ለማሳየት ነው:: ይኸውም በቃል ብቻ ሳደሆን ደግሞም በመኖር ጭምር ነው:: በዚህ ምድር በተሰፈረው ዘመናችን በእኛ ህይወት የበራውን ብርሃን ክርስቶስን ለማብራት መጠራታችን ትልቅ እድል ነው::

View Details

የሰማነው ወይም ያየነው ነገር ሳይሆን የሞተ ነገራችን ነው ታማኝ የሚያደርገን። ከምድር ወጥተን ከስጋችን ተለይተን የላይኛውን ማየት ስንጀምርና የደህንነታችን መሰረት የሆነውን ክርስቶስን ተደግፈን በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ስንሆን መፅናት እንችላለን።

ሰው በሐይሉ አይበረታም እንደሚል የእግዚአብሔር ቃል፣ የሚያበረታን ፀጋው ነው። ሰይጣን ግን ሁልጊዜ በትጋታችን ሊያስመካን ይጥራል።

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በህይወታችን ወደ እግዚአብሔር ሀሳብ እንዴት ነው የምንመጣው? 2. ይሁዳ ከጌታ ጋር ሦስት ዓመት ተኩል ከቆየ በሗላ ጌታ አሳልፎ ወደ መስጠት የመጣበት ምክንያት ምንድን ነው? 3. በምናልፍበት ህይወት ላይ በእምነት ጌታ ብርሃኔ ነው ማለት የምንችለው እንዴት ነው? 4. ጌታን በህይወታችን ብቁ እንዳይሆን የሚያደርጉ ነገሮች ምንድን ናቸው? 5. በፀሎት ጌታን እንጠይቃለን ወደ ጌታ ግን አናመጣውም የሚለውን ብታብራራልን። 6. ጣርያ ነድለው ወደ ጌታ ያመጡትን ሰው ጌታ የፈወሰው ያመጡትን ሰዎች እምነት አይቶ ነው ወይስ የሰውየው እምነት?

View Details

የሐዋርያት ሥራ.25:12-27 ክፍል 91

View Details

በአንድ አማኝ ህይወት ውስጥ ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ከሞት ወደ ህይወት የመጣበት ዳግመኛ የተወለደበትና የእግዚአብሔር መንግስት ዜጋ የሆነበት የጉብኝት ቀን እጅግ አስደናቂ ሁልጊዜም የሚታሰብና ደስም የምንሰኝበት ነው:: እንደዚሁም ደግሞ በተለየ ሁኔታ የእግዚአበሔር ጉብኝት ወደ ህይወታችን ይመጣል:: ሰለዚህ ከጉብኝቱ ጋር እንዳንተላለፍ ዘወትር በጥንቃቄና በተቀደሰ ህይወት እንደ እግዚአብሔርም ፈቃድ ልንመላለስ ያስፈልጋል::

View Details

ትልቁ የአማኝ በረከት የዘላለም ህይወት የኃጢአት ሰርየት መፅናናተ ሰላምና ደሰታ የሆነው ጌታ እግዚአብሔር የእኛ መሆኑና እኛም ለእግዚአብሔር መሆናችን ነው:: ይህም በረከት ከእግዚአብሔር ነውና ከእኛ ማንም ሊወስደው አይችልም:: ሰለዚህም የአግዚአብሔር በሆኑት ላይ የበረከት ተቃራኒ እርግማን እንዳይሰራ እናያለን:: ነገር ግን ከእግዚአብሔር ፈቃድ በወጣንና ባልታዘዝን ጊዜ በህይወት ጉዟችን ሊያገኙን ያሉት በረከቶች ይያዛሉ:: ሰለዚህ ለእግዚአብሔር በመገዛት በመታዘዝም በመንገዱ በእውነትና በፅድቅ ልንሆን ያስፈልጋል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.25:1-12 ክፍል 90

View Details

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አንዲሆን እየሔድንበት ካለው ከራሳችን ሀሳብ ደግሞም ከክፉ ስራችን መመለስ ያስልጋል:: እዲሁም ደግሞ በምናልፍበት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ከተናገረን ከቃል ኪዳኑ የተነሳ እርሱ ከእኛ ጋር ይሆናል:: የተቀበልነው ተልዕኮም የወንጌል ስራ የእርሱን አብሮነት ይጠይቃልና ሰለወንጌል በምናልፍበት ፈተና ውስጥ ጌታ ከእኛ ጋር ይሆናል:: እግዚአብሔር እርሱ በቃሉ የታመነ አምላክ ነው::

View Details

የክርስትና ህይወት የተጀመረው ካሸናፊነት ነው። ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ሞታችንን ሞቶ፣ የዕዳችንን ጽሕፈት ደመስሶ፣ በእርሱ የኃጢአትን ስርየት አግኝተን የድል ሕይወትን ስጥቶናል። የድል ሕይወትን ስለሰጠን ደግሞ የድል ኑሮን እንድንኖር ይጠብቅብናል። የድል ኑሮን ለመኖር፣ እርሱን ድል የሰጠንን አምላካችንን በማክበር፣ ሁልጊዜ እራሳችንን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ማየት ይኖርብናል። የተለያዩ ችግሮች በመነንገዳችን ሲገጥሙን፣ ከእግዚአብሔር ጋር በመስማማት፣ የገባልንን የተስፋ ቃል አያሰላሰልን፣ አልፈን ማየት መቻል ይኖርብናል።

View Details

የሐዋርያት ሥራ.24:20-27 ክፍል 89

View Details

በዮሐንስ ራእይ ውስጥ በተደጋጋሚ "መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ" እያለ ሲናገር የቤተክርስቲያንን ሕንፃ ሳይሆን እኛን ክርስቲያኖችን ነው የሚያመለክተው። በዚህ ትምህርት ውስጥ የዚህን መንፈስ ከብዙ ስራዎቹ ጥቂቶቹን ስንማር፣ ክዚህ ህያው ከሆነው የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ጋር ላለመተላለፍ፣ ከጌታና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የጠበቀ ህብረት በማድረግ ቃሉን ለማወቅ መትጋት እንዳለብን እናያለን።

View Details

ማርያምና ሌሎችም የእግዚአብሔርን ቃል በመተማመን የጠበቁ ሰዎች፣ በትልቅ ድል ውስጥ እንዳለፉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተፅፎልናል። የምንሰማውን ቃል ሁለንተና ካደረግነው እንጠብቀዋለን፣ በመጠበቃችን ደግሞ እንከብራለን ያልጠበቅነው ቃል ደግሞ ሕይወት አይሆንልንም። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ያለን ቃልና እኛ የምናልፍበት ሁኔታ በጣም የተራራቀና ያለንን የሚያስጥል ሊሆን ይችላል ሆኖም ግን እግዚአብሔር አንዱ መንፈሳዊነትን የሚያለማምደን መንገዱ በመጠበቅ ውስጥ ነው።

View Details

በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሁሉ በምድር ሲኖር ተልዕኮ አለው:: ተልዕኮውም ጌታ ኢየሱስን ለሌሎች ማሳየት ነው:: በቃልና በሰራ በኑሮ:: ይህንንም ተልዕኮ እለት እለት ለመፈፀም መታዘዝ ስርአትና እምነት ከእኛ የሚጠበቁ ናቸው:: - ለጌታ ፈቃድ ለቃሉ በመታዘዝ እንዲሁም የራሳችንን ክብር ጥለን ለሌሎች እንቅፋት ባለመሆን ደግሞም በእምነት መራመድ::

View Details

እግዚአብሔር ባሰበን ጊዜ የእርሱ ባርኮት ወደ ህይወታችን ይፈሳል:: የፀሎት መልስ ይሆናል:: ተስፋ ያደረግነውም እውን ይሆናል:: የሚሆነው ሁሉ የሚሆነው ግን በእኛ ጊዜ አይሆንምና አንዳንድ ጊዜ ተስፋ እንቆርጣለን:: ከምናልፍበት ሁኔታ የተነሳ እግዚአብሔር እኔን ረስቶኛል ለማለትም ደፍረን ይሆናል:: ጌታ ግን ሁሉን በራሱ ጊዜና ሰአት በወደደውም መንገ ውብ አድርጎ ይገልጠዋል:: እግዚአብሔር እርሱ አይለወጥም:: ዛሬም ያስባል::ይጎበኛልም:: እኛ ግን በጊዜውም አለጊዜውም በምስጋና ሆነን በፊቱ ልንቆይ ያስፈልጋል::

View Details

እግዚአብሔር ለእስራኤል የተናገረው የተስፋ ቃል ሁሉ ተፈፅሟል :: መንገዳቸው በበረሀ ውስጥና በብዙ ፈተናም የተሞላ ቢሆንም በእግዚአብሔር ላይ የታመኑ እንደተባለላቸውም በተስፋው ቃል የፀኑ የጉዟቸውን ፍፃሜ መዳረሻ አይተዋል:: ወደ ተስፋውም ምድር በድል በሞገስ ገብተዋል:: በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከኃጢአት ባርነት ተላቀን ከአለም ወጥተን ወደ መንግስቱ የፈለስን አኛም እንደ እስራኤል ሁሉ ለህይወት ጉዟችን የተሰጠ መመሪያ አለ:: ይህንን በዚህ መልዕክት በጥልቀት እንማራለን::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.23:1-11 ክፍል 86

View Details

የክፉ መናፍስት ሥራ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የለውን ህብረት ማበላሸት ደግሞም በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነትና መታመን መሸርሽር ያለንንም ተስፋ ማጨለም ነው:: ስለዚህ ሁልጊዜ ለክፋት በተለያየ መንገድ የሚተጋ ጠላት እንዳለብን አማኞች ልናስተውል ፀንተንም በእግዚአብሔር ቃልና በፀጋው ልንዋጋውና በአሸናፊነት መንፈስ ልንቆም ያስፈልጋል:: በዚህ መልዕክት የክፉውን አሰራርና በሌላ በኩል ደግሞ በክርስቶስ ያገኘነውን የአሸናፊነት ህይወትና የፀጋውን ጉልበት እንማራለን::

View Details

መንፈሳዊ አይኖቻችን ሲከፈቱ የምናየውና የምንሰማው ደግሞም ሁለንተናችንን የሚወርሰው የሚገዛው የሚመራውም የእግዚአብሔር ድምፅ ይሆናል:: ለተጠራንለትም አላማ እንኖራለን:: በህይወታችን የሚሆኑትን ነገሮች ሁሉ በስሜት ሳይሆን በማስተዋልና በጥንቃቄ ማየት እንጀምራለን:: አሻግረን ወደፊት ማየት እንችላለን:: በእምነት እንበረታለን ሀይልና ጉልበት ተስፋም ይሆንልናል::

View Details

እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው:: እርሱ የእኔ ነው :: ለሚል ደግሞም በስፍራው ፀንቶ ለቆመ ለእርሱ የታመነበት ደግሞም አለኝ ያለው ጌታ ባለበት በሁኔታው ላይ ይመጣል:: ክብሩንም ይገልጣል:: ታምኗልና:: በእኛ ዘንድ ያበቃለት ተስፋም የተቆረጠበት ጉዳያችን ሁሉን ቻይ በሆነው ጌታ የእኛ በሆነው በእርሱ ዘንድ ቀላል ነው:: ሞቷል ለምንለውም እንኳ ህይወት ይሰጠዋል:: እንዴት ይሆናል ተብሎ አይጠረጠርም

View Details

የሐዋርያት ሥራ.23:1-5 ክፍል 85

View Details

እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያደላም:: ነገር ግን እርሱ ለሚጠሩት ሁሉ ሙሉ ደግሞም ባለጠጋ ነው:: በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ባመንን ጊዜ ህይወታችን በሰማያዊ ስፍራ ተሰውሯል:: በምድር ላይ በሚኖረን ዘመን ሁሉ ደግሞ ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁለንተናችን በመለኮት ጥበቃ ውስጥ ነው::የሚሆነውና የምናልፍበት ሁሉ በእርሱ ፊት የታወቀ ነው:: በዚህም ውስጥ ታላቅነቱን ደግሞም ሁሉንቻይነቱን እናያለን

View Details

የአማኝ እድል ፈንታ እርሱ አንዳሰበው፣ አንደሰማው ወይም እንዳየው ሳይሆን እግዚአብሔር እንዳዘዘው ነው።

አንድ አማኝ ወደ እግዚአብሔር በቀረበበት መጠን የእግዚአብሔር የሆነው ነገር በህይወቱ ስፍራን እየያዘ፣ የእግዚአብሔር ያልሆነው ነገር ደግሞ እየቀለለበት ይመጣል፣ የእግዚአብሔርን አዋቂነት በበለጠ በመረዳት በሚያልፍበት የህይወት ውጣ ውረድ ሁሉ፣ ጥያቄው ለምን? ሳይሆን እግዚአብሔር ብሏል ወይ? ይሆናል።

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በብሉይ ኪዳን “ በሀጢያት ምክንያት ሴቶቻችሁ ያምጣሉ ፅንሱ በቀጥታ አይወጣም ልጆቹም አህምሮ የጎደላቸው ይሆናሉ።” የሚለው ቃል ይብራራልን። 2. ምህረት ማድረግ ምርጫ ነው ወይ? 3. ይቅርታ ማለት ነገርን መርሳት ነው ወይስ ነገሩ እያለ መተው ነው? 4. የእግዚአብሔር ፍቃድ እንዲከናወንልን ራስን አሳልፎ መስጠት አለብን የሚለው ይብራራልን? 5. በእግዚአብሔር ፍቃድ ለመደሰት ሂደት ነው ወይ? የእግዚአብሔር ፍቃድ እኛን ለማስደሰት ሗይል አለው ወይ? ይህ መረዳት እኛን ይጠቅመናል ወይ? 6. የእግዚአብሔር ፍቃድ ከእምነት ጋር ይያያዛል ወይ? 7. እንደተነገረን ቃል መኖርና በውጭ ላሉት ተጠንቅቆ መኖርን እንዴት ነው በህይወታችን የምናስታርቀው? 8. ራሳችንን ትልቅ ባደረግንበት ሆነ ሰዎች ትልቅ ባደረጉን ነገር ጌታን ማየት ትተናል ማለት ነው? 9. ልጆችን ካደጉ በሗላ እንዴት ነው ማስተካከል የምንችለው?

View Details

እግዚአብሔር የጠራን ለብርታት ሳይሆን፣ የእርሱ ኃይል መገለጫ እንድንሆን ነው። ጌታ ጳውሎስን ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና እንዳለው፣ ዛሬም የእግዚአብሔአ ፀጋ በእኛ የሚገለፀው በበቃንበት ሳይሆን ባልበቃንበትና ኃይል ባጣንበት ነው። የሰው ውድቀትና ኪሳራው፣ ከድካሙ ይልቅ በራሱ ሀይል መመካት ሲጀምር ነው።

View Details

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌዴዎን የተባለ ስው ምድያማውያንን ፈርቶ በተሸሸገበት ስፍራ፣ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት አንተ ጽኑዕ ኃያል ሰው፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው አለው። ጌዴዎን የነበረበት ሁኔታና መልአኩ ተገልጦ የነገረው ቃል በፍጹም አብሮ የሚሄድ አልነበረም። ነገር ግን እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከህዝቡ ጋር ነው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የመሆኑ መለኪያው የምናልፍበት ጊዚያዊ ሁኔታ ሳይሆን፣ የነገረን ቃሉ ነው። እስከ አለም ፍጻሜ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ ስላለን፣ በምናልፍበት በማናቸውም ሁኔታ፣ በክርስቶስ እየሱስ ያገኘነውን አብሮነት እያጣጣምን ልንኖር ይገባናል።

View Details

የሐዋርያት ሥራ 21:27-40 ክፍል 82

View Details

የዲያብሎስን ሽንገላ ለመቃወም፣ ክርስቲያን በክርስቶስ ፅድቅ ውስጥ መሸፈን አለበት። ትግሉ ከሰው ጋር ሳይሆን ከሰዎች ጀርባ ካለ ከክፋት መንፈሳዊ ጋር መሆኑን በመረዳትና የሰይጣንን ሐሳብ ላለመሳት፣ በእግዚአብሔር ቃል እውነት ማደግ እንዲሁም በፅድቅና በቅድስና ሊኖር የተገባ ነው።

View Details

ፀሎት ማለት ሐይማኖታዊ ልምምድ ሳይሆን ከምንጠይቀውና ከምንቀበለው ያለፈ፣ በመንፈስ ቅዱስ መገኘት፣ ወደ ውስጠኛው የጌታ ህልውና ውስጥ ገብተን ከጌታ ጋር የአባትና የልጅ ሕብረት ማድረግ ማለት ነው። ለዚህም ነው መፅሐፍ ቅዱሳችን የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች ብሎ የሚመክረን።

View Details

ሁሉም ፀጋ የሚለቀቀው ሰው ለጌታ ፈቃድ ሲመች ነው። ለፈቃዱ ለመመቸት ከራሳችን ፈቃድ ወጥተን ለእግዚአብሔር መሆንና አርሱ የሚወደውን መውደድ ይጠይቃል ደግሞም የእግዚአብሔር ፈቃድ ደስታችን ሊሆን ይገባል።  ለሰው ትልቁ የመንፈስ ኪሳራ፣ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይመች ሲቀር ነው።

View Details

ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የእግዚአብሔር ልጆች የሆንን እና በመነንፈስ ቅዱስም የታተምን ሁላችን መሪያችን እርሱ መንፈስ ቅዱስ ነው:: እርሱ የአሁኑን ደግሞም ወደፊት የሚሆነውንም የሚያውቅ ጌታ በቀናው ጎዳና በጽድቅና በቅድስና በእውነትም እንደ ፈቃዱ ይመራናል:: በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ እንሁን የእኛ መሰጠት ደግሞም ለምንሰማው ድምፅና ምሪት መታዘዝ እሺ ማለት ከእኛ የሚጠበቅ ነው::

View Details

ለተቀበልነውና በስሙ ለምናምን፣ የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ስልጣን ተሰጥቶናል። ይህንን የዘለአለም ሕይወት ተስፋ ለመጨበጥ፣ ልጅ ከመሆን ይጀምራል። እንደ ልጅ፣ ያዳነንን እርሱን ጌታችንን ደስ ለማሰኘት ስንተጋና፣ የተስፋችን ፍፃሜ የሆነውን አምላካችንን ለመገናኘት ስንናፍቅ፣ ይህንን ተስፋ ለመጨበጥ የሚያስችል ፀጋ ይለቀቅልናል።

View Details

ቃሉን ሰምቶ መታዘዝ የሉቃስ ወንጌል 10: 1-11

መታዘዝ ቃሉን ከማድመጥ ይጀምራል። ጌታ እየሱስ በመጀመሪያ ደቀ መዛሙርቶቹ እንዲለማመዱ የፈለገውና ዛሬም አማኞች የሆንን ሁላችን ልናደርገው የሚገባን፣ ለሰማነው ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝን ነው። ለክርስቶስ ያለንን ፍቅር የምንገልፀው፣ ቃሉን በመስማትና በመታዘዝ ሲሆን፣ ይህ ለቃሉ በመታዘዝ መኖር ደግሞ ክርስቶስን ወደ መምሰል ያደርሰናል።

View Details

የሐዋርያት ሥራ 21:17-26 ክፍል 81

View Details

እግዚአብሔር በባሕሪው ማንንም አይረሳም።  በሰው አይምሮ ነገራቸው ሁሉ ያለቀና የተረሱ የሚመስሉ ብዙ ሰዎች በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ምሳሌነት ተጠቅሰውልናል፣ በመጨረሻ ግን በእግዚአብሔር ታስበው፣ ዛሬም ያለፉበትን የሕይወት ውጣ ውረድ ስንማር ያስደንቀናል።  እግዚአብሔር ፍርድ የሚያደላድለው፣ ሰውን የሚያስብ አምላክ በመሆኑ ነው።

View Details

የአማኝ መንፈሳዊ ጉዞ ከሀይል ወደ ሀይል ከክብርም ወደ ክብር ነው:: ደግሞም የማያቋርጥ ለውጥ በህይወቱ ይኖራል:: በህይወታችን የሚኖረው ለውጥ እንዲያድግ እግዚአብሔር የወደደው የልጁን መልክ ወደ መምሰል ነው:: ይህ ደግሞ ራስን ከመካድና ዝቅ ከማለት ደግሞም ከመታዘዝ ይጀምራል:: በዚህ መልዕክት በቀደሙት የተለያዩ ሰዎች በህይወታቸው የተገለጠውን የለውጥ አይነት በማየት ዛሬ ደግሞ ለእኛ የህይወት ለውጥ ይጠቅመን ዘንድ በስፋትና በዝርዝር ቀርቧል::

View Details

ኢያሱ በፊቱ ተሰብስቦ ላለው ለእስራኤል እግዚአብሔርን ፍሩ ብሎ አወጀ::በጉዞው ሁሉ ደግሞም ወደፈት ሊኖርበት ባለውም ምድር የእስራኤል ጉልበት እግዚአብሔርን መፍራቱ ነውና:: በክርስቶስ ኢየሱስ ከሞት ወደ ህይወት ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የተጠራን አኛ ሁልጊዜም በልባችን ሊኖር የሚገባው አንድ ነገር እርሱም ከራሳችን የሆነ አንዳች የሌለ ደካሞች እንደሆንን ነው:: በመንግስቱ ውስጥ ግን በእግዚአብሔር ሀይል እንወጣለን እንገባለን ደግሞም በእርሱ ሀይል እናገለግላለን እርሱንም ለማክበር እንኖርማለን::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.20:13-30ክፍል 78

View Details

እግዚአብሔር እርሱ በሰማይና በምድር አምላክ ነው::ብላ ያመነች ደግሞም የመሰከረች ረዓብ ከሚጠፉት ጋር አብራ አልጠፋችም:: ምንም ታናሽና ደካማ ብንሆን በእምነት በፊቱ እንሁን እንጂ እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን ሊሰራ ፈቃዱ ነው:: በዚህ መልዕክት ትናንት በረዓብ ህይወት ድንቅን ያደረገ ጌታ ዛሬም በእኛ እንዴት እንደሚሰራ እንማራለን::

View Details

እግዚአብሔርን እንደትናገረው ካላመንን አይመችንም ስንታመነው እንደቃሉ ስናየው ንብረታችን አቅማችን ነው ችግር የለም ማለት አይደለም ከችግር በላይ ነው ማለትና ማመን ግን ሃይል ማግኘት ነው ነገር ግን ሰይጣን ይህ እውነት እንዳይገባን ይታገልናል ስለዚህ ጨለማውን እያየን ተስፋ መቁረጥ የለብንም

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ፍርድ ካለበት ፀሎት እንዴት ነው መውጣት የምንችለው? 2. የወንጌል ትኩረት ወደ ራስ ጥቅም የለወጠው ምንድን ነው? 3. ወንጌልን ስንመሰክር ስለ ወንጌል መናገር ያለብን ምን መሆን አለበት? 4. በቤተ ክርስትያን እናት ሳይሆኑ እናት የሆኑ አሉ የሚለው ሀሳብ ቢብራራልን።

View Details

የሐዋርያት ሥራ.20:1-12 ክፍል 77

View Details

የሰው ፈቃድ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ሲተያይ ሰማይ ከምድር እንደሚርቅ እንዲሁ የራቀ ነው:: ነገር ግን እግዚአብሔር ፀጋን እየሰጠ ደግሞም በራሱ መንገድ በመምራት ሰውን አሰቀድሞ ወደ ተፈጠረለት ወደ ፈቃዱ ያመጣዋል:: ሰው ግን ራሱን ባዶ ሊያደርግ ደግሞም በእርሱ ያለውን የጌተን ፈቃድ ለማድረግና ለእርሱም ለመኖር መምረጥ ይኖርበታል:: ይኸውም በስጋ ሳይሆን ነገር ግን አይናችን ተከፍቶ አይተን የምንመርጠው ነው:: - ሰው ራሱን በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ያገኘበት ሰአት ያ እጅግ የተወደደ ሰአት ነው::

View Details

ለሚታዘዝ ለእርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከት ደግሞም ክፉውን የሚቃወሞበት ሀይልና ጉልበት ይሆንለታል:: መታዘዝ ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም እንኳ ፍሬው ግን በብርሃን የተሞላ የእግዚአብሔርን ክብር ክንዱንም የምናይበትና ለምስጋናም በፊቱ የሚያቆመን ነው::

View Details

በቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ አንዱና ዋናው አገልግሎቱ ኢየሱስ ክርስቶስን መግለጥ ነው:: ማክበርም ነው:: የእውነት መንፈስ አርሱ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ውስጥ የሚኖር ወደ እውነት የሚመራ የሚያፅናና እና በተስፋ እንድንፀና በተዕግስት እንድንሆን ደግሞም በፍቅር እንድንኖር ያደርጋል:: ፈቃዳችንን ለእርሱ ባስገዛን መጠን መንፈስ ቅዱስ እንደወደደ ለአካሉ ጥቅም ይሆን ዘንድ ፀጋን ይሰጣል:: ፈቃዱንም ያደርጋል::

View Details

የፀሎታችን ግብ የመጀመሪያው ለእግዚአብሔር ክብርን ያመጣ ዘንድ ያለመ መሆን አለበት:: ጌታ ኢየሱስ በምድር በስጋ በነበረበት ጊዜ ይናገር ከነበረውና ከፀሎቱም የምናየው ይህንኑ ነው:: የትምህርቱም ሆነ የፀሎቱ አላማ አባቱን ማክበር ነው:: እግዚአብሔርን የሚያከብር ፀሎት መልሱ የፈጠነ ነው:: ከፀሎቱ መልስ በላይ የበለጠ እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ ያመጣናል:: እምነት ተስፋና መፅናናት ሀይልም ይሆንልናል:

View Details

የአማኞች በምድር ላይ መኖር የእግዚአብሔርን መንግስት ለማወጅ ነው:: ለማስፋትም ነው:: በዚህ የጨለማው አለም የእግዚአቤሔር መንግስት የምትሰፋው በመውረሰ ነው:: በመማረክ ነው:: ይህም የሚሆነው አማኞች የእግዚአብሔር ልጆች በፀሎት ሆነው መንግስትህ ትምጣ እያሉ የኢየሱስ ክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ በማወጅ ደግሞም በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ዝቅ በማለት በትህትና በቅድስናና በፅድቅ በመመላለስ በኑሮ በመስከር ነው:: በዚህ መልዕክት ስለ እግዚአብሔር መንግስት ስርአት ደግሞም በውስጧ እንዴት ባለ ሁኔታ ልንኖር እንደሚገባ በስፋት እንማራለን::

View Details

የእግዚአብሔር ቃል እውነትና የታመነ ነው፣ ጌታም እንደቃሉ ነው። እኛም እግዚአብሔርን እንደ ቃሉ ካየነው፣ የምናልፍበት ማንኛውም ከባድ የህይወት ውጣ ውረድ ይቀልልናል። በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ለሰው አይምሮ የማይቻል የሚመስሉ ሁኔታዎች ተፅፈዋል ሆኖም ግን አግዚአብሔርን በቃሉ ያዩትና እንደ ቃሉ የተቀበሉት፣ መከራቸውን ሁሉ በድል አልፈው፣ በረከታቸውን ተቀብለዋል።

View Details

የሐዋርያት ሥራ.19:8-10ክፍል 74

View Details

ጌታ በህይወታችን ያደረገውን የማዳኑን እውነት ምህረትና ቸርነቱንም በመመሰከር ልንመላለስ የእለት ተእለት ኑሮአችንም የህንኑ የብርሃን ህይወት ሊያንፀባርቅ የተገባ ነው:: ጌታም እንደ ተስፋ ቃሉ ለዚህ የሚረዳንን ብቃትም የሚሆነንን ፀጋ ይሰጠናል:: ይህ መልዕክት የማርያምን የማርታንና የዓልአዛርን ህይወት በመዳሰስ አኛነታችንን እና ከእነርሱም ህይወት ልንማር የሚገባውን ያሳያል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.19:1-7ክፍል 73

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ሰው ጌታን ሲቀበል ወዲያው መንፈስ ቅዱስ ይሞላል (ያድርበታል) ወይ? 2. ሰው ጌታን ሲቀበል በመንፈስ ቅዱስ ከታተመ ለምን ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት መፀለይ እለበት? 3. በመንፈስ ቅዱስ ባንሞላ የሚጎድልብን ምንድን ነው? 4. የመንፈስ ቅዱስ በሙላት መፈለግ አለብን ወይ? 5. መንፈስ ቅዱስን እንዴት ነው የምንሞላው? 6. በህይወታችን ጌታ የተናገረን ሲለዝምብን ለምንድን ነው የሚጨልምብን?

View Details

በዘመኑ ሁሉ በተሰጠው የአገልግሎት ስፍራ በታማኝነት አገልግሎ በእድሜው መጨረሻ ላይ የህዝቡን መሪዎች ሰብስቦ ሊከተሉ የሚገባውን ስርዓት ያሳሰበበትንና በእግዚአብሔር ፊት በጥንቃቄ ደግሞም በትጋት ሊሆኑ እንደሚገባ ያስጠነቀቀበትን ደግሞም ለእኛ ለዛሬው ህይወታችን የሚሆነውን የምክር ቃል በዚህ መልዕክት እናገኛለን:: በእግዚአብሔር አብሮነት ውስጥ ያለ ህዝብ ለእግዚአብሔር ለፈቃዱ የሚታዘዝ ራሱንም ከርኩሰትና ከነውር የሚቀደስ በዘመኑ ሁሉ ከአምላኩ ጋር የተጣበቀ ሊሆን ይገባል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.18:9-22 ክፍል 71

View Details

ተስፋውን የሰጠው እግዚአብሔር ከሆነ፣ እርሱ የታመነ እና የተናገረውን የሚያደርግ አምላክ መሆኑን በማመን፣ ምንም እንኳን የሕይወት ውጣ ውረድ ቢበዛም ጌታን በትዕግስትና በዕርጋታ መጠባበቅ ያስፈልገናል።  እግዚአብሔር የሰጣቸውን ተስፋ ደግሞ እየተጠባበቁ ለአሉት ሰዎች እንቅፋት ላለመሆን ዘወትር እራሳችንን ልንመረምር ይገባናል።

View Details

የሰው ልጅ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ባህሪይ የለውም፣ ጌታ ግን የሰውን ህይወት ለማዳን የሚጠቀምበት አንዱ መንገድ በችግር ውስጥ እርሱን እንድንፈልግ ማድረግ ሲሆን፣ የሰው ድርሻ ደግሞ በሚያልፍበት ማንኛውም ችግር እግዚአብሔርን ማመን ነው። እምነት ነገራችንን ሁሉ ጌታ ወደ አለበት ያደርሳል።

View Details

የቅዱሳን ጠላት፣ ሰይጣን ሁል ጊዜ በውጊያ ላይ እንዳለ በማወቅ፣ ክርስቲያን በጌታና በሃይሉ ችሎት የበረታ ሆኖ እንደ ወታደር ነቅቶ መጠበቅ አለበት።

የአለም ጨውና ብርሃን መሆኑን በመረዳት፣ ከማንኛውም ሐጢያትና ዐመፃ በመራቅ፣ የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ፣ ደግሞም የድሉ ባለቤት መሆኑን አውቆ በእምነት መኖር አለበት።

View Details

በዚህ ትምህርት ውስጥ ረዓብ የተባለች፣ ከአብርሐም ዘር ያልሆነች፣የተቀበሉት እንኳን ለማመን የተቸገሩበትን የእግዚአብሔርን የበላይነት፣ በሰማይም በምድርም እርሱ ብቻ አምላክ መሆኑን የሰማች፣ የሰማችውን ደግሞ አምና የተቀበለች ሴት እንዴት አድርጋ አገሩን ሊሰልሉ የተላኩትን ሁለቱን ሰዎች ሸሺጋ አንዳዳነች፣ እንዲሁም ራሷንና ቤተሰቦቿን ከጥፋት እንዳተረፈች እናያለን።

View Details

የሐዋርያት ሥራ.181-11 ክፍል 70

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ለምንድን ነው አይሁዶች ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ያልተቀበሉት? 2. ቤተ ክርስትያን ስለ አይሁድ ምን ትላለች? 3. አይሁድ ስለ እምነት ምን አመለካከት አላት ከ3ተኛው ክፍለ ዘመን እስከ 21ድኛው ክፍለ ዘመን? 4. ላባችን እየተቃጠለ ዐይናችን ሊከፈት የማይችልበት መንገድ ምንድን ነው? 5. ድሆችን ማሰብ ትተን እኛ የሚመቹንን አብሮ ለመሆን ስንፈልግ ይህ ለቤተ ክርስትያን መውደቅ ምክናያት ሆናል የሚለው ይብራራልን። 6. ሰው ደህንነትን ከተቀበለ በሗሏ ወደ መንፈስ ቅዱስ ሙላት መምጣት የለበትም ወይ? መሞላቱስ ከግለኝነት ህይወት ወደ ህብረት ህይወት እንዲመጣ ይረዳዋል ወይ? 7. እነ ጳውሎስ እስር ቤት እያሉ ይዘምሩ የነበሩት ዝማሬ ህይወታቸው ስለሆነ ነው ወይ? 8. ከእግዚአብሔር መንፈስ ሳይሆን ሰዎች ትክክለኛ ትንቢት ሊናገሩ ይችላሉ ወይ? ከቻሉስ እንዴት ነው መጠንቀቅ የምንችለው?

View Details

የሐዋርያት ሥራ.17:18-34 ክፍል 69

View Details

የሐዋርያት ሥራ.17:10-18 ክፍል 68

View Details

እግዚአብሔር በህይወታችን የሚሰራውን ሁሉ በራሱ ጊዜና በራሱ መንገድ ለራሱ ክብር ይሰራል:: በእኛ ሚዛን ትልቅና ትንሽ ወይም ከባድና ቀላል የምንለው ጉዳይ ሊኖር ይችላል:: ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ፊት ሁሉም ነገር የእርሱን ክብር የሚገልጥበት ነውና በራሱ ጊዜና ሁኔታ ወደ ጉዳያችን ይመጣል:: የአማኝ ድርሻው በእምነት መቆም ደግሞም በተስፋ መፅናት ነው:: የጉዳያችን ክብደት ደግሞም የጊዜው ርዝመት እምነታችንን ሊፈትን ተስፋችንንም ሊያጨልም ይችላል:: ጌታ ግን ከእምነታችንም ሆነ ተስፋ ካደረግነው በላይ ነው:: ደግሞም እርሱ ተስፋን የሰጠ የታመነ አምላክ ነው::

View Details

የኣንድ መንፈሳዊ ሰው ከፍታ፣ሙሉ ህይወት አና ክፍተት የሌለበት የሚሆነው፣ አየሱስ ይበቃል ወደሚል መረዳት ሲደርስ ነው። አየሱስ ይበቃኛል ስንል አርሱ ሁሉ በሁሉ ነው ማለታችን ነው።

ማርያም ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች፣ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች። ኢየሱስም መልሶ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት። ይህ ጥቂት ወይም አንድ ነገር ለሁሉም መልስ አና ሁሉንም የሚሞላ ነው፣ አርሱም አየሱስ ነው። ሉቃስ 10:41-42

View Details

መታዘዝ በአማኝ የየእለት የህይወት ጉዞ ውስጥ ዋና የሆነና ደግሞም ከጌታ የተማረው ህይወት ነው:: ሰለዚህ በመንፈሳዊ ህይወት ጉዟችን ቆም እያልን ራሳችንን መጠየቅና ምናልባት ከመታዘዝ የጎደልንበት እንዳለ በጌታ ፊት ራሳችንን ልናዋርድና ልንመረምር የተገባ ነው:: አማኝ እለት አለት ራሱን ሊጠይቅ ደግሞም ሊኖርባቸው ከሚገቡት ትእዛዞች ጥቂቶቹን ከዚህ መልእክት እንማራለን::

View Details

አማኝ በውስጡ ያለውን የሚመክረውን የሚወቅስና የሚገስፀውን በመንገዱም በቀና ጎዳና የሚመራውን መንፈስ ቅዱስን በቃሉ እንደተገለጠው ማወቅ እምነታችንን ያሳድጋል:: በፈተና ውስጥም ፀንተን መቆም እንችላለን:: በዚህ መልዕክት መንፈሰ ቅዱስ ሁሉን የሚያይ ሁሉ በፊቱ የተገለጠ ደግሞም በሁሉ ላይ ስልጣን ያለው ሁሉን ቻይ መሆኑ እንማራለን::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.17:1-10 ክፍል 67

View Details

ጌታ ኢየሱስን የተቀበልነው ደግሞም የምንከተለው ለህይወት ነው:: በዚህ አለም ስንኖርም እርሱ ጌታችን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የቅርባችን ችግራችንንም የምናካፍለው ወዳጃችን ነው:: የጠየቅነው ሁሉ አንዳይመለስ የፈለግነውንም ሁሉ እንዳናገኝ ግልፅ ነው:: ይሁን እንጃ ሁሉ ለመልካም ነው::ለበጎ ነው:: በጊዜውም አለጊዜውም በጌታ ላይ ባለን እምነት ፀንተን እንቁም:: ሰለዚህ በህይወታችነ ቀዳሚው በነገሮችና በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ደግሞም የማይናወጥ በጌታ ላይ ያለን እምነት ነው::

View Details

በዚህ ምድር ስንኖር በአንድም ወይም በሌላ ትንሽም ይሁን ትልቅ ሰው ሁሉ የራሱ የሆነ አንድ ተስፋ የሚያደርገው የሚኖርለት ነገር አለው:: ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሆነ ደግሞም የተበረከ አማኞች ሁሉ እለት እለት የሚኖሩለት ተስፋ አለ:: እርሱም የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ በክብር መምጣት ነው:: በዚህ መልዕክት ይህን የተባረከ ተስፋ እለት እለት እነዴት ባለ ህይወት እየተጠባበቅን ልንኖር እንደሚገባን እንማራለን::

View Details

መንፈሳዊ ተሀድሶን ወደ አማኝ ህይወት የሚያመጣው እግዚአብሔር ራሱ ነው:: አላማውም የሰውን ሁለንተና ወደ ራሱ ፈቃድ መመለስ ደግሞም በቤተክርሰቲያን በአማኞች መካከል ክብሩን በመግለጥና ሰዎችን ወደ ህይወት ወደ ብርሃን ማምጣት ነው:: መንፈሳዊ ተሀድሶ ሲመጣ ምስጢር ይገለጣል:: የንስሃ ጥሪ ለሰው ሁሉ ይሆናል:: የእግዚአብሔርም የማዳኑ ጉልበት ይገለጣል:: ድንቅና ተአምራት ይሆናልም:: በዚህ መልእክት እግዚአብሔር መንፈሳዊ ተሀድሶን ወደ ህይወታችን የሚያመጣባቸውን መንገዶች እንማራለን::

View Details

ብዙ ደስ የሚያሰኙ ነገሮች በዚህ ምድር ሊኖሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን ጊዝያዊ አና ተለዋዋጭ ናቸው። የማይለዋወጥ ዘመን የማይሽረው የዘለኣለም ደስታ ግን የሚገኘው በጌታ በአየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።

View Details

የሐዋርያት ሥራ 16:40 ,17:1-3ክፍል 66

View Details

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከክፉው ወጥመድ ከጨለማው ያመለጠ አማኝ መግባትና መውጣቱ ደግሞም ሁለንተናው በጌታ ጥበቃ ውስጥ ይሆናል:: ይሁን እንጂ ጠላት ዝም ብሎ አይቀመጥምና ውጊያ አለበት:: ውጊያውም መንፈሳዊ ውጊያ ነው:: የአማኝ ህይወት ከሁሉ አስቀድሞ ትህትናን የተሞላ ደግሞም ራሱን ዝቅ ያደረገና ራሱነ የሚገዛ ሊሆን አንደሚገባና አንዲሁም ለመንፈሳዊ ውጊያ ሊኖረን የሚገባውን ዝግጅትና በዚህ በተሸነፈው አለም እለት እለት በአሸናፊነት እንዴት ልንመላለስ አንደምንችል በዚህ መልዕክት በስፋት ተዘርሯል::

View Details

ፀሎት አንዱ የአማኝ የህይወት ክፍል ነው:: ሰለዚህ ዘወትር የምንከውነውና የምንኖረው ነው:: ፀሎት በአግዚአብሔር ፊት ቀርበን ከእርሱ ጋር የምንነጋገርበት ለእርሱ የለንንም ወዳጅነት የምንገልጥበትና ከእርሱ ዘንድ ምክርና መመሪያ የምንቀበልበት ነው:: መቼና ለምን እንፀልይ? እንዴትና ሰለምን እእፀልይ? ለሚሉትና ለሌሎችም ጥያቄዎች የተብራራ መልስ በዚህ ትምህርት እናገኛለን::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.16:16-18 ክፍል 64

View Details

የሐዋርያት ሥራ 16:19-40 ክፍል 65

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በአይምሮ ህመም ያሉ ሰዎች እንዴት ነው ወደ ንስሀ መምጣት የሚችሉት? 2. “አንድ መንፈስ፣ አንድ ልብ ነበራቸው” የሚለውን ብታብራራልን? 3. ዛሬ እንደ እስጢፋኖስ በህይወታቸው ምስክር የሚሆኑን ሰዎች ስለሌሉ ነው እኛ በህይወታችን ምስክር መሆን ያልቻልነው? 4. ልጆች መጠመቅ ያለባቸው በስንት እድሜአቸው ላይ ነው? 5. ህይወታችን ጌታ ከሆነ ለምንድን ነው በህይወታችን ተቅበዝባዥ የምንሆነው? ከዚህስ እንዴት ነው መውጣት የምንችለው? 6. ኑሮአችንን ከጌታ ጋር ካነካካን የመለየት ስጦታ አለን ማለት ነው ይህ ከሌለን ግን መንፈሳዊ ህይወታችንን መጠበቅ እንችልም የሚለው ሀሳብ ቢብራራልን? 7. ጌታ በመጀመሪያ የሚያየው የእኛን ማንነታችንን ነው ከዛ በኋላ ነው ፀሎታችንን የሚሰማው ሀሳብ ቢብራራልን?

View Details

የሐዋርያት ሥራ.16:11-15 ክፍል 63

View Details

የሐዋርያት ሥራ.9:10-22 ክፍል 32

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ቤተ ክርስትያንን ሊከፍል ሊለያይ የሚመ’ጣ የወንጌል ትምህርት ወደ ቤተ ክርስትያን ሲመጣ የአንድነት እና የህብረት መሰረት ሆነን መቆም የምንችለው እንዴት ነው? 2. ሰው እግዚአብሔርን እያወቀ መከተል የሚችለው እንዴት ነው? ሳያውቅ ከመከተል ኪሳራስ ለመውጣት ምን ማድረግ አለበት? 3. በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውንና ያልሆነውን ስለት አውቀን መመለስ የለብንም ወይ? 4. እጊዚአብሔር አብረውን እንዲቆሙ የሰጠንን ሰዎች ማንነታቸውን አካሄዳቸውን ማወቅ አለብን ወይ? 5. በልማድ በምናደርገውና በእምነት በምናደርገው መካከል ያለውን ግንኙነት ብታብራራልን? 6. የምናደርገው ነገር ከእግዚአብሔር ነው እያልን ወደ ብርሃን መምጣት የሚያቅተን ለምንድን ነው? 7. ሁለት ዐይነት ሰዎች አሉ የራሳቸው መንፈሳዊ ትክክል የሚመስላቸውና ሌሎቹ ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈሳዊ ትክክል ነው የሚሉ የሚለውን ብታብራራልን? 8. ካልጠበቅነው ነገር እግዚአብሔር መልስ አለው የሚለው ይብራራልን። 9. የእኛ ነገር የእግዚአብሔርን ግቡኝት እንዲፈጥን ያደርገዋል ወይ?

View Details

እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ከጨለማው አለም ወደ ብርሃኑ መንግስት ካመጣን በኃላ ብቻችንን የተወንና በራሳችን እንድንቆም የለቀቀን አይደለም:: ነገር ግን ዘወትር በእጁ የተያዝንና የተጠበቅን ነን እንጂ:: የምናልፍበትና ያለንበት ሁኔታ የሚያስፈራ ደግሞም ብቻችንን የሆንን የተተውንም መስሎ ቢታየንም እንኳ በዚህም ውስጥ አጁ ይዛናለች:: ትመራናለችም:: የጠራን ጌታ እርሱ የታመነ ነው:: - ጌታ ይረዳኛልና አለፈራም ተብሎ እእደተፃፈ በእምነት ፀንተን እንቁም::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.9:1-9 ክፍል 31

View Details

የሐዋርያት ሥራ 16:6-10 ክፍል 62

View Details

የእግዚአብሔር ህዝብ በህይወት ጉዞው ላይ ሊጠነቀቅ ከሚገባቸው ነገሮች አንዱ ቸልተኝነት ነው:: ቸልተኝነት የተነገረውን ሰምቶ ከማድረግ ለከናወን የሚገባውን ከማከናወን መዘግየት ወይም እንደ ቀላል ቆጥሮ አሳንሶ ማየት ...ወዘተ ነው:: የክርስትና ህይወትና ኑሮ የድል የመሻገር ወደ ፊት የመራመድ ህይወት ነው:: ሰለዘህ በአንደዚህ አይነት ህይወት ቸልተኘነት ሰፍራ ሊኖረው አይገባም:: በመሆኑም እለት አለት ቸል ያልኩት ምን አለ? እያልን ራሳችንን እየጠየቅንና እየመረመርን የምንኖረው ኑሮ ነው:: - ከቸልተኝነት ስንላቀቅ ማምለክ እንደሚገባን እናመልካለን:: መፀለይ እንደሚገባን እንፀልያለን:: ማገልገል እንደሚገባንም እናገለግላለን:: ምንም በድካም ብንሆን የሚያበረታ ጌታ ፀጋን ሊሰጠን ከቸልተኝነት ወጥተን በትጋት እንድንሆን ሊረዳን የታመነ ነው::

View Details

ከእግዚአብሄር ጋር ሳይስማማ የምድር ሕይወት ዘመኑን የሚኖር ሰው ሰላም እና ደስታ እፎይታ የሌለበት ህይወትን ይኖራል፡ከእግዚአብሄር ጋር በተስማማንበት ነገር ላይ ሁሉ ነገር ዕረፍት እና ደስታ አለበት። ለሌሎች ያልተመቸ ነገር ከእግዚ ጋር ብቻ ሰለተስማማን ያ የማይመች ነገር ለኛ የተመቸ ይሆናል። በቃሉ ውስጥ ከእግዚአብሄር ጋር በመስማማታቸው ብቻ በረሃብ ዘመን የጠገቡ ሰዎችን ታሪክ በዚህ ትምህርት ላይ በስፋት ተጠቅሰዋል። በዚህ መልዕክት ከእግዚአብሄር ጋር ያልተስማማንባቸውን ጉዳዮች እንድናስተውልባቸው ይናገረናል።

View Details

ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ ሁሉ ህይወታቸው የሚመራው በውስጣቸው በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ነው:: ሰለዚህ አማኝ በውስጡ ያለውን የሚያስተምረውን ከክፉ የሚጠብቀውንና በቀና ጎዳናው የሚመራውን የእርሱን የመንፈስ ቅዱስን ማንነት ደግሞም አሠራሩን እንደሚገባ ማወቅና መረዳት ይገባዋል:: በዚህና በሚቀጥሉት ተከታታይ ትምህርቶች የመንፈስ ቅዱስን ማንነት አሰራርና አመራሩንም እንማራለን::

View Details

እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ያለው ፍቅር በሙላት የተገለጠው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ አለም በስጋ በመገለጡ በሞቱና በትንሣኤውም ምህረትንና ደህንነትን በማወጅ ነው:: ይህ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቅር እኛን ከነካን በኃላ እኛም ለዚህ ፍቅር የምንሰጠው ምላሽ በተለያየ መንገድ ይገለጣል:: በጌታ ፊት የምናሰቀድመው ምን ሊሆን እንደሚገባ እንድናስተውልና በቅን ልብ ልንሆን የተገባ ነው:: - በፍቅሩ ውስጥ ከሆንን በሰላሙና በእረፍት ውስጥ እንሆናለን:: በመባከን ህይወት እንዳንጠመድ ይልቁንም በእግሩ ስር ልንሆን ከቃሉም ማዕድ ልንመገብ የእርሱ ፈቃድ ነው::

View Details

እግዚአብሔር የበረከት አምላክ ነው። አብርሃምን እግዚአብሔር በባረከበት በረከት ውስጥ አብርሃም በዚያ በተባረከበት ሕይወት ውስጥ ሕይወቱን ጠብቆ እንዳይኖር ብዙ ትግሎችን አሳልፏል። እግዚአብሔር በባረከን በረከት ውስጥ በታማኝነት ጸንተን በመመላለስ በረከታችንን ጠብቀን ልንኖር እንደሚገባን ይህ መልዕክት ያስተምራል።እግዚአብሄር የባረከንን በረከት ማንም ሊወስድብን አይችልም። እግዚአብሄር የባረከንን በረከት ማንም ሊሽር አይችልም ሰይጣን ግን በዚያ በረከት ውስጥ እንዳንመላለስ እኛ እና በረከታችን እንዳንገናኝ ከመስመር ሊያስወጣን ብዙ ይጥራል። በዚህ ትምህርት ውስጥ እንዴት በበረከታችን ውስጥ ጸንተን ሥፍራ ሳንለቅ መጠበቅ እንዳለብን ያስተምረናል።

View Details

በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሁሉ በፊቱ ሞገስ አግኝቷል:: ይህ በጌታ ፊት ያለው ሞገስ የሚጠበቀው ግን አግዚአብሔርን በመፍራት ህይወት ውስጥ እስከኖረ ድረስ ብቻ ነው:: ከዚህ በወጣ ግን በደልና መተላለፍ አመፅና ድፍረት ባለበት ከቃሉ ከፈቃዱም የወጣ አካሔድ ባለበት በዛ ሞገስ አይኖርም:: ፀሎታችንም አይሰማም:: ደግሞም ዋጋ ያስከፍለናል:: የምናልፍባቸው ሁኔታዎች የሚያስጨንቁን ቢሆኑም እንኳ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ በሆነልን ጊዜ እምነትና ተስፋ ብርታትም ይሆንልናል:: ሰለዚህ እግዚአብሔርን በመፍራት ህይወት መኖር ዋና ነገር ነው::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.15:36-41 ክፍል 60

View Details

የሐዋርያት ሥራ 16:1-5 ክፍል 61

View Details

የሐዋርያት ሥራ.15:12-35 ክፍል 59

View Details

ይህ ትምህርት በውስጡ እግዚአብሄር የተሃድሶ አምላክ እንደሆነ እና ሰይጣን ደግሞ ነገሮችን ለማፍረስ የሚተጋ ፉ መሆኑን የምንማርበት ነው። በዚህ በመጨረሻው ዘመን መንፈስ ቅዱስ እውነተኛ አዳሽ ሆኖ በየዕለቱ ያድሰናል። የኛ ድርሻ ወደዚህ የተሃድሶ አምላክ መቅረብ ብቻ ነው። ስለዚህ እግዚአብሄር ግለሰቦችን ቤተስብን እንደዚሁ ቤተክርስቲያንንም ያድሳል። ይህን መልዕክት ለመስማት የታደማችሁ መንፈስ ቅዱስ በዚህ መልዕክት ተሃድሶን እንደሚሰጣችሁ እናምናለን

View Details

ሰው በሕይወት ዘመኑ ነገሮችን የሚለይበት መንፈሳዊ ብቃት ከሌለው ለብዙ አደጋ የተጋለጠ ነው። በዚህ ትምህርት ውስጥ መንፈሳዊ ሰው ሁሉን ይመረምራል እሱ ግን በማም አይመረመርም የሚለውን የቃሉን እውነት እንማራለን።በዘመናችን ነገሮችን ሳናመዛዝን እና በመንፈስ መለያትን ሳናደግ ለገባንባቸው ስህተቶች ሁሉ አስተማሪ የሆነ መልዕክት ነው። መረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ የተመረኮዘ መለየት እና መንፈሳዉ መለየት የተለያዩ ነገሮች እንደሆኑ በዚህ ትምህርት ላይ ተብራርቶ ተሰጥቷል።

View Details

የሐዋርያት ሥራ 15:1-11 ክፍል 58

View Details

ብዙ ደስ የሚያሰኙ ነገሮች በዚህ ምድር ሊኖሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን ጊዝያዊ አና ተለዋዋጭ ናቸው። የማይለዋወጥ ዘመን የማይሽረው የዘለኣለም ደስታ ግን የሚገኘው በጌታ በአየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።

View Details

የኣማኝነት ታማኝነት በአግዚአብሄር መታመን ነው። አምነት ደግሞ ከመስማት ነው መስማትም ከአግዚአብሄር ቃል ነው። የአግዚአብሄርን ቃል ስንሰማ በአርሱ አየታመንን አንሄዳለን አርሱ ደግሞ ጋሻችን አንደሆነ አንረዳለን። በአግዚአብሄር ላይ ያለን የአረፍት መጠን፣ የሰላሙ መጠን አና የደስታው መጠን፣ በአግዚአብሄር የታመንንበትንና የተደገፍንበትን ያህል ነው።

View Details

የሐዋርያት ሥራ.14:19-28 ክፍል 56

View Details

መንፈሳዊ ከፍታችን መለኪያው በእኛ ሁኔታ እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ የገለጠበትና በተገለጠልንም እኛ የተካፈልንበት ህይወት ነው:: በእርግጥ እግዚአብሔር የበራለት እርሱ በቀደመው ማንነትና መንገድ ላይ አይገኝም:: እግዚአብሔር ራሱን በገለጠለት የብርሃን ህይወት ውስጥ ስለሚሆን የሚያየውም የሚሰማውም ከዚሁ ብርሃን ውስጥ የሚወጣውን ነውና:: የአማኝ መንፈሳዊ ህይወት እግዚአብሔርን እንደ አምላክነቱ ቃሉንም እንዳለው ባመነውና በተቀበለው ልክ ከከፍታ ወደ ከፍታ የሚያድግ ህይወት ነው:: የልጁን መልክ ልንመስል ተጠርተናልና::

View Details

የሐዋርያት ሥራ 15:1-10 ክፍል 57

View Details

እስራኤል ከግብፅ ባርነት ነፃ ወጥተው ወደ ተስፋ ምድር ሲጓዙ ብዙ ጊዜ ከእግዚአብሔር ከአምላካቸው ፈቃድ ሲወጡ ከሚመራቸውም ከሙሴ ጋር ሲጋጩ ይህም እንቅፋት ሲሆንባቸው እናያለን:: አብዛኛው መሰናክሎች ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ ከራሳቸው የሆነ አንቅፋት ነበር:: በግብፅ ሳሉ ይበሉትና ይጠጡት የነበረውን መናፈቃቸውና የእግዚአብሔርን መግቦት መናቃቸው ነው:: - ዛሬም ቤተክርስቲያንን የሚፈትናት ትልቁ እንቅፋት መከራ ሳይሆን ከውስጥ የሆነ የአለምና የስጋ ምኞት ነው:: በክርስቶስ ያገኘነውን ቤዛነት ደህንነትና ነፃነት አክብረን ልንይዘው ይገባል:: ለስጋና ለአለም ምኞት ለፈቃዱም እምቢ ለሚል ለእርሱ የሚረዳ የሚያግዝ ፀጋ ከጌታ ዘንድ አለ:: አርሱ የታመነ ነውና::

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. እግዚአብሔር የሚፈልገው በሥፍራችን እንድንሆን ነው የሚለው ይብራራልን። 2. እግዚአብሔር በሰጠን አገልግሎት ሳይሆን እኛ በምንፈልገው አገልግሎት ብናገለግል እግዚአብሔር አያውቀንም ማለት ነው? 3. እግዚአብሔር በህይወታችን የሚሰራው በሰጠን ህይወት ነው ተብሎ ተምረናል። ወደ ዚህ ህይወት እንዴት ነው የምንመጣው? 4. እንዴት ነው ይቅርታ የምንጠይቀው? ይቅርታ የጠየቅነው ሰው ይቅርታ ስንጠይቀው ይቅር ብያለው ማለት አለበት? 5. የእግዚአብሔር መገኘት ከህይወታችን ልናጣው (ሊጠፋብን) ይችላል? 6. መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ከየት ነው መጀመር ያለብን? እንዴትስ ነው ማንበብ ያለብን? 7. መንፈሳዊ ህይወት መለቀቅ አለበት የሚለው ይብራራልን። 8. መንፈሳዊ ሰው ነፍሱን ማዳመጥ ሲጀምር እግዚአብሔር ሩቅ ይሆንበታል፣ የተተወ የተጣለ ይመስለዋል የሚለው ይብራራልን።

View Details

አማኝ በሚያልፍበት በማንኛውም ፈተናና አሰጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ፀንቶ የመቆሙና በችግሩ አስፈሪነት ያለመናወጡ የሚለካው መንፈሳዊ አይኖቹ ተከፍተው የእግዚአብሔርን የሀይሉን ታላቅነት ባየበትና ባወቀበት ልክ ነው:: የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነትና የሀይሉ ታላቅነት እውቀት ሆኖ ሲገዛንና የተስፋ ቃሉን ከችግሩና ከፈተናው በላይ ማሰብና ማመን ስንጀምር ጌታ በነገሮቻችን ላይ መልስ አለው:: ምስጋናም ይበዛልናል:: ይህ የእግዚአብሔር የሀይሉ ታላቅነት ተፈትኖ የተገለጠ ነው:: ይኸውም በኢየሱስ ከርስቶስ ትንሣኤ ሞትንና የሞትን ሀይል ድል በማድረግ የሚያምኑትንም በህይወት ለዘላለም አንዲኖሩ ይህን ታላቅ ተስፋ በመስጠት ነው::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.14:7-17 ክፍል 55

View Details

እግዚአብሔር ማንንም አይጥልም:: ምክንያቱም ይህ የእርሱ ባህርይ አይደለምና:: እርሱ የቃል ኪዳን አምላክ ደግሞም የተናገረውን ሊፈፅም የታመነ ነው:: ነገር ግን ከምናልፍበት ሁኔታ የተነሳ ደግሞም የፀሎታችን መልስ የመጎብኘታችንም ጊዜ በዘገየና ሁኔታችንም ባስጨነቀን ጊዜ እግዚአብሔር እንደተወን እንደጣለንም እናስባለን:: እግዚአብሔር ግን ጊዜ አለው:: በምንም ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው ወደሚል የእምነት ከፍታ እንድንመጣ የእርሱ ፈቃድ ነው:: × አልለቅህም ከቶም አልተውህም ያለ ጌታ የታመነ ነው::

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በህይወታችን የሚያልፉት መከራዎች ጌታን የሚያከብሩና የማያከብሩ መሆናቸውን እንዴት እናውቃለን? 2. በመንፈሳዊ ህይወታችን አድገናል ብለን በጌታ አንዳንዴ መመካት ሌላ ግዜ ደግሞ አለመመካት እንችላለን ወይ? 3. በህይወታችን በሚያልፈው ሁሉ በጌታ መመካት አለብን የሚለው ቢብራራ። 4. መንፈሳዊ ህይወታችን ሳይዛባ መቆም እንዴት ነው የምንችለው? 5. ሁል ጌዜ በህይወታችን ዝቅ ማለት የምንችለው እንዴት ነው? 6. ጌታን ስንከተል ትችኛውን መምረጥ ያለብን ለምንድን ነው? 7. በእምነት ከመፀለይ ወደ ልምምድ የፀሎት ህይወት መግባት ይቻላል? 8. ከምንሰማው ሚድያ ተነስተን ወደ ትክክል ፀሎት ለመምጣት እንዴት ነው የምንችለው? 9. እጅ መንሻ ሕግን ያዛባል የሚለው ቢብራራልን።

View Details

አማኝ ዝቅ ብሎ የመኖርን ህይወት በመረጠበት በዛ ውስጥ በምንም አይነት ሁኔታ ይለፍ ጌታ ከእርሱ ጋር ይሆናል:: ድምፁን ይሰማል:: ማፅናናቱንም ያያል:: የዝቅታን ህይወት መርጠን መጓዝ ስንጀምር ያ ጌታ ሊያመጣን ወዳለው የህይወት ከፍታ የመሄጃ ጅማሬ ነው:: በየትኛውም ጉድለትና መከራ ውስጥ እናልፍ ይሆናል ነገር ግን እይታችን ይለወጣል:: የእግዚአብሔርን ትልቅነት እናያለን:: በእምነትና በምስጋና የተሞላ የብርሃን ህይወት ይሆንልናል::

View Details

ይህንን ርዕስ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ አስተማሪዎች ተምራችሁት ይሆናል በዚህ መልዕክት ውስጥ ግን በሌላ አቅጣጫ መታዘዝ የሚለውን ርዕስ ትማሩታላችሁ። በዚህ ትምህርት ውስጥ ከተነሱት ዋና ዋና ነገሮች አንዱ መታዘዝ የጽድቅ ምንጭ ሲሆን አለመታዘዝ ደግሞ ከአመጻ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ያስተምራል

View Details

እግዚአብሔር እርሱ መልካም እረኛ ነው:: ሰለዚህ ለእያንዳንዳችን ግድ ሰለሚለው በሰው ሁሉ ዘንድ የተጣልንና የተተውን በሆንንና ብቸኝነት በተሰማን ጊዜ ከጎናችን የሚቆም ካለንበት ሊያወጣን ሊፈውሰንና እደገና ጨለማችንን ሊያበራ ተስፋችንንም ሊያድስ የታመነ ጌታ ነው:: ጨለማው የበራለት እስራቱም የተፈታለትና ተስፋው የታደሰለት እርሱ ኢየሱስ ወደ ህይወቱ ገብቷልና ጌታን ለመከተል አይቸገርም:: ደግሞም ህያው ምስክር ይሆናል:: በዚህ መልዕክት ይህንን በስፋት እንማራለን::

View Details

አማኝ በዚህ ምድር ላይ ሲኖር በእግዚአብሔር ፊት ራሱን በማዋረድና ዝቅ በማድረግ ነው:: ይህ በእግዚአብሔር ቤት ያለው የህይወት መርህ ነው:: በዚህ መርህ የሚኖር አማኝ ደግሞ እግዚአብሔርን ይሰማልና እርሱ ከፍ ያደርገዋል:: ሰለዚህ የአማኝ ከፍታ በህይወቱ የጌታ ፈቃድ የሚፈፀምበትን ቃሉን የሰማውን ያህል ነው:: ቃሉ ይመራል ይጠብቃል ያኖራል ደግሞም ከፍ ያደርጋል:: በምንሰማው የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ራሳችንን ስናይ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፈቃድ እንረዳለን:: በዙሪያችን ያለው የሚያደክምና ባዶ ሆኖ ቢታይ እንኳ በቃሉ ውስጥ ሆነን ስናይ ግን ሀይል ይሆንልናል እንበረታለን:: እምነት ይሆንልናል ተስፋችን ይታደሳል:: በፊቱም ያለን ብልፅግናና ከፍታ ይታየናል::

View Details

አላማ ሲኖረን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል እንደዚሁም በቤቱ ስንኖር ዋጋ ስንከፍል ደስ ይለናል፤ በቤቱ ውስጥ ስንመላለስ ኑሮአችን አላማ ያለው ይሆናል ለምን በቤቱ እንደምንኖርና እንዴት እንደምንኖር እናውቃለን፤ ሊመጣ ያለውን ተስፋችንን እየጠበቅን አላማ እንዳለው ሰው የምንኖርለት ጌታ ሊመጣ ስለሆነ ተዘጋጅተን እንጠብቀው::

View Details

ጌታ ያለበትን መምረጥ ከክፉው ወጥመድ ማምለጫ ነው:: ጌታን የመረጠ ባህርይውንም መርጧል:: ይኸውም ራስን ዝቅ ማድረግ :: ራሱን ባዶ አድርጎ ሥጋን ለብሶ የተገለጠው ጌታ የከፍታ የማሸነፍና የፀጋው መቀበያ መነገዱ ዝቅ ማለት እንደሆነ አሳይቶናል:: ሰው ዝቅታውን ባልመረጠበት በዛ ጌታን አያገኘውም:: ከከፍታ ሩቅ ነው:: ከአሸናፊነት ከፀጋውም ሩቅ ነው:: የዝቅታ መንገድ ለስጋ አይመችም ለሰይጣንም እንዲሁ:: ነገር ግን ለጌታና ለፀጋው ቅርብና ምቹ ነው:: ሰለዚህ ምርጫችንን ልናስተካክል ያስፈልጋል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ. 14:1-6 ክፍል 54

View Details

የሐዋርያት ሥራ.13:42-52 ክፍል 52

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በሐዋርያት መመስረት እና ከሐዋርያት ትምህርት ከእውነት ከክርስቶ ትምህርት መውጣት ነው የሚለው ይብራራልን። 2. ሐዋርያት በክርስቶስ ስም አጥምቀዋል ጌታ “ኢየሱስ በአብ፣ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እያጠመቃችሁ” ብሏል። በኢየሱስ ማጥመቅ የሚለው ምን ማለት ነው? 3. ደዌ እና ህመም የሚለው ቃል ይብራራልን። 4. የድሮ ባህሪያችን ተለውጦ በድሮ ባህሪያችን የሚያውቁን ሰዎች ፊት እንዴት ነው ወንጌል ለመመስከር የምንችለው? 5. ህይወታችን ተቀይሮ እመለክታችን ላይለወጥ ይችላል? ወደ እዚህስ እንዴት ነው የምንመጣው?

View Details

ሰው ይብዛም ይነስ የኔ የሚለው የሚቆጥረው የሚኮራበት ልቡንም የሚጥልበት ደግሞም የሚመካበት ነገር አለው:: እውቀት ሀብትና ውበት እንዲሁም ዘመድ የቅርብ የምንለው ሰው ወዘተ... በአንድም በሌላ ሰው ከሚመካባቸው ጥቂቶቹ ናቸው:: እነዚህ ሁሉ ግን እንድ ቀን የሚክዱን ደግሞም ተስፋ የማይደረግባቸው ይሆናሉ:: በጊዜውም አለጊዜውም የማየከዳና የማያሳፍር ፅኑ መመኪያ ግን እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ብቻ ነው:: እግዚአብሔርን በተመካንበት በዛ ሰላም ይኖረናል:: ተስፋችንም እውን ይሆናል::መፅናናት ሀይልና ብርታትም ይሆንልናል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.13:42-52 ክፍል 53

View Details

እግዚአብሄር የጠራን ለድል ስለሆነ በሃጢያት በበደለኛነት ከመኖረ ሊታደገን ለሚጣራን ፈቃደኛ ባለመሆን በቸልታ ስንመላለስ ሀይወታችን እግዚአብሄርን የሚያሳዝን ስለሚሆን ከሃጢያት ሸሽተን ማምለጫ ተዘጋጅቶልናል ይህ ማምለጫ ሮጦ ለሚመጣ ሁሉ መደበቂያ ይሆናል ስለዚሀ የተዘጋጀልንንማምለጫ እንዳናጣው ልንጠነቀቅ ይገባናል፤

View Details

የሐዋርያት ሥራ.13:15-41 ክፍል 51

View Details

በህይወታችን ቅድሚያ የምንሰጠው ማንኛውም ነገር እርሱ ከፊታችን ያለውን መንገዳችንን ይወሰናል:: ለበረከት ለፈውስና ለመፅናናት ይሆናል:: ወይም ደግሞ ለምሬት ለሀዘን ለሽንፈትና ለውድቀት ይሆናል:: ከነገሮቻችን በፊት እግዚአብሔርን ማስቀደም ፈቃዱንም መጠየቅና የእርሱን መገኘት ወይም አብሮነት ማረጋገጥ በአማኝ ህይወት ውስጥ እጅግ ዋና ነገር ነው:: በዚህ መልዕክት ይህንን በስፋት እንማራለን::

View Details

እግዚአብሄርን ማመስገን በፈቃዳችን የሚሰጥ ነገር ቢሆንም እግዚአብሄርን ማመስገን ግን የርሱ በጎ ፈቃድም ጭምር እንደሆነ ማወቅ እንዳለብን ይህ ትምህርት ያሳስባል። በሁሉ ማመስገንን በተለየ መልኩ የምንማርበት መልዕክት ነው። አንዳንድ ስዎች በተለያዩ ችግሮች ውስጥ እያለፍኩ ነው እንዴት አድርጌ ነው እግዚአብሄር የማመሰግነው ብለው ይጠይቃሉ። ነገር ግን በዚህ ትምህርት ውስጥ እንዴት እያለፍንበትን ያሉትን ነገሮች ለክብሩ በምስጋና እየቀረብን ድልን እንደምናገኝ ያስተምረናል።

View Details

የአማኝ ህይወት በምድር ላይ የመስቀል ጉዞ ነው:: በመስቀል ጉዞ ውስጥ የሰይጣን ውገያና ፈተና አለ:: ደግሞም በዙሪያችን ባሉ ሰዎች መገፋትና መጣል አለ:: መከዳትና መተውም አለ:: በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን የማይናወጥ ዋስትና አለን:: የሚያበረታን ጉልበትና በመከራ ውስጥም ፅናት የሚሆነን ጌታ እርሱ ከእኛ ጋር ነው:: እስከ አለም ፍፃሜ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ የሚለው የተስፋ ቃሉ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ የማይናወጥ ፅኑ የተስፋ ቃል ነውና::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.13:13 ክፍል50

View Details

የሐዋርያት ሥራ.13:1-4 ክፍል 48

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ከምናለቅስበት ለመፈወስ የምንጎበኝበትን ቀን መቼ እንደሆነ የምናውቀው እንዴት ነው? 2. ሥፍራ ወደ አለመልቀቅ የምንደርሰው እንዴት ነው? 3. በህይወታችን ውስጥ የሚፈራረቁበትን ቀኖች እንዴት ነው የበረከት ይሁኑ አይሆኑ የምንለየው? 4. የጌታ ቀን ወደ እኛ ሲመጣ እንዴት ነው የምናውቀው? 5. ስለ ጌታ የምንቀበለውን መከራ ከሌላ መከራ ለይተን በህይወታችን የምንቀበለው እንዴት ነው? 6. ሰው በችግር ውስጥ ሲያልፍ ለመርዳት ያንን ችግር እንዴት ነው የምናውቀው?

View Details

የሐዋርያት ሥራ.13:4-12 ክፍል 49

View Details

እግዚአብሔር በመንገዱ ፃድቅ የሆነ እውነተኛ አምላክ ነው:: ስለዚህም ሰውንም በእርሱ መንገድ እንዱሄድ ይፈልጋል:: የሰው በረከት ፈውሰና ጉብኝት ያለው በእግዚአብሔር መንገድ ላይ በሆነበትና በተገኘበት መጠን ነውና:: በዋጋ ተገዝተናልና የራሳችን አይደለንም:: ስለዚህ መንገዳችን ደግሞም በረከታችን ያለው የጌታ መንፈስ በሚመራንና በሚያስኬደን በኩል ነው::ከዚህ የወጣ ለጊዜው መልካምና በረከት የሞላበት ይምሰል እንጂ ፍፃሜው ኪሳራና ውድቀት ነው:: በእግዚአብሔር መንገድ እንሁን እንጂ ነገሮች ያልተሳኩ ደግሞም ጉድለትና እጥረት ያለበት ኑሮ ቢመስልም እንኳ የጌታ ጉብኝትና በረከት በራሱ መንገድ በጊዜው ይሆናል:: በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ሰላምና እረፍት እምነትና ተስፋ የሞላው ህይወት ይሆንልናል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.12:12-25 ክፍል 47

View Details

መታዘዝ ባለበት በዛ ዋጋ መክፈል አለ:: ይህንን ደግሞ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሞት እስኪስጥ ድረስ አባቱን በታዘዘውና የመታዘዝ ፍፁም ምሳሌያችን በሆነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናያለን:: ከመታዘዝ የጎደለ ህይወትና ማንነት ያለው እርሱ ከእግዚአብሔር የተስፋ ቃልና ከበረከቱ ደግሞም ከፀጋው የራቀና የጎደለ ነው:: ከምንም በላይ በእግዚአብሔር ላይ ማመፅና ለጌትነቱ የሚገባውን ክብር አለመስጠት ነው:: - መታዘዝ የእውነተኛ ደቀመዝሙር ህይወት ነው:: ስለዚህ ጌታን እንከተላለን እያልን ከዚህ ህይወት ጎድለን እነዳንገኝ ልንጠነቀቅ ይገባል::

View Details

ሰው በህይወቱ የሚያርፈው በጌታ ልቡ ሲጠበቅለት ነው፤ ያላረፈ ሰው ልቡ ሙሉ ለሙሉ በጌታ ያላረፈ ሲሆን ነው፤ ሰው የሚፈልገውን ማግኘቱ እረፍት አይደለም እረፍት አገኝበታለሁ ብሎ የሚገባበት ነገር እረፍት የሚነሳው ይሆንበታል ፤ ከሁሉም በላይ የነፍስ እርፍት ክርስቶስ የኛ ሲሆን ነው እርሱ ካላሳረፈን ምንም አያሳርፈንም፤

View Details

የአማኝ መንገድና ህይወት የእለት ተእለት ኑሮውም እነደ እግዚአብሔር ቃል የሆነ ደግሞም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሊሆን ይገባዋል:: እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ማንነት እንዲኖረን ደግሞ ምርጫችን ሁልጊዜ በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ መሆን ዋናውና የመጀመሪያው ነው:: በዚህ መልዕክት የአማኝ ህይወት በእግዚአብሔር ፊት እና እግዚአብሔርን በሚወዱ ሰዎች መካከል ምን ሊመስል እንደሚገባ እንማራለን::

View Details

ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ ሲመላለስ የመስቀል ጉዞ ነበር የተጓዘው:: የመስቀል ጉዞ ደግሞ በመጀመሪያ ራስን ዝቅ ማድረግን ይጠይቃል:: ራሱን ባዶ አድርጎ በስጋው ወራት የተመላለሰበት የጌታ ህይወትና ኑሮ ዛሬ እኛ የእርሱ ተከታዮች ልንኖረው የሚገባውን ኑሮ ያሳያል:: እውነተኛ ደቀመዝሙር ኢየስሱን በቃልና በስራ በህይወቱ የሚያሳይ ሲሆን የመስቀሉንም ጉዞ ሲጓዝ ብቻውን ሳይሆን ነገር ግን ታላቅ ተስፋን ከሰጠው አሸናፊ ከሆነው ጌታ ጋር በመሆን ሌሎችን ደቀመዝሙር ለማድረግ የሚተጋ ነው::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.12:1-11 ክፍል 46

View Details

እግዚአብሔር ዛሬም ሰውን ይጠራል:: ከኃጢአት ከበደል ከአመፅ ስፍራ ይጠራል:: እርሱ ከማይከብርበት ደስም ከማይሰኝበት ስፍራ ይጠራል:: ሲጠራንም ሊወቅሰን ወይም ሊፈርድብን ሳይሆን ነገር ግን ለበረከትና ለፈውስ ነው:: እግዚአብሔር ከጠራን በኃላ በቀደመው ማንነታችን እንድንቀጥል አይደለም:: በህይወታችን ለውጥ ይሆናል:: ለፈቃዳችን ሳይሆን ለፈቃዱ ልንኖር እንጀምራለን:: ተስፋችን ከምድር ላይ ተነስቶ የጠራን ጌታ ባለበት በሰማይ ይሆናል:: ሰላምና እረፍትም ይሆንልናል::

View Details

በዚህ ትምህርት የጌታን ማዳን በህይወታችን እንዴት ልናገኝ እንደምንችል ከኛ የሚጠበቅብንን ያላስትዋልነውን ፈውሳችንን ያዘገየብንን የችግራችንን ቁልፉን እንድንረዳና አቅጣጫችንን እንድንለውጥ ያደርገናል:: አልፈንም ወደ ትክክለኛ መረዳትና ውሳኔ ያደርሰናል::

View Details

አይኖቻችን ያሉበት ህይወታችንን ይወስናል:: በየትኛውም ችግርና ፈተና ውስጥ ብንሆን አይኖቻችን ተከፍተው ጌታን ስናይ ፍፁም ለውጥ ይሆናል:: ነገሮቻችን ባይለወጡ እንኳ የኛ መለወጥ ግን እርግጥ ነው:: እግዚአብሔርን ማየት ሁለንተናን ይፈውሳል:: ከክፉዉ ዘመንና ጥፋቱ ማምለጫው ይኸው ነው:: ጌታን ማየት:: ጌታን ስናይ መፅናናት ሰላምና እረፍት ይሆንልናል:: በምንሰማውና በምናየው አንናወጥም አነደነግጥምም ይልቁን ምስጋናና ምህረት ባርኮትም ይበዛልናል:: እረጅም መንገድ የመጓዛችንም ሀቅም አይኖቻችን በጌታ ላይ በተተሉበት መጠን ልክ ነውና: አይኖቻችን ማንንና ምን ላይ እንደሆነ ራሳችንን ልንጠይቅ ያስፈልጋል

View Details

የሐዋርያት ሥራ.11:27-30 ክፍል 45

View Details

በዚህ ትምህርት እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ቃል ከገባላቸው የቀረ ምንም እንዳልነበረ ሁሉ በመደበላችው ሁሉ መኖር የሚገባቸውን አይነት ኑሮ እንዲኖሩና ርስት ያልነበረውን ህዝብ ባለርስት ካደረገ እንዲሁ ዛሬም ለክብሩ የተለየን ሰማያዊ ርስት የተሰጠን እንደሆንን እንድንገነዘብ ይረዳናል::

View Details

እግዚአብሔር ለህዝቡ የማይለወጥ ፍፁም ፍቅር አለው:: እርሱ ለእኛ ያለው ይህ መውደድ የሚገለጠው ግን እኛ በጠበቅነውና በእኛ መንገድ ሳይሆን ለእኛ በሚጠቅመን እርሱንም በምናከብርበት መንገድ ይገለጣል:: እግዚአብሔር እንደሚወደን በቃሉ ተፅፎልናልና እንደ ቃሉ እንደምንወደድ ልናምን አስፈላጊና ዋና ነገር ነው:: አለበለዚያ ለጊዜው ከሚከሰቱ ሁኔታዎች ተፅዕኖ ስር አንሆናለን:: በእግዚአብሔር ለመወደዳችንም ተጠራጣሪዎች ያደርገናል:: ይህ ደግሞ ሰላማችንን የሚጎዳ ጌታንም ደስ የማያሰኝ ህይወት ይሆናል:: እግዚአብሔር አመፀኛውን እንደሚቀጣ የእርሱን ጉብኝት በተዕግስት የሚጠብቀውን ፃድቁን በመከራ ውስጥ ይጠብቀዋል:: ፅድቁን በሚገልጥበትና በሚሰራበት ጊዜ ገንዘቡ የሆናል:: ከችግሩ በላይ በእርሱ ላይ ያለውን የጌታ መውደድ አይቷልና::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.11:19-26 ክፍል 44

View Details

የሐዋርያት ሥራ.11:1-18 ክፍል 43

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ስንፀልይ “መንፈስ በማይናገ መቃተት ይማልዳል” የሚለው በልሳን መፀለይ ነው ወይ? በአንዳንድ ሁኔታ መፀለይ ሲከብደን በልሳን መፀለይ አለብን ወይ? 2. 1ዮሐንስ 2፡27 “ማንም ሊያስተምራችሁ አይገባም” የሚለውን ብታብራራልን። 3. የእግዚአብሔርን ሞገስ ለማግኘት የእኛ ድርሻ አለ? ካለስ ምን ማድረግ ነው ያለብን? 4. ፊሊ 3፡13-16 በጌታ እንዳንረካ የሚያደርጉን ነገሮች ምንድን ናቸው? 5. ለተቀበልነው ወንጌል ራሳችንን እንድንሰጥ የሚረዳን ምንድን ነው?

View Details

ይህንን ትምህርት ሲያዳምጡ የተለየ መረዳትን ያገኛሉ በተለይም ጠላት በህይወታችን ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል እንዳንኖር ለማቋረጥ የሚጠቀምባቸውን ልዩ ልዩ ዘዲይዎችን እንዴት እንደሚያቀናብርና ልንደርስ ካለው መንፈሳዊ ብቃት እንደሚያስተጓጉል፡ ከቃሉ በሆነ አቅም ውስጣችን ሲሞላ ግን የማያቋርጥ መነቃቃትን ውስጣችን ይጨምራል ከመንፈስ ቅዱስ የሆነን በረከት እንዴት መጠቀም እንዳለብን እንድናውቅ ና በእውነትኛ መርህ እንድንኖር የሚየደርገንን ማስተዋል ያገኛሉ

View Details

የሐዋርያት ሥራ - ምዕራፍ 10:36-48 ክፍል 42

View Details

ከእግዚአብሔር የአባትነት ባህርይ አንዱ መጋረድ ወይም መሰወር ነው :: የእርሱ የሆኑትን ልጆቹን ከጥፋት ደግሞም ከመከራ ይሰውራል:: ከአመፀኛው አመፅና ክፋት ከጥፋቱም የሰውራል:: "በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛል" እንዳለ ዳዊት በዘመናት መካከል የማይለወጥና የማይቀያየር ጌታ ዛሬም አካሄዱን ከእርሱ ጋር ያቀናውን ህዝቡን በፈቃዱና እርሱ ባለው የተገኘውን ዛሬም ከጥፋት ከመከራ የሰውራል::

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. በዛሬ ጊዜ መልአክት የመስማት ልምምድ ሊኖር ይችላል ወይ? መልአክት ያነጋግሩናል ብለን መጠበቅ እንችላለን ወይ? 2. እግዚአብሔርን ወደ መስማት የፀሎት ልምምድ ውስጥ እንዴት ነው የምንገባው? 3. እምነት ከሰማነው ከእግዚአብሔር ቃል ነው የሚለው ቢብራራ። 4. ጌታን ታምነን ግን ለጥቅማችን የምናልፋቸው ችግሮችን ለመረዳት እንዴት ነው የምንችለው? 5. ሳዖል የተለየው ሞገስ ነው እንጂ ስልጣኑን አይደለም የሚለውን ብታብራራልን። ሞገስ ከእኛ የሚለየው እንዴት ነው? 6. ሞገስ ሲመጣ ከእድል ፈንታችን ጋር ያገናኝናል፤ በክብሩ ባለጠግነት ይሞላናል ከሞገሱ ከጎደልን ግን ዋጋ ያስከፍለናል የሚለውን ብታብራራልን። 7. የተጎዳንበትን ነገር እንዴት መርሳይ እንችላለን?

View Details

የሐዋርያት ሥራ.10:33-39 ክፍል 41

View Details

እግዚአብሄር ታማኝ መሆኑን በግለሰብ ህይወት፣ በጠራው ህዝብ ላይ፣ እና በሚሰራቸው ተአምራት ታማኝነቱን ገልጧል፡፡ የእግዚአብሄር ታማኝነትን እኛ አመነው አላመነው እርሱ የታመነ አምላክ ነው፡፡እግዚአብሄር ለተናገው የተስፋ ቃል ታማኝ ነው፡፡ በርሱ የሚታመኑትን በሚገባ ያውቃቸዋል እና ፈጽሞ አይጥላቸውም፡፡ በእግዚ ታማኝነት ላይ ያለን እምነት እና መደገፍ ትልቅ ቢሆንልን በብዙ እንጠቀማለን፡፡ባያድንውንም እንኳ ለቆመው ምስል አንሰግድም ያሉትን ታማኝ ልጆቹን የማያሳፍር አምላክ ነው፡፡ በምድርምሆነ በሰማይ እግዚአብሄርን የሚያህል ታማኝ መቼም አናገኝም፡፡

View Details

የሐዋርያት ሥራ.10:23-33 ክፍል 40

View Details

በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሰንገባ ከምንቀበላቸው የመዳን በረከቶች አንዱ የነፍስ እረፍተና ሰላም ነው:: በዚህ ምድር እረፍት ለማግኘት ሰዎች በብዙ ይደክማሉ:: ስጋን ከማሳረፍ ያለፈ ነፍስን የሚያሳርፍ ግን ምንም ማንም የለም:: ነገር ግን ሰላሜን እሰጣችኃለሁ እኔ የምሰጠው ሰላም አለም እንደሚሰጥ አይደለም ያለው እርሱ ጌታ ኢየሱስ ብቻ የነፍስን እረፍትና ሰላም ይሰጣል:: - ይህም የጌታ ሰላምና እረፍት ቃሉን በመስማት እርሱ የተናገረንን በእምነት በመቀበልና እንደ ፈቃዱም በመሆን አነዲሁም ሁልጊዜ በእርሱ ፊት በመሆን በቃሉና በፀሎት በመትጋት ወደ ነፍሳችን ይፈሳል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.10:9-23 ክፍል 39

View Details

አማኝ በሁለት ጉዳዮች ላይ ሊያተኩር ይገባዋል አንደኛው በክርስቶስ ያገኘው መዳን ላይ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ያንን ያገኘውን የዘላለም ሕይወት መጠበቅ ናቸው። ስለዚህ እነዚህን ሁለት ነገሮች እያጣ የመጣ አማኝ በህይወቱ ውስጥ፡ሊስተካከል በማይችል ጥልፍልፍ ነገር ውስጥ ሊገባ ስለሚችል መጠንቀቅ አለበት። ሐናንያ እና ሰጲራ ጌታን ያገኙ መንፈስ ቅዱስ የተሞሉ ናቸው ድነዋል መንፈሱን ተሞልተዋል ግን መዳናቸውን እና ያገኙትን ሕይወት አጥብቀው ባለመያዛቸው እና ለምኞታቸው ታልፈው ስለተሰጡ ባገኙት ህይወት መቆምላይ ጸንተው መቆም ባለመቻላቸው ሊያጠፋቸው ቻለ። ይህንን እና የመሳሰሉትን ቁምነገሮች በዚህ መልክት ውስጥ እናገኛለን።

View Details

በክርስትና የህይወትጉዞ ከተካፈልነው መንፈሳዊ ህይወት ውስጥ አንዱ ቤተሰብነት ነው:: የእግዚአብሔር ቤተሰብ:: ይህ ቤተሰብ የሆንበት የእግዚአብሔር ቤት ለምን ለማንና እንዴት እንደምንኖር በማወቅ የምንኖርበት ቤት ነው:: - በሞቱና በትንሣኤው የተገለጠው የክርስቶስ ፍቅር በቤቱ ቤተሰብ ልንሆንና ልንኖር ምክንያት እንደሆነን በማወቅ:: - ለእኛ ለሞተውና ለተነሳው ለእርሱ እንኖር ዘንድ ለአለም ለስጋና ለኃጢአት የሞትን መሆናችንን በማወቅ:: - በመስቀል በተወገደው በአሮጌው ሰውና በክርስቶስ በሆነው በአዲሱ ሰው መካከል ያለውን ልዩነትና ማንነት ለይቶ በማወቅ:: የምንኖረው ኑሮ ነው::

View Details

ወደፊት መመልከት እድንችል ያለፈውን ታሪካችንን እየረሳን በተፈወሰ ማንነት ወደኋላ ማየት እስከሚያቅተን ድረስ እግዚአብሄር ነጻ ያወጣናል ይቀይርልናል ከኛ የሆነ መፍትሄን ለማግኘትም ብዙ ብንጥርም መፍትሄን ስለማናገኝ የእይታ ለውጥ ያስፈልገናል፤ ህይወታችን ተቀይሮ እይታችን ካልተቀየረ ፈውስ ልናገኝ አንችልም ያለፈውን እያስታወስን ለምን ሆነብኝ እያልን በባለፈው ዕይታ ነገን ለምንመለከት እግዚአብሄር ጣልቃ ይገባልንና ንጻ ያውጣናል ስለዚህ ካለፈ ነገር ስንፈወስ ነገን በተስፋ መጠባበቅ እንችላለን ነጋችንን ስናይ በትላንቱ እይታ ማየት ወደክስረት ስለሚወስደን የእይታ ለውጥ ማግኘት ዋና ነገር ነው

View Details

የአማኝ ህይወት በምድር ላይ ጌታን በማመን ብቻ የሚቆም ሳይሆን ነገር ግን የጌታ ተከታይ ደቀመዝሙር በመሆን የሚቀጥል ነው:: የክርስትና መንገድ ኢየሱስን እያየን የምንሄደው የመከራ ደግሞም የተስፋና የበረከት የሰላም መንገድ ነው:: ኢየሱስን መከተል:- - በራስ ላይ መፍረድን የራስን መተው ይጠይቃል:: - አሰቀድሞ ዋጋ መተመንን ይፈልጋል:: - መጣል ያለብንን መጣል መውጣት ካለብንም መውጣት የግድ ነው:: -ባልተከፈለ ልብ ፍፁም እኛነታችንን ሙሉ በሙሉ መስጠትን ይጠይቃል:: - ጌታን ስንከተል እርሱን እያከበርንና ለእርሱ ምስክሮች በመሆንም ነው:: - መከተል እስከፍፃሜ መሄድ ነው:: በምናልፍባቸው በማንኛውም ነገርና ሁኔታ ውስጥ ፀንቶ መከተል ነው::

View Details

እግዚአብሔር የህዝቡ ጠባቂ ነው:: ደግሞም እውነተኛና ፅኑ መሸሸጊያና ማምለጫም ነው:: ከሞተ ፍርሀት ያድናል:: ከዘላለም ፍርድ ይታደጋል:: ከኃጢአት ጉልበትና ከአለም ደግሞም ከክፋቱ ያድናል:: - የመማፀኛ ከተሞች ከበቀለኞቹ ብቸኛ ማምለጫ እንደሆኑ ለኃጢያተኛው በዘላለም ፍርድ ስር ላለ ብቸኛው ማለጫ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ነው:: - ጌተ ኢየሱስ እርሱ ስለ ሀጢአተኛው ራሱን መስዋዕት አድርጎ ያቀረበ ደግሞም የዘላለም ሊቀ ካህን ወደ እርሱ ለሚሸሹ ሁሉ ፅኑ መማፀኛና እውነተኛ መሸሻና መዳኛ ነው::

View Details

ሰው በህይወቱ የእግዚአብሔር ምሪት የሚገለጠው በመንፈስ ሲመራ ነው:: በእግዚአብሔር መንፈስ ለመመራት የመጀመሪያውና ዋናው ከራስ ፈቃድ መውጣት ነው:: በራሳችን መንፈሳዊ ነው ያልነው ወይም ያደረግነው ሁሉ መንፈሳዊ አይደለም:: እግዚአብሔር ባለን ውስጥ ራሳችንን የምናገኝበት እርሱ ነው የመንፈስ ምሪት :: ይህን በሚመለከት ጥልቀት ያለው ትምህርት በዚህ መልዕከት እናገኛለን::

View Details

የሐዋርያት ሥራ 10:1-8 ክፍል 38

View Details

የሐዋርያት ሥራ.9:36-43 ክፍል 36

View Details

በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ያመንነው ደግሞም በመከተል ላይ ያለነው ምክንያቱ ምንድን ነው? ይህ መልዕክት በስፋትና በዝርዝር የሚመልሰው ጥያቄ ነው:: እያለፍንባቸው ባሉት ነገሮችና ሁኔታዎች የተነሳ በዝለትና በድካም ደግሞም በብዙ ጥያቄዎች ተሞልተን ይሆናል ነገር ግን ስፍራን ባለመልቀቅ በተናገረን ላይ በተዕግስት ፀንተን ልንጠብቅ ነገሮች ባይገቡን እንኳ በምስጋና ሆነን በፊቱ ልንቆይ የጌታ ፈቃድ ነው:: በዚህም ውስጥ ህይወትን በክርስቶስ ውስጥ ሆኖ የመኖርን ትርጉምና ፍሬ እናያለን::

View Details

የሐዋርያት ሥራ 10:1-5 ክፍል 37

View Details

በአማኝ ህይወት ውስጥየእግዚአብሔር ፅድቅ ከሚገለጥበት አነዱ ጣልቃ መግባቱ ነው:: ለማዳን ከጥፋት ለመመለስ ደግሞም የክፉውን ስራ ለማፍረስ:: በምናልፍበት የትኛውም ፈተናና መከራ በእግዚአብሔር ዘነድ ገደብ አለውና ከገደቡ እንዳያልፍ እርሱ ጣልቃ ይገባል:: - ለእግዚአብሔር በህይወታችን ጣልቃ መግባት የኛ በፅድቅ መቆምን በእውነትና በቅድስና ደግሞም በንፅህና መሆንን ይጠይቃል:: የን ጊዜ ካልተጠበቀ ስፍራና ሁኔታ የእርሱን ጠልቃ መግባት ያሳያል:: - አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን ጌታ ጣልቃ የመግባቱ ሁኔታና አደራረጉ ላይገባን ይችላል:: ደግሞም ነገሮች አንደምንጠብቃቸው ላይሰካኩ ፍፁምም ሊፈራርሱ ይችላሉ:: እግዚአብሔር ጣለቃ ሲገባ እኛ እንደምናየው የዛሬን ወይም ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ወደፊት ሊሆን ያለውን ከማወቁና ለእኛም ከሚጠቅመን አንፃር ነው::

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ኮከብ ቆጣሪዮች በአዲስ ኪዳን አሉ ወይ? ከዋክብት ዘመንን መናገር ይችላሉ ወይ? 2. የሙሴ አማት ኢትዮጵያዊ ነው ወይ? 3. ይሁዳ የተፈጠረው ጌታ ኢየሱስን ለመሽጥ ነው ወይ? ባይሸጠው ኖሮ ጌታ ይሞት ነበር ወይ? 4. በደቀመዛሙርቱ ላይ የደረሰው ስደት ጌታ “ወደ አለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ስበኩ” ሲላቸው እነርሱ ግን በኢየሩሳሌም ስለነበሩ ወደ አለም እንዲሄዱ የመጣ ስደት ነው ወይ? 5. ወንጌልን ለሌሎች እንድናደርስ በእኛ ላይ ስደት ሊመጣ ይችላል ወይ? 6. ወንጌልን ለመመስከር አቅም የምናገኘው እንዴት ነው? 7. ሰዎችን ይቅር ስንል (ስንፈታ) የበረከት ተካፋዮች ይሆናሉ ወይ?

View Details

እግዚአብሔር በቤቱ በህዝቡ መካከል ከሚገለጥባቸው መንገዶች አንዱ ሞገስ በመሆን ነው:: ጌታ ለህዝበ ደግሞም ለግለሰብ ሞገስን ይሰጣል:: ሞገስ በእግዚአብሔር ፊት ተተቀብሎትን ማግኘት ነው:: ይህ ሞገስ በክርስቶስ ኢየሱስ ለሚያምኑ ሁሉ የሚሆን ነው:: ለሚታዘዘው በፈቃዱ ለሚሄድ በእርሱ ላይ ለታመነውና ለተደገፈው ሞገሰ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆንለተል:: እግዚአብሔር ሞገስ እንደሚሰጥ እንዲሁ ደግሞ ከፈቃዱ ከወጡና ካልታመኑት ካልታዘዙትም ላይ ሞገሱን ያነሳል:: ይህ ሲሆን በረከት ይጎላል:: ሰላም ይጠፋል:: ለፀሎት መልስ አይመጣም:: ቋንቋ ይቀየራል:: ህይወት በፍርሀትና በድካም ይሞላል:: - በመመለስ ራስንም በፊቱ በማዋረድ ሞገሱን ልንቀበል የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.9:32-35 ክፍል 35

View Details

እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መንግሥቱ በጠራው በህዝቡ ላይ ራሱን ይገልጣል:: ደግሞም በግል ህይወታችን እለት እለት በመግባትና በመውጣት በኑሮአችን በስራችን ሆነ በንግግራችን ጌታ በእርግጥ የኛ ጌታና መሪ መሆኑ የታወቃል:: በዚህ መልዕክት እግዚአብሔር በህዝቡ ላይ የሚገለጥባቸውን ሁኔተዎች:- - የአመፅንና የክፋትን ጉልበት በመስበር - ለወንጌልና ለወንጌል ስራና አላማ የቆረጡ በቃሉና በፀሎት የተጉ ሰራተኞችን በመጨመር እና - ህዝቡን የእርሱ ማደሪያው በማድረግ ሲሆን ሌሎችንም በስፋት እንማራለን::

View Details

እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን ሁሉ ለህይወት ጠርቷል:: ጥሪውን ተቀብለን ምላሽ ለሰጠን በመንግስቱም በአገልግሎት ለተጠመድን ለእኛ የኑሮ መለኪያ አለን:: እርሱም የክርስቶስ ህይወት ነው:: ብፅዕና ያለው ህይወት:: በዚህ መልዕክት የኑሮ መለኪያዎችን በዝርዝርና በስፋት አንማራለን::

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ሌሎችን ከመፍታታችን በፊት መፍታት ያለብን ራሳችንን ነው ወይ? 2. ከአልተፈታ ህይወት እንዴት ነው መውጣት የምንችለው? 3. ካልተለቀቀ ህይወት እንዴት ነው መውጣት የምንችለው? 4. እኛ ለቀን ሰዎች ካልለቀቁን ምንድን ማድረግ ያለብን? 5. ለበደሉን ሰዎች ክፉ ሲደርስባቸው ባንፀልይላቸው በደል ነው ወይ? 6. ሰዎች የምንሰራውን ሥራ ከጌታ መሆኑን እንዲያምኑልን ምን እናድርግ? 7. ሰው የተጠራው የራሱን ሸክም ይሸከም ዘንድ ነው የሚለው ይብራራልን። 8. በረከታችን ያለው እግዚአብሔር ባስቀመጠን ቦታ ስንቀመጥ ነው የሚለው ይብራራልን።

View Details

የሁኔታዎች አለመስተካከል እና ድርብርብ የሆኑ ችግሮች በላያችን ላይ መብዛታቸው ነገራችንን የሚያጨልሙ ቢመስሉም እግዚአብሔር ግን በዚህ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ከማይቻል ነገር ውስጥ መፍትሄን ማዘጋጀት እንደሚችል ማሳየት ይችላል፡፡ ለዚህ ነው በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ባለቀ ነገር ላይ የተገለጠ የእግዚአብሄርን የዝግጅት ችሎታውን እናነባለን፡፡ እኛ አንድን ነገር ማዘጋጀት ብንችል እንኳ ባለ ነገር ላይ እንጂ በሌለ ነገር ላይ ምንም ማዘጋጀት አንችልም እግዚአብሔር ግን በባዶ ነገር ላይ ተገልጦ ሁሉን ማዘጋጀት ይችላል፡፡

View Details

እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ማዳኑን ከገለጠ ጊዜ ጀምሮ አለም የሰው ዘር በሁለት ተከፍሏል:: ይኸውም በፀጋው የሚኖር ህዝብና ያለፀጋው በራሱ ጥረትና ግረት የሚኖር እንደፈለገውም የሚወጣና የሚገባ በፍረድ ስር ያለ ህዝብ:: - በፀጋው የሚኖረው ህዝብ ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀስ እንዲሁም የሚያደርገውንም ሁሉ እንደ እግዚአብሔስ ፈቃድ ለእግዚአብሔር ክብር ይንቀሳቀሳል ያደርጋልም:: ስለዚህም በሚገባበት ስፍራም ሆነ በሚሰራው ሁሉ የጌታ በረከትና ሞገስ ከእርሱ ጋር ይሆናል:: - ያለ እግዚአብሔር አንቀሳቃሽነት የምናደርገው እንቅስቃሴና የምንሔድበት ስፍራ ከበረከቱና ከሞነሱ የጎደለ ነው:: ይሁን እንጂ በመመለስና በንስሀ እንደገና ከራሳችን ልንወጣ ወደ ሞገሱና በረከቱ ልንገባ የጌታ ፈቃድ ነው::

View Details

ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የገባ ሁሉ የህይወት ጉዞው እግዚአብሔር እንደወደደና ፈቃዱም ባለበት ነው:: ሰለዚህ በህይወታቸን አጋጣሚ የምንለው ወይም በአጋጣሚ የሚሆን ነገር አይኖርም:: ይህንንም ማወቅና መረዳት ሰለ ራሳችን ያለንን አተያይ የስተካክላል:: - እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለውን መልካሙን አላማና በእርሱ ዘንድ ያለንን ክብር እናያለን:: - ክርስቶሰ በእኛ ውስጥ አለና ልዩነት ያለው እልፍ ያለ ህይወትና ኑሮ እንደተሰጠን እናያለን:: - በክርስቶስ ትምህርት የመኖር ህይወት እንደተሰጠን እናያለን:: - በቃሉ የሚታዘዝ ህይወት እንደተሰጠን እናያለን:: በአጠቃላይ በዚህ ምድር ስንኖር እልፍ ባለ ህይወትና ኑሮ ለወንጌል ስራ እንድንኖር ይህ በእኛ ላይ ያለው የእግዚአብሔር አጀንዳ ነው::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.9:31 ክፍል 34

View Details

እግዚአብሔር ዓላማውን እና ሃሳቡን ባስቀመጠባቸው ሰዎች ላይ ያን ጊዜ ሰይጣንም የክፋት ኢላማውን ያደርጋቸዋል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ዓላማውን ባደረገባቸው ልጆቹ ላይ ጥበቃውን እና ማዳኑን ያበረታል፡፡የእግዚአብሔር እጅ በዳዊት ላይ እንደነበረች ሁሉ የንጉሱ ሳኦል እጅ ደግሞ በዳዊት ላይ ነበረች፡፡ ዳዊት በሳኦል ክፋት እና ተንኮል ዳዊት ህይወቱ ያድግ ይሆን እንጂ ዳዊት በሳኦል እጅ አይጠፋም፡፡ እግዚአብሔር በምናልፍበት ሁኔታ ውስጥ የሚያድገውን ማንነታችንን ማየት ያስደስተዋል ምክንያቱም በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ በኛ ህይወት ማደግ እግዚአብሔር ይከብራል ስለዚህ ማንኛውም ነገር እኛን እንዲያጠፋን ሳይሆን እኛን እንዲያሳድገን ጌታ በማዳን እና በጥበቃው ውስጥ ጋርዶን ያሳድገናል፡፡

View Details

የሐዋርያት ሥራ.9:25-31 ክፍል 33

View Details

የእግዚአብሔር ፅድቅ ሰውን ከገነት እንዳስወጣው የእግዚአብሔር ምህረትና ፍቅር ደግሞ ሰውን ከወደቀበት ለማንሳት ከኃጢአት ከክፉ ከአጋንንት እስራት ደግሞም ከህይወት እስራት ነፃ ሊያደርግ ሊፈታው ወደ ምድር ወርዷል:: ጌታ እኛን ሁኑ ያለን እርሱ ለአኛ የሆነልንን ነው::ምህረትንና ፍቅርን እንደተቀበልን እኛም ልንሰጥ:: ነፃ ነኝ የሚል የተፈታ እርሱ ፍቅርና ምህረት የተሞላ ነው:: የሚሰማውንና የሚያየውን ሁሉ በፍቅርና በምህረት ውስጥ ያያል:: - ወንጌል ነፃ ያላወጣው እርሱ ራሱ አልተፈታምና ሌላውን መፍታት አይችልም::

View Details

ጌታ ወደ ህይወታችን ወደ ነገራችን የሚመጣው ለጥየቄያችንም መልስ የምናገኘው እኛ በፈለግነውና በራሳችነም እየተጋን ባለንበት ሳይሆን ነገር ግን በራሱ ጊዜና ሁኔታ ይመጣል:: በተለይ በራሳችን የሆነውን ጥረት ባቆምንና ረዳት በፈለግንበት ወቅት:: ጌታ ወደ እኛ ሲመጣ አይኖቻችንን ይገልጣል: :ለጌታ ያለን ፍቅር ይታደሳል:: ከለፋንለት ነገር ይልቅ የእርሱን ታላቅነትና ምሪት እናያለን:: በእርሱም በረከት እንሞላለን:: ጌታ በእኛ ህይወት ዋናው አላማ ፈፅመን እንከተለው ዘንድ ነው:: በዚህ ውስጥ :- - ለጥያቄ መልስ ይገኛል:: - ከእርሱ ጋር ህብረት ማድረግ ይኖራል:: - እውነተኛ ፍቅር በተሞላን መጠንም እንዲሁ ጌታን ፈፅሞ መከተል ይሆንልናል::

View Details

እግዚአብሔርን በአንድ ላይ ስናመልክና ስናገለግል በመንፈሳዊ ህይወታችን ከሚያስፈልገን ነገር አንዱና ዋናው እርስ በእርስ መቀባበል ነው:: በዚህ መቀባበል ውስጥ አንዱ ለሌላው መንፈሳዊ በረከት ይሆናል:: ይህ እንዲሆን ደግሞ እይታን ማስተካከል የግድ ነው:: ይኸውም ሰውን በተላንትና ድካሙና ባልበቃበት በኩል ያለውን በመቁጠር ሳይሆን እግዚአብሔር እንደሚያይ አይቶ በመልቀቅ ነው:: ሰለዚህ ሌሎች በእኛ ህይወት ውስጥ መነፈሳዊ በረከት ሊሆኑን የሚችሉት እኛ የለቀቅናቸውን ያህል ነው:: እኛም ለሌሎች መንፈሳዊ በረከት መሆን የምንችለው እንዲሁ ሰዎች እኛን በለቀቁን መጠን ነው:: - አማኝ በውስጡ ያለው ፀጋ ጎልቶ እንዲወጣ እንዲጠቅምና ለበረከትም እንዲሆን ሊለቀቅ ያስፈልጋል::

View Details

አማኝ እግዚአብሔርን ለመምሰል ደግሞም እግዚአብሔርን እንደ ቃሉ ወደ ማወቅ ማንነት ያድግ ዘንድ የሚሰራበት መንገድ አንዱ የእግዚአብሔር መዘግየት ነው:: በእግዚአብሔር መዘግየት ውስጥ ትክክለኛው ማንነትችን ደግሞም ያለን መንፈሳዊ ደረጃና መረዳት ደገለጣል:: በእግዚአብሔር መዘግየት ውስጥ ትዕግስትንና ትህትናን ዝቅ ማለትን እንማራለን:: *** በእግዚአብሔር መዘግየት ውስጥ በምስጋና ሆነው በትዕግስት የሚጠብቁ እነርሱ በፀጋው ውስጥ ናቸው:: ነገር ግን ከምስጋና ርቀው በማጉረምረም ያሉ እነርሱ ከፀጋው የወጡ ናቸው::

View Details

ወደ ጌታ ፊት በእምነት ሰንቀርብ ለጥያቄአችን መልስ እንገኛለን:: መፅናናትና ፈውስም ይሆንልናል:: ጌታ የሚያደርገውን ያውቃል:: ደግሞም መቼና እንዴትም እንዲያደርግ አርሱ ያውቃል:: በእኛ ዘንድ ያለው ነገርና ሁኔታ የሚያደክም ደግሞም ተስፋ የሚያስቆርጥ ሊሆን ይችላል:: ነገርግን በእኛ ሰራ የጀመረ እርሱ እንዲፈፅመው የታመነ ነው:: በፊቱ በእምነት ልንሆን አጥብቀንም ልንፀልይ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው:: ጌታን ጠብቆ ያፈረ የከሰረም የለም:: ይልቁንም ከለመነውና ከተጠባበቀው በላይ ይሆንለታል እንጂ::

View Details

የመንፈሳዊ ህይወታችን የአድማስ ስፋት ሰውን ሁሉ በክርስቶስ ፍቅር የማየታችንና የመቀበላችን መጠን ህሊናችን ኀፁህ የሆነውን ያህል ነው:: ነፃ ባልወጣንበትና ባልተፈታንበት በዛ የክርስቶስ ህይወት ወደ ሌሎች አያልፍም:: በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ያዘንበት አልፎም የተጎዳንበት ህሊናችንም ያልነፃበት ጊዜዎች ሁኔታዎችና ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ:: ይሁን እንጀ በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር የተቀበልነው ፀጋ ይህን ሁሉ ልናልፍ በወጥመዱም እንዳንያዝ እንድናሸንፍ የሚያበቃ ፀጋ ነው:: - ህሊናው ንፁህ የሆነና የተፈታ እርሱ እጆቹን ወደ እግዚአብሔር ለማንሳት ደግሞም ለመፀለይና ለማምለክ ነፃ ነው::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.8:25-40 ክፍል 30

View Details

የሐዋርያት ሥራ.8:14-25 ክፍል 29

View Details

  1. ወደ ወጥመድ እንደገባን እንዴት ነው የምናውቀው? ለመውጣትስ ምን ማድረግ አለብን?
  2. በልምምድ ህይወትን መምራት ክስረት ነው ወይ?
  3. እኛ እውነት በመሰለን ነገር መንፈስ ቅዱስ አይወቅሰንም ወይ?
  4. በህይወታችን ያለውን አረም እንዴት ነው የምናስወግደው?

View Details

ሰው ትክክለኛ ማንነቱን ሊያይና ራሱን ሊያዋርድ የክርሽቶስን ህይወት እንዳይኖር መሰናክል የሆነውን በውስጡ ያለውን እርም ማስወገድ የሚችለው የእግዚአብሔር ብርሃን በበራለት መጠንና በብርሃኑ ውስጥ ራሱን ባየበት ልክ ነው:: ይህ ሲሆን ከማይበቃ ማንነታችን ውስጥ በእርሱ ፀጋ የሚበቃውን አዲሱ ማንነታችን ይወጣል:: አዲሱ ሰው የሚታዘዝ ነው:: አካሄዱ ከእግዚአብሔር ጋር ነውና:: የእርሱ ክብር ሞገስና በረከትም ያለው በመታዘዝ ውስጥ ነወ:: እንደ እግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው አዲሱ ሰው የጌታ ብርሃን የበራለት እርሱ ስጋን ይከለክላል:: ሰራውንና ሀሳቡን ይቃወማል:: የመግዛት ሀቅሙም የጨምራል:: በመከራ ውስጥም ለማለፍ በዚህም ውስጥ እንኳ ለመታዘዝ የሚበረታ ነው

View Details

የሐዋርያት ሥራ.8:14-25 ክፍል 28

View Details

የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰው ከመንገዱ ይመለስና ለፈጠረው አላማ ይኖር ዘንድ ደግሞም የይድን ዘነድ እንጂ ሰው ይጎዳ ደግሞም ይጠፋ ዘንድ ፈቃዱ አይደለም:: እኛ የእግዚአብሔር የባህርዩ ተካፋዮች ነንና ከእኛ ዘንድ አንድ ነገር ማየት ይፈልጋል:: ምህረት ማድረግን:: ከምህረት የጎደለ እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር መራመድ አይችልምና:: *** አካሔዳችንን መመርመር የየእለት ተግባራችን ሊሆን የተገባ ነው::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.8:14-25 ክፍል 27

View Details

  1. አንድ አገልጋይ ፀጋው እንዲለቀቅ በተገለጠበት ፀጋ ብቻ መወሰን የለበትም ማለት ነው?
  2. ከእግዚአብሔር የሚመጣውንና በአለመታዘዝ የሚመጣውን መከራ እንዴት እንለየዋለን?
  3. የወደቀውን ለማንሳት የደከመውን ለማበረታታት ምንድን ነው ማድረግ ያለብን?
  4. ራሳችንን ለማግኘት ምን እናድርግ?
  5. ከወጥመድ ለመውጣት ቃሉን ምንበብና መፀለይ አለብን ወይ?

View Details

በአማኝ ህይወት ውስጥ የእርሱ በረከት መጠኑና ስፋቱ ለሌሎች ለመሆን ለመትረፍ የመቻሉም ጥልቀቱ ያለው መታዘዙ ላይ ነው:: ሙሉ መታዘዝ:: ይኸውም ሰለ ጥቅም ወይም ከመታዘዛችን የተነሳ ስለምናገኘው ወይም ስለሚሆንልን የምንታዘዘው አይደለም:: ደግሞም ስለቀለለን የምንፈፅመው ስይሆን ነገረ ግን ራሳችንን ሰጥተነ የእግዚአብሔር ፈቃድና ሀሳብ በፀጋው በእኛ እንዲፈፀም የምንታዘዘው ነወ:: - መታዘዝ ዝቅ ማለት የእግዚአበሔር የአገዛዝ መዋቅር ነው:: ኢየሱስ እርሱ ከእግዚአበሔር ጋር እኩል ሥልጣንና ክብር ያለው ጌታ ሲሆን ሳለ ለአባቱ ያለው መታዘዝ የተገለጠው ራሱን ዝቅ በማድረግ ደገሞም እስከ መስቀል ሞት ድረስ በመታዘዝ ነው:: ውጤቱም እጅግ የከበረ ለሰው ሁሉ መዳን ምክንያት የሆነ ነው:: - በአማኝ ህይወት ውስጥ በረከት ፈውስና መፅናናት ወደ ህይወቱም ሆነ ለሌሎችም መትረፊያ መንገዱ በመታዘዙ ውስጥ ነው::

View Details

አማኝ በህይወት ጉዞው ውስጥ ፍፁም በእግዚአብሔር ሥልጣን ስር መሆኑና መገዛቱ የሚገለጠው በመታዘዝ ነው:: መታዘዝ በሌለበት ህይወት አያልፍም:: የጌታ ኢየሱስ ህይወት ወደ ሚያምኑት ሁሉ ያለፈው ከመታዘዙ የተነሳ ነው እስከ መስቀል ሞት የታዘዘ ሆኗል :: እግዚአብሔር የተናገረው የበረከት ቃሎች ወደ ህይወታችን የሚያልፈው እለት እለት በታዘዝንበት በኩል ነው:: በአለመታዘዝ ምክንያት ወደ ህይወታችን ከመፍሰስ የቆመውን በረከት በፆምና በፀሎት ማግኝት አንችልም:: የእኛን መታዘዝ የሚጠይቁ ናቸውና በአለመታዘዝ ምክንያት እስራኤል በምድረ በዳ እንደቀሩ ሁሉ እኛም በዚህ መንገድ እንዳንሄድ ህያው ቃሉ ይመክረናል:: - ለጌታ የመገዛታችን ፍሬ መታዘዛችን ነው::

View Details

በአማኝ የህይወት ጉዞ ውስጥ ብዙ መሰናከል ብዙ ወጥመድ ብዙ ፍርሀት አለ:: ነገር ግን ወደ ፊት ሂዱ ደግሞም ተሻገሩ ያለ ጌታ እርሱ የታመነ ነው:: ያሻግራል:: አላሳልፍ ያለ ማዕበል ጌታ ሲመጣበት ፀጥታ ይሆናል:: ከማዕበሉ በላይ የሆነው ጌታ ይራመድበታል:: እኛንም ያራምዳል:: - መሻገር አይቀርም ጌታ ከእኛ ጋር ስለሆነ:: ነገር ግን ለመሻገር መመሪያ መጠበቅ የግድ ነው:: በራሳችን እውቀትና መንገድ መሔድ ወደ ኪሳራ ያመራል:: - ለመሻገር መቀደስና ራስን ለፈቃዱ ማስገዛት ደግሞም በእምነት መሆን የስፈልገናል::

View Details

አማኝ ተስፋውን አፅንቶ እንዲይዝ ደግሞም በሰማው ህያው ቃል ላይ በእምነት መቆም ይሆንለት ዘንድ የመንፈሳዊ አይኖቹ መከፈት ዋና ነገር ነው:: መንፈሳዊ አይኖቻችን ሲያዙ:- - ኢየሱስን ከሙታን መንደር እንፈልገዋለን:: ህያውነቱ ይሰወርብናል:: - ከሰማነው ህያው ቃል እሩቅ እንሆናለን:: - በእምነት ሳይሆን ስጋዊ አይኖቻችንና እውቀታችን በሚመሩን ብቻ እንጓዛለን:: - ከአድናቆት ያለፈ ህይወት አይኖረንም:: - ተመራማሪ እንሆናለን:: አይንን የሚከፍት እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ነው:: ከእውነተኛው መአድ በመካፈልና በመመገብ አይን ይከፈታል:: ወደ እውቀት ወደ መረዳትም ያመጣናልና::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.8:14-25 ክፍል 26

View Details

የሐዋርያት ሥራ.8:9-13 ክፍል 25

View Details

የሐዋርያት ሥራ.8: 4-8 ክፍል 24

View Details

እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ወደ መንግስቱ እንድንገባ ብቃት ሆኖናል:: ደግሞም ወደዚህ ወደ ከበረው የዘላለም መንግስት መግባታችን በሙላት እንዲሆንም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው:: - ወደ እግዚአብሔር መንግስት የገባንና የከበረ ተስፋ ያለን አኛ ሁልጊዜ ልናስብና በተግባርም ልንኖርበት የሚገባን አራት ዋና ዋና ምክሮችን በዚህ ትምህርት በጥልቀት እንማራለን:- 1 - ከቅዱሳን ጋር ያለንን አንድነት በመጠበቅ ፀጋን መካፈል:: 2 - ወደ ኃላ የሚጎትተንን ሸክምና ኃጢአት በየእለቱ በማስወገድ መሄድ:: 3 - እግዚአብሔርን በመፍራትና በማክበር በፍቅር በፅደቅና በቅደስና በሰላምም መኖር:: 4 - ከስህተት ትምህርት መጠበቅ:: ከተቀበልነው የከበረ ተስፋና እውነት ከሚያወጣና ከሚያዝል ከሚያደክም ትምህርት መጠበቅ:: የዳንበትንና የተመሰረትንበትን የእግዚአብሔር ቃል እውነት ጠንቅቀን ልናውቅ የከበረውንም ተስፋ አጥብቀን ልንይዝ ያስፈልግል::

View Details

እግዚአብሔር በህይወታችን ላለው አላማ ስንኖርና ሰንጓዝ ጉዟችንን ለማሰናከል ሰይጣን ወጥመድ ማዘጋጀገቱ የማይቀር ነው:: ይህ የእርሱ የአለት ተእለት ተግባሩ ነውና: ለወጥመዱ የምንጋለጠው ወይም ምቹ የምንሆነው :- - ብዙ ተመክረን ወይም ተገስፀን አንመለስ በልንበት በዛ ወጥመድ አለ:: - በችኮላ ባለማስተዋል ዘለን የምንገባበት ሁኔታ ለወጥመዱ ምቹ ነው:: - ያለ ንፅህናና ያለ ቅድስና ያለ እውነትና ያለ እምነት ባልሆንበት:: - ጌታን በርቀት መከተል እንዲሁም የማይገባ ክብርና ዝና ወደ ወጥመዱ ስበው ይከቱናል:: በህይወት ጉዟችን ከክፉው ወጥመድ የምንሰወረው ወይም የምናመልጠው :- - እግዚአብሔርን መፍራት ዋናው ከወጥመዱ ማምለጫ ነው:: - ለመንፈስ ቅዱስ ምቹ በሆንበት - ቅድስናና ፅድቅ በመረጥን ጊዜ አንዲሁም የቃሉን እውነት ትህትናን እና አውነትን...ወዘተ በመረጥን ጊዜ ወጥመዱን እናመልጣለን::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.8:1-3 ክፍል 23

View Details

በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህ አለም ከተያዝንበት ከጨለማው አሰራርና ከኃጢአት ከዘላለምም ፍርድ አምልጠን ወደ መንግስቱ ሲያፈልሰን በሚመጣው አለም ብቻ ሳይሆን ዛሬም በዚህ ምድር በሙላት ልንኖር የአግዚአብሔር ፈቃድ ነው:: በተሰጠን ማመስገንና መርካት ቀዳሚ ሲሆን ሌላው ደግሞ ፈፅመን ለጌታ ያላስገዛነውን ወይንም ያላስወረስነውን ማንነታችንን ልናይና ሙሉ በሙሉ ለእርሱ ልናስገዛ ይፈልጋል:: በጥቂቱ መታመን የበለጠውን ለመቀበል የመዘጋጀት ምልክት ነው:: የጌታም ፈቃድ ባለን ታምነን ሰለ ጥቂቱ እንድናመሰግን ነው:: እርሱ በጥቂቱ የታመነውነ በብዙ ይባርካልና::

View Details

እግዚአብሔር ለዘላለም አይቆጣም እንደገና ይመለሳል:: ምህረትንም ያደርጋል:: ይፈውሳል ተስፋንም ያድሳል:: የረዘመች ተስፋ ነፍስን ታዝላለች እንደሚል ነፍሳችን ዝላ ተስፋ እንዳንቆርጥ የእግዚአብሔርን ባህርይ ማሰብ ይጠቅማል:: መሀሪነቱን ደግሞም የመመለስ የመፈወስና የመጎብኘት ጊዜ እንዳለው:: ይህን ማሰብ ሀይልና ብርታት ይሆንልናል:: - እርሱን በመምረጥ በትህትና ከልብ በመመለስ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከህዝቡ ፊት እንባን ማበሱ አይቀርም:: - አንዳንድ ነገሮች በጣም የሚያስጨንቁ ነፈስንም የሚያዝሉ እስከመቼ የሚያስብሉ ይሆናሉ:: ነገር ግን ነውጡ ባየለ ጊዜ አዲስ ነገርን ሊያስከትል የእግዚአብሔርም ክንድ የሚገለጥበት ይሆናል::

View Details

አማኝ ሁሉ በዚህ አለም ሲኖር መከራ አለበት:: ይሁን እንጂ በመለኮት ጥበቃ ውስጥ ሆኖ ነው:: የሚያፀናችሁ ከክፉም የሚጠብቃችሁ የታመነ ነው ተብሎ እንደተፃፈ እግዚአብሔር ህዝቡን በታማኝነት ይጠብቃል:: ደግሞም ይጠነቀቃል:: ክፉው የመለኮትን ጥበቃ አልፎ በእኛ ላይ ምንም ማድረግ ስለማይችል ክፉ መሻትን ወደ እኛ ውሰጥ በመወርወር በራሳችን ክፉ መሻት በመታለል እኛው ራሳችን በኃጢአት እንድንጠላለፍ ያደረጋል:: ያን ጊዜ በሁከት እንሞላለን ለወጥመዱም የተመቸን እንሆናለን:: እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የሆነ አማኝ እርሱ በፈተና ውስጥ ቢያልፍ እንኳ በሰላም የተሞላ ነው:: የመለኮት ጥበቃ ከበራለት በላይ ጠላትንና አሠራሩን አቅልሎ የሚያይ የለም::

View Details

እግዚአብሔር አርሱ ቸር አምለክ ነው:: ቸርነቱም በረከት በመስጠት ይገለጣል:: የአማኝ በረከትም እግዚአብሔር እርሱ በሆነለት ነው:: እግዚአብሔር ሆነልን ማለት: እርሱ ሰላማችን ይሆናል ሀብትና እውቀታችንም ይሆናል ሀይልና ጉልበት ብርታታችንም የሆናል:: ሰለዚህ ለአማኝ በረከት ባከማቸው ሀብትና ባለው እውቀት ደግሞም በራሱ ትጋትና ሩጫ አይደለም ነገር ግን ለእርሱ ከሆነለት ከእግዚአብሔር ነው እነጂ:: የአማኝ በረከት እግዚአብሔር ባለው ውስጥ ደግሞም ከእርሱ በሆነው ነው::

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ማቴ 26፡36 እነርሱ ቢተጉ ኖሮ ይሆን የነበረው ምንድን ነው? ነገሮች ይለወጡ ነበር? 2. እርግማን ከደኅንነታችን ጋር የተያያዘ ነው ወይስ ከበሽታችን ጋር ነው የሚያያዘው? 3. እኛ የጌታ ሆነን ልጆቻችን ሳይሆኑ መርገም ያገኛቸዋል ወይ? 4. 1ቆሮ 5፡5 “ሥጋውብ ለጠላት ይሰጥ” ሲል ምን ማለት ነው? ይህ መርገም ነው ወይ? 5. ዘፍ 12፡2 አብርሃም በረከት ለማግኘት ያደረገው የራሱ አስተዋፅኦ አለ ወይ? 6. የተሻረው እና ያልተሻረው ሕግ የትያው ነው? 7. ዘፍ 39፡5 ይህ በረከት እኛ በምንሠራበት ቦት ለሰዎች ይደርሳል ወይስ ለዮሴፍ ብቻ ነው? 8. ከእግዚአብሔር ውጭ የምናስበውን ጠላት ይጠቀምበታል የሚለው ምን ማለት ነው?

View Details

የሐዋርያት ሥራ.7: 47-60 ክፍል 22

View Details

1.በጊዜ አገልግሎታችንን ካላደረግን ችግር አለው ወይ? 2. በአዕምሮ ላይ ያለው መንፈሳዊ ተፀዕኖ ምንድን ነው? 3.የጠላት መጠቀሚያ ላለመሆን ምን እናድርግ?

View Details

የሐዋርያት ሥራ.6:8-15 ክፍል 20

View Details

በረከት ማለት ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶ በሰው ህይወት ኑሮና ዘር ላይ የሚገለጥ የእርሱ ቸርነት ነው:: ይህ የእግዚአብሔር ቸርነት በተስፋ ቃልና እንዲሁም ደግሞ አካሔዱን ከእርሱ ጋር ያደረገውን ሰው በመባረክ ይገለጣል:: በክርስቶስ አምኖ የዳነ ሰው በአንድም ወይም በሌላ ከራሱ ድካም ኃጢአትና በደል የተነሳ ሊፈተንና ተፅእኖ ውስጥ ሊገባ ቀንበርም ሊሆንበት ይችላል:: ነገር ግን እርግማን በአማኝ ላይ ፈፅሞ አይሰራም ደግሞም አይከተለውም:: ይልቁንም አማኝ ሊባርክ ተጠርቷል:: በረከት በክርስቶስ ኢየሱስ በአማኝ ራስ ላይ ነውና::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.7 :1-8 ክፍል 21

View Details

እግዚአብሔርን ጠብቆ የከሰረ ወይም ያፈረ ማንም የለም:: ነገር ግን የጌታ መምጫው በእኛ ሰአትና ፍላጎት ሳይሆን በራሱ ጊዜና ሰአት በወደደው ሁኔታ ነው:: በመጠበቅ ውስጥ ብዙ ፈተና ደግሞም የጠላት ውጊያ አለ:: በስፍራችን ሆነን እንዳንገኝ የሚዋጋ ጠላት:: ይሁን እንጂ ፀጋን የሚሰጥ ጌታ እርሱ የታመነ ነው:: እግዚአብሔር ባስቀመጠን ሰፍራ መገኘት በዛም ቆይቶ መጠበቅ ደግሞም ልንፈፅምና ልናከናውን የሚገባንን የእርሱን ፈቃድ በመፈፀም መገኘት ያስፈልጋል:: ዋጋችን በታመነው ጌታ እጅ ነው::

View Details

በዚህ ምድር ያለ ባለጠግነት የሚሰፈር የሚወሰንና የሚወሰድ ደግሞም በጊዜ ወስጥ የሚጎድል ወይም የሚጠፋ ነው:: በእኛ ዘንድ ያለው ክርስቶስ ግን የማይወሰንና የማይጎድል ሰማያዊ ክብር ያለው ባለጠግነት ነው:: ይህ ባለጠግነት ሰው በራሱ ጥረትና ግረት የሚያገኘው ሳይሆን በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ ፀጋ ነው:: ይህም ፀጋ በሚያስፈልገን ጊዜ የሚረዳን ነው:: በሀዘን ጊዜ መፅናናት በድካም ጊዜ ሀይልና ብርታት ጉልበትም ይሆናል:: አማኝ ከፀጋው የተነሳ በቅድስናና በፅድቅ ሊኖር በመከራ ሊፀና ደግሞም በምህረትና በይቅርታ ሊመላለስ ሀይል ይሆንለታል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.6:1-7 ክፍል 19

View Details

እግዚአብሔር ሰውን ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃኑ ወደ ልጅነት ያመጣው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱና በትንሳኤው ነው:: ይህም የዘላለም ተስፋ አስተማማኝነቱ በራሱ ችሎት የተሰራ በመሆኑ ነው:: እውነተኛ መንፈሳዊ ህይወት እግዚአብሔር ወዳቀደልን ልጁን ወደ መምሰል እንድናድግና በምድርም ላይ የእርሱ ምስክር እንድንሆን የምንኖረው እንጂ በዚህ አለም ማትረፊያ እንዲሆነን አይደለም:: - የተቀበልነው አዲሱ ህይወት በአለም ካለው ክፋት ጋር መደበላለቅንና አብር መቆምን አይፈቅድም::ይልቁንም በጨለማው ላይ የጽድቅና የእውነት ብርሃን እያበራን የምንኖርበት ህይወት ነው:: - ህይወቱ በትጋት ደግሞም በፀጋው ችሎት የሆነ አማኝ ፍፃሜው የዘላለም መንግስት በክብር መሆን ነው:: ይህ ፍፃሜ ደግሞ አስተማማኝ ተስፋ ያለው ነው:: ሰለዚህ ከፊት ይልቅ አብልጠን እንትጋ:: ተስፋን የሰጠ እርሱ የታመነ ነው::

View Details

በኢየሱስ ክርስቶስ በማዳኑና በፀጋው የተካፈልነው ህይወትና ኑሮ ታላቅ ብድራት ያለው በእውነትና በፅድቅ ደግሞም በጥንቃቄ ልንኖረው ልንጠብቀውም የሚገባ ነው:: በክርስትና እምነት ውስጥ ካሉት ታላላቅ እውነቶች አምስቱን በዚህ ትምህርት እንማራለን:-- - መዳናችን እጅግ ታላቅ ነው:: ከሞት ወደ ህይወት ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የመጣንበት:: - የጌታ እረኝነት:: ነፍሱን ሰለ በጎቹ አሳልፎ የሰጠ መልከምና ታላቅ እረኛ:: - የጌታ የሊቀ ካህንነት ሥራ:: ፍፁም የሆነ የዘላለም ሊቀካህን:: - ታላቅ ብድራት:: ጌታን በማመን የምናገኘው ብድራት እጅግ ታላቅ ነው:: - ታላቅ መጋደል:: በነፃ የተቀበልነው የክርስትና ህይወት ታላቅ መጋደል ያለበት መፅናትንም የሚጠይቅ ነው:: ክርስቶስ የሰራውና እኛም የእርሱ የሆንበት ነገረ እጅግ ታላቅ ነውና ከዚህ ሌላ ተመክህት አይኖረንም:: ሰለዚህ ትምክህታችንን አንጥልም ብድራቱ እጅግ የላቀ ነውና::

View Details

በማንኛውም ሰአትና ቦታ የምንናገረውንና የምናደርገውን ካልተጠነቀቅንና በእምነትና በፀሎት ከእውቀትና እንደ እግዚአብሔር ቃል ካልሆነ ለጠላት ፍለፃውን መወርወሪያ ምክንያት ለውጊያውም ሜዳ ያገኛል:: *** ከእኛው ወጥቶ እኛን ራሳችንን የሚዋጋበት መንፈሳዊ ጦርነት :-- -- እንደበራልን ካልተናገርን -- በመንፈስ ቅዱስ ካልተከለልንበት -- በመሰለን ከጌታ ቃል ያልሆነ በተናገርንበት -- መራራነት ተሞልተን በተናገርንበት -- ከፀሎት በፊት የፍርድ ቃል በተናገርንበት -- ተቃራኒ ነገርን ባሰብንበት እና ልባችንን ባጠነከርንበትና ሌሎችም... በዚህ ትምህርት በጥልቀት አንማራለን:: በምንሰማውና በምናየው ነገር በመጀመሪያ በውስጣችን ብቅ የሚለው እርሱ የእኛነታችን ትክክለኛው መገለጫ ነው:: በመጀመሪያ በውሰጣችን ሊከብድ የሚገባው ምህረት ነው:: ይቅርታና ሰላም ያለበት ፍቅርና በጎነት ያለበት ነው:: ከእነዚህ ተቃራኒ ከሆነ ጠላት የሚጠቀምበት ሰለሆነ ልነጠነቀቅ ይገባል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.5 :12-42 ክፍል 18

View Details

የሐዋርያት ሥራ.4:32-37 ክፍል 16

View Details

የሐዋርያት ሥራ.5 :1-16 ክፍል 17

View Details

ሰው እግዚአብሔርን በፅድቅና በቅድስና እንደ ቃሉ የሆነ ህይወት አእንዳይኖር ለማሰናከል በአምላኩም ላይ እንዲበድል ዘወትር ያለ እረፍት የሚተጋ ጠላት አለበት:: አርሱም የፅድቅ ጠላት አሳች የተባለው ሰይጣን ነው: አማኝ ዘወትር ራሱን በጌታ ውስጥ እንደሆነ እርግጠኛ ሊሆን ይገባል:: ሰይጣን እኛን ለማሳት ለመዋጋት በርና እድል ፈንታ የሚያገኘው ራሳችንን በጌታ ውስጥ ሆነን ባልተገዛንበት በኩል ነውና:: አማኝ በእግዚአብሔር ቃል አዕምሮው ካልተቀደሰና ነፃ ካልወጣ በመንፈስ ቅዱስም ህይወቱ ካልተያዘ ለሰይጣን ፍላፃና ለስህተት አሰራሩ የተጋለጠ ይሆናል:: *** ክፉው እኛን የሚፈትንባቸውና የሚዋጋባቸው መንገዶች:- - እግዚአብሔርን በምንበድልበት በኩል - በምንታበይበትና በምንዳፈርበት በኩል - በምንፈራበትና በምንሰጋበት በኩል - ቃሉን ባዛባንበትና በእምነት ባልቆምንበት በኩል ... ወዘተ ነው:: ሰለዚህ እግዚአብሔርን በመፍራት በፀጋው ችሎት ችግራችንን ማወቅና ባወቅነው ችግርም ላይ እርምጃ ልንወስድ ይገባል::

View Details

ካሌብ በእግዚአብሔር ላይ ፍፁም የሚደገፍ ራሱንና አካባቢውን ወይም ሁኔታን ሳይሆን የተደገፈውን የእግዚአብሔርን ብርቱ ክንድ ብቻ የሚያይ ሰው ነው:: ስለዚህም ከስለላ መልስ በከተማይቱ ውስጥ ካያቸው ረጃጅምና ሀያላን ሰዎች ይልቅ በህዝቡ ሁሉ ፊት ታላቅና የሀያላን ሀያል የሆነውን አግዚአብሔርን ሲያውጅ እናያለን:: የምናልፍበት ሁኔታ የሚያደክመን የያዝነውን ተስፋ ሊያስለቅቀን የሚታገል ቢሆን እንኳ በእምነት ፀንተን ተስፋችንን መያዝ ደግሞም አለመናወጥ የምንችለው ብርቱ የሆነውን ጌታ በማየትና ታላቅነቱንም በሚያስጨንቀን ሁሉ ላይ በማወጅ ነው:: እግዚአብሔር በልጁ ወደ ገለጠልን ሙሉ በረከት እንገባ ዘንድ መነገዱ ይኸው ነው:: በነገር ሁሉ ውስጥ ጌታን ማየት በፍፁም ልብም እርሱን መከተል:: ብንደክምም እርሱ ሀይልና ብርታት ይሆንልናል:

View Details

ሰው እግዚአብሔርን በፅድቅና በቅድስና እንደ ቃሉ የሆነ ህይወት አእንዳይኖር ለማሰናከል በአምላኩም ላይ እንዲበድል ዘወትር ያለ እረፍት የሚተጋ ጠላት አለበት:: አርሱም የፅድቅ ጠላት አሳች የተባለው ሰይጣን ነው: አማኝ ዘወትር ራሱን በጌታ ውስጥ እንደሆነ እርግጠኛ ሊሆን ይገባል:: ሰይጣን እኛን ለማሳት ለመዋጋት በርና እድል ፈንታ የሚያገኘው ራሳችንን በጌታ ውስጥ ሆነን ባልተገዛንበት በኩል ነውና:: አማኝ በእግዚአብሔር ቃል አዕምሮው ካልተቀደሰና ነፃ ካልወጣ በመንፈስ ቅዱስም ህይወቱ ካልተያዘ ለሰይጣን ፍላፃና ለስህተት አሰራሩ የተጋለጠ ይሆናል:: *** ክፉው እኛን የሚፈትንባቸውና የሚዋጋባቸው መንገዶች:- - እግዚአብሔርን በምንበድልበት በኩል - በምንታበይበትና በምንዳፈርበት በኩል - በምንፈራበትና በምንሰጋበት በኩል - ቃሉን ባዛባንበትና በእምነት ባልቆምንበት በኩል ... ወዘተ ነው:: ሰለዚህ እግዚአብሔርን በመፍራት በፀጋው ችሎት ችግራችንን ማወቅና ባወቅነው ችግርም ላይ እርምጃ ልንወስድ ይገባል::

View Details

መነፈሳዊ ጦርነት ሰይጣን ወደ አማኝ ህይወት ኑሮና ማንነት ከሚልከውና ሊፈፅም ከሚፈልገው ክፉ ስራው ጋር መጋጠም ነው:: ሰይጣን ክፉ የሆነ ስራውን አላማውን ለመፈፀም ለማሳካት የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀማል:: በሚያሰፈራና በሚያስጨንቅ ሁኔታ ወይም ደግሞ መልካም በሚመስል በሚሸነግል ማታለያ መንገድ ይመጣል:: የሰይጣን የመጀመሪያውና ዋናው ውጊያው ከህልውናችን ጋር ነው:: ለሰይጣን ትልቁ ችግር የክርስቲያን መኖር ሰለሆነ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ አማኝን ማጥፋት ተቀዳሚ አላማው ነው:: አማኝ መንፈሳዊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ጌታ እነደሚጠቀምበት ስጋዊ በሆንን ጊዜ ደግሞ ለሰይጣን ክፉ ሀሳብ መጠቀሚያ እንሆናለን:: የእግዚአብሔር ቃል እነደሚመክረን በአዕምሮአችን መታደስ ልንቀደስ ደግሞም ዘወትር መንፈሳዊ ልንሆን ዋናና አስፈላጊ ጉዳይ ነው::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.4:23-31 ክፍል 15

View Details

በየትኛውም ዘመንና ጊዜ የሰይጣን ተቀዳሚ አላማ እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔር የሆነውን መተካት ነው:: ይህን ለማድረግ ደግሞ እጅግ ረቂቅ ደግሞም የተገለጡ ዘዴዷዎችን ይጠቀማል:: ይህን አሰራሩን ደግሞ የተቀበሉ እነርሱ የክፋቱ መጠቀሚየ ይሆናሉ:: የክፋት የረኩሰትና የሀሰት ምንጭ እርሱ ነው::ሰለዚህ አማኝን ማርከስ በክፋት መሙላት አመፀኛ ማድረግ ወዘተ ... የዘወትር ተግባሩ ነው:: ወደ እግዚአብሔር ያልተጠጋ በፀሎትም ያልተከደነ ለክፋቱ የተጋለጠ ይሆናል:: ሰይጣን እኛን በቀጥታ ማግኘት አይችልም:: የምናመልከው ጌታ ታማኝ ነውና ከጥበቃው አልፎ ወደ እኛ የሚመጣ ሊኖር አይችልም:: ነገር ግን ወደ ስጋዊነት ባመዘንንና ከፀሎትና ከቃሉ በራቅን ጊዜ ለሰይጣነ ጥቃት የተጋለጥን እንሆናለን:: ለአማኝ እግዚአብሔርን መፍራት ዋናው ከክፉ ሁሉ መጠበቂያው ነው::

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ለወንጌል ዋጋ መክፈል የምንችለው እንዴት ነው? 2. የሚመጡትን መልዕክቶችና የጌታን ድምጽ የምንለየው እንዴት ነው? 3. ወንጌልን ተቀብለን ለምን እንለወጥም? ከዚህስ ነገር እንዴት ነው የምንወጣው? 4. የጌታን ትእዛዝ እና አብሮነት እንዴት ነው የምናውቀው?

View Details

እግዚአብሔር ድንቅ መካር ነው:: የእግዚአብሔር ምክር ባለበት ህይወታችን የተጠበቀ ነው:: ከክፉውም የምንሰወረው ምክሩ ባለበት ነው:: ይሁን እንጂ ከዚህ ድንቅ መካር ጋር የሚያጋጥመን የሚያስማማን ደግሞም ተጠቃሚ የሚያደርገን ግን ተመካሪ ልብ ካለን ብቻ ነው:: *** መመከር ባላየነውና ባልጠበቅነው በኩል ያለውን እይታ እውቀት የምናገኝበት እድል ነው:: ደግሞም በመመከር ቤትን ለማቆም ከጉዳት ለመታደግ ከዚህ አልፎ ለሀገር ለህዝብ መትረፊያ ይሆናል::

View Details

የእግዚአብሔር ቃል ፀንታችሁ ቁሙ እንደሚል መቆም ማለት በጌታ ሆኖ እግዚአብሔርን የእኛ ማድረግ ማለት ነው:: ጌታን ደግሞ የእኛ ማድረግ ማለት በህይወታችን ሁሉ በመባትና በመውጣት ሁሉን በፀጋው ችሎት ማለፍ ማለት:: በመንፈሳዊ ጦርነት አንዱ ጠለትን ድል መንሻ መቆም ነው:: በሰላም ወንጌል ተጫምታችሁ ቁሙ ተብሎ እንደተፃፈ:: በእለት ተእለት ህይወታችን የምናልፍባቸው የተለያዩ ችግሮች ይኖራሉ:: ይሁን እንጂ እኛ የምንጠነክርባቸው በጌታ ሆነን የምንገለጥበት በእርሱ በፀጋው ችሎት መደገፋችን ::የሚታይበትነው::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.4:13-21 ክፍል 14

View Details

የእግዚአብሔር ድምፅ ህይወት ነው:: የሚቀድስ የሚያጠራ ደግሞም የሚፈውስ ድምፅ:: ብዙ ግራ የሚያጋቡ የሚያውኩና የሚያስቱ ድምፆች እጅግ በበዙበት በዚህ ዘመን የጠራውን የጌታን ድምፅ ማግኘት መስማትም ዋና ነገር ነው:: እግዚአብሔር በአንድም በሌላ ነገር ይናገራል::የተናገረውም ደግሞ ይሆናል:: የሚከለክልም የለም:: ጌታ በእኛ ሁኔታ ሲናገር ምንም እንኳ በብዙ ፈተና ውስጥ ብንሆንም እንኳ ድምፁ ለህይወት ለፈውስና ለበረከት ነፃ ለማውጣት ይመጣል::

View Details

እግዚአብሔር ሂድ ውጣ አድርግም ብሎ በተናገረን ማንኛውም ነገር ስንታዘዝ ስንዘረጋ እርሱ ቀድሞ ከፊት ነው:: ጨለማ ነው ተራራ ነው ባልነው እርሱ ይቀድማል:: ብርሃንና ደልዳላም ይሆናል:: የማይቻለውን እንዲቻል የማይሆነውን እንዲሆን ያደርጋል:: ከፊት ወጥቷልና:: የእግዚአብሔር ምክር ባለበት እርሱ ቀዳሚ ነው:: ጌታ ደቀመዛሙርቱን ወደ ማዶ ተሻገሩ ብሎ ሲልካቸው እርሱ ቀድሞ እንደተገኘ:: እግዚአብሔር ሲቀድም እርሱ ከኃላም ነው::

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ወንጌልን ለስዎች እንዴት ነው ማድረስ የምንችለው? 2. በቅዱሳን ላይ ሽንፈት የሚመጣው ለምንድን ነው? 3. ወንጌልን ለመናገር ብዙ የቃሉ ሙላት ያስፈልጋል ወይ? 4. አማኝ በእድል መደገፍ ይችላል ወይ? 5. ፀጋ ተቀብለን ለሌሎች የምንሆነውና የማንሆነው እንዴት ነው?

View Details

የሐዋርያት ሥራ.4:1-12 ክፍል 13

View Details

የሐዋርያት ሥራ.3:11-26 ክፍል 12

View Details

የእግዚአብሔር ህዝብ የእግዚአብሔር ምስክር ነው:: ማዳኑን ታላቅነቱንና ድንቅ ስራውን የሚመሰክር:: እግዚአብሔር እስራኤልን በድንቅና በተአምራት ከባርነት ነፃ ሲያወጣ የእስራኤል አምላክ ተብሎ ታላቅ ስሙ በህዝቡ ላይ ተጠርቷል:: በዚህ አለም የመኖራችን አንዱና ዋናው ምክንያት ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃኑ የጠራንን የማዳኑንም ሥራ ልንናገር በቃልና በሰራ ምስክር ልንሆን ነው:: ለዚህም የሚሆን የሚረዳ የሚያግዝ የእግዚአብሔር ፀጋ አለ::

View Details

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ልጆች ላደረገን ለአኛ እግዚአብሔር ያወረሰን ርስት እርሱን ራሱን ነው:: ይኸውም የክብር ሙላት ያለው ጌታ ፀጋንና እውነትን ተሞልቶ በእኛ ማደሩ ነው:: አይኖቻችን ተከፍተው ያለን ርስት ክብሩና ታላቅነቱ ምን ያህል እንደሆነ ልናይ ያስፈልጋል:: ሐዋርያውም ሰለዚሁ ጉዳይ ነው እፀልይላችኃለሁ ያለው:: የክብር ተስፋ ያለው ጌታ ከእርሱ ጋር እንደሆነ አይኖቹ ተከፍተው ያየና የተረዳ አማኝ እርሱ በሚሞት ስጋ ውስጥ ቢሆንም ነገር ግን በሞት ላይ አሸናፊ ካደረገው ጌታ የተነሳ ከሞት ባሻገር ክብር በሞላበት የዘላለም መንግስት በክብር እንዲኖር ይረዳል:: ደግሞም በብዙ ችግርና ፈተና ውስጥ ቢያልፍም እንኳ ታላቅ ሰላምና ደስታን የተሞላ የእውነትም አገልጋይ የሆናል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.3:1-16 ክፍል 11

View Details

እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰራውና የገለጠው መዳን እጅግ ታላቅ ነው:: ሰው በራሱ ጥረትና ድካም የሚያገኘው ሳይሆን እንዲሁ በፀጋው በነፃ የሚቀበለውና የሚቀደስበት የሚኖርበትም ድንቅ ስጦታ ነው:: የአማኝ ድፍረት በመስቀሉ ላይ የተሰራው የደህንነት ሥራ ነው:: ከሞት ወደ ህይወት ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የመጣበት ደግሞም በእግዚአብሔር ፊት ያለነውርና ያለነቀፋ ሊቆም የቻለበት:: ይህ ታላቅ መዳን አለንና ሁልጊዜ ራሳችንን ከአለም እድፍ እየጠበቅን በእርሱ ላይ ያለንን ድፍረት ሳንጥል በፊቱ በእምነት ፀንተን ልንቆም የተገባ ነው::

View Details

እግዚአብሔር እንደ ተስፋ ቃሉ እንደተናገረውም ነው:: ይሁን እንጂ አማኝ ብቻውን እእደሆነና ችግሩና እርሱ ብቻ የተፋጠጡ ተስፋ የሰጠውም ጌታ በአጠገቡ እንደሌለ እስኪሰማው ድረስ በታላቅ ፈተና ውስጥ አንዳንድጊዜ ሊያልፍ ይችላል:: ጌታ ደቀመዛሙርትን ወደ ማዶ እንዲሻገሩ ግድ ካለቸው በኃላ ራሳቸውን በታላቅ ማዕበል ውስጥ እንዳገኙት:: ይህ አይነቱ ጉዞ ጌታን ካወቅነው በላይ የምናውቅበት ደግሞም የሚያፀናና ወደ እምነት ከፍታ የሚያወጣንን ድመፅ የምንሰማበት የህይወት ጉዞ ነው:: እግዚአብሔር የተናገረን ይሆናል:: ጊዜውን የሚያውቅ እርሱ ነው ደግሞም በራሱ መንገድ ይመጣል:: እኛም እንደተናገረ አንዲሁ እንጠብቀው::

View Details

እግዚአብሔር ለላቀ ክብር የለያቸው ሌዋውያን በምድረ ርስት የተካፈሉት ርስታችን የሚሉት መሬት አልነበረም:: እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ርስታችሁ እኔ ነኝ::ብሏቸዋልና ለጌታ ለመሆን ከወሰንበት ቀንና ሰአት ጀምሮ የእኛ እድል ፈንታ ርስታችን አርሱ ራሱ ጌታ ነው:: በዚህ ምድር ተስፋ የምናደርገውና የምንናፍቀው ነገር የለንም:: ይሁን እንጂ ይሄና ያ ጎደለብኝ ብለን የምናማርር የምናንጎራጉርም ከሆነ የርስታችንን ክብርና ታላቅነት አጥርተን እንዳላየን ያመለክታል:: አማኝ በዚህ ምድር እንደ መፃተኛ ሊኖር ደግሞም ተስፋው የከበና የታመነ እንደሆነ በቃልና በኑሮ እየመሰከረ ሊኖር የተገባ ነው::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.2:43-47 ክፍል 10

View Details

እግዚአብሔር ይናገራል:: መናገር አንዱ ባህርይው ነውና:: ነገር ግን ሲናገር በራሱ መንገድ ደግሞም በወደደው መንገድ ነው:: ምናልባት የምናልፍበትንና ጌታ እንደተናገረን ራሳችንን በእግዚአብሔር ፀጋ ውስጥ ስናይ ፈፅሞ የማይገጣጠም ነገር ሊሆን ይችላል:: ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የተናገረውን በህይወት ሒደት ውስጥ ይፈፅማል:: *** እግዚአብሔር የተናገረውን ለመፈፀም የኛን አብሮ መራመድና በእርሱ መደገፋችንን ይፈልጋል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.2:14-28 ክፍል 8

View Details

የዛሬ ጥያቄዎች 1. ቅባት ምንድን ነው? በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ እና ሙላት ምን ማለት ነው? 2. ቤተ ክርስትያን የጌታ መንግሥት መገለጫ ናትን? 3. በጌታ ኢየሱስ ስም መጠመቅ ምን ማለት ነው? 4. በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት እንዴት ነው መጸለይ ያልብን?

View Details

የሐዋርያት ሥራ.2:33-47 ክፍል 9

View Details

አማኝ በዚህ ምድር ሲኖር የሚኖርለት ምክንያት አለው:: በሚገባን ደግሞም በማይገባን ሁኔተ እግዚአብሔር ወዳየልን ልናከናውን ራሱንም በእኛ ሁኔታ ሊገልጥ ወደ ወደደው ወደ ተጠራንበት ሊያደርሰን ወደመሆንም ያመጣናል:: የምናልፍበት ሁኔታ እኛ ያለመረጥነው ደግሞም ያልተጠባበቅነው ሊሆን ይችላል:: ይሁን እንጂ ሀጢአትና አመፅ የሌለበት እርሱ እኛ የምንሰራበት ወደ ፈቃዱና ሀሳቡ ለመድረስ የምነጓዘበት ነው::

View Details

ሰው ኃጢአተኛና ከእግዚአብሔር ክብር የጎደለ ከመሆኑ የተነሳ በራሱ መልካም መሆንና ጽድቅንም መፈፀም አይችልም:: ሰለዚህ የሆነውና እያደረግንም ያለው በጎና መልካም ነገር ሁሉ ሁኑ ካለን ደግሞም እንደፈቃዱ እንድንሆን የሚረዳንን ፀጋ ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው:: ጌታ የበዛውን ኃጢአትና ድካማቸንን አልፎ ነው የረዳን ነፃ ያወጣን:: አግዚአብሔር በእኛም ህይወት ይህንን ለሌሎች መሆንን መድረስን ማየት ይፈልጋል:: ከእግዚአብሔር የተቀበልነው ደግሞም ወደ ፊቱ በቀረብን ጊዜ ሁሉ የሚሰጠን ፀጋ የልጁን መልክ እንድንመስል የሚያሰችል ፀጋ ነው::

View Details

መለኮታዊው ነገር ከላይ የሆነ ደግሞም መንፈሳዊ ከመሆኑ የተነሳ የሰው አውቀት ሊደርስበት አይችልም:: በቀላሉም ሊረዳውና ሊቀበለው የማይቻለው እውነት ነው:: ሰለዚህ የአማኝ መንፈሳዊ ከፍታ ኢየሱስን ያወቀውንና ለቃሉም በእምነት የታዘዘውን ያክል ነው:: *** እግዚአብሔርን ደግሞም የቃሉን እውነት ሰምተው ለሚያምኑትና ለሚታዘዙት ለእነርሱ ወደ ፊት የሚራመዱበት ጉልበት ያገኛሉ:: ለሌሎችም በረከት ይሆናሉ::

View Details

የዛሬው ጥያቄዎች 1. ስለምንወስደው ዕብስትና ፅዋ (የጌታ ሥጋና ደም) 2.የክርስቶስ ደም ለእኛ የሠራው ሥራ 3.እየሱስ ሕዝቡን በደሙ መቀደሱና በበር ውጭ መከራን ስለመቀበሉ

View Details

የሐዋርያት ሥራ.2:1-21 ክፍል 7

View Details

የመጀመሪያው የወንጌል መልዕክት ለእግዚአብሔር መኖር ነው:: እስራኤል ከግብፅ ሲወጣ እግዚአብሔርን ሊያመልክና ለእርሱ ሊኖርም እነደሆነ ሁሉ ሰው በክርስቶስ በማመን ከአለም ሲወጣ በፀጋው ለጌታ እንዲኖር ነው:: እግዚአብሔር በምህረቱ ባለጠጋ ስለሆነ ከሰው ጋር ይኖራል:: ሰው ደግሞ በፀገው ወደ እግዚአበሔር የሚቀርብ ሆነ::: ይህም ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ተከናውኗል:: እግዚአብሔር በምህረቱ በክርስቶስ ወደ እኛ መጥቷል:: ፅድቅና በጎነት የሌለን እኛ ደግሞ በክርስቶስ በፀጋው ወደ እግዚአብሔር ቀርበናል:: አማኝ ሁሉ ይህ የወንጌል ዕውቀት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ደግሞ ሁልጊዜ የሚያነቃቃና ስላልዳኑት የምስክርነት ትጋት የሚሰጠን የዚህ የወንጌል መንፈስ ሊኖረን ይገባል::

View Details

ከሰው በህርይ አንዱ ዛሬ ላይ ቆሞ ሰለ ነገ ማሰብና መጨነቅ ነው:: አማኝ ግን ጌታን ከፊቱ ያሰቀድማል:: እግዚአብሔር ከፊት የሚቀድምለት አረሱ በጌታ ፈቀድ የተሞላ እርሱንም የሚፈልግ ደግሞም በፈቃዱ የወጣና የሚመራ ነው:: ሰለዚህ በነገር ሁሉ ጌታን ይጠብቃል ደግሞም የሰቀድማል::

View Details

እግዚአብሔር ሊሰራ ያለውን የማዳን ስራ አስቀድሞ ተስፋን የሰጠበትና በአባቶች እንዲሁም በነቢያቱ የተናገረበት እርሱ የተስፋ ወንጌል ወይም የእግዚአብሔር ወንጌል ተብሎ ይጠራል:: ይህ የተስፋ ወንጌል ደግሞ የተፈፀመበትና ማዳኑ የተገለጠበት እርሱ የክርስቶስ ወንጌል ተብሎ ተጠርቷል:: ስለዚህ ሰው ሁለቱንም በመስማት ሙሉ ሊህን ይገባዋል:: *** በዚህ ትምህርት ይህንን እና ከዚሁ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ሀሳቦችን በጥልቀት እንማራለን::

View Details

እሺታና እምቢታ በሰው ህይወት ውስጥ የሚታዩና የማነነታችን አንዱ መገለጫ የሆኑ ተቃራኒ ነገሮች ናቸው:: እምቢታ የኃጢአት የአመፅና የእልከኝነት ፍሬ ነው:: እሺታ ግን ከእግዚአብሔር የሆነና ሰውን ወደ በጎና መልከም ወደሆነ መንገድ የሚመራበት ነው:: ዳዊት " በእሺታ መንፈስ ደግፈኘ" ብሎ እንደፀለየ:: የእኛን እሺታ የሚፈልጉ ነገሮች በእኛ ሚዛን ሲመዘኑ ፈፅሞ ስፍራ የማንሰጣቸው የተናቁ ሊሆኑ ይችላሉ:: ነገር ግን እሺ ብለን ብንታዘዝ ለፈውሳችንና ለበረከታችን መለቀቅ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉና:: ንዕማን እሺ ብሎ እርሱ በናቀው ውሃ ውሰጥ ገበቶ ፈውሱን እንደተቀበለ:: *** ነገሮች በእኛ ፊት የተናቁና ክብደት የሌላቸው ወይንም ደግሞ አሰፈሪዎችና እንዴት ይሆናል የምንለው ቢሆን እንኳ የእኛን እሺታ እሰከፈለጉ ድረስ በጌታ ፀጋ ልንዘረጋ የተገባ ነው::

View Details

በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱና በትንሣኤው በማመን ወደ መንግስቱ የገባን ሁላችን የልጁን መልክ ልንመስል የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው:: እውነተኛ ተከታይነታችንም በቃልና በስራ ሊገለጥ የተገባ ነው:: ጌታ በመከራ ሁሉ እንደታገሰ በክፉ ፈንታ ክፉንም እእዳልመለሰ እንዲሁ በእኛም ህይወት ይህና ሌሎችም የጌታ ባህርያት ሊንፀባረቅ ያስፈልጋል:: ፈፅሞ ጌታን መከተል ዋጋ የሚያስከፍል ለስጋም የተመቸ እንዳልሆነ የተገለጠ ነው:: ነገር ግን ከጌታ ዘንድ ለዚህ የሚሆን ፀጋና ሽልማት እንዳለው በማየት በታማኝነት ልንከተል ይገባል::

View Details

በአማኝ ህይወት ውስጥ ወንጌል እየበራ አየጨመረ ሲመጣ እኔ ከሚለው ከማንኛውም መመካት አውጥቶ በእግዚአበሔር ወደ መታመንና መመካት ፈፅሞ ሁሉን በእርሱ ላይ ወደ መጣል ከፍታ ያደርሰዋል:: የሰማነውና ወደ ዘላለም መንግስት የጠራን የወንጌል እውነት በእኛ ዘንድ ፀንቶ ፍሬ ይታይብን ዘንድ በመንፈስ ቀዱስ ሀይል በብዙ መረዳት በፀጋው ልናድግ ያስፈልጋል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.1:17-26 ክፍል 6

View Details

የወንጌል ዋና ተልዕኮ ሰዎችን ከተበላሸ አካሄድ ማረም ወይም ማስተካከል አይደለም:: እንዲሁም ፈውስና ተአምራቶች ምልክቶች እእጂ ዋና ነገር አይደሉም:: የወንጌል ዋና ተልዕኮ ወይም ትኩረት ሰለ ህይወት ነው:: ይህም ህይወት ወደ ሰው ሁሉ የመጣው ሊቀበለውም የተገባው ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው:: *** ኢየሱስ:- ከሞት ፍርሀት ያድናል - ከዘላለም ፍርድ ያድናል - ከጨለማ ፍርሀት ያድናል - ከዚህ አለም ያድናል - ከኃጢአት ያድናለ - ከዘላለም ሞት ያድናል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.1:14-16 ክፍል 5

View Details

የሐዋርያት ሥራ.1:6-14 ክፍል 4

View Details

አማኝ ሁልጊዜ ሊረዳውና ላይዘነጋ ከሚገባው ነገር አንዱ ካለበት የከበረ ህይወት ሊያወጣው ወደ ቀደመው የጨለማ ህይወት ለማስገባት የሚጎትት የሚፈትን ጠላት እንዳለው ነው:: በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ወደ ዘላለም ህይወት ወደ መንግስቱም ገብተናል:: ልጆቹ የተስፋውም ወራሾች ሆነናል:: ይህንንም በማመን አዲስ ፍጥረት ሆነናል:: ይህ ደግሞ ታላቅ መዳን ተብሎ ተጠቅሷል:: የአማኝ ትምክህትም ይኸው ነው:: አንዳች የጎደለን እንዳለ እያሳየ ወደኃላ የሚጎትተን እንዳይኖር እንጠንቀቅ:: ታላቅ ብድራት ያለውንም ድፍረታችንንና ትምክህታችንን አናቃልል::

View Details

በወንጌል የተገለጠው አንዱና ዋናው የእግዚአብሔር ፀጋ ነው:: ይህ ፀጋ ከኃጢአተኝነት ነፃ የሚያወጣ ብቻ ሳይሆን በዚህም ምድር የሚያኖርም ነው:: ሰለዚህ ከወንጌል የተነሳ በዚህ አለም ያሉትን ሰዎች ለሁለተ ከፍሏል:: በራሳቸው ጥረትና ግረት የሚኖሩ እኔ ሰራሁት አደረኩት የሚሉ የዚህ አለም ልጆች እና ከእኔ ምንም የሆነ የለም የሚሉ በፀጋው የሚኖሩ አማኘ:: እግዚአብሔር ራሱን የገለጠው በወንጌል አማካኝነት ነው:: ስለዚህ በወንጌል በኩል እግዚአብሔር ሳይበራለት እግዚአብሔር ቢል የራሱ መረደት እንጂ በመንፈስ የሆነ መገለጥ አይደለም:: የአማኝ መንፈሳዊ መረዳት መጠኑ በአዕምሮው ላይ ባለው እውቀት ሳይሆን በወንጌሉ ፀጋ የበራለትን ያህል ነው"

View Details

የሐዋርያት ሥራ.1:6-26 ክፍል 3

View Details

ስፍራውን ለማስለቀቅ በአማኝ ህይወት ዙሪያ ብዙ የሚያስጨንቁና የሚያናውጡ ነገሮች ይኖራሉ:: ይሁን እንጂ ሰው እግዚአብሔርን እንዳወቀ በእርሱም እንደታመነና እንደተመካ ደግሞም እንዳረፈ የእምነቱ መጠን የሚለካው በጊዜውም አለጊዜውም በስፍራው ፀንቶ መጠበቁ ነው:: በስፍራው በጌታ ዐጋ ፀንቶ የቆመ እርሱ የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ ይሆናል:: ደግሞም አርሱ ለቤቱና ለሀገሩ ለትውልዱም የሚተርፍ ይሆናል:: *** ሰፍራችን በሆነበት ቦታ በዛ በእግዚአብሔር እጅ ተይዘናል::

View Details

የክርስቶስ ባለጠግነትና ሁሉን ቻይነት ለሰው ሁሉ የተገለጠው በወንጌል ነው:: በዚህም ወንጌል ሰውን ሁሉ ኃጢአተኛ እንደሆነ የሚያሳየው የእግዚአብሔር ፅድቅ ደግሞም እግዚአብሔር የሁሉ አምላክና ጌታ እንደሆነና ለሁሉ የሆነውም ምህረቱ ተገልጧል:: *** ሰው ከኃጢአተኛ ማንነቱ በፀጋው ነፃ ሊወጣና ሊቀደስ ይገባዋል:: እንዲሁም ደግሞ ለክፉ ተግባሩ ከጌታ ዘንድ ምህረትን ሊቀበልና ሰላምን ሊያደርግ ይገባዋል:: ይህም ስለሆነ ወንጌል ለኃጢአተኛው ፅድቅን እነዲሁም ቅድስናንና ሰላምን ያውጃል::

View Details

ወንጌል:- - ከሰው ልጅ ውድቀት ጀምሮ ረጅም ዘመናትን የተሻገረ የእግዚአብሔር የማዳን ሀሳብ ነው:: - የእግዚአብሔርን የማዳን ሀሳብ የምስራች እንደያዘ እንደዚሁ ደግሞ ፍርድንም የሚናገር ነው:: - ለሰው ሁሉ የሆነ ሁሉን ያካተ ለኃጢአተኛ የተሰጠ ነው:: ወንጌል አንዱን ጌታና አዳኝ እየተናገረ ነገር ግን የተለያዩ ስሞችን ይዟል:: ከእነዚህም ውሰጥ:- - የእግዚአብሔር ወንጌል , የክርስቶስ ወንጌል , የመዳን ወንጌል , የፀጋ ወንጌል , የትነሳኤ ወንጌልና የዘላለም ወንጌል ሌሎችም:: በዚህና በሚቀጥሉት ተከታታይ ትምህርቶች ዝርዝር ሀሳቦችን እንማራለን::

View Details

እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከህዝቡ ጋር ነው:: የልመናቸውንም ድምፅ ይሰማል ይመልሳልም:: ነገር ግን አማኝ አንዳንድ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለፀሎቱ መልስ የማያገኝበት ደግሞም የጨለማ መንገድ በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ያልፋል:: ይሁን እንጂ አሁንም በእግዚአብሔር መታመን ደግሞም በትዕግስት መጠበቅ ያስፈልጋል:: ጌታ የሚምር የሚራራም ነውና በራሱ ጊዜና ሁኔታ ይመጣል ይገለጣልም:: እግዚአብሔርን ከመጠበቅና በእርሱም ከመታመን ይልቅ የራሳችንን አማራጭ መውሰድ ፍፃሜው ምሬትና ድካም ኪሳራም ይሆናል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.1:1-26 ክፍል 2

View Details

የሮሜ መልዕክት. 16: 5-24

View Details

በእግዚአብሔር ፊት ተቀብሎት (ሞገስ) ያገኘነው በፊቱ እናመልከውና እናገለግለው ዘንድ ወደ እግዚአብሐር ፊት ካስገባን ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሳ ነው:: እለት እለት መውጣትና መግባታችን በእርሱ ሞገስ ነው:: *** በእርሱ ፊት ሞገስ ያገኘ እርሱ:- - እግዚአብሔር ለሰላሙ ይጠነቀቅለታል:: - ቢፈተንም በአሸናፊነት ወደ ፊት ይሄዳል:: - በጨለማው ላይ እግዚአብሔር ትዕዛዝ ያወጣለታል:: - መነገዱ ሁሉ በፅድቅና በእውነት ይሆናል::

View Details

የሐዋርያት ሥራ.1:1-5 ክፍል 1

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 28

View Details

የሮሜ መልዕክት. 7: 1-6

View Details

የሮሜ መልዕክት. 16: 1-2

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 27

View Details

በአማኝ ህይወት መንፈሳዊ ውጊያ የሚጀምረው ጌታ ኢየሱስን ህይወቱ ካደረገበትና መንፈሳዊ ሰው ከሆነበት ቀን ጀምሮ ነው:: የእያንዳዳችን የመንፈሳዊ ውጊያ የጦርነቱ ምክንያትና ደረጃ እንዳየለንበት መንፈሳዊ እድገት ደረጃ ይለያያል:: *** በዚህ ትምህርት በመንፈሳዊ ህይወታችን ለምን እንደምንፈተን የፈተና አይነትና ከፈተና መውጫውም እንዴትና በምን እንደሆነ እንማራለን::

View Details

አንዳንድ በህይወታችን የሚያልፉ ሁኔታዎችና ነገሮች በማስተዋል ከመረመርናቸውና ካዳመጥናቸው ወደ ጌታ አንድንመለስ የሚናገሩ መልዕክቶች ናቸው:: መመለስ ዋጋ ያሰከፍላል ነገር ግን በረከትና ፈውሱ ብዙ ነው:: መመለስ ከልብ ወደ ጌታ ሀሳብ ወደ ጌታ ፈቃድ መመለስ ነው:: ከጌታ ርቀን ዙሪያችን ሰላምና ደሰታ ቢመስለን አንታለል:: ለጊዜው ሰለሆነ:: እግዚአብሔር ግን እንድንመለስ በተለያየ ሁኔታ ድመፁን ሲያሰማን ደግሞም ሲጠብቀን ለአሁን ህይወታችን ደግሞም ለዘላለም ለሆነው ሰላምና ደሰታ ነው::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 6: 5-23

View Details

የሮሜ መልዕከት.15:22-33

View Details

እግዚአብሔር ቸርና መልካም አምላክ ነው:: የሚያይና የሚሰማ ደግሞም የሚናገር ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በምናልፍበት ሁኔታ ውስጥ የሚያፅናና ደግሞም ለፀሎታችን መልስ የሚሆን ድምፁን ከማሳየት ይዘገያል:: በራሱ ጊዜ የከበረውን ሀሳቡን እስከሚገልጥበት ሰአት ድረሰ አና እንዲሁም ነገን ሊናገረን ሲፈልግ ዛሬ ዝም ይለናል:: የእግዚአብሔር መዘግየት በራሱ ጊዜ ሊገለጥ ካለው ነገር ጋር የተያያዘና ደግሞም ከእምነትና ከህይወት ምስክርነት ነገ ሊሆን ካለው ነገር ጋር የተያያዘ ነው::

View Details

ሰዎች በሚያልፉበት ወይንም በድካማቸውና በውድቀታቸው ልንፈርድና ራሳችንንም ልናፀድቅ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም:: ፍርድ የእግዚአብሐር ነው:: እኛ ግን እግፈዚአብሔርን በመፍራትናበትህትና ልንኖር ያስፈልጋል:: እውነተኛ ነስሃ ልብን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድና ዝቅ በማለት ይጀምራል:: ደግሞም መፀፀትና ማዘን ብቻ ሳይሆን ንስሃ አቅጣጫ መለወጥና የንስሃ ፍሬ ማፍራትን ይጠይቃል::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 15: 14-33

View Details

የሮሜ መልዕከት.15:17-33

View Details

የሮሜ መልዕክት. 15: 7-13

View Details

የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት የትንሳኤ ትምህርት ነው:: ይኸውም ትንሣኤና ህይወት እኔ ነኝ ያለውን ጌታ በማመን የሚገኘውን የክብር ትንሣኤና የዘላለም ህይወት:: የዳንኤል መጽሐፍም ከብዙ ዘመናት በፊት ይህንኑ አስቀድሞ ይገልጣል:: ምንም እንኳን በዚህ ምድር እየሆነ ባለው ሁኔታ ብዙ ብንፈተንም ነገር ግን ትንሣኤ ሙታን ደግሞ ከጌታ ጋር አብሮ መገለጥ የመሆኑ ተስፋ ፅኑ ነው:: በፈተና ውስጥም የሚያ ፅናንና የሚያበረታን የነፍሳችን መልሕቅ ነው::

View Details

ሰው ፈቃዱና ሀሳቡ ስጋዊ ወደ ሆነውና ወደዚህ አለም አመፅ ባዘነበለ ጊዜ ለክፉው መጠቀሚያ ይሆናል:: በተቃራኒው ደግሞ ሰው ራሱን ቀድሶ እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለማስከበር ቀናውን ነገር ሲያስብ ለእግዚአብሔር የሚጠቅም የክብር ዕቃ ይሆናል:: ዳንኤልም አንዱ የእግዚአብሔር የክብር ዕቃ ነው:: በመሆኑም ከሩቅ ዘመን ሆኖ የዘመንን ፍፃሜ የሚገልጥ ሆኗል:: በዚህ ትምህርት ነገር ሁሉ ወደ ፍፃሜው እየፈጠና አሰቀድሞ የተነገረውም ሁሉ እየተፈፀመ መሆኑን እናያለን:: በዚህ ሁሉ ግን አሁንም ወንጌል የምስራች ነው::

View Details

በዚህ የዳንኤል መፅሐፍ አንዱና ዋናው ጎልቶ የሚታየው ሀሳብ ይህ አለም ወደ ፍፃሜው እየፈጠነ መሆኑ ነው:: ስለዚህ እለት እለት ለኃጢአትና ለአመፅ እየሞትን ለፅድቅና ለእውነት እንኖር ዘንድ እጅግ አስፈላጊ ነው:: *** እግዚአብሔር የሚጠቀምበት የክብር ዕቃ እርሱ ሰባራ ማንነት ያለው ረሱን ዝቅ ያደረገና ትሁት ደግሞም የፍቅር ሰው ነው::

View Details

የሮሜ መልዕክት.15:1-6

View Details

የሮሜ መልዕክት. 14: 13-23

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 26

View Details

ዳንኤል በእግዚአብሔር ፊት በፀሎት ሲተጋ በብዙ ዝቅታና ራስን በማዋረድ በብዙ ትህትና ሆኖ ነው:: ስለዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኘው መልስ የራሱን ዘመን አልፎ እስከ ዘመን ፍፃሜ ያለውን የሚያሳይ ሆኗል:: በፀሎታችን ውስጥ የሚረዳን የጌታ መንፈስ እንዳለ ሁሉ ከትክክለኛው የፀሎት መንፈስ ሊያወጣን የሚዋጋን እንዳለ ልናስተውል ይገባል:: አማኝ የክፉውን ውጊያ ሊያሸንፍና ፀሎቱም ከጌታ ዘንድ መልስ የመጣ ዘንድ በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ በጎ ህሊና ሊኖረው የተገባ ነው::

View Details

ጥያቄ እና መልስ ክፍል 25

View Details

የሮሜ መልዕክት. 13: 11-14

View Details

የሮሜ መልዕክት.14:1-12

View Details

በእግዚአብሔር ፊት በፆምና በፀሎት መሆን አስፈላጊና ከእርሱ ዘንድ ወደ እኛ የሚመጣውን ፈቃዱን የምንሰማበት ወደፊትም ያለውን ሀሳቡን የምንቀበልበት ነው:: እግዚአብሔር በማንኛውም ሁኔታ ውስጥና ጊዜ ሊያናግረን ለጸሎታችንም መልሰ ሊሰጠን ይችላል:: ነገር ግን አዕምሮአችንና ልባችን በእርሱ ቁጥጥጥ ስር መሆን አለበት:: *** በክፉው ወጥመድ እነዳንያዝ የጌታንም ድምፅ ከመስማት እንዳንከለከል በዙሪያችን ከምናየውና ከምንሰማው ልንጠበቅ ያስፈልጋል::

View Details

እኔ በልቤ የዋህና ትሁት ነኝ እንዳለ ጌታ እንዲሁ አማኝ ከአለምና ከኃጢአት ነፃ ያወጣውን ጌታ ኢየሱስን ሊመስል ተጠርቷል:: ከአለም ስንወጣ አለምን እንመስል የነበረበትን ሁለንተና ጥለን ነው:: *** ሰው የውጭውን ያያል እግዚአብሔር ግን የውስጥ ማንነታችንን ያያል:: በእግዚአብሔር ፊት የልጁን መልክ መስለን እንታይ ዘንድ በቃልና በሰራ በእውነት በተለወጠ ማንነት ልንመስለው ይገባል::

View Details

አማኝ ይህን አለም ማየት ያለበት አለማውያን ከሚያዩት በተለየ መንገድ በተከፈቱ መንፈሳዊ አይኖች ነው:: ይህ ሲሆን በዙሪያው ካለው ደግሞም ከሚያልፍበት ማንኛውም አስጨናቂ ሁኔታ ባሻገር ያለውን የዘላለም ተስፋ ያያል:: ደግሞም የክብር ተስፋ ያለው ጌታ ከእርሱ ጋር መሆኑን ያያል:: *** አይኖቹ የተከፈቱለት አማኝ ከእግዚአብሔር የሆነውንና ከአለም ወይም ከስጋ የሆነውን ለመለየት አይቸገርም:: በፈተናም ውስጥ የፀና ምስጋናም ደግሞ የበዛለት ነው::

View Details

ዳንኤል አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያቀና ሰው ነው:: በህልምና በራዕይ በመሰተዋል በእግዚአብሔር ፊት ያደገ ነው:: እግዚአብሔር በህይወት ዘመናችን ሊገልጥልን ያለውን ነገር የሚገልጥልን እራሳችንን በሰጠንበትና አካሔዳችንን ከእርሱ ጋር ባቀናንበት አካሄድ ነው:: *** እግዚአብሔር የተናገረን ቃል ህይወታችን ይሆን ዘንድ ደግሞም የቃሉ ትርጉም የኛ ሀሳብና ስሜት ሳይሆን የራሱ የጌታ ሀሳብ እንዲሆን የተሰበሰበ መንፈስና የሚያስተውል ልብ ሊኖረን ያስፈልጋል::

View Details

የአማኝ ትክክለኛው ፀሎት የሚጀምረው እግዚአብሔርን ፃድቅ በማድረግ ነው:: ደግሞም ራሱን በማዋረድና ዝቅ በማድረግ :: የዳንኤል ፀሎትም የሚያስተምረን ይህንኑ ነው:: እግዚአብሔር ለምን? ተብሎ አይጠየቅም:: እርሱ ፃድቅና እውነተኛ አምላክ ነውና:: ነገር ግን በምናልፍበት ሁኔታ ውስጥ ሁሉ የእርሱን ፈቃድና ከመከራው ባሻገር ምን እንዲሆን ማየትና መስማት ይሆንልን ዘንድ በማስተዋል በፊቱ ልንሆን ያስፈልጋል::

View Details

የሮሜ መልዕክት.13:8-10

View Details

በህይወት መንገዳችን ነገሮችን እያገጣጠመ በእኛ ሁኔታ ፈቃዱን የሚፈፅም እርሱ እግዚአብሔር ነው:: እርሱ በስውር የጠየቅነውን በግልፅ በአደባባይ የሚመልስ የሚባርክ ነው:: እኛ በስፍራችን በእምነት እንጠብቅ እንጂ:: እኛ የምንንቀሳቀስበት ጊዜ አለ ደግሞም በስፍራችን ሆነን በእምነት ዝም ብለን ጌታን የምንጠባበቅበት ጊዜም አለ:: የምናልፍበት መንገድ ላይገባን ይችላል:: ነገር ግን ጌታን መጠበቅ ወደ ፍፃሜው እድንደረስ ፍሬውንም ወደ መብላት ያደርሳል::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 13: 1-7

View Details

በሰማይ ቢሆን ሀምድር ያለ እግዚአብሔር ፍቃድ የሚሆን አነዳች ነገር የለም:: የሚሆነው ሁሉ ከላይ እንደ ተፃፈው ይሆናል:: ዳንኤል ይህን ረጅሙን ዘመን ተሻጋሪውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነው ያየው::ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር ህዝብ አይኑን በምድር ላይ ከሚሆነውና ከሚፈራረቀው ነገርና ሁኔታ ላይ አንስቶ ከአግዚአብሔር ሀሳብ ጋር እንዲስማማ ነው::: ***ከእግዚአብሔር ጋር ረጅሙን መንገድ የሚራመዱ እነርሱ የሚያስተውሉ የተናገራቸውንም ቃል ደግሞም መንፈሱን የሚጠብቁ ናቸው::

View Details

በምድር ላይ ብዙ ጥሩና መልካም የሆኑ የሚያፅናኑ ምክሮች ይኖራሉ:: ነገር ግን በመከራና በችግር ሁሉ ውሰጥ አልፎ ማስኬድ የሚችል እውነተኛው ምክር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው:: እግዚአብሔር በምክር ግሩም ነው ተብሎ እንደ ተፃፈ:: ደግሞም እርሱ በምናልፍበት ሁሉ አብሮን አለ:: ሁኔታዎች መልካም ባይሆኑምና ተስፋ በይሰጡም እንኳ በዚህም ውስጥ እግዚአብሔር አለ:: ይህንን ማየትና በእርሱ ላይ መታመን ይህ የአማኝ ትልቁ ሀብት ነው:: በመንፈስ ቅዱስ የሆነ መፅናናትም ለእርሱ ይሆናል::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 12:9-21

View Details

በእግዚአብሔር ላይ የታመነውና መደገፊያውንም እርሱን ያደረገ ዳንኤል በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛል አነዳለ አማኝ የእግዚአብሐርን ክብሩንና ሉአላዊነቱነ የሚያይበት መንገዱ ቅንነት ነው:: ይህ ደግሞ አንዱ የጌታ ባህርይ ነው:: ቅንነት ባለበት በዛ ንፁህ ህይወት ይገለጣል:: ትእግስት የበዛለት በእውነትና በፅድቅ የሚኖረው ፀጋም የሚበዛለት እርሱ በቅንነት የሚሄደው ነው:: *** አማኝ ከቅንነት ከጎደለ ህሊናው ንፁህ አይሆንም:: በቅንነት የሚራመድ እርሱ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ይራመዳል:: የዛሬን ብቻ ሳይሆን የወደፊት ዘመንም አሻግሮ ያያል

View Details

ይህ አለም ጅማሬ እንዳለው ሁሉ ፍፃሜም ያለወ ነው:: የዳንኤል መፅሐፍ የትነቢቱ ፍፃሜ ይህንኑ የሚገልፅ እስከ ዘመን ፈፃሜ እሰከ ጌታ ዳግመኛ በክብር መገለጥ ድረስ የዘለቀ ነው:: ይህ ደግሞ ከሰው እውቀት የመነጨ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለሆነ በጥንቃቄ የምንመረምረው ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ እንዳታ የምንረዳው ነው:: *** በአለም ያለው ክፋት እየጨመረ ጨለማውም እየከበደ እንደሚሔድ የተገለጠ እውነት ኀው:: ቤተክርስቲያን ግን እየታደሰች አማኞችም በመከራ ውሰጥ በፀጋው ኃይል በድል ነሺነት ለመሻገር የሚተጉበት የሚዘጋጁበትም ዘመን ነው::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 12: 1-21

View Details

አማኝ ሊመስል የሚገባው ማንን እንደሆነ የእግዚአብሔር ቂል በግልፅ ይናገራል:: ሁላችን ክርስቶስ ኢየሱስን እንመስል ዘንድ ተጠርተናል:: ልጅ ወላጆቹን እንደሚመስል እንዲሁ ኢየሱስን በማመን የእግዚአብሔር ልጆች የሆን እኛ ሁላችን ጌታን እመስላለን:: *** የእግዚአብሔር ልጆች በእውነትና በፅድቅ እርሱን በመምሰል ስንንኖር ዋጋ ሊያሰከፍለን ግድ ነው:: ይሁን እንጂ ዋጋችን በጌታ ፊት እጅግ የከበረ ነው:: እለት እለት እርሱን ለመምሰል ራሳችንን እናስለምድ:: ጌታም የሚረዳ ፀጋውን ይሰጠናል::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 24

View Details

አማኝ በዚህ አለም ሲኖር ከሚያልፍበት ፈተናና መከራ ባሻገር ያለውን የዘላለም ህይወት ተስፋ እያየ በአሸናፊነት መራመድ የሚችለው መደገፊያውና መታመኛው እግዚአብሔር ን ያደረገውን ያህል ነው:: *** እግዚአብሔር ለሚታመኑበት ጋሻ ነው:: በእርሱ የታመነ የተደላደለ ነው:: ብዙ ስራም የበዛለት: በመከራ ጊዜ እረፍተና መፅናናት በአሰጨናቂውም ሰአትና ሁኔታ ሰላም ሀይልና ብርታት ይሆናል::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 23

View Details

የሮሜ መልዕክት. 12:1-8

View Details

የሮሜ መልዕክት. 12: 1-2

View Details

አማኝ ባለው ሥልጣን እውቀትና ሀብት እግዚአብሔርን ለማምለክ ራሱን ባያዋርድ ለመውደቅ ለመዋረድ ምክንያት ይሆናሉ:: ሥልጣን ድፍረትን እውቀት ትእቢትን አንዲሁም ሀብት ደግሞ ትምክህትን ያመጣሉና:: የእግዚአብሔር ልጆች እኛ ያለን ሁሉ ከእግዚአብሔር እንደተቀበልን ደግሞም የተቀበልነውን እርሱን በማክበር የምንጠቀምበት ሊሆን ይገባል:: በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ጠላት ሰጋና አለም በብዙ ቢፈትኑንም ፈተናውን ሳንፈራ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ በፀጋውም ጉልበት ድል እያደረግን እንጓዛለን::

View Details

አማኝ ለበራለት በትክክል ለተረዳውና ላመነው ጌታ ራሱን መሰዋዕት እሰከማድረግ ድረስ ፀንቶ ለመቆም የጨከነ ነው:: ይህም ደግሞ የፀጋውን ችሎት የሚያሳይ ነው:: የዳንኤል ህይወት ለዚህ ድነቅ ምስክር ረው:: ነገሮች በዙሪያችን ክፋታቸው በዝቶ ጫፍ ሲወጣ ሊያጠፉን የደረሱ እስኪመስል ድረስ ሊያስጨንቁን ይችላሉ:: ነገር ግን ይህ ሁኔታ አግዚአብሔር ፅድቁን የሚገልጥበት እኛም ክብሩንና ታላቅነቱን የምናይበት ይሆናል:: እግዚአብሔር ይናገራል አሁንም ይናገራል:: ሰውም ሰምቶ እስኪመለስ አብዝቶ ይታገሳል:: ደግሞም በፅድቅ የሚፈርድ ሰለሆነም በፍርድ ይገለጣል::

View Details

ኑኃሚንና ሩት ተቀናጅተው በፍፁም መሰጠትና ፍቅር እርስ በአርሳቸው እየተመካከሩ መራመድ የጀመሩት ህይወት ጥንቃቄና ጥበብ የሞላበት አካሔድ እንደሆነ እናያለን:: በቤት ቢሆን በቤተክርስቲያን አብረን ህይወት ጎዳና ከምንጓዘው ወይንም አብረን በቤቱ ከምናገለግላቸው ወገኖች ጋር ስንቀናጅ የመጀመሪያው በፍፁም መሰጠት በታማኝነትና በፍቅር ለመመካከር ደግሞም ለመታዘዝ ዝግጁ መሆን ነው:: *** በህይወታችን ታማኝ መሆን ደግሞም ታዛዥ መሆን ለመባረካችንና ለመፈወሳችነ ደግሞም ለመንገዳችን መቃናት መሠረት ነው::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 10: 14-17 , 11: 1-11

View Details

በሁሉ ላይ ገዢ የሆነው እግዚአብሔር ደግሞም መሪ የሆነው እግዚአብሔር እርሱ ታዳጊም ነው:: በዳንኤልና ጓደኞቹ ህይወት የተገለጠውም ይኸው ነው:: ከእሳት ሲታደግ ከአንበሳም ሲያሰመልጥ:: ሀአማኝ ህይወት የእግዚአብሐር ገዢነት መሪነቱና የሀይሉ ችሎት የሚገለጠው እኛ ለእግዚአብሔር በሆንለት በተገዛንለትና በተገኘንለት መጠን ነው:: *** በአለም ያለው ጨለማ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይሄድም:: ነገር ግን እግዚአብሔር በዘላለም እቅዱ ለእርሱ በሚገኙለት የክብር ዐቃዎች ሉአላዊነቱን ክብሩንና ብርሃኑን እለት እለት ይገልጣል::

View Details

ዘመኑ እየከፋ በሔደበትና የምናያቸውና የምንሰማቸው ነገሮች በሙሉ አስጨናቂና ተስፋ የሚያስቆርጡ በሆኑበት በዚህ ጊዜ የልቡናችን አይኖች ሊከፈቱና አርቀንም ልናይ ያስፈልጋል:: የልቡናችን አይኖች ሲበሩ ተሰፋችን ከምድር ላይ ተነስቶ የዘላለም ህይወት ተስፋ ላይ ይሆናሉ:: *** ሀአማኝ ህይወት ላይ የተጠራበት የዘላለም ህይወት ተስፋ ገዢ ሲሆን እለት እለት የሚያወራውና የሚናፍቀው ደግሞም በዝግጅት የሚኖርለት ይሆናል::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 11: 1-36

View Details

እግዚአብሔር ፈቃዱን ደግሞም ክብሩን በቃሉ ይገልጣል::የእግዚአብሔር ቃል ለመምከር ለመገሰፀ ደግሞም ለመባረክ ወደ ሰው ይመጣል:: ከወረድንበት ጥልቅ ጉድጓድ ከተስፋ መቁረጥ ያወጣናል:: ለቃሉ በህይወታችን ሰፍራ እየሰጠን በመጣን መጠን የጌታ ብርሃን ወደ ህይወታችን ይበራል አማኝ በቦታው ሲገኝ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጉብኝት ይሆናል:: የእርሱ ጉብኝት ደግሞ ወደ ክብር ያወጣል: የህይወት መታደስ ይሆናል:: ጨለማው በብርሃን ይሞላል:: ልምላሜና በረከትም ይሆናል::

View Details

በዚህ አለም ብዙ እውቀት ጥበብና ሥልጣኔ አለ:: ደግሞም እየጨመረ ይሄዳል:: ነገር ግን ይህ ሁሉ የአለም ጥበብ አውቀት በእውነትና በፅድቅ እግዚአብሔርን ለሚያመልከው ህዝብ ለቤተክርኝቲያንም ፈተና የሚሆን ዋጋም የሚያስከፍል ይሆናል:: በዳነኤልና ጓደኞቹ ዘመን የሆነውና ተጽፎ የምናገኘው ለዛሬ ደግሞም ወደፊትም ሊሆንና ሊገለጥ ላለው ጥላ ነው:: ሰለዚህ በዚህ ትምህርት ውስጥ ናቡከደነፆር ያየውን ህልምና የህልሙን ፍቺ ከእኛ ዘመን ጋር ያለውን ዝምድና እንማራለን::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 10: 1-17

View Details

ዳንኤልና ጓደኞቹ በልጅነታቸው የተቀረፁበትና ያደጉበት የእግዚአብሔር ቃል (የህጉ መፅሐፍ ) ለዛሬው ህይወታቸው ፅኑ መሰረት ነው:: እኛም ለልጆቻችን የወደፊታቸውን ቀን ወይም ዘመን መፍጠር አንችልም:: ነገር ግን ለነጋቸው የሚያበቃቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ልንሞላባቸው በዚህም ልናሳድጋቸው ያስፈልጋል:: የነገ ዋስትና ጌታ ብቻ ነው:: *** በምድር ላይ ብዙ ነገሮች ልናገኝ እንችላለን ነገር ግን ማምለጫው በአንድ አቅጣጫ ብቻ ነው:: ለእግዚአብሔር በተገዛንለት በኩል:: የህ ደግሞ የእርሱን ታላቅነትና ክብር ወደ ምንገልጥበት ከፈታ ያመጣናል::

View Details

የሮሜ መልዕክት.10:1-21

View Details

ናቡከደነፆር ያየው ህልምና ዳንኤል የተረጎመው የምሰሉ ምስጢር እኛ አስካለንበት ደግሞም እስከ ጌታ ዳግም መምጣት ድረስ የሚዘልቅ ነው:: የዳንኤል መፅሐፍ የአለምን ሁኔታ እስከ ዘመን ፍፃሜ የሚሆነውን የሚገለፅ መፅሐፍ ነው:: በምድር ላይ ሊሆን ያለው የመለኮት ፈቃድ መተርጎሙ ትልቅ ነገር ነው:: ወደ ፈቃዱና አመራሩ መምጣት ደግሞ ታላቅ በረከት ነው:: እግዚአብሔር ገዢ ነው:: ደግሞም መሪ ነው:: እርሱ ሲመራን መንፈሱ ወደ እውነተኛ ንስሀ ይመራናል:: በፊቱም ትሁት እንሆናለን::

View Details

አማኝ በዚህ አለም ሲኖር እንደፈለገው ሊወጣና ሊገባ በተሰማውና ባየው የሚሰራና የሚናገር ሳይሆን ህይወቱን በመርህ የሚመራ ነው:: የእግዚአብሔርን ቃል መርሁ ያደረገ ነው:: *** የእግዚአብሔርን ቃል መርሁ ያደረገ አማኝ በመጀመሪያ የእምነት ሰው ነው:: በነገር ሁሉ ወስጥ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ያያል:: ደግሞም እንደ ቃሉ ይፀልያል በትህትናና በፅድቅ እግዚአብሔርን በመፍራት ይመላለሳል::

View Details

የሮሜ መልዕክት.9:5-21

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 21 AM

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 22 PM

View Details

አማኝ በህይወቱ በብዙ ከፍታና ዝቅታ ውስጥ ያልፋል:: በዚህን ጊዜ በተለይም በምናልፍበት አሰጨናቂና ከባድ የፈተና ጉዞ ለምን? ደግሞም እስከ መቼ? በሚሉ መልስ በሚፈልጉ ጥያቄዎች ሁለንተናችን ይያዛል:: እግዚአብሔር ግን አሰጨናቂው ጊዜ ያልፋል:: ደግሞም ጨለማው ይነጋል ይላል:: *** እኛ በቃሉ ስንገሰፅ ስንመከርና ስንታዘዝ እሺ እንበል እራሳችንንም አዋርደን በፊቱ እንሁን እንጂ: ጨለማው ይነጋል:: ሲነጋም ነገር ሁሉ ይቀየራል:: ጠላት ወዳጅ ይሆናል:: የራቀው ይቀርባል:: ሀዘንም ይሸሻል:: ሰላምና ደሰታ ይሆናል:: ምስጋናም ይበዛልናል::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 20

View Details

እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠራን በመነግስቱ ውስጥ ልንተጋ ደግሞም እሰከፍፃሜው ድረስም እንድንሄድ ነው:: ለዚህም ከእርሱ ዘንድ የሚረዳ ፀጋ አለ:: እሰከ ፍፃሜው የመሄጃው መንገድ ጠባብ መንገድ ነው:: ወደ ኃላ የሚጎትተንን በፍፃሜውም ከሚኖረን እረፍት ሊያሰቀረን የሚታገለንን ሁሉ ወደኃላ እየጣልን ወደ ፊት ብቻ የምንሄድበት መንገድ ነው:: ደግሞም ጌታም አብሮን የሚጓዝበት የመንፈስ ቅዱስም መፅናናት ያለበት ነው::

View Details

የአማኝ ህይወት ድል የመንሳት ህይወትና ኑሮ ነው:: በኃጢአትና በስጋ ላይ ደግሞም በአለምና በሰይጣን ላይ:: ድል የመንሳት ህይወትና የአሸናፊነት ኑሮ የሚጀምረው ራስን ለጌታ ለፈቃዱና ለሀሳቡ በማሰገዛት በመሸነፍ ነው:: *** ለጌታ የተሸነፈ አርሱ በሚይልፍበት ሁሉ በጌታው ላይ የሚደገፍ በእምነት ፀንቶ የሚቆምና ደግሞም በፀሎት የሚተጋ ነው::ሰለዚህም በድል አድራጊነት ይጓዛል::

View Details

የሮሜ መልዕክት.9:1-33

View Details

በመንፈሳዊ ህይወታችን መታደስ ማለት ከእግዚአብሔር ጋር የነበረንን ግንኙነት ከደከምንበት ከራቅንበት ወደ እርሱ መለስን ያመለክታል:: ለመመለስ እምቢ ባልን መጠን ከጥበቃውና ከቸርነቱ እንርቃለን:: ከእርሱ እየራቅን በሄድን ልክ ደግሞ ወደ ክፉው ወጥመድ እየገባን እንሄዳለን:: ይህ ሲሆን ሰላም ይርቃል በረከትና ሞገስ ይሸሻል:: *** እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የሆና በስፍራው ያለ ሰው ታላቅ ሰላምና እረፍት ይሆንለታል:: እግዚአብሔር ለእርሱ ክብር ነው:: ሞገስም ነው:: እርሱ ክብር የሆነለት አማኝ በህይወቱ ትልቅ ለውጥ ይሆናል::አንደበቱ በፀጋ ቃል የተሞላ ደግሞም በሞገስ የሚወጣ የሚገባ ይሆናል::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 8: 31-39

View Details

የእግዚአብሔርን ቃል መስማት እጅግ መልካም ነው:: ነገር ግን ቃሉ የሚጠቅመን ደግሞም ፍሬ የምናፈራው የሰማነውን ቃሉን ለመጠበቅ ደግሞም ለተነገረን ቃል ለመታዘዝ ዝግጁ ስንሆን ነው:: ስለዚህ የአማኝ መንፈሳዊ ህይወት ጉልበትና ጥንካሬ ደግሞም በረከቱ የእግዚአብሔን ቃል ሰምቶ የጠበቀውን ያህል ነው:: እኛ ባልነው ሳይሆን ጌታ እርሱ ባለው ቦታና ሁኔታ ይገኛልና ሰምተን የምንጠብቀው ቃል ሰላምና እረፍት ይሆንልናል:: ተስፋን ያድሳል ቸርነቱና በጎነቱ የሚገለጠውም በዚሁ ነው::

View Details

የሮሜ መልዕክት 9:1-5

View Details

በሰው ህይወት ውስጥ መስማትና ማየት ትልቁን ሰፍራ ይይዛል:: ሰለዚህ ሰው መስማትና ማየት ያለበትንና የሌለበትን በጥንቃቄ ሊለየው ይገባል:: ምክንያቱም ሰው በሚሰማውና በሚያየው ይወድቃል ከበረከትም ይጎድላል:: እንዲሁም በሚሰማውና በሚያየው ይታነፃል ሀይልና ብርታት ይሆንለታል:: አማኝ ሁልጊዜም ሊሰማው የሚገባው አንድ ድምፅ አለ:: እርሱም የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ነው:: እርሱም የትናንትናን ያሳስባል የነገውንም ይናገራል:: እንዲሁም ደግሞ ሊያየው የሚገባው እርሱን በሁሉ ላይ ስልጣን ያለውንና ታዳጊውን ጌታ ነው:: በዚህም ውስጥ ሰላም ደግሞም ሀይልና ብርታት ይሆንልናል::

View Details

ትዳር ማለት መውሰድ እንዲሁም ደግሞ መወሰድ ማለት ነው:: ከፈጥረት መጀመሪያ አዳም ሄዋንን ከእግዚአብሔር እጅ ተቀብሎ እንደወሰዳት እነዲሁ ዛሬም አንዳችንን ለአንዳችን የሚሰጥ ትዳርን የሚሠራ እርሱ እግዚአብሔር ነው:: ሰለዚህ የተወሰደ አይመለስም:: ምክንያቱም ሁለቱ ተጣብቀዋልና:: አንድ ስጋ ሆነዋልና:: ትዳርን የሚጠብቀው ሁለቱም በመንፈሳዊ ህይወታቸው በሁለት እግራቸው የቆሙና በብርሃን ውስጥ መሆናቸው ነው:: *** - በግል ህይወቴ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት በፅድቅና በአውነት አለሁ ወይ ? - አልሆነችልኝም ወይም አልሆነልኝም ሳይሆን እኔ ሆኜለታለሁ ወይ ? ወይም ሆኜላታለሁ ወይ ? ብሎ መጠየቅ ከሁለቱ የትዳር አጋሮች ይጠበቃል:

View Details

ሰው መንፈሳዊ አይኑ ተከፍቶ ካለበት ሁኔታ አልፎ የእግዚአብሔርን ፈቃድና ሀሳብ ማየት ካልቻለ በእርሱ ሊሆን ካለው የጌታ ሀሳብ ጋር ይተላለፋል:: አልፎ የሚያይ አማኝ ህይወቱ በከፍታ የሆነ ከእግዚአብሔርም ጋር የተስማማ ነው:: ሰለዚህ የመንፈሳዊ ህይወታችን እድገትና ያለንበት ከፍታ አይኖቻችን ተከፍተው በዙሪያችን ካለው ሁሉ አልፈን የጌታን ፈቃድና ሀሳብ ያየነውን ያህል ነው:: ***አማኝ በእምነት ፀንቶ ሊቆም ደግሞም በአምላኩ ሊታመን የሚችለው ካለበት ሁኔታና ነገሮች ባሻገር አልፎ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃሉን በማየት ነው::

View Details

እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ ውብ አድርጎ ይሰራል:: ካለንበት ሁኔታ ወይንም ከምንልፍበት ነገር ተነስተን የተረሳን የተተውን ቢመስለን እንኳ እግዚአብሔር ግን ታናሽ የተባለውን የተናቀውን ነገርና ማንነታችንን ሊጠቀም ከዘላለም በፊት በእኛ ላይ ወዳለው ሀሳቡ እኛን የሚያስጠጋበት ወደ ከፍታውም የሚያወጣበት ይሆናል:: *** እግዚአብሔር የመልካም ገር ሁሉ ምንጭ ነውና የእርሱ ጊዜ ብቻ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር መራራ የተባለውን ህይወታችንን እና ነገራችንን ወደ ጣፋጭ ሊቀይር የታመነ ነው:: እኛም ፀንተን እንጠብቀው::

View Details

የሮሜ መልዕክት.8:18-30

View Details

እግዚአብሔር ያሰበልንን የአሁኑንም ሆነ ዘላለማዊውን እርስት ለመውረስ ቀዳሚው እኛ በጌታ ልንወረስ ያስፈልጋል:: በጌታ ያልተወረሰ ለእርሱ ያልተገዛ ማንነታችን ከጌታ ለምንቀበለው ማንኛውም ነገር እንቅፋት ይሆናል:: በአመታት መካከል እስራኤልን በድንቅ የመራ የረዳ ዛሬም ለህዝቡ ጌታ ታማኝ ነው:: ይመራል: ሞገስ ይሆናል: ይባርካል: ብርታትና ጉልበትም ይሆናል:: ከእኛ የሚጠበቀው ሙሉ በሙሉ ራስን ለፈቃዱ ማስገዛት ደግሞም ጌታ ለእኛ ያሰበልንን ማየት ነው::

View Details

ልጆች በወላጆቻቸው ዘንድ ማደጋቸው በጉጉት የሚጠበቅና ደስ የሚያሰኝ እንደሆነ እንዲሁ በመንፈሳዊ ህይወታችን በነገር ሁሉ ማደጋችን በእግዚአብሔር ዘንድ የሚጠበቅና ደስ የሚያሰኝ ነው:: በመንፈሳዊ ህይወቱ ያደገ ሰው በፅድቅ ይገለጣል:: እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኘውን ሁሉ ኃጢአትንና ሰጋን እምቢ የማለት ሀቅም ይኖረዋል:: *** ያደገ አማኝ በአምላኩ የሚታመን የሚመካም ነው:: በዙሪያው ከሚያየውና ከሚሰማው በላይ እግዚአብሔር ትልቅ ነው ይላል::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 8: 1-17

View Details

የሮሜ መልዕክት.8:14-27

View Details

እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ያለው በጎ ፈቃዱ በልጁ አምነው የዘላለም ህይወት አንዲሆንላቸው ደግሞም በዚህ አለም እንዲያገለግሉት ሀሳቡንም እንዲያከናውኑ ነው:: ከዘላለም የሆነው የመለኮት ሀሳቡም የሚያርፍበት እርሱ እግዚአብሔር በግል ያገኘው ሰው ነው:: በግል ለጌታ ያልተገኘ ሰው የጠራ ፍሬ ያለው የጌታ ሀሳብ በህይወቱ አይታይም:: እግዚአብሔር ብቻችንን ሲያገኘን እኛም ደግሞ ስንገኝለት ፀጋ ይጨመራል:: በእግዚአብሔር ቃል እናድጋለን አከሔዳችን የተለየ ይሆናል:: ከማያንፅ ፍሬ ከሌለው ከአለም ሀሳብና ስራ እንለያለን::

View Details

እግዚአብሔር የእርሱ የሆኑትን አይተውም እንደ ተስፋ ቃሉ ያስባል:: አያለፍንበት ያለው ህይወትና ኑሮ:: እንደጠበቅነው ወይንም እንደተባለልን ባይሆንም እንኳ ጌታ የታመነ አምላክ ነው:: ያስባል:: በጊዜውም ይመጣል:: አስበኝ ያሉ ሁሉ ታስበዋል:: *** እግዚአብሔር ህዝቡን ያስባል :: ባህርይው ስለሆነ:: በዚህም ለእኛ ያለው በጎነቱና ፍቅሩ ደግሞም ምህረትና ቸርነቱ ይገለጥበታል::

View Details

የሮሜ መልዕክት.8:1-11

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 19

View Details

አማኝ ለብቻው ለእግዚአብሔር መገኘቱ ለመንፈሳዊ ህይወቱ ወሳኝ ነገር ነው:: ከእግዚአብሔር ደግሞም ከፀጋው ችሎት የሆነ አሸናፊነት በረከትና መንፈሳዊ ብልፅግና በህይወታችን የሚሆኑት ለእርሱ ብቻችንን ከመገኘታችን አንፃር ነው:: *** ፈፅሞ በክርስቶስ የረካ ማንነት ሊሆንልን የሚችለው ብቻችንን ለጌታ ስንገኝ ነው:: ይህም ደግሞ በክርስቶስ ሙሉ ሰው ጠንካራ ሥር የሰደደና የተተከለ ያደርገናል::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 18

View Details

የሮሜ መልዕክት. 5: 12-17

View Details

የሮሜ መልዕክት.7:1-25

View Details

የአማኝ ሰላምና እረፍት መፅናናትና ደስታ ከውጭ ፈልጎ የሚያገኘው አይደለም:: ነገር ግን በእምነት ከተቀበለው ከጌታ ኢየሱስ በውስጡም ካደረው ከመንፈስ ቅዱስ ነው::ከፀጋው ችሎት የተነሳ በውስጣችን ያለው ሰላምና እረፍት ከእኛ አለፎ ለቤታችንና ከእኛ ጋር ላሉት ሁሉ ይፈሳል:: **** የሰላማችንና የእረፍታችን ምንጭ ኢየሱስ በእምነት በእኛ ውስጥ እንደሆነ እኛም ደግሞ በእርሱ ወስጥ ልንሆን ሙሉ በሙሉ በፈቃዱ ውስጥ ልንገኝ ያሰፈጋል::

View Details

እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ የዘላለምን ህይወት ብቻ ሳይሆን በምድርም ሳለን በኃጢአት በሰጋና በአለም ላይ በድል አድራጊነት እንዲመላለሱ ሰጥቷል:: የእግዚአብሔር ቃል የሰው ህይወት በምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ ነው ይላል:: ነገር ግን በክርሰቶስ ኢየሱስ ላሉት ሰጋን ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋር የሰቀሉ እነርሱ በአሸናፊነት ይመላለሳሉ:: *** አማኝ ህይወቱ በድል አድራጊነት እየበረታ እነዲሄድ ህይወቱን እንደ እግዚአብሔር ቃል ሊመራ ደግሞም በፍቅር ሆኖ ሊመላለስ ይገባዋል::

View Details

የእግዚአብሔር ፈቃድ የተገለጠላቸው ሰዎች ትጉዎች ናቸው::በጸሎት በስራና በህይወት ትጉህ ይሆናሉ:: የተገለጠው የጌተ ፈቃድ ትጋትን ይጨምርላቸዋልና:: አማኝ በህይወቱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ ነው:: መንፈሳዊ ህይወቱ ትርጉም ያለው ይሆናል:: የእግዚአብሔር ፈቃድ ሲበራልን የምናልፍባቸውን ችግሮች የምናየው በተለየ እይታ ነው:: ልንደርስበት ወዳለው የጌታ ፈቃድ ለመድረስ የምናልፍባቸው አንደሆኑ እናያለን:: ሰለዚህ መንፈስ ቅዱስ በሚሰጠን ፀጋ በጸሎት የምንተጋ እንሆናለን::

View Details

መቆም ማለት በጌታ ተስፋ ቃል ላይ እንዲሁም በእኛ ሁኔታ በተገለጠልንና በተናገረን ላይ ተመስርተን በእምነት የተዋሀደን ያ የቆምንበት ነው:: ቆምን ማለት ቃሉ በእምነት ተዋህዶን የሆንበተ ማንነት ነው:: ደስ የምንሰኝበት የሚሰማንና የምንነካባቸው ሁሉ የቆምንባቸው አይደሉም:: መንፈሳዊ ነገር ሰሜት ላይ ብቻ የሚቀር ሳይሆን ከዚህ ያለፈ ወደ መሇን የሚደርስ ነው:: *** እግዚአብሔር የሚፈልገው ውጫቸውን በውስጣቸው በቆመ ማንነታቸው ያሸነፉ የገዙ ሰዎች ማውጣት ነው:: እነዚህ ናቸው ሁሉን ፈፅመው በሰው ልጅ ፊት ለመገለጥ የሚበቁት::

View Details

የእግዚአብሔር ቃል ለአማኝ የህይወቱ መርህ ነው:: እለት እለት ለዚህ የህይወቱ መርህ ለሆነው ለእግዚአብሔር ቃል የሚታዘዝ ደግሞም ህይወቱ ያደረገ አማኝ እርሱ ጥልቅ በሆነ መሠረት ላይ ተመስርቷል:: ተስፋውም የፀና ነውው:: *** የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተን መታዘዝ በሆነልን ጊዜ በማንኛውም በሚያናውጥ ነገርና ሁኔታ ፀንተን እንድንቆም ዋነኛ ምክንያት እርሱ ነው::

View Details

ዛሬ አለም አጥብቃ የምትፈልገው ሰው ሁሉ የሚሻው አንድ ነገር ሰላም ነው:: እውነተኛው ሰላም ግን ከሰላም አምላክ ከእግዚአብሔር ነው:: ሰለዚህ በእየለቱ ራሳችንን ልንጠይቅ የሚገባው ጥያቄ አንዱ በአንደበታችን ከምንናገረው በላይ በህይወታችን በነፈስ በመንፈሳችን የጌታ ሰላምና እረፍት አለ ወይ? ብለን ነው:: *** አማኝ እይታው ከዚህ ምድር አልፎ እግዚአብሔር ለልጆቹ ያዘጋጀውን ዘላለማዊ እርስት የጌታንም ዳግም መምጣት ሲያይ ሰላሙና እረፍቱ የበዛ ተስፋውም የፀና ይሆናል::

View Details

ሰው ሁሉ የየራሱ የሆነ ምርጫ አለው:: ነገር ግን እግዚአብሔር ልጆቹን እርሱ በፈቀደው መንገድ ይመራል:: ስለዚህ የልባችንን ፈቃድ ትተን በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ልንገባ ያስፈልጋል:: የማይመች እንዲሁም ትንሽና የተናቀ መስሎ ቢታየንም እንኳ በዛ ውስጥ የእግዚአብሔር ታላቅ ፈቃዱና ሀሳቡ እንዲፈፀም የስራው መጀመሪያ ነው:: ትንሽ ነው የተዋረደ ነው ባልንበት በዛ የእግዚአብሔር ታላቅነትና ከፍታ ይታያል:: ለእኛም መባረክና ወደ ከፍታ መውጣት ይሆናል::

View Details

የሚፀልይ ሰው ረጅሙን የእግዚአብሔርን ሀሳብና ሊሰራያለውን ዕቅዱን ያያል ደግሞም ይሰማል:: ባየውና በሰማውም በትጋት ይፀልያል:: እግዚአብሔር ሸክምን ወደ ሰው ሲያመጣ ያን ሸክም የራሱ አደድርጎ አንዲማልድ እንዲፀልይ ነው:: የሚፀልየውም በአዕመሮው እየተጨነቀ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ እየተረዳ ደሰ እየተሰኘ ይፀልያል:: *** ህይወት በዚህ ምድር በብዙ መከራና ፍርሀት የተሞላ ነው:: ነገር ግን ሰላምና እረፍት ወደ ህይወታችን የሚመጣው በፀሎት ሰንሆን ነው:: በእግዚአብሔር ፊት በፀሎት በቆየን ቁጥር ህይወት እየተሰራ ይሔዳልና::

View Details

የሮሜ መልዕክት.6:1-4

View Details

የሮሜ መልዕክት.5.12-21

View Details

እስራኤል በመንገዱ ሁሉ በጠላቶቹ ፊት የማሸነፉና የመሸነፉ ጉዳይ የሚያያዘው ለእግዚአብሔር ከመታዘዙና አለመታዘዙ ጋር ነው:: ምንም እንኳ ጠላቶቻቸው አሰፈሪዎች መስለው ቢታዩም እግዚአብሔር ግን እየመጣ አትፍሩ እኔ ከእናንተ ጋር ነኘ ይላቸዋል:: ደግሞም በድል ያስኬዳቸዋል:: እግዚአብሔር ዛሬም በቃሉ የታመነ ነው:: በየእለቱ ከሚከበን የስጋ የአለምና የሰይጣነ ፈተና ከውጊያው በአሸናፊነት አልፈን በእረፍትና በሰላም እንድንሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው::

View Details

የአማኝ መንፈሳዊ ሕይወት ከሚሰፋባቸው መንገዶች አንዱ ፀሎት ነው::ፀሎትም በእግዚአብሔር ቃል ነው:: የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ የእግዚአብሔርን ሀሳብ ፈቃዱንም ይገልፃል:: የእግዚአብሔር ቃል እነደሚያሳየንና ሸክም አድርጎ እንደሚሰጠን የማንፀልይ ከሆነ በዙሪያችን ካለው ከምንሰማውና ከምናየው ተነስተን ብቻ እነጨነቃለን:: ችግሮች የሚመሩን እንሆናለን:: በፀሎት ሕይወት እያደግን ስንሄድ በእግዚአብሔር በሆነው ፅድቅ ደግሞም እኛም መሆን ባለብን ግድ ወደሚለን ደረጃ እንመጣለን::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 5: 6-11

View Details

ጸሎት ከሚታየውና ከተሰማው ከምንናወጥበት ችግር አልፎ እግዚአብሔር ምን ይላል ብሎ መጠየቅና ማየት ከመትረዳውም የጌታ እጅ ጋር መገናኘት ነው:: በዙሪያው ካለው ድምፅና ጭንቀት ነፃ የወጣ እርሱ ከአርያም ያለውን ድምፅ ይሰማል:: ነገሮች ሳይለወጡም የእርሱ ህይወት በመንፈስ ቅዱስ ይለወጣል:: **** በዚህ የጸሎት ትምህርት በአንድ አማኝ መንፈሳዊ ህይወት ውስጥ የህይወትና የሸክም ጸሎት ምን እንደሚመስሉ በጥልቀት አናያለን::

View Details

ፀሎት አንዱ እግዚአብሔርን የምንማርበት ህይወት ነው:: በቃሉ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን መህረትና ቸርነት ደገሞም የማዳኑን ሀይልና ታማኝነቱን በፀሎታችንውስጥ እንማራለን:: የእምነት ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የሚያነካካን ነው:: በእምነት ወደ እግዚአብሔር ፊት የቀረበ ሰው ከፀሎቱ በኃላ በቀደመው ማንነትና ስሜት አይሆንም:: በመፅናናትና በተሰፋ በተሞላ በሌላ ማንነት በአሜን ይነሳል:: *** ነገሮችን ሁሉ በራሳችን ከማየት ወጥተን በእግዚአብሔር አይን ስናይ ፀሎታችንም በፊቱ እነደ እርሱ ፈቃድ ይመለስልናል:: እኛም ከድንጋጤና ፍርሃት ይልቅ በምሰጋናና በተሰፋ እንሆናለን::

View Details

የእግዚአብሔር ሰዎች መውጣትና መግባታቸው የሚሰሩትና የሚናገሩትም በእግዚአብሔር ፈቃድ ቁጥጥር ውስጥ ራሳቸውን አሰገዝተው ሊሆን የተገባ ነው:: ሰሜትና ሁኔታ የሌሎችም ሰዎች ፈቃድ አይገዛቸውም:: ከፈቃዱ ቁጥጥር በወጣን ጊዜ የሚገዛን የስጋ የአለምና የኃጢአት ሀሳብ ነው:: በዛ ደግሞ ብዙ ኪሳራ ፍርሀትና ድንጋጤ ተሰፋ መቁረጥ ይሆናል:: *** የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይገልጣል:: ሰለዚህ ለቃሉ የተከፈተ ልብ ሊኖረን ይገባል:: ለዚህም ደግሞ የሚረዳ ፀጋ አለ::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 17

View Details

አባትነት የጀመረው የሁሉ አባ ከሆነው ከእግዚአብሔር ነው:: አባት ተብሎ ሲጠራም ቸርነቱን ለጋስነቱን ተንከባካቢነቱንና ደራሽነቱን ይገልፃል:: ሰውም አባት ሲሆን ይህን በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው የአባትነት ባህርይ በጥቂቱም ቢሆን እንዲገለጥበት ነው:: አባት ለቤቱ መሪ ራስ ልጆቹም ደግሞ አባት ነው:: ስለዚህ የአንድ ቤት የመንፈሳዊነት ጣሪያው አባት ቤቱን ይዞ በእግዚአብሔርፊት በጸሎት በአምልኮ የመገኘቱን ያህል ነው:: እንዲሁም የቤቱ ሰላም ደግሞ የሚጠበቀው በነገሮች ሁሉ አባት ከሚኖረው የልብ ስፋት መጠንና ራሱነም ለመለወጥ ዝግጁና ፈቃደኛ የሆነው ያህል ነው:: *** በዚህ ትምህርት የአባትን በቤቱ ላይ ያለውን ድርሻና ከልጆቹም ጋር ሊኖረው የሚገባውን ግንኙነት በጥልቀት እንማራለን::

View Details

አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ አማኝ በየእለት ጉዳይ በሚያየውና በሚሰማው አይያዝም ደግሞም አይጨነቅም:: ምክንያቱም ልቡ የተያዘው በዘላለሙ ነገር ለላይ ሰለሆነ:: ከእግዚአብሔር ጋር ስንራመድ አካሄዳችን እርሱን ደስ የሚያሰኝ እንዲሆን የሚረዳንን ፀጋና የመንፈሱንም ማፅናናት የምንቀበለው የለይኛውን ትልቁን አይታ እንዳየን መጠን ነው: *** እለት እለት በፈታችን ከሚቀመጡት እንቅፋቶች ባሻገር ዘላለማዊውን በማየት ከምሬትና ከሀዘን ደግሞም ተስፋ ከመቁረጥ እንጠበቃለን:: የምስጋና ሰዎችም ያደርገናል::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 16

View Details

የእግዚአብሔርን ኤልሻዳይነት መመስከር መናገር የምንችለው አይናችን ተከፍቶ እርሱን ያየነውን ያህል ነው:: የልብን አይን የሚከፍት እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነው:: በስጋ አይን የምናየው የምንጠይቀውም ምድራዊ የሆኑ ለጊዜው የሆኑ ደግሞም የሚያልቁና የሚጠፉ ናቸው:: የልብ አይን ሲከፈት ግን ለአሁኑ ደግሞም ለወደፊት ለዘለአለም የሆነውን ሁሉ ነው:: እርምጃችንም በመሰለኝና በተሰማኝ ሳይሆን ተረድተንና አይተን እንራመዳለን:: *** የመጨረሻው ዘመን ትልቁ ችግር በጸሎት ያለመፅናት ነው:: በመቆየት በፀሎት ፀንቶ በመቆም የእግዚአብሔር ጉብኝት ይመጣል:: ማየት ይሆናል:: ወዳዘጋጀውም ህይወትና በረከት መግባት ይሆናል::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 5:1-5

View Details

የሮሜ መልዕክት. 4:1-25

View Details

እግዚአብሔር ሰውን በፊቱ እንዲሆን በንፅህና እንዲያመልከውና እንዲያገለግለው የመረጠው አለም ከመፈጠሩ አሰቀድሞ ነበር:: ይሁንጂ በአለመታዘዝ ምክነያት ሰው ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ:: በተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቅር በልጁ በኢየሱስ ከርስቶስ በሞቱና በትንሣኤው ወደ ወጣበት ወደ እግዚአብሐር ክብር ወደ ፊቱ ተመልሷል:: ሰለዚህ አማኝ በእግዚአብሔር ፊት ፀንቶ የሚቆመው በመንፈስ ቀዱሰ ቁጥጥር ስር የሆነውን ወፅድቁና በፀጋው የተሞላውን ያህል ነው:: በፊቱ መሆን በፀጋው ነው:: በፊቱ መፅናት ግን ዋጋ በመክፈል ነው ለአለም ለኃጢአት ለሰጋ እምቢ በማለት:: በመሞትነው::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 3:1-31

View Details

ለሰው ሁሉ የጥያቄ መልስ የሚሆነው ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሰው የተሰጠ ጨለማውንም የገለጠ እርሱ ወንጌል ነው:: ወነጌል ሁሉ ሊቀበሉት የሚገባ አስደናቂው የእግዚአብሔር መህረት የተገለጠበት ነው:: ወንጌል የእውነት ሁሉ ሚዛን ነው:: እርሱም ክርስቶስ ኢየሱስ ነው:: *** አማኝ በዘመኑ ሁሉ ሊኖረው የሚገባ የማይለወጥ ትልቁ አጀንዳ የተቀበለውን ይህን የወንጌል እውነት ለሌሎች በቃልና በኑሮ ማወጅና ማሳየት ነው::

View Details

ክርስቲያን የላይኛውን ዙፋን የእግዚአብሔርን ክብር በዚህ ምድር ለሠወከል በመጀመሪያ በላይ ያለው ክብር ሊበራለት ይገባል:: ያለበለዚያ የሚሰማውና የሚያየው ሁሉ የሚያሰፈራውና የሚያስደነገጠው ይሆናል:: ሰውን በዚህ ምድር ሊያስፈራውና ሊየሰጨንቀውና ሊያውከው የሚችለው ትልቁ ሞት ነው:: አኛ ደግሞ የተረዳነው በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ጌታ ነው:: *** ቤተክርስቲያን ይህን ትልቁን ስልጣን እየተለማመደች ስትመጣ ለማንኛውም አንበርካኪ ጉልበተኛ የማትገዛ ትሆናለች::

View Details

በዚህ ምድር ስንኖር በቁጥር በተወሰነች ዘመናችን የመኖራችንና የሰላማችን ዋሰትና እግዚአብሐር ነው:: እረፉ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ እንዳለ:: የእግዚአብሔር ቃል የአግዚአብሔርን ፈቃድ ሀሳቡንም የገልጣል:: በተገለጠልን የቃሉ ብርሃን ልንገኝ ሁልጊዜም በብርሃኑ ፊት ልንሆን ያስፈልጋል:: *** በሚያስፈራ ደግሞም በሚያስጨንቅ ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ እንኳ በዚህም ውስጥ ሰላምና ተስፋ ሀይልና ብርታት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 1: 18-32

View Details

የሮሜ መልዕከት.2:1-29

View Details

በሰው ህይወት በዙ ውጣ ውረድ ደግሞም ብዙ መውደቅ መነሳት አለበት:: በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰው ይመለስ ዘንድ ነው: ለዚህም እንደገና እድል ይሰጣል:: *** ከመመለስ ጋር የእግዚአብሔርን ሞገስ ደግሞም በረከቱን እናያለን:: የእግዚአብሔርን አብሮነትም እለት እለት በኑሮአችን እናያለን::

View Details

ለአማኝ የተቀደሰው ሰፍራ የሰላም ወንጌል ነው:: በዚህ ሰፍራ መቆሙን ማስተዋልና ሊያደርግ የሚገባውን ሊያደርግ የተገባ ነው:: ይኸውም የመጀመሪያው የራስን ሸክም መጣልና የእግዚአብሔርን ሸክም መሸከም ነው:: የእግዚአብሔር ሸክም ደግሞ ሰላም የሞላበት ተስፋና መፅናናት ያለበት ነው:: የሰው ታሪክ በመለኮት ከሚተረጎምበት ቀን ጋር እስኪገናኝ ሰው በፀሎት ስፍራው ለም በዚህ አልፋለሁ ለምን ይሁ የሆንብኛል እያለ ያለቅሳል:: ለቅሶው የሚቆመው የሸክም ለውጥ የታሪክ ለውጥ ሲሆን ነው:: የእኛ ሸክም የእግዚአብሔር ሸከም ሲሆን የመለኮተ ትርጉ ሲመጣ:: *** ትክክለኛው የህይወታችን ታሪክ የሚተረጎመው ሁሉን በሚቆጣጠር በመለኮት ነው::

View Details

እስራኤል ለእግዚአብሔር በመገዛት በመታዘዝም በሄደበት በመንገዱ ሁሉ በጠላቶቹ ላይ ድል እያደረገ ተጉዟል:: ጌልጌላ አንዱ ከእግዚአብሔር ጋር ለመስማማታቸው ምልክት የሆነ ሁልጊዜም የሚያስታውሱት ሰፍራ ነው:: ዛሬደግሞ የክርስቲያን በህይወቱ የድል ብስራት የታወጀበት ቀራኒዮ ነው:: ሁልጊዜ የሚተወስ ሀይል የሚታደስበት ደግሞም ጌታንና የድሉን አዋጅ ሁልጊዜ የምንሰማበት::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 1: 17-18

View Details

የአንድ አማኝ የመነፈሰዊ ህይወቱ ጥንካሬ እዚአብሔር ሁለን ቻይ ደግሞም ሁሉን የሚቆጣጠርና ከእርሱ የሚሰወር የሌለ መሆኑን በተረዳበትና በተገለጠለት መጠን ልክ ነው:: የምናልፍበት ሁኔታ አሰጨነቆን በጌታ ያልታየን ቢመሰለን እነኳ እግዚአብሔር ግን ማንንም አያሰጨንቅም ነገር ግን ከቁጥጥራችን ውጭ በወጣው በዛ እርሱ እኛን በግላጭ የሚያገኝበት ይሆንል:: *** ሁላችን ሁሉን በሚቆጣጠር በእግዚአብሔር አይኖች ፊት ነን:: በምንም ሁኔታ ውስጥ እንለፍ እርሱ እግዚአብሔር ለኛ በሆነልን ውሰጥ ያሳልፈናል::

View Details

በእግዚአብሔር ቃል የተሞላ በተስፋውም ያለ ሰው እርሱ አዕምሮው የተለወጠ የራሱን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ትክክል የሆነ ነው:: የተሞላነው የአግዚአብሔር ቃል አዕምሮአችንን ያድሳል ቋንቋችንንም ይቀይራል:: በጎውንም እንናገራለን መሪያችንም አርሱ ቃሉ ይሆናል:: *** አዕምሮው በቃሉ ለተሞላ ለእርሱ በዚህ አስጨናቂው አለም ዕረፍት ይሆናል ሰላምና ተስፋም ይሆናል:: ራሱንና የራሱ የሆነውን ሁሉ ለጌታ አሳልፎ ይሰጣል ደግሞም ለሌሎችም ይተርፋል::

View Details

እግዚአብሔር ብርሃን ነው:: ይህን ብርሃን የምንካፈለው የእግዚአብሔርም ፊት የሚበራልን እኛም በቤቱ ፍርሀትና ትህትና የሚኖረን ደግሞ በቃሉ ነው:: ሰለዚህም ሰው ለእግዚአብሔር የሚሆነው ቃሉ የበራለትን ያህል ነው:: *** ቃሉ ሲገለጥ በረከትና ህይወት እንደሚገለጥ እንዲሁ ቅድስናም ይገለጣልና ቃሉ እንዲጠቅመን በብርሃኑ ውስጥ ራሳችንን ልናይ ያሰፈልጋል::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 1:14-17

View Details

ሁኔታ ላደከመውና ላዘነው ደግሞም ነገሬ ሞቷል ብሎ ተስፋ ለቆረጠ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሁልጊዜም ተስፋ አለ:: ተስፋን የሰጠውም ጌታ እርሱ የታመነነው:: ወላጆች በልጆቻቸው እውነተኛ ተጠቃሚ የሚሆኑት በአለም ከሚደርሱበት ስኬት ይልቅ በጌታ ሲያገኟቸው ነው:: *** ከሁሉ አስቀድሞ ግን እኛ ራሳችን የራቅን ልንቀርብ ለፈቃዱም የተገዛን ልንሆን ልንመለስ ለጌታም የተገኘን ልንሆን ያስፈልጋል:: ለዚህም የሚረዳ ደግሞም የታመነ ፀጋ አለ::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 15

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 14

View Details

ሰው በእግዚአብሔር ትአዛዝ ውስጥ ሲሆን ደግሞም በፈቃዱ በሆነበት በዛ እግዚአብሔርን ካወቀበት በላይ የሚያውቅበት እግዚአብሔርም ራሱን የሚገልጥበት ነው:: እየታዘዝን በፈቃዱ ስንኖር እግዚአብሔር በዙሪያችን ያለውን ስለእኛ ያዝዛል:: ብርሃንን በጨለማው ላይ ያወጣል:: የማይቻለውን እንድንችል አይሆንም የተባለው እንዲሆን ያዝዛል:: *** አማኝ የሚኖረው በበቃበት ነገር ሳይሆን በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው:: እግዚአብሔር ለአሁን ደግሞም ወደፊት ለዘመኑ ሰለእርሱ ያዛል::

View Details

ሰው እግዚአብሔርን አሰቀድሞ አይቶ ራሱን ሲያይ ትክክለኛ ማንነቱን ደግሞም በትክክል ያለበትን ሁኔታ ያያል:: የልቡናው አይኖች ያልበሩለት አርሱ ወዴት እንደሚሄድ ምን እንደሚያደረግም አያውቅም:: በፊቱ ያለውን ብቻ በስጋ አይኖቹ ያያልና:: ስለዚህ እግዚአብሔርን ማየት የምንችልበት የልቡና አይኖቻችን ሊበሩልን ያስፈልጋል:: *** የልቡና አይኖቻችን ሲበሩልን ከምሬትና ተስፋ ከመቁረጥ ደግሞም ከክፉዉ ወጥመድ እናመልጣለን:: ከፊታችን ያለው መንገድ የቀና ይሆናል:: በምስጋናም እንሆናለን::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 1:11-13

View Details

ሁለንተናውን ለእግዚአብሔር የሰጠ ያስግዛ እርሱ እግዚአብሔር አለኝ እርሱ የእኔ ነው ለማለት አይቸገርም:: እግዚአብሔርም ለራሱ መንገድ የሚያደርገው ለሌሎችም እንዲተርፍ ለበጎ ነገር የሚያዘጋጀው እንደዙህ አይነቱን ሰው ነው:: እግዚአብሔር በህይወታችን የሚያልፈው በቃሉ አማካኝነት ነው:: ሰለዚህ ቃሉ ካለን እግዚአብሔር ይገለጥናል:: ከፊታችንም ያለውን ነገራችንን አቅልሎ ያሳየናል ሀይልና ጉልበትም ይሆንልናል::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 1- 7

View Details

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከእግዚአብሔር ጋር ላልታረቀ የዘለአለሙን ብቻ ሳይሆን በዚህም ምድር እውነተኛ ነፃነት ሰላምና እረፍት አይሆንለትም:: እውነተኛ ነፃነት ሰላምና እረፍት የሚሰጥ እርሱ ወንጌልና ወንጌል ብቻ ነው:: *** ወንጌል ለሰው ሁሉ ነው:: ይህም ወንጌል ሊመጣ ያለው ተስፋችን የሆነ ክርሰቶስ ነው:: በዚህ ምድር የመኖራችን የላቀው አላማ ይህን የመዳን ወንጌል ላልሰሙት ማሰማት ማወጅ ነው::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 1: 1-17

View Details

እግዚአብሔር ምህረትን በህይወታችን ከሚገልጥባቸው ሁኔታዎች አንዱ ከወደቅንበት እንድንነሳ ከሳትንበትም እንድንመለስ ሁለተኛ እድል በመስጠት ነው:: ይህን ምህረቱን የሚገልፀው ደግሞ በመንገዳችን ለሀዘናችን መፅናናት ከወደቅንበትም ለመነሳት ምክንያት የሚሆኑ ሰዎችን በመስጠት ነው:: *** ምን እንኳ የምናልፍበት ሁኔታ ብዙ ፈተና ብዙ ምሬት ያለበት ቢሆንም እኛ ለመመለስ በፈቀድን ጊዜ እግዚአብሔር ይመራል እደገና እድል ይሰጣል::

View Details

የአማኝ የሰላሙ መጀመሪያ የእግዚአብሔር ን ታላቅነት ባየው ነው;: ያደከመን እረፍት ያሳጣን ነገር ሁሉ ከእርሱ ታላቀነት በታች ነው:: ነጋችንን የሚያውቅ ጌታ እንድንታመንበት ይፈልጋል:: ችግሩ እያለ ማስፈራራቱም እያለ ሰላማችን ግን የበዘ ይሆናል:: ማረፍ ማለት ነገርን ሁሉ ለጌታ መተው ነው::ደግሞም ጌታ አለኝ እርሱ አለኝ ብሎ በእርሱ መደገፍ ነው: በቃሉ መታመን ነው::በዚህች በምትናወጥ አለም ፈውሰ መፅናናት ሰላምና እረፍት በእርሱ ነው::

View Details

የሮሜ መልዕክት. 1: 1-25

View Details

እምነት ጉዞ ነው:: ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምተን የምንጓዘው የህይወት ጉዞ:: ከማየት ከመዳሰስ ወጥተን እንደሰማን እንደበራልን ጌታ እንዳለን ብቻ ማድረግ እርሱ አንዳለ መሆን መብቃተ ነው:: *** እምነት የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው:: ነገር ግን ደግሞ በእውቀት የምንወስደው እርምጃ መኖር አለበት::

View Details

አማኝ በጌታ የሚኖረው የሚመላለሰውም የእምነቱን መጠን ያህል ነው:: መቆማችን በፈተናም ሁሉ ፀንተን መቆማችን ያመነውን ያህል ነው::ሰለዚህ አንዳንድ ጊዜ ከእምነታችን መጠን ያለፈ ችግር ሲደርስብን እግዚአብሐር የተወን እሰኪመስለን ድረስ እንጨነቃለን:: ጌታ ግን በፀጋው ይረዳንና በእምነታችን እንድናድግ ያደርጋል:: የህይወታችን አሸናፊነትና ድል እግዚአብሔርን በእምነት በመኖር የሚሆኑ ናቸው::

View Details

የይሁዳ መልዕክት:: ከቁጥር 1-25

View Details

ጠላት ብዙዉን ጊዜ ሊያጠምደን የሚሞክረው እውነት ባልሆነ ነገር ግን እውነት በሚመስል ነገር ነው:: ስለዚህ ነው በነገሮች ላይ ወስነን አንድ እርምጃ ከመራመዳችን በፊት ልንመረመር ደግሞም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ ያለብን:: *** ጠላት ይሸነግላል አማኝ ግን የሚመራው በእግዚአብሔር መንፈስ ሰለሆነ አስቀድሞ የመነፈስ ቅዱስን ድምፅ በመስማት ነገሮችን ይመረምራል::

View Details

አማኝ በዚህ ምድር የሚኖረው ራሱን ላሰገዛለት ለጌታ ነው:: ለእግዚአብሔር መንግስት የመኖራችንም ፍሬ ከራሳችን ወጥተን ለሌላ ስንሆን ነው:: ለሌላው ለመሆንና የመንፈስን ፍሬ ለማፍራት ደግሞ ዋናውና ቀዳሚው የራስ ሸክም የሆነውን በጌታ ላይ መጣልና ከጭንቀት ከፍርሀት ነፃ መሆን ነው:: *** ለሌሎች መሆን አንዱ በእግዚአብሔር ፀጋ ታግዘን ዋጋ የምንከፍልበተና ጌታን የምናሳይበት ከራሳችንም ወጥተን ለተፈጠርንበት የእግዚአብሔር አላማ የምንኖርበትነው::

View Details

የይሁዳ መልዕክት:: ከቁጥር 21-25

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 13

View Details

የይሁዳ መልዕክት:: ከቁጥር 20-21

View Details

የይሁዳ መልዕክት:: ከቁጥር 12-16

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 12

View Details

አማኝ ሊደርስ ወደሚፈልገው መድረስ ሊያገኝ የሚፈልገውን የሚያገኘው መሆን የሚፈልገውንም መሆን የሚችለው ከፊት ለፊቱ ያለውን ቅጥር በማለፍ ነው:: ያለበለዚያ ምኞት ብቻ የሆናል:: ፍርሀት ይሉኝታ የቅር አለማለት ዝናና ከብር ሌሎችም እነዚህን የሚመስሉ ሁሉ ከፊታችን የሚቆሙ ቅጥሮ ናቸው:: *** በመንፈሳዊ ህይወታችን ባለጠጎች ልንሆን ደግሞም በድል አድራጊነት መጓዝ የምንችለው ከፊታችን ያለውን ቅጥር አልፈን ስንሄድ ነው::

View Details

የአንድ መንፈሳዊ ሰው ጥንካሬ ወደፊት ሄዶ የእግዚአብሔርን ፀጋ መቀበሉ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የተቀበለውን መጠበቁ በተቀበለውም መገኘቱና መቆሙ ነው:: የተቀበለውን ፀጋ ለማሰጠበቅ ደግሞ ዋጋ ማስከፈሉ ግድ ነው:: በህይወታችን ምንም ያህል እናድርግ ምንም ያህል ፀጋ በህይወታችን ይገለጥ ህይወታችንን የመጠበቅ አቅማችን ያለው ራሳችንን ለእግዚአብሔር የሰጠነውን ያህል ነው:: ሰለዚህ ዕለት ዕለት ህይወታችንን እየመረመርን ለእግዚአብሔር ያልተሰጠውን ማንነታችንን ልናስገዛ ልንቀድስ ያስፈልጋል::

View Details

የይሁዳ መልዕክት: ከቁጥር 10-11

View Details

በደረሰብንና በምናልፍበት ችግርና ፈተና ውስጥ ሳናማርር ወይንም መራራ ሳንሆን በፀሎት ራሳችንን በማዋረድ የጌታን ፊት ልንፈልግ ደግሞም የጠፋብንን ያጣነውን ብቻ ሳይሆን ከጌታ የተቀበልነውን ብዙዉን ልናይ ምስጋናና እምነት ሊሆንልን የተገባ ነው:: *** ጠላት ችግራችንን አግዝፎ እንድንማረር ያደርጋል:: እግዚአብሔር ግን በችግራችን ላይ ምህረቱንና ቸርነቱን ይገልጣል:: ሁኔታዎቻችንንም ይለውጣል::

View Details

እግዚአብሔር የሚለውን ተረጋግቶ መስማት ለመፅናናታችንና ለፈውሳችን ደግሞም ከክፉ አደጋና ፈተና ለመዳናችን ምክንያት ይሆንልናል:: ዛረ የምንሰማው ነጋችንን ብሩህ ያደርጋል:: ደግሞም በመከራ ውስጥ አፅንቶ ያቆመናል:: *** በህይወት ዘመናችን አለኝ ብለን የምንኮራበት የምንመካበትና የምንተማመንበት ነገር ቢኖር እርሱ እግዚአብሔር የተናገረን እኛም የሰማነው ነው::

View Details

አማኝ በዚህ ምድር ሲኖር የልጁን የኢየሱስ ክርስቶስን መልክ እንዲመስል የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው:: ይኸውም በፅድቅና በእውነት ሊመላለስ በጨለማው አለም ብርሃን ጣዕም ለሆነው ለሌለው አለም ጨው ሆኖ መገለጡ ነው:: የልጁን መልክ መምሰላችን መገለጫው በጊዜውም አለጊዜውም በእኛ ህይወት የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ባህርያት መንፀባረቁ ነው::

View Details

የይሁዳ መልዕክት: ከቁጥር 7-10

View Details

የይሁዳ መልዕክት: ከቁጥር 1-8

View Details

አማኝ በመንፈሳዊ ህይወቱ በጎ ከመኘት ከማሰብና ከመፈለግ አልፎ ወደ መሆንና ወደ ማድረግ መንፈሳዊ ደረጃ የሚመጣው ለዛ ያልበቃውን ማንነቱን በብርሀን ውስጥ እያገኘ በእግዚአብሔር ፀጋ ዋጋ መክፈል ያለበትን አየከፈለና መውጣት ካለበትም እየወጣ ሲሸጋገር ነው:: *** በብርሀን ውስጥ ያልበቃውን ማንነታችንን ባገኘን ጊዜ የሚረዳንን ፀጋ ተቀብለን ካለንበት ለመውጣት ፈቅደን ራሳችንን ልናዋርድ የተገባ ነው::

View Details

አግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ከራሱ ጋር አሰታርቆናል:: ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋው መቆረስ የጥሉን ግድግዳ ስላፈረሰ እዳችንም ሰለተከፈለ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አድርገናል:: ይህም የህይወት ሰላም በእኛ ዘንድ የሚጠበቀው በክርስቶስ ውስጥ በመሆን ነው:: *** ሰላም ህይወት ነው ሰላም ኑሮም ነው:: በክርስቶስ ውስጥ እስከሆን ደግሞም የምናከናውነውን ሁሉ በጌታ ፍቅር ወስጥ ሆነን እስካደረግን ድረስ:: በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ ጌታ ሰላማችን ነው::

View Details

እጃችን አይታጠፍ ኢያሱ.8:18-26

View Details

የአማኝ ትልቁ ዋስትና የሚያመልከው እርሱ እግዚአብሔር የሚሰማ አምላክ ነው:: የሚለው ነው:: በእኛ ሁኔታ ደግሞም በነገሮች የማይወሰነው ጌታ የሚሰማው ሁልጊዜ ነው:: መልሱ ግን በራሱ ጊዜና በወደደው መንገድ ነው:: ትልቅነቱን ታማኝነቱን ደግሞም እንደ ቃሉ መሆኑን በማስረገጥ ይመልሳል:: *** የምናልፍበት ነገርና ሁኔታ እንዳልተሰማን አስመስሎ ጨለማውን ቢያሳየንም ጌታ ግን በክብር ይመጣል ብርሃንም ይሆናል::

View Details

የይሁዳ መልእክት ቁጥር 3-8

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 11

View Details

የይሁዳ መልእክት:: ቁጥር 1-5

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 10

View Details

እግዚአብሔር በባህርዩ ፃድቅ አምላክ ነው:: ይህም የትክክለኛነቱና የቅንነቱ መግለጫ ነው:: ይህ የተሰወረበት አማኝ ለራሱ የመሰለውን ይናገራል :: በእግዚአብሔርም ላይ የድፍረት ቃል አስከ ማውጣት ይደርሳል:: የእግዚአብሔር ፅድቅ የተገለጠለት እርሱ በመጀመሪያ ከራሱ ነገር ይወጣል ራሱንም በፊቱ ያዋርዳል:: መንፈሳዊ ጤንነታችን ያለው እግዚአብሔር ፃድቅ ነው ባልንበት ላይ ነው::

View Details

እግዚአብሔር ለጥያቄዎቻችን መልስ የሚሰጠው በእኛ ጊዜ ደግሞም እኛ በምንጠብቀው መንገድ አይሆንም:: ሰለዚህ ብዙ ጊዜ ጌታ የዘገየ ደግሞም የተወን ይመስለናል:: ነገር ግን እግዚአብሐር ሁሉን ለክብሩ በሚሆን መንገድ ይመልሳል:: ባልተጠባበቅነውም ሁኔታ ራሱን ይገልጥበታል :: ሁሉን ቻይነቱን ማዳኑን ቸርነቱንና በጎነቱን::

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 8:7-14

View Details

ጥያቄ እና መልስ ክፍል 9

View Details

አማኝ እግዚአብሔርን አንደ አምላክነቱ መጠን እያወቀው በሄደ ቁጥር እረፍት እየተሞላ ይሄዳል:: ታላቅነቱንና ሁሉን ቻይነቱን ታማኝነቱንና የማይለወጥ እንደ ቃሉ መሆኑን መረዳት: ከምናልፍበት አንዳንድ ሁኔታዎች ተፅእኖ ሥር እንዳንወድቅ ደግሞም በክፉው የማስፈራሪያ ወጥመድ ውስጥ እንዳንወድቅ ያደርጋል:: የእግዚአብሔር አይኖች በምድር ዙሪያ ሀሉ ያያሉ:: ስለዚህ የኛ ነገር ሁሉ በእርሱ ፊት ነው:: ይህን ማወቅ እግዚአብሔርን በአምላክነቱ ችሎት ማወቅና ማክበር ደግሞም በእርሱ መደገፍ ነው::

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 8:4-7

View Details

የፅድቅና የህይወት ጉዳይ ጌታ በመስቀል ላይ ራሱን የሰጠበት ጉዳይ ስለሆነ በዚህ መደራደር ወይንም ይህን ተክቶ በህይወታችን ስፍራን የሚይዝ ሊኖር ፈፅሞ አይገባም:: እግዚአብሔር በፀጋው የሚገልፀው ወይም የሚሰራው የእኛን ህይወት ሳይሆን የሚያሳየው የፀጋውን ነገር የእግዚአብሔርን ሉዐላዊነትና ምህረት ነው የሚያሳየው:: *** በዘመናችን ደግሞም በዙሪያችን ያለውን ክፋት አሰራሩንም እያሰተዋልን በፅድቅ ልንነቃ ከኃጢአትና በደልም ልንርቅ ጊዜው ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው::

View Details

ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ህይወታቸው አላማ ወንጌል ነው:: ያለተስፋ በጨለማ ላሉት ብንሃን በረከትና መፅናናት ለመሆን ነው:: የምናልፍባቸው ፈተናዎችና አንዳንድ አስጨናቂ ሁኔታዎች የሚያጠፉን ሳይሆኑ በእኛ ሁኔታ እግዚአብሔር ሊስራ ያለውን የዘላለም ፈቃዱን ሊገልጥበት ደግሞም እኛንም ወደ ላቀው የመኖራችን ምክንያት ወደ ሆነው ወደ ወንጌል እውነት ምሰክር ሊያመጣን ነው::

View Details

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የዘለዓለም ህይወት እንድናገኝ ከዘለዓለም በፊት በእግዚአብሔር የተወሰነ የመዳን መንገድ ነው:: የዳኑትም ደግሞ የልጁን መልክ እንዲመስሉ እነዲሁ በዘለዓለሙ ጌታ ከዘለዓለም በፊት የተወሰነ ነው:: የልጁን መልክ ወደ መምሰል የምንመጣው ሠራተኛ የሆነው ጌታ እግዚአብሔር በመንፈሱና በቃሉ እየቀረፀ ደግሞም በማንወዳቸው አንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ በማሳለፍ ነው:: *** የምናልፍበት ሁኔተ ሁሉ በእግዚአብሔር እውቀት ውስጥ ያለ ሲሆን ለእኛም ደግሞ የሚያበረታ የሚያቆምና የሚየፀናም የእርሱ ፀጋ አለ::

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን -ምዕራፍ 7:11,12 ምዕራፍ 8:1-3

View Details

ኢሱስ ክርስቶስን በማመን በዳግም ልደት የእግዚአብሔር ልጆች በሆንን ጊዜ የእርሱ መንፈስ በእኛ ውስጥ ይኖራልና መንፈሳውያን ሆነናል:: የእግዚአብሔር ልጆች በአለም ካሉት የሚለዩት በሚታየውና በሚሰማው ሁሉ በደስታም ሆነ በሀዘን ተፅዕኖ ውስጥ የማይወድቁ ነገር ግን ከነገሮች በስተጀርባ ያለውን የእግዚአብሔር ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ የሚረዱ በመሆናቸው ነው:: *** በነገሮች ላይ መንፈሳውያን በመሆናችን ከጠላት ማታለል ደግሞም ማስፈራራት እንጠበቃለን:: ከእኛም አልፎ ለሌሎች በረከትና መፅናናት ምክንያት እንሆናለን::

View Details

ፍፃሜያችንን ብዙ ጊዜ የሚወስነው ዛሬ የምንወስነውና የምንሰራው ነው:: እግዚአብሔር ማንንም በክፉ አይፈትንም ተበሎ እንደተፃፈ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ እግዚአብሔር ፃድቅ አምላክ ነውና የመጀመሪያውን ጥያቄ መጠየቅ ያለብን ራሳችንን ነው:: በመከራ ጊዜም የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ ደግሞም በተዕግስት መቆየት ለመፅናናት ብሎም ከችገር ለመጣት መንገዱ ነው:: *** እግዚአብሔር የመፅናናታችን እንጂ የመከራቸን ምክንያት አይደለም::

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 7:1-13

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 6:1-12

View Details

እግዚአብሔር የፈጠረውን ሁሉ ለራሱ ክብር ፈጥሮታል:: ሰውም የተፈጠረው ለእግዚአብሔር ክብር ነው :: በእርሱ ክብር ውስጥ ሆኖ ለእግዚአብሔ የሚገባውንም ክብር እንዲያመጣ::

ከኃጢአት በሰተቀር ሰው የሚያደረገውን ሁሉ የሚያደርገው የእግዚአብሔርን ክብር ማዕከል በማድረግ ነው:: ኃጢአት ከሰው ህይወት የእግዚአብሔር ክብር እንዲጎግል ምክክያት ሆኗል:: ስለዚህ ሰው እንደቃሉ ሲኖን ደግሞም ስለ ኃጢአቱ ንስሀ ሲገባ ለእግዚአብሔር ክብርን ያመጣል:: *** እግዚአብሔር ለልጆቹ የሚያደርገው ሁሉ በክብር ነው:: የምናልፍበት ባይገባንም ያለ ጌታ ፈቃድ አንዳች በእኛ ላይ አይሆንምና ይህም ለእርሱ ክብር ነው::

View Details

እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የጠራን ለድል ህይወት ነው:: ለአሸናፊነት ህይወት ነው:: ይህ የአሸናፊነት ህይወት ደግሞ እውን የሚሆነው በቃሉ እውነት በተመላለስንበት በፅድቅና ቅድሰና በኖርንበት ነው:: በአንደም ወይም በሌላ የተሸነፍንበት ነገር ቢኖር ያለንንም አሰማርከን ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ወደ ፈቃዱ በመመለስ ቃል ኪዳናችንን በማደስ በዛ እንደገና ድል አለ የምርኮ መመለስም አለ::

View Details

ተስፋ ቃል ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል አሁንስ ተስፋዬ ማነው? እግዚአብሔር አይደለምን እንደሚል : ተስፋ ራሱ እግዚአብሔር ነው:: አግዚአብሔር ከተሰጠን ተስፋ በላይ ነው:: ነገር ግን ወደ እኛ የሚመጣው እግዚአብሔር ለእኛ የሚሆንልን እንደሰጠን ተስፋ መጠን ልክ ነው:: *** መንፈሰ ቅዱስ በእኛ ውስጥ የመኖሩ አላማ ተሰፋችንን ለማስረገጥ ለማድመቅ ነው:: ተስፋ ደምቆ ባለበት በዛ መሄድ መሻገር አለ:: ሞትም ቢሆን በዛ መንገድ አለ:: ምክንያቱም ተስፋ የሰጠው የታመነ ነውና::

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 5:9-16 ምዕራፍ 6:1-3

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 5:1-9

View Details

የምንሰማውንና የምናየውን ነገር በእኛ ላይ እንደሚሆን እንደሚደርስብንም አድርገን ስንቆጥር እንፈራለን:: የእግዚአብሔር ቃል እመን እንጂ አትፍራ እንደሚል በፊታችን ያለው አሰፈሪ ነገር ደግሞም የማስፈራራቱ ድምፅ እያለ ነገር ግን አለመፍራት የምርጫ ወይም የችሎታ ጉዳይ አይደለም:: የፀጋ ጉዳይ ነው እንጂ:: እምነት በጨመርን ቁጥር የሚያስፈራውን ነገር ከላይ ወደ ታች መመልከት እንጀምራለን:: እምነት ፍርሀትን አይቀበልምና:: *** የእግዚአብሔር ድምፅ በየዘመናቱ ደግሞ ዛሬም ለሕዝቡ አትፍሩ የሚል ነው::

View Details

ጥያቄ እና መልስ ክፍል 8

View Details

ጥያቄ እና መልስ ክፍል 7

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 4:1-16

View Details

አማኝ እግዚአብሔር እንደሚያየው በመንፈሱ እርግጠኛ በሆነበትና መንፈስ ቅዱስም ይህንን መረዳት በሰጠው መጠን መጽናናት ሀይልና ብብታትም ይሆንለታል:: በሚያየውና በሚሰማው ደግሞም ከፉቱ ከሚየሰፈራራው አየደነግጥም :: የእግዚአብሔርን የፊቱን ብርሀን በማየት ሁኔታዎች እያሉ የተስፋ መታደስና የእምነት ሀይል ይሆናል *** ልባችንን ባቀናን እለት እለትም ፊቱን በፈለግን ቁጥር የፊቱ ብርሀን በእኛ ላይ ደግሞም በነገራችን ላይ ይበራል::

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 3:5-11

View Details

የተያዝንበትን የጌታን አጅና የፀጋውን ጉልበት ባልተረዳንበትና ባላስተዋልንበት ደግሞም አብልጠን ድካማችንንና የሚፈትነንን ድምፅ ብቻ በሰማንና አተልቀን ባየን ጊዜ ጠላት እኛን ለመጣል መንገድ ያገኛል:: ነገር ግን በእምነት ማየት ያለብን የያዘችንን ብርቱዋን የእግዚአብሔርን አጅ ደግሞም የፀጋውን ጉልበት ነው:: *** የአንድ አማኝ ዋስትናው ሰላምና ደህንነት መሆኑ አይደለም:: ነገር ግን የተያዘበት ፅኑ የእግዚአብሔር እጅ ይህንንም ደግሞ ማስተዋሉ ነው::

View Details

እያለፍን ያለንበትን አስፈሪና አሰጨናቂ ሁኔታ እግዚአብሔር እንድንሻገረው ሲያደርግ ሲፈውሰንና ሲያፅናናን አላማው ከእኛ ባለፈ በእኛ ጉብኝት ሌሎችንም በምህረቱ በማዳኑና በማፅናናቱ ለመድረስ ነው:: *** በዚህ ምድር የመኖራችንን ምክንያት እንደሚገባ በተረዳን ጊዜ በመከራና በፈተና ሁሉ ውስጥ ፀንቶ ለመቆም ሀይልና ብርታት ተሰፋም ይሆንልናል:: የላቀው የመኖራችን ምክንያት ወንጌል ነው::

View Details

መኃልየ መኀልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ 3:1-4

View Details

እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘው ሰው እርሱ ኑሮው የተለወጠ መውጣት መግባቱም በልዩነት የሆነ ደግሞም ባገኘውና በያዘው ጌታ በመታመን የፀና ነው:: እግዚአብሔር ያገኛቸውን እነርሱን ፈቃዱንና ሀሳቡን ያገለግሉ ዘነድ በራሱ መንገድ ይመራቸዋል:: *** በእግዚአብሔር የተገኘ እርሱ ኑሮዬ ይበቃኛል ይላል:: ደግሞም ሌላው ይተርፋል::

View Details

በሆኑልን በተሳኩልንና በተከናወኑልን ድልም ባገኘንባቸው ነገሮች ሁሉ እውቅናና ምስጋና ሊቀበል የተገባው እርሱ እግዚአብሔር ነው:: እንደገናም ድል ባላገኘንባቸውና ባልተሳኩልንም በሁሉ ልናመሰግን ይገባል እግዚአብሔር ፃድቅ ታማኝ አምላክ ነውና:: *** ህይወታችን ከማንጎራጎር ነፃ ወጥቶ በሁሉ ማመስገንን የሚያስቀድም በሆነ ጊዜ በምሰጋና ውስጥ በዙፋኑ ላይ ዛሬም በክብር ያለውን ጌታ እናከብራለን:: ከዛም በሚመጣ በረከት ፈውስና መፅናናት እንሞላለን::

View Details

አማኝ ሊኖረው ከሚገባው መረዳት አንዱና ዋነኛው ነገር የተቀበለውን ፀጋ ነው:: ይህ ፀጋ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንድንሆን እንድንበቃን እንድናደርግ የተሰጠ ፀጋ ነው:: በመንፈሳዊ ህይወት ያለፀጋው ምንም የሆነ የለም ወደሚል በቃል በቻ ሳይሆን ነገር ግን ወደ ህይወት ምስክርነት መምጣት ከሀጢአት ከጠላት ክሰና ከፈተና ይጠበቃል:: *** ያለእውቀትና ያለመረዳት በምንሔድበትና በሚጓዝበት ጊዜም መንፈስ ቅዱስ የሚያደርገው ይህንኑ የተሰጠንን ፀጋ በእምነት አይን እንድናይናእንድንረዳ ማድረግ ነው::

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 2:4-7

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 2:1-7

View Details

እግዙአብሔር ሰዎች ሊረዱ በሚችሉበት ሁኔታ ረሱን በማዳን ይገልጣል:: ደግሞም የሰጠውን ተስፋ በእምነት ለሚጠብቁ ተሰፋን ለማፅናት በመባረክ ይገለጣል:: የመጀመሪያው በረከት አራሳችንን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ሰናገኘው ነው:: ይሄን ጊዜ በእምነት አሸናፊዎች እንሆናለን:: *** ተስፋ ያደረግነው ደግሞም በእምነት የተከተልነው ጌታ በእኛ ሁኔታ ለብቻችን በተገለጠልን በታየልን ጊዜ አሰፈሪ ሁኔታው አያለ እኛ እንለወጣለን:: ድፍረት ሀይልና በረከት ይሆንልናል::

View Details

ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምተን እንደ ፍቃዱ እንድንኖር ሁልጊዜም በሀጠአትና በከፉው ላይ አሸናፊዎች እንድንሆን የእርሱ ፈቃድ ነው:: የፀጋው ሀይልና ጉልበት ይህን ያደርጋል:: ዛሬን የመቆማችን የብርታታችን ምክንያት እርሱ ትናንት የረዳን ያገዘን ያቆመን በድል የመራን ጸጋውን ያበዛልን እርሱ ጌታ እግዚአብሔርነው:: *** ሁልጊዜ በጉዞ ላይ በውጊያ እንዳለን እያየን በንቃት ሆነን ለፈቃዱ እየታዘዝን በጽድቅና በእውነት ልንኖር ያስፈልጋል::

View Details

በሆኑልን በተሳኩልንና በተከናወኑልን ድልም ባገኘንባቸው ነገሮች ሁሉ እውቅናና ምስጋና ሊቀበል የተገባው እርሱ እግዚአብሔር ነው:: እንደገናም ድል ባላገኘንባቸውና ባልተሳኩልንም በሁሉ ልናመሰግን ይገባል እግዚአብሔር ፃድቅ ታማኝ አምላክ ነውና:: *** ህይወታችን ከማንጎራጎር ነፃ ወጥቶ በሁሉ ማመስገንን የሚያስቀድም በሆነ ጊዜ በምሰጋና ውስጥ በዙፋኑ ላይ ዛሬም በክብር ያለውን ጌታ እናከብራለን:: ከዛም በሚመጣ በረከት ፈውስና መፅናናት እንሞላለን::

View Details

እግዚአብሔር ታውቆ የማይጨረስ ዘለአለማዊ አምላክ ነው:: በመሆኑም እግዚአብሔርን አውቄ ጨርሻለሁ የሚል የለም:: በህይወት ዘመናችን እግዚአብሔርን ማወቅ የማይቆም የሚቀጥል ነው:: እግዚአብሔርን እያየን ወደ ደስታችን ከፍታ መድረሰ የምንችለው መንፈስ ቆዱስም በእኛ ውስጥ ክርስቶስን የሚገልጠው ነፍሳችንን በተውንበትና በጣልንበት መጠነ ነው

Activity

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 1:8-17

View Details

ጥያቄ እና መልስ ክፍል 6

View Details

የሰማነው የእግዚአብሔር ቃል እንዲሁም ያነበብነው እና የተረዳነው ሙሉ እውቀት የሚሆነው ከኢየሱስ ጋር ሲያገናኘንና ሲገለጥልን ነው:: የለበለዚየሰ እውቀት ብቻ ይሆናለ:: አነዳንድ መከራዎቻችን የምናልፍባቸው አስቸጋሪ ሁኔተዎች የእግዚአብሔር መታያ መንገዶች ናቸው:: በተለየ መንገድ እርሱን የምናይበት:: ለምስጋናና ለውዳስ የሚያደርጉን:: *** ጌታ ለእኛ በሚታይበት በዛ በምናልፍበት እርሱ ይጨከናል:: ስለዚህ የግድ በሆነበት በዚህ ሁኔታ እኛ ግን የሚያስችል እስክናየው የሚያፀና ፀጋውን ልንለምን ያስፈልጋል::

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 1:1-11

View Details

ጥያቄ እና መልስ ክፍል 5

View Details

ቀኑ እየመሸ ሲሄድ በተፈጥሮ የምናውቀው እንደሚጨልም ነው:: እግዚአብሔር ግን ሲመሽ ብርሀን ይሆናል ይላል:: እግዚአብሔር እኛ በጠበቅነው ሳይሆን እርሱ እንደወደደ የሚገለጥ ጊዜ ቦታና ሁኔታ የማይወስነው ከአዕምሮ በላይ በሆነ መንገድ ወደ እኛ ወደ ኑሮአችን ወደ ህይወታች የሚመጣ አምላክ ነው:: *** አለቀ: መጨረሻ ነው ሞቷል ተስፋ የለውም በምንለው ነገራችን ላይ በራሱ ጊዜና ሁኔታ የሚገለጥ እግዚአብሔር ሲመሽ ብርሀን ይሆናል ይላል::

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 1:1-7

View Details

መንፈሳዊ ሰው ከውጭ የሚሰማው ተፅዕኖ አያደርግበትም:: ነገር ግን ያን የሰማውን ወደ ጌታ ያቀርባል::የእግዚአብሔርን ሀሳብ ይጠይቅበታል:: መንፈሳዊ ስንሆን እግዚአብሔር በቀላሉ አያልፈንም:: ይናገረናል:: *** ለመንፈሳዊ ምሪት ከሚያስፈልገን አንዱ የትብብር መንፈሰ ነው:: ምሪቱን ከተቀበለው ጋር መተባበር::

View Details

ሁለንተናችንን ወደሚቆጣጠር ጠሊቅ ወደሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ስንገባ ወደ ጠለቀ ፀሎት ውስጥ እንገባለን:: ወደዚህ ፀሎት ስንገባ የመጀመሪያው በጌታ ፊት ራስን ማዋረድና ዝቅ ማድረግ ነው:: ከራሳችን ፈቃድ ወጥተን ለጌታ ፈቃድ እንገዛለን እንታዘዛለንም:: ጌታም ወደ ከፍታ ያወጣናል:: *** ነጋችን ሲያስፈራን: ከእኛ ያለፈ ለአካባቢ ለህብረተሰብ ለሀገር ሸክም ሲኖረን እነዲሁም በመንፈሳዊ ህይወታችን ፈተና ሲመጣ ወዘተ.. የጠለቀ ፀሎት ውሰጥ እንድንገባ ምክንያቶች ናቸው::

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 1:1-6

View Details

ፀሎት ሸክም ነው :: ደገሞም ተዕዛዝ ነው:: ፀሎት በጉዳያችን ውስጥ ጌታን ማኖር ነው:: የሚፀልይ ሰው የሌለውን ነገር ወደፊት ያያል በፈረሰው ላይ ቆሞ የሚገነባውን የሚተደሰውን ያያል:: ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን ያያል:: *** ሁላችን የምንፀልየው በሊቀካህኑ በኢየሱስ ስር ሆነን ነው:: ሰለዚህ ፀሎታችን ኢየሱስን በመምስል መሆን አለበት:/ የፍቅር ሰው: ይቅር ባይ: ትሁት ወዘተ.../::

View Details

እግዚአብሔር አዲስ ነገር አደረጋለሁ የቀደመውን አታስቡ ሲል: በዘመናት ድንቅን የሚያደርግ ክንዱን ሀይሉንና ብርታቱን ሳይሆን: አታስቡ የሚለው አደራረጉን ነው:: እግዚአብሔር እርሱ ሀሳቡን እንደወደደ በራሱ መንገድ ይሰራልና አሰራሩ ሁልጊዜ አንድ አይነት አይደለም:: *** የእግዚአብሔር ህልውና መገኘት ከእኛ ጋር ይሁን እንጂ ከፊታችን ባለው አስፈሪና አሰጨናቂ ሁኔታ ላይ የምንሻገርበትንና የምናልፍበትን ያልተጠባበቅነውን አዲስ ነገር ያደርጋል:: ምስጋናም ይበዛልናል::

View Details

መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - ምዕራፍ 1:1-4

View Details

እውነተኛ የሆነ የክርስቶስ ህይወት ኑሮ ባለበት በዛ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት አለ:: በመንፈስ ምሪት ውስጥ ያለውም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው:: የእርሱም ፈቃድ በእኛ የሚሰራው ደግሞ የራሳችንን ፈቃድ በተውንበት በጣልንበት ነው:: *** ሁሉን የሚችል አምላክ ፈቃዱን በእኛ ድካም ውስጥ ሊፈፅም በወደደ ጊዜ የእኛ ድርሻ ምሪቱን መቀበል መታዘዝ ደግሞም ፈቃዱን የሚፈፅመውን ጌታ ማሰቀደም እኛም ደግሞ መከተል ነው::

View Details

እግዚአብሔር ሰላምና እረፍትን ወደ ህይወታችን ሲያመጣ አላማው ወደ እርሱ እንድንጠጋና በምስጋና እንድንሆን ነው:: በሰላም ጊዜ እግዚአብሔር እንዳለና እንደሚመራን እንዲሁ የጨለማ ጊዜ የመከራ ጊዜ በምንለውም ውስጥ እርሱ አለ ይመራናልም:: በዚህም ውስጥ ምስጋና ለእግዚአብሔር ነው:: *** በነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ስናመሰግን የምናደርገው እግዚአብሔርን ከፊት እኛን ከኃላ::

View Details

እኛ ሰዎች ነንና የመንፈስ ቅዱስን ፈቃድ የምናውቀው ከፍለን ነው:: ምሪቱ የሚገባን ደግሞም ፈቅደን የምንቀበለው በራሳችን ነገርና ሁኔታ ባልተያዝንበት መጠን ነው:: የመንፈስ ምሪት ትክክለኛውን መንገድ እንድንሔድ እንድንኖርም ያደርጋል:: ይህ በፀጋው ችሎት እነጂ በእኛ አይደለም:: *** የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ለህይወታችን ደግሞም በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ለምንስራው ስራ ፍሬያማነት ዋነኛ ነው::

View Details

እግዚአብሔር ህዝቡን በመንገዱ ይመራል:: ሲመራም በድልና በሸናፊነት ነው:: በመንገዳችን እርሱ ከእኛ ይሁን እንጂ ተግዳሮቶቻችንን እናልፋቸዋለን:: በእኛ ማንነት ሳይሆን በፀጋ ሐይልና ጉልበት:: *** እግዚአብሔር የሚያስኬደን መንገድ ሁልጊዜ በእምነትና በመታዘዝ አንድንከተል የሚጠይቅ ደግሞም ሰላምንም የሚሞላ ነው::

View Details

የመንፈስ ቅዱስ ምሪት በመጀመሪያ በእርሱ ላይ የተጣለ ማንነትን ይሻል:: በእርሱ ላይ የተጣለ ደግሞ የእኔ የሚለው አማራጭ ሰለማይኖረው በምሪቱ ደስተኛ ነው:: እግዚአብሔረም በራሱ መንገድ ነገሮችን መገጣጠም ይጀምራል:: *** እግዚአብሔር እርሱ በማይቀድምበት አይመራንም:: ጌታ ሲመራን ከፊት ያለውን የሚያይልን ጌታ እርሱ ይቀድማል እኛም እነከተላለን::

View Details

ምሪት የሚያስፈልገን የምንኖረው ኑሮ የእግዚአብሔር ኑሮ ሲሆን ነው:: በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር ሰንሆን በእውቀት እያደግን ስንመጣ ወደ እገዚአብሔር ፈቃድ የምንደርስበትን ምሪት እንቀበላለን:: ሰው ከእግዚአብሔር ሰአት ጋር የሚራመደው ራዕይ ስላለው ሳይሆን ምሪት ስላለው ነው:: ያለ ምሪት የሆኑ ሰዎች እነርሱ በራሳቸው ጊዜ ይወጣሉ በራሳቸው ጊዜ ይገባሉ::

View Details

ጥያቄ እና መልስ ክፍል 4

View Details

መንፈሳዊ ከፍታ የእግዚአብሔረ አላማ በህይወታችን የሚከናወንበት በእርሱም በረከት የምንባረክበት ደግሞም በእርሱ አሸናፊነት አሸናፊውን ህይወት መኖር የምንጀምርበት ነው:: *** በእግዚአብሔረ ፀጋ ውስጥ ራሳችንን ያገኘንበት: ጨርሰን ከራሳችን ወጥተን ፀጋው ብቻ በእኛ የሚሰራበት እርሱ ነው ከፍታችን::

View Details

ጥያቄ እና መልስ ክፍል 3

View Details

በክርስትና ህይወታችን እየተሰራን ጌታን የህይወታችን ሙላት ወደ ማድረግ የምናድግበት መንገድ አንዱ መጠበቅ ነው:: እግዚአብሔርን መጠበቅ ማለት በእርሱ መንገድ መሄድ ማለት ነው:: እግዚአብሔር በአጋጣሚ አይባርክም በዘላለም ሀሳቡ እንዳቀደ በራሱ መንገድ እንጂ:: ጌታን የሚጠብቅ እርሱ ሰውን አያይም በሰውም አይጎዳም ደግሞም በመጠበቅ ውሰጥ ጊዜ አይወስንም ጌታ የራሱ ጊዜ አለውና::

View Details

እግዚአብሔር በተናገረው ቃል አይኖቻችን ሲበሩ እኛ በዛ ቃል ውስጥ እንሆናለን:: ቃሉን ብዙ ልንናገር እንችላለን: ነገር ግን ቃሉ ተገልጦልን በርቶልን እግዚአብሔርን ካየነው በላይ ማየት አንችልም:: ፍሬያችንም በተናገርነው መጠን ሳይሆን በቃሉ ባየነው ልክ ነው:: *** እግዚአብሔር በቃሉ የተናገረው በተናገረውም ውስጥ ራሱን ያገኘ እርሱ በጉድለት በፈተናና በመከራም ውስጥ ቢሆንም እንኳ ነገሮች ሳይለወጡ የተረጋጋና የፀና ነው::

View Details

የሰው ህይወቱ በመፈለግ የተሞላ ነው:: መንፈሳዊውንም ሆነ ስጋዊውን እንፈልጋለን:: በህይወታችን ሳንፈልገው ያገኘነው መዳንን ብቻ ነው:: ጌታ ራሱ ፈልጎ አገኘን እንጂ:: ከዳንን በኃላ ግን ብዙ የምንፈልጋቸው ነገሮች አሉ:: የእግዚአብሔርም ቃል ፈልጉ ታገኛላችሁ ሲል መፈለግ አንዱ የህይወታችን ክፍል እንደሆነ ይጠቁማል:: *** የምንፈልገውን ሁሉ እንደምናገኝ ወይም እንደምንቀበል ዋስትና አልተሰጠንም ነገር ግን እግዚአብሔር እነደ ወደደ ለእርሱ ክብር የሚያመጣውን ለእኛም ደግሞ የሚጠቅመንን ይሰጠናል እንጂ::

View Details

እግዙአብሔር አሰራሩ ውስን ስላልሆነ የቀደመውን አታስታውሱ ይላል:: ሰለዚህም ደግሞ አዲስን ነገር አሁን አደርጋለሁ ይላል:: አደራረጉ አይለመድምና የጌታ ስራ በልምድ አይሰራም:: *** በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ እንሁን አዲስን ነገር አደርርጋለሁ ያለ የእርሱ መገኘት ችግሮቻችን ሳይለወጡ ለእኛ የህይወት ለውጥ በረከትና ክብርን ያመጣል:;

View Details

አግዚአብሔር ቃሉን ሲልክ ቃሉን ሲያፈስ ፈቃዱን ለመግለጥ ነው:: ደግሞም ቃሉን ተከትሎ የሚገለጥ የአግዚአብሔር ክብር አለ:: ቃሉ ፈቃዱን እንዲፈፅም ደግሞም ፍሬ እነዲያፈራ ቃሉ የሚወድቅበት ልብ ወሳኝ ነው:: በፈተና ውስጥም ያልፋል:: በዚህ ትምህርት አራት አይነት የቃሉን አቀባበልና ፍሬ ማፍራት እናያለ::

View Details

የእግዚአብሔር ጥልቅ ምስጢር ጌታ ኢየሱስ ነው:: ይህም ምስጢር ስጋና ደም ሊረዳውና ሊያውቀው የማይችል ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ የሚገለጥ ነው:: ወደ እግዚአብሔረ ጥልቅ ነገር መግባት መድረስ የምንችለው ጌታ ወደ እኛ ጥልቅ የደረሰውን ያህል ነው:: ደግሞም ጌታ ወደ ህይወታችን ጥልቅ የሚደርሰው እኛ የፈቀድለትን ያህል ነው:: *** ጌታ ምን ያህል ወይም የት ድረስ ነው ወደ ህይወቴ ጠልቆ የገባው? እኔስ ምን ያህል ነው ወደ ጌታ ጥልቅ ነገር የገባሁት? የሚሉት ጥያቄዎች ሁልጊዜ አማኝ ራሱን የሚያይበት ጥያቄዎቸ ናቸው::

View Details

አማኝ ሁልጊዜ የህይወት ሙላት እንዲኖረው የእግዚአብሔረ ቃል ያዛል:: የአገዚአብሐር ነገር በእኛ ውስጥ ሲያልፍ ስንፀለይ ቃሉን ስናነብ ከቅዱሳን ጋር ህብረት ስናደርግ ለመነፈሳዊ ህይወታችን ሙላት ይሰማናል:: በጌታ ተምህርት ምክርና ምሪት ውስጥ የሆነ አርሱ በሙላት ውስጥ እንዳለ ይታወቀዋል:: ነገር ግን የጌታን ምክር በራሱ ሀሳብ የተካ በምክሩም ያልተመራ በባዶነት ይኖራል:: *** በሙላት ውስጥ ያለ ሰው እርሱ የራሱን ነገር ወደ ጌታ አምጥቶ የጣለ የእግዚአብሔርም ፈቃድና ሀሳብ በእርሱ ውስጥ የሚያልፍነው::

View Details

አግዚአብሔርን ማወቅ ብቃት ነው:: የሰው መንፈሳዊ ብቃቱ እግዚአብሔርን ባወቀበት ልክ ነው:: በመከራ በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ እርሱ ይበረታል ይፀናልም:: *** በዚህ አሰጨናቂ አለም ክፉውን ፀንተን መቃወም የምንችለው ተስፋችንም እለተ እለት የሚታደሰው ጌታ ከእኛ ጋር መሆኑን ባወቅነው መጠን ነው::

View Details

ጥያቄና መልስ

View Details

እግዚአብሔር እርሱ ሉአላዊ አምላክ ነው:: ስህተት በእርሱ ዘንድ የለም የፈቀደውን ያደርጋል:: ይህን ሲያደርግ ደግሞ አርሱ ፍፀም ፃድቅ ነው:: ሰለዚህ አካሔድን ከእርሱ ጋር ለማድረግ ወደ ልቡ ፈቃድ መድረስ ሀሳቡንም መረዳት ያስፈልጋል:: ወደ ልቡ ፈቃድ ለመድረስ ቀዳሚው ደግሞ ከራሰ መውጣት ነው:: *** ከራሱ የወጣ ወደ ጌታም ወደ ልቡ ፈቃድ የደረሰ እርሱ የእግዚአብሔር ምስጢረኛ ነው ደግሞም መልካም ሰለሆነው ብቻ ሳይሆን መልካም በማይመስለውም ሰለሁሉ ያመሰግናል:

View Details

እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ገዢው የሆነ መሪው የሆነ ሰው በሚያልፍበት ማንኛውም ችግር መፍትሔ የሚያገኘው ከራሱ ከእግዚአብሔር ነው:: ሰው በራሱ የሚወሰደው አርምጃ ራሱ የሚጎዳበት ደግሞም አግዚአብሔርን የማያሰከብር ይሆናል:: *** ለችግሮቻችን መፍትሔ የሚመጣው የሚመነጨው የአካሉ ራስ ከሆነው በነገር ሀሉ ክብርን ልንሰጠው ከተገባው ከእግዚአብሔር ዘንዱ ነው:: አኛን ይጠቅማል ጌታንም ያከብራልና::

View Details

ክርስትና የግለኝነት ህይወት አይደለም:: የተጠራነው ደግሞም የምንኖረው ለአካሉ ነው:: የአንዱን መከራ ሌላው እየተሰማው በፀጋው አቅም የምንኖረው ኑሮ ነው:: በፀጋው ለመኖር መረጥን ማለት ደግሞ ለመስቀሉ በቃን ማለት ነው:: መሰቀልን ያራቀ ደግሞም ወደ ህግ ዘወር ያለ ህይወትና ኑሮ እውነተኛውን የወንጌል ኑሮ እየኖረ አይደለም::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል

View Details

እግዚአብሔር ወደፊት የሚያሰኬደን ደግሞም የሚባርከን በጎውን ሀሳብ በቃሉ አማካኝነት ወደእኛ በማምጣት ነው:: ቃሉ ሲመጣ የአሰተሳሰባችን ቅኝት ይቀየራል ከወንድሞች ጋርም ያለን ህብረትም ይፈወሳል:: ጠላትም ሊጎትተን ደግሞም ሊጥለን ሲፈልግ ሥራ የሚጀምረው ሀሳባችን ላይ ነው:: ዛሬ የምናስበው ሀሳብ የነገውን ቁመናችንን ይወስናል ወደፊት ለመሔድ ወይንም ለመቆማችን ምክንያት ነው::

View Details

የእግዚአብሔር አለሁነት ፍጥረት ሊረሳው በማይችል ሁኔታ ይገለጣል:: እርሱ ፃድቅ ፈራጅ ነውና ፍርድን በማደላደል ይገለጣል:: ደግሞም በማዳን በፈውስና በማፅናናት ይገለጣል:: እውነተኛው ምስክርነት እርሱ ብሏል ማለት ብቻ ሳይሆን እኛም ደግሞ እውነት ነው እርሱ ያለው ለእኔ ሆኗል ሰንል ነው:: ደግሞም በአስፈሪውና በአስጨናቂው ፊት እርሱ ብሏልና እኔም እላለሁ ብለን ፀንተን ስንቆም ነው:: *** አንድን አማኝ እግዚአብሔር ጠንካራ ማድረግ የሚፈልገው ሲያለቅስ በመስጠት ሳይሆን ነገር ግን በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ እኔ አለሁ በሚል ነው::

View Details

ሰው በሀይሉ አይበረታም እንደሚል የእግዚአብሔር ቃል መነፈሳዊ ህይወታችንን ስንመለከት ሀቅም ባጣንበትና በደከምንበት ሁሉ እርሱ ብርታት ጉልበት ይሆናል:: በምናልፍበት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥም ብቃት የሚሆነን እርሱ ነው:: *** የተጠራነው ለአሸናፊነት ነው:: ልናልፍበት ያለውን ሁሉ የምናልፈው ራሳችንን በሰጠንበትና እግዚአብሔርም ለእኛ በሆነልን ልክ ነው::

View Details

እግዚአብሔር የራሱን ፅድቅ ያቆመው ለሰው ሁሉ ሲሆን የሚያምኑትን ለማፅደቅ ነው:: ያለ ሥራ እንዴው በፀጋው ይፀድቃሉ:: የፀደቀም አማኝ እለት እለት ይቀደሳል:: ህግን በመፈፀምለመፅደቅ የሚታገል እርሱ ግን ከክርስቶስ ተለይቶ ከፀጋው ይወድቃል:: በእምነት በሆነ መስማማት በፀጋው የዳነ ህይወት የሚሰጠውንም መንፈስ ቅዱስን የተቀበለ አማኝ ለሀጢአት ሞቶ ለፅድቅ ይኖራል እንጂ ወደ ህግ አይመለስም::

View Details

የእግዚአብሔርን ቃል መስማት እጅግ መልካምና ዋና ነገር ነው:: ነገር ግን የምንሰማው የእግዚአብሔር ቃል የሚጠቅመን በእምነት ከህይወታችን ጋር ሲዋሀድ ነው:: ይህ ሲሆን ፍሬ ማፍራት እንጀምራለን እግዚአብሔር ልንደርስ ወደሚፈልገውም ከፍታ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ መምሰል ህይወት እናድጋለን:: ሰው የሰማው የእግዚአብሔር ቃል የህይወቱ መሠረት እንዲሆንለት ፍሬም እንዲያፈራ ለሰማው ቃል መታዘዝና መወሰን ዋጋም ለመክፈል መጨከንን ይጠይቃል::

View Details

እግዚአብሔር እንዳለ እናውቃለን ደግሞም እናምናለን:: በህይወታችን የእርሱ ክብር የእርሱ ችሎት እንዲገለጥ ግን አብሮነቱ ሊበራልን ሊገለጥልን ያስፈለጋል:: ይህም ደግሞ የሚሆነው እኛ ለእርሱ ምቹ ሆነን በተገኘንበት መጠን ነው:: *** እግዚአብሔር ለእኔ አለ የሚል አብሮነቱም የተገለጠለት እርሱ በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ ፀንቶ የሚቆም ደግሞም ምስጋና የሚበዛለት ነው::

View Details

እግዚአብሔር ሁሉን ለክብሩ ፈጥሮታልና እኛን ወደ አካሉ ሲጠራን ለእርሱ ክብርን እናመጣ ዘንድ ነው:: ለእርሱ የሚገባውን ክብር ለማምጣት ደግሞ ምንጩ በክርስቶስ መሆናችንና ተፈትነን በወጣነበት ልክ ነው:: *** ራሳችንን ካጣንበት ጌታ ብቻ ማንነታችንን ከሞላበት ከዛ ከሞተው ማንነታችን ለእርሱ ክብርን እናመጣለን::

View Details

ሰው ህግን በመጠበቅ ሳይሆን የህግ ፍፃሜ የሆነውን ኢየሱስን በማመን ነፃ ይሆናል:: ከኩነኔ ከፍርድ ነፃ ይሆናል:: በክርስቶስ ነፃ የወጣ ሰው እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ያለነውርና ያለነቀፋ ይታያል:: እግዚአብሔር አባት ነው ብሎ በደስታ በነፃነት ያመልካልም:: *** ነፃነታችን እንደፈለግን ልንሆን ሳይሆን ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስ ሆነን ልናመልከው ነው እንጂ::

View Details

አማኝ በጌታ መገኘት ራሱን ማግኘት የሚችለው ብቻውን የሆነውን ያህል ወይንም ለጌታ የተገኘውን ያህል ብቻ ነው:: ምክንያቱም ለእርሱ ከተገኘንበት በላይ ለመሆን ብቃት የለንምና ነው:: ለጌታ ብቻውን መገኘት የሚችለው እርሱ ሁሉን የተወ ጥያቄው እግዚአብሔር ብቻ የሆነው ነው:: ለብቻችን ለጌታ የተገኘንበት ማንነተ በአርሱ ሙሉ ከመሆኑ የተነሳ ወደጎን ከቅዱሳን ጋር ያለንም ግንኙነት በረከትና ሰላም ያለው ይሆናል ::

View Details

እውነተኛ ወንጌል ሰውን አያቆላምጥም ወይንም ደግሞ አያባብልም:: ነገር ግን እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ፅድቅ ይገልጣል የሰውንም ሀጢአተኛነት ይናገራል:: ደግሞም መዳንን ሰው ህግን በመጠበቅ በስራው የሚያገኘው ሳይሆን በፀጋው ብቻ በእምነት የሚገኝ መሆኑን ያበስራል:: በፀጋው ራሱን ያወቀ ሰው እርሱ ራሱን ይገዛል:: እኔ አልችልም የቻልኩትን ሁሉ የቻልኩት በፀጋው ነው ይላል:: ሰለዚህ የሚናገረውንና የሚሰራውን ሁሉ በማስተዋል ያደርጋል:: በደረሰበትና በተቀበለው ፀጋ ልክም ይመላለሳል::

View Details

አማኝ በጌታ መገኘት ውስጥ አየኖረ ነው የሚባለው እርሱ ሞቶ በሁለንተናው ጌታ የሚኖርበት ህይወት ሲኖር ነው:: በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ የሚኖር እርሱ የእኔ የሚለው እውቀት ትምክህትም የለውም በማናቸውም ሁኔታ ትምክህቱ ጌታ ነው:: ይህም ትምክህት ደግሞ የሚፈተንበት ቀን ይመጣል ያንጊዜም ከብሮ ይወጣል:: ክርስቶስን በህይወታችን የምንኖረው በእርሱ የተመካንበትን ያህል ነው::

View Details

አንድ አማኝ የመነፈስን ምሪት የሚያገኘው በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ ራሱን ባገኘበት ነው:: ወደ እርሱ መገኘት የሚያስገባን ደግሞ የሞተ ማንነታችን ነው:: የእኛ ብቃት ያለው በጌታ መገኘት ውስጥ ነው:: በዛ ውስጥ ለጥያቄ ሁሉ መልስ አለ:: ባልተመለሰውም ጥያቄ እንኳን በሚሰጠን ፀጋ በምስጋና ውስጥ ሆነን በእውነተኛ አምልኮ እንቀጥላለን::

View Details

የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰው ለእርሱ እንዲሆን ነው:: ይህ ደግሞ ከመፈጠራችን በፊት የነበረ የእርሱ ፕላን ነው:: ይሁን እንጂ ሰው በኃጢአት ምከንያት ከዚህ የጌታ ፈቃድ ቢወጣም በልጁ በኢየሱስ ክረስቶስ ወደ ተፈጠርኖበት አላማ እንድንመለስ አድርጓል:: *** ሰው ለእግዚአብሔር ሲኖር ሰላም ይኖረዋል:: በምድረበዳ ብንሆን በሸለቆ ህብረታችን ከጌታ ጋር ስለሆነ ነፍስና መንፈሳችንን የሚያረካ የእርሱ መንፈስ ይደግፈናል::

View Details

እምነት በጌታ ላይ መደገፍን ሀሳብን በእርሱ ላይ መጣልና በነገር ሁሉ በጌታና በቃሉ ላይ መታመንን ሁሉ የሚመለከት ነው:: አማኝ ከእምነት ወደ እምነት እያደገ እንደሚሄድ ሁሉ በተቃራኒው ደግሞ ከእምነት እየተንሸራተተ የሚወርድበት ብሎም እምነቱን የሚጥልበት ጊዜ አለ:: እመነታችንን ከጌታ ጋር ያለን ህብረትና የህይወታችን ሁኔታ ፅድቅና ቅድስና ለቃሉም ያለን መታዘዝን መኖር ይወስነዋል::

View Details

እምነትና ፀሎት የማይነጣጠሉ የአማኝ ህይወትና ኑሮ ናቸው:: በእምነት የሩቁን አሻግረን እናያለን:: እግዚአብሔርንም ደስ ማሰኘት በእምነት ነው:: ተስፋችንም ፅኑ እደሆነ የምናየው በእምነት ነው:: *** እምነት ካለን ተክክለኛና መሠረት የያዘ እውቀት ይመጣል:: የእምነትም መሠረት የእግዚአብሔር ቃል ነው:: ወደ ቃሉ እንመለስ::

View Details

አንድ አማኝ ጌታን ተቀብሎ በእምነት በሚገኝ መዳን የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ በኃላ መዳኑ ሙሉ እንዳልሆነ ቢያሰብ ህግንም ለመጠበቅ ወደኃላ ቢመለስ ይህ ወደ አለማወቅ ወራት መመለስ ነው:: ከፀጋውም መውጣት ነው:: ****በክርስቶስ መሆናችን በነገር ሁሉ ራሳችንን ለእርሱና ለመነፈሱ ለማሰገዛት ለእግዚአብሔርም ነፃ ለመሆን ነው::

View Details

በሰው ህይወት በተለይም በሸለቆና በምድረበዳ በሚያይልፉ ውሰጥ ብዙ ጥያቄ አለ:: ለጥያቄ ሁሉ መልስ ግን ከእግዚአብሔር በሰተቀር ከወዴትም አይገኝም:: በኃጢአት መክንያት ካልሆነ በሰተቀር የመናልፍበት አሰቸጋሪ ሁኔታ እግዚአብሔር እኛን ብቻችንን የሚያገኝበት አኛም ደግሞ ፈቃዱንና ሀሳቡን የምንረዳበት ስፍራና ጊዜ ይሆናል:: *** አግዚአብሔር አኛን በፍቅሩ ውሰጥ እንድንሆን ከእቅፉም እንዳንወጣ የያዘበት መንገድና ሁኔታ አሳምሞን ቢሆንም እነኳን ለጥቅማችን ነው::

View Details

እግዚአብሔር የበጎ ነገር ሁሉ ምንጭ ነው:: እስራኤልን በምድረበዳ መና እየመገበ ያስጓዘ ጌታ የተስፋይቱንም የምድር እንዲበሉ ታማኝነቱን አሳይቷል:: ህዝቡ ደግሞ ወደጌልጌላ ሊመጡ በዛም ከአምላካቸው ጋር ከሀሳቡና ከፈቃዱ ጋር ሊስማሙ ግድ ነው:: ***በዚህ ትምህርት እሰራኤል በእግዚአብሔር ፊት በጌልጌላ ምን እንዳደረገ ደግሞም ምን እንደተገለጠለት የምናያቸው ሀሳቦች እኛም ዛሬ የክርስትና ህይወታችን ብዙ መጋደል ላለበት ምሳሌዎቻችንና የምንማርባቸው ናቸው::

View Details

በአለም ብዙ እውነት የሚመስሉ ነገሮች አሉ:: ነገር ግን እውነት አንድ ነው እርሱም እግዚአብሐር ነው:: ይህም እውነት የተገለጠው ወደ ሰውም የደረሰው በከርስቶስ ነው:: ከእውነት የሆነም እርሱ ነፃ የወጣ ነው:: *** እውነትን ህይወት: ኑሮ ያደረገ ነው ለመውደድ ለመማር ለመራራትና የክርስቶስን ህይወት ለመኖር ሊበቃ የሚችል::

View Details

የህይወት ለውጥ የሚጀምረው ጌታ ራሱን ለእኛ ከገለጠበት ብርሀኑን ካበራልን ነው:: አማኝ በጌታ በኢየሱስ ሲያምን ለኃጢአት ሞቶ ለፅድቅ እንደሚኖር ይህንንም መቀበል ደግሞም መኖር አለበት:: *** ፅድቅ ባመንን እንድ ጊዜ ቦታ የሚወስድ ነው:: ሰለዚህ ሁልጊዜ በመፅደቃችን እርግጠኞች እየሆንን እለት እለት ግን ለመቀደስ እንኖራለን:: ቅድስና ኑሮ ነው::

View Details

እውነተኛ ወንጌል በመጀመሪያ የሚያደርገው ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን መግለጥ ነው:: ሰውም ይህ ብርሀን በበራለት ጊዜ ለተገለጠለት የወንጌል እውነት ይታዘዛል ይገዛል:: ወንጌልም በእምነት ብቻ በፀጋው የሆነ መዳንን የሚገልጥ ነውና:: ስለዚህ ጌታን መቀበል ማለት ኃጢአተኛ መሆንን ማመን በደለኛነትን መረዳትና በእኛ ምትክ ሰለኃጢአተ ስርየት ለመስዋዕት ራሱን የሰጠውን ጌታ ኢየሱስን ማመን ነው:: መዳን በእኛ ሳይሆን በእርሱ ችሎት ብቻ የሆነ ነውና::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 42

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 41

View Details

አንድ ሰው በጌታ በኢየሱስ አምኛለሁ ሲል ለማመኑ ምልክቱ በመንፈስ ቅዱስ መሞላቱ ነው:: የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በአማኞች ህይወት ውስጥ መቀመጡ ነው:: መንፈስ ቅዱስም ስራውን በእኛ የሚሰራው አኛ በእግዚአብሔር ላይ የታመነውን ያህል ነው:: ***ለማመናችን ምክንያቱ ሰለ ኢየሱስ የተገለጠልን እውነት ነው:: ለመዳናችን ምክንያቱ ደግሞ የተገለጠልንን እውነት ማመናችን ነው::

View Details

የቤተክርስቲያን ጤንነት የሚጠበቀው ጌታ ባስተማረው ትምህርት ስንኖር ነው:: ዝቅ ማለት ከተቀበልነው የመዳን ፀጋ ሳንወጣ መኖርና እርስ በእርስ መቀባበል ዋናዎቹ ናቸው:: በትህትና በፍቅርና በመቀባበል ህብረት የተጠበቀ ይሆናል ተሀድሶና የመንፈሰ ቅዱስም ጉብኝት ይሆናል::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 40

View Details

መንፈሳዊ ነገራችን የተቀመጠው በእምነትና በመታዘዝ ላይ ነው። የእምነት መነሻና መደምደሚያው መታዘዛችን ነው።

View Details

የእግዚአብሔር ቃል በህይወታችን ስፍራ ባገኘው መጠን ህይወታችንን ይነካል ወደ ውሰጥ ይገባል ያነቃቃናል ከፍ ያደርገናል ደግሞም ይባርከናል:: *** በዚህ ትምህርት ውሰጥ በህይወታችን የእግዚአብሔር ቃል ሰፍራ እነዲኖረው ማድረግ የለብንን ሰባት ነጥቦችን እናያለን::

View Details

የእግዚአብሔርን ባህርይ አሰራሩንም ባለማወቅ ወደ ህይወታችን ከሚመጣው ፈተና የተነሳ ለፀሎታችን መልስ ሳናገኝ ሰንቆይ የሚደግፍ አይዞህ የሚል ሲጠፋ ያንግዜ እግዚአብሔር ረሰቶኛል ማለት ነው? እንላለን:: እግዚአብሔር ህዝቡን ከቶውንም አይጥልም ነገር ግን አመጣጡን አሰራሩን አደራረጉን አሰፍተን እንድናይ እንድንጠብቅም ይፈልጋል:: በማናውቀው መንገድ ይመልሳል ይመጣልም::

View Details

ሸክም አለን ማለት መደረግ ያለበት ይሁን የሚለው ነገር እንዲደረግ እኛ ውስጥ አለ ማለት ነው:: ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም አብረን እንሰራለን:: ምኞትግን ሸክም ሊሆን አይቸልም:: *** ለተቀበልነውና በውስጣችን ላለው ሸከም መሰራት ከመንፈሰ ቅዱስም ተጠቃሚ የምንሆነው በእርሱ የምንጠበቀውም በመታዘዝ ውሰጥ ብቻ ነው::

View Details

የብርሀን ወንጌል በህይወታችን ሲበራ በእኛ ላይ ከሚሰራው ነገር አንዱ ካለፈው ታሪካችን ያወጣናል ይገላግለናል:: የብርሀን ወንጌል የብርሀን ሰው ያደርገናል:: *** በብርሀኑ የተነካ እርሱ ለመማር ለመስተካከል ለመታረምም ራሱን ትሁት አድርጎ የሰጠ ነው::

View Details

ሰው በጌታ በኢየሱስ ሊያምን የሚችለው ሰለተማረና ሰላወቀ ሰለተረዳ አይደለም:: ነገር ግን ጌታ ራሱ በሰው ልብ ውስጥ ባለው ጨለማ ላይ ብርሃን ያበራል:: ያን ጊዜ በበራለት ብርሀን ምክንያት ያምናል:: መንፈስ ቅዱስም ህይወትን ይቀይራለ:: **** ጌታ በፀጋው ጠራን በፀጋው ለየን በፀጋው አዳነን በፀጋው እንኖራለን በፀጋው እሩጫችንን እንፈፅማለን::

View Details

ሸክም ማለት ሰው ከእግዚአብሔር ነገረ (ሀሳብ ወይምፈቃድ) ጋር የሚነካካበት ማለት ነው:: በእግዚአብሔር ሸክም አስቀድመን ካልተያዝን በሰው ህይወት ውሰጥ ሀሳባችንን ህይወታችንን የሚቆጣጠሩ ሌሎች ነገሮች አሉ:: ከእግዚአብሔርም ሩቅ ያደርጉናል:: *** የራሳቸውን የተዉና ለጌታ ሸክም ራሳቸውን ባዶ በማድረግ የሰጡ እነርሱ ፀጋን የተሞሉ በእርሱ መገኘት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው::

View Details

እግዚአብሔርን በሙሉ ሀይሉና ፈቃዱ በሙሉ ልቡና ሀሳቡ የሚወድ እርሱ ለእግዚአብሔር የተገዛ ነው:: እግዚአብሔር ገዢ ነውና ሰው ለእግዚአብሔር በግርማው ይገዛል ወይንም በስልጣኑ ይገዛል:: ከዚህ ውጭ የሚሆን የለም:: *** ለእግዚአብሔር በደስታ የተገዛ ሰው ነፃ የወጣ ነው:: የህይወት ሙላትም ያለው በዛ ውሰጥ ነው::

View Details

የገላትያ መልዕክት ሰለ ነፃነት ነው:: ከሀጢአት እስራት ነፃ ስለመውጣት ነው:: በሀጢአት ቀንበር ስር ያለ ሰው ለክርስቶስ መኖር አይችልም:: *** አርነት መውጣት ማለት ክርስቶስን የመኖር ብቃት ማግኘት ማለት ነው::

View Details

እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ላይ ያለውን መልካም ሀሳብ እንዲፈፅም እምነት ከእኛ ይጠበቃል:: በእምነት ለምነበረታ ለእኛ ደግሞ እውቀትና ምሪት ይሰጠናል:: በጌታ በእምነት የሆነ እውቀትና ምሪት በህይወታች ያለውን ክፍተት ይሞላል::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 39

View Details

በዚህ ክፍል ውስጥ ሐዋርያው በወንጌል ያገኛቸውን ወንድምና እህቶችን ካሳዩት ፍቅርና ስጦታ ምክንያት ይባርካል:: የአማኝ የኑሮ መርህ ያለኝ ይበቃኛል የምኖረው በፀጋው ነው በሚል መሆን አለበት:: ካለን ከሞላን ይልቅ በሌለን ላይ ጌታ በፀጋው ይገለጣል::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 38

View Details

የምንኖርበት ይህ አለም በብዙ የሚያደክም ደግሞም የሚያታክት እንደሆነ ግልፅ ነው:: የእግዚአብሔርን ፊት በመፈለግና እርሱን በመጠበቅ ግን አንዳንታክት እንዳንደክምም ቅዱስ ቃሉ ይመክረናል:: በእምነት እግዚአብሔርን መጠበቅ በውስጡ ሀይል አለው ተስፋ አለው ክብር አለው:: እግዚአብሔር በቃሉ የታመነ ነውና::

View Details

የእለት ተእለት ህይወታችን እግዚአብሔር ቀደም ካልሆነ የዘመኑን ክፋት ማየት ደግሞም መዋጀት አይቻለንም::   ** እግዚአብሔርን ያስቀደመ: ፈቃዱን ያስቀደመ: መስቀሉን ያስቀደመ እርሱ ነው ለጌታ የተሰጠ በክፋት እየጨመረ የሚሄደውንም ዘመን የሚዋጅ::

View Details

የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን በመንፈስ ቅዱስም መታተማችን መዳናችን በእምነት ነው:: በዚህ ምድር ስንሆን እንድንኖር የተፈቀደልን በእምነት ነው:: በዚህም ምክንያት ሰለሁሉ እንፀልያለን:: እንደዚሁም እውቀትና ምሪተም አሰፈላጊዎቻችን ናቸው:: በህይወት ጉዟችን ተፈትነን መንፈሳዊ ሆነን ያልተገኘንበት ያ የኛ ክፍተት ነው::

View Details

ለአንድ ክርስቲያን ኑሮ የእግዚአብሔር አብሮነት ወሳኝና እጅግ አስፈላጊ ነው:: የእግዚአብሔር አብሮነት ለብርታታችንና ከክፉ ለመጠበቃችን ምክንያቱ እርሱ ነው:: *** የእግዚአብሔር አብሮነት ከእኛ ጋር እንዲሆን በቃሉ ውስጥ ልንሆንና ልንታዘዝ እንደ ፈቃዱና እንደ ሀሳቡም ልንኖርና ልንመላለስ ያስፈልጋል::

View Details

በእግዚአብሔር ፈቃድና ሀሳብ ውስጥ ስንኖር በምናልፍበት ማንኛውም አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ዛሬም በአጠገባችን የሚቆም የሚረዳንና የሚያግዘን የሚያፅናና ተስፋችንንም የሚያድስ እርሱ ትናንትን ያሳለፈን ጌታ ነው:: *** ችግርና መከራ የሚለውን ሳያይና ሳይሰማ ልቡን በእግዚአብሔር በአምላኩ ላይ ያበረታ እርሱ ይሻገራል::

View Details

የወንጌል ትልቁ በረከት ሰዎችን ወደ እረፍት ወደ ደስታና ሰላም ማሰገባት ነው:: ይህ እረፍት ወደ መንፈሳዊ የህይወት አረፍት በጌታ ፀጋ የምንገባበት ነው:: *** አማኝ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ የራሱ ባደረገው ጊዜ ሰላሙ አነደ ፅድቅ ወንዝ ይፈሳል::

View Details

በአዳም ሀጢአት ምክንያት እኛ ሁላችን ከእግዚአብሔር ፊት ከክብሩም ወጥተን ነበር::  በኢየሱስ ክርስቶስ ግን ሙሉ ወደሆነው የመለኮት ተቀብሎት ገባን::     ** ዛሬ በምድር የምንኖረው ህይወት በላይ በፊቱ ያለንና ያገኘነው ተቀብሎት ነፀብራቅ ነው::

View Details

በክርስትና ህይወት ውሰጥ: ሚዛናዊ ህይወትና ሚዛናዊ አገልግሎት ሁለቱ የማይነጣጠሉ ዋና ነገሮች ናቸው:: ** ክርስትና የክርስቶስን ህይወት መሞላት ነው:: አገልግሎታችንም የሚመሰረተው ራሳችንን ባዶ ባደረግንበትና ክርስቶስን በተሞላንበት ላይ ነው::

View Details

እግዚአብሔር በፍቅር በመስማማትና በመቀባበል ውስጥ የሚሰራ አምላክ ነው:: ከዚህ ስንጎድል ችግር ይሆናል:: ነገር ባለበት ወንጌል አይሮጥም መገለጥ አይኖርም ሁሉ ነገር ይቆማል:: *** ብዙ የሚያናውጡ ነገርች በቤተክርስቲያን ይከሰታሉ:: ከዚህ ውስጥ የሚያመልጡ እነርሱ ወደየትኛውም ያላዘነበሉ በጌታ የቆሙ ህይወት ቀደም የሆኑና መዳን ህይወታቸውን የሞላው ናቸው::

View Details

የክርስትናን ህይወት ያለ ተስፋ መኖር አይቻልም:: ተስፋን የሚሰጥ አግዚአብሔር የታመ ነውና የተቀበልነው ተስፈ ሳይፈፀምአይቀርም:: ነገር ግን ደግሞ ከእኛም ሁኔታ ጋር የተገናኘ ነው:: *** በዚህ ትምህርት ውስጥ ተስፋችንን ለመውረስ በእኛ በኩል የሚጠበቁብን ነገሮች ተዘርዝረዋል::

View Details

ሐዋነርያው ጳውሎስ ትልቅ መንፈ ሳዊ ነገር የተቀበለ ደግሞ ያየና የሰማ ሲሆን ነገር ግን ትንሽ መሆን የቻለ ሰው ነው:: *** ጤነኛ መንፈሳዊ ህይወት በተቀበልነው ወይንም ባየነውና በሰማነው ትላልቅ መንፈሳዊ ሰጦታዎቸ ላይ ራሳችንን ትነሽ ለማድግ በተለማመድንበት ነው::

View Details

ክርሰትናን ስንጀምር የነበረው ህይወታችን: ሁሉን በጥንቃቄ የያዝንበትና : በፍቅር የተመላለስንበት እንዲሁም ህይወታችንን ከሐጢአት ለመጠበቅ የነበረው ቆራጥነት እየዋለ እያደረ እየተለወጠ መጥቷል:: በእግዚአብሔር ቤት ቆይታ እውቀት እያገኘን ስንመጣ እውቀታችን ህይወት እየሆነ ክርስቶስ ወደ ጎን እየተተወ የመጣበት ሁኔታ ነው ያለው::  --  ለሚዛናዊ ህብረት ክርስቶስን ጌታና ራስ ማድረግ ያስፈልጋል::

View Details

በአማኝ ህይወት ሊቀድም የሚገባውና ሁለንተናውን መግዛት ያለበት እግዚአብሔር ያለውን ቅድሚያው በማድረግ ነው:: በቀረው ነገር ላይ እግዚአብሔር አባት ነውና አትጨነቅ ይላል:: እግዚአብሔር ያለው አርሱ ቅድሚያችን ሲሆን እየተሞላን አንሄዳለን:: በእግዚአብሔር መንፈስ ልባችንና አዕምሮአችን የተጠበቀ ይሆናል:: በጥበብና በማስተዋልም እንጨምራለን::

View Details

በመንፈሳዊ ህይወታችን ሚዛን ጠብቀን መኖር እጅግ አሰፈላጊ ጉዳይ ነው:: ይህ ባይሆን ግን የውስጥ ጠላት ወይንም የክርሰቶስ መስቀል ጠላቶች እንሆናለን::  በትምህርት ውስጥ በተዘረዘሩት 7 ነጥቦች ሚዛናዊ ህይወታችን የትጋ እንዳለን መመልከት እንችላለን::

View Details

ጌልጌላ እያሱ 4:16--5:12

በፓስተር ሰመረ

እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን እያሸነፉ በድል እየገሰገሱ ቢሔዱም: ደግሞ ቆም ብለው ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ራሳቸውን የሚያሰማሙበት ደግሞም እረፍት የሚያደርጉበትና ለሚቀጥለው ጉዞ ምሪት የሚቀበሉበት ሰፍራ ነበረ ጌልጌላ:: - ዛሬም እኛ ቆም ብለን የጌታን ፈቃድ የምንጠይቅበት ደግሞም ምሪት የምንቀበልበት ጊዜና ቦታ ያስፈልገናል::

View Details

እግዚአብሔር ሰውን ወደራሱ ለመጥራት ውጫዊ ነገራችንን ሊጠቀም ይችላል:: ሰዎች ልባቸው በተሰበረበት ሰዓት አለኝ የሚሉትን ሲያጡ ሀዘን ሲጫናቸው ተስፋ ሲቆርጡ ወደ ጌታ ዘወር ለማለት ምቹ ሁኔታ ይፈጥርላቸዋል:: ይህንን ከሩት ህይወት እንማሰለን::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 37

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 36

View Details

በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ:: የክርስትና ህይወት ሁለት ዋና ነገሮች አሉት፤ ሰው ሁልጊዜ በጌታ ደስተኛ መሆንና  ፥ ሰው ለአምላኩ ክብር መኖር::

View Details

የነፍሳችን መዳን አንድ ጊዜ የተከናወነና በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት የተረጋገጠ ሲሆን ነገር ግን ዘወትር በእርሱ ማዳን የምንኖር ሰዎች ነን:: እግዚአብሔር ዘወትር ማዳን አለው ፥ መውጫ አለው ይህ ማዳን ደግሞ የማያቋርጥ ሒደት ነው እርሱ በማዳኑ የታመነ አምላክ ነው::

View Details

ጳውሎስ በተለይ በአይሁድ ወገኖቹ በኩል በመከራ ውስጥ ቢያልፍም የአይሁድ ሸክም ግን ሁልጊዜ በልቡ አለ:: አገልግሎቱን የሚያከበር እርሱ ከሚችለው በላይ እንደማይፈተን የተረዳ ነው:: በተሰጠን ዘመን ልናደርግ የሚጠበቅብን አንዱና ዋናው ወንጌልን ልንመሰከር እንደሆነ ጳውሎስ ምሳሌያችን ነው::

View Details

መፅሐፍ ቅዱስ የሗላችንን ወይንም የትኛው ትናንትናችንን ልንረሳ እነደሚገባ እንደሚነግረን እንዲሁ ደግሞ ትናንትናችንን ለምን መርሳት እንደማይገባን ይመክራል:: *** ትናንት በእግዚአብሔር አብሮነት የእርሱን ምህረትና ጥበቃ ያስተዋለ ሰው ነው ከፊቱ ያለውን ተግዳርት በድል ሊሻገር የሚችለው::

View Details

ኢየሱስ ክርስቶስ የህይወት ብርሃን ነው:: አማኞች ደግሞ የአለም ብርሃን ናቸው:: ሰለዚህ የብርሃን ልጆች ብርሃን ካልሆኑ ይህ አለም ምን ተስፋ አለው? እምነታችን በመልካም ምሳሌነት ሊገለጥ ይገባዋል:: *** የእግዚአብሔር መገኘት በመሀላችን እንዲሆን በብርሃንነታችን ልንመላለስ ደግሞም ህብረትና አንድ ልብ ሊኖረን ይገባል:: በዛም በረከትና ፈውስ መፅናናትም ይኖራል::

View Details

ጳውሎስ ይህንን መልእክት የፃፈው በሁለት ነገሮች መካከል ሆኖ ነው:: ወደ ጌታ መሔድና በዚህ ሆኖ የወንጌል ስራውን መቀጠል ቤተክርስቲያንን የመጥቀም ሀሳብ: ነገር ግን የቱን እንደሚመርጥ እንደተቸገረ ይገልጣል::

View Details

ሳሙኤል እሴይ ቤት ሔዶ በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው ይህ ነው ብሎ ኤልያብን ሊቀባው ተነሳ:: አንዳንድ ጊዜ መንፈሳዊ ነገር በውስጣችን ሲያልፍ እርግጠኛ ላልሆንባቸው ነገሮች መጋለጥ እንጀምራለን::

View Details

ማሪያም እና ማርታ እየሱስ ምንም እንኳ ወዳጃቸው ቢሆንም  እነርሱ በላኩበት ጊዜ ሳይሆን: ነገር ግን እርሱ በፈቀደው ሰአት መጣ:: የጌታ መምጣትና የነገሮቻችንም መለወጥ እኛ በምንፈልገው ጊዜ ሳይሆን ለጌታ ክብር በሚሆንበት ጊዜና ሰአት ይሆናል::

View Details

ለፊሊጵስዩስ ስዎች መልክቱን በሚፆፍበት ወቅት በእስር እንደነበር እና ይመልክቱ ዋና አላማ በሚደርስበትሁሉ ደስታው በጌታ እንደሆነ ይናገራል::

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 35

View Details

ውጤታማ ፀሎት 2ኛ ዜና:20 በፓስተር ሰመረ

እዮሳፍጥ እግዚአብሔርን ተስፋ ያደረገ ንጉሥ ነበረ:: በተጨነቀ ጊዜ እራሱን አዋርዶ የጌታን ፊት ፈለገ: በመሰጋናም ወደ ፊቱ መጣ:: በተጨነቅን ጊዜ ከማጉረምረም ወጥተን በምስጋና የአግዚአብሔርን ፊት ልንፈልግ እንደሚገባ ከእዮሳፍጥ ህይወት እንማራለን::

View Details

አግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ለመኖሩ ምልክቱ የተቀበሉትና የሚኖሩበት የሚተዳደሩበት ህግ ነው:: እንደፈለጋቸው እንዳይወጡና አንዳይገቡ የእግዚአብሔር ህልውና እየተሰማቸው በፈቃዱ ውስጥ እንዲሆኑ የተሰጣቸው ህግ ዋና ጉዳይ ነው:: *** በአዲስ ኪዳን ለምንኖር ለእኛ ደግሞ እግዚአብሔር ከፊተኞቹ ይልቅ በራሳችን ጥረት ሳይሆን በሚረዳን ፀጋ ይበልጥ በፈቃዱና በሀሳቡ ውሰጥ ልነሆን ይፈልጋል::

View Details

እግዚአብሔር ባለበት የሚገኝ ሰው ነገን ያየዋል :: እርሱ ባለበት መገኝት ዋጋ ይስከፍላል::

View Details

እግዚአብሔር ሁሉን ስለፈጠረ ክፉንም ደጉንም ያያል። ክርስትያን የተደላደለ ህይወት የሚኖረው እግዚአብሔር እንደ ሚያየው ሲረዳ ነው። እግዚአብሔር እንደሚያየው ሲረዳ ለህይወቱ ይጠነቀቃል።

View Details

ጥያቄና መልስ ክፍል 34

View Details

እግዚአብሔር  ሊሰራብን ክብሩንም ሊገልፅብን ወደ ሚፈልግበት ማንነት መሻገር የምንችለው ፤ ከእኛ ማንነት ከወጣንበት፣እንዲሁም ራሳችንን ለፈቃዱ ለማስገዛት በወሰንበት ነው:: የተሻገረ ሰው እርሱ ለእግዚአብሔር መሆን አይከብደውም::

View Details

በእግዚአብሔር በአርሱ ምርጫ ተወደናል::  በስራችን ግን ጠላቶች ነበርን:: ሰለ ፅድቃችን ሳይሆን ሰለ ፅድቁ ተወደናል:: ስለዚህ ከመዳናችን በፊት ለመዳናችን ከዳንን በኃላ ደግሞ ለተጠበቀልን የዘላለም ተስፋ እንድንበቃ በእርሱ የተጠበቅን ነን::

View Details

ነገራችንን ለጌታ ባልተውንበት ሁኔታ ውስጥ የጌታን ባለጠግነት ማየት አንችልም:: እስራኤላውያን ከግብፅ ሲወጡ የተቦካ ሊጥ ይዘው ነበር የወጡት ያግን የሚያኖራቸው አልነበረም::  በምድረበዳ ያኖራቸው የእግዚአብሔር ባለጠግነት ነው::

View Details

ሆሴ:6

እግዚአብሔር ምህረትን እንወድድ ዘንድ ጠርቶናል::  በዘመናት መካከል በጣም አስቸጋሪ ነገሮች ሲመጡ እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው ምህረትንና እርህራሔን እንድንለምን ነው::