This is a podcast from the Ethiopian Christian Fellowship in Finland, where you can listen to biblical teachings, messages, and sermons. May God bless all our listeners.
"የኢየሱስ ስም ኃይል አለው!" በሚል ርዕስ በእህት ቤተልሔም ሲሳይ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ሐዋ. 3፡1-16
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ማቴ. 18፡18-20፣ ሐዋ. 2፡1-4
"በህልውናው ውስጥ የሚገኝ እውነተኛ ዕረፍት!" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ክፍል፡ ዘጸ. 33፡14
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዘጸ. 33፡12-17፣ መዝ. 4፡8፣ ምሳሌ 1፡33፣ ማቴ. 11፡28፣ መዝ. 62፡1-2፣ መዝ.121፡1-8
"አይዞሽ አታልቅሺ!" በሚል ርዕስ በእንግዳ አገልጋይ በፓስተር ሚልክያስ ደገፉ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ሉቃ. 7፡11-17
"ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ይቻላል!" በሚል ርዕስ በሉቃ.18፡18-26 ባለው የእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመሥርቶ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
"የዘላለም ህይወት ቃል!" በሚል ርዕስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ላይ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት።
መነሻ ክፍል፡ ዮሐ. 6፡68-69
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዮሐ. 6፡1-68፣ ዘፍ. 2፡7፣ ዮሐ. 1፡3-4፣ 1 ቆሮ. 2፡13-15፣ 2 ቆሮ. 4፡16-18፣ ዮሐ. 17፡3፣ ዘፍ. 3፡22-24፣ 1 ቆሮ. 1፡8
ይዘት
መግቢያ
1) ህይወት
2) የዘላለም ህይወት
3) የዘላለም ህይወት ቃል
ማጠቃለያ
"አብረኸኝ መከራን ተቀበል!" በሚል ርዕስ በ2 ጢሞቴዎስ ላይ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 2 ጢሞቴዎስ 1-4
ሀ) መግቢያ / ዮሐ. 16፡33፣ ሐዋ. 21፡1-14፣ ሐዋ. 9፡10-16፣ 2 ጢሞ. 1፡1-5
ለ) ሐዋሪያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን፣ "አብረኸኝ መከራን ተቀል!" ሲል ምን ማለቱ ነው?
1) በጌታችን ምስክርነት ወይም በእሥረኛው በእኔ አትፈር ማለቱ ነው። 2 ጢሞ. 1፡15-18፣ ሮሜ 1፡16
2) የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገርና የማያሳፍር ሠራተኛ ሁን ማለቱ ነው። 2 ጢሞ. 2፡15-19
3) በንጹህ ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፣ እውነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን ተከተል ማለቱ ነው። 2 ጢሞ. 2፡22፣ ምሳሌ 4፡23፣ ሉቃ. 6፡45
4) በተማርኽበትና በተረዳህበት ጸንተህ ቁም ማለቱ ነው። 2 ጢሞ.
5) አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ ማለቱ ነው። 2 ጢሞ. 4፡5
"ምሥጋናውን አትርሳሺ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ መዝ. 103፡1-6
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዘዳ. 8፡1-20፣ መዝ. 106፡1-13፣ 1 ሳሙ. 7፡1-24
"አምላካዊ መልስ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ሮሜ 11፡1-6፣ 1 ነገ. 19፡1-18
መግቢያ
አምላካዊ መልስ የመጣላቸው 3 ሰዎች
ሀ) የኤልያስ ክስ ዝርዝር (1 ነገ. 19፡10 እና 14)
ለ) አምላካዊ መልስ ሲመጣ ምን ሆነ? (1 ነገ. 19፡15-18)
ሀ) የህዝቡ ዕይታ/ 14፡10-12
ለ) የሙሴ ምላሽ/ 14፡13-14
ሐ) አምላካዊ መልስ/ 14፡15-18
ሀ) የሰዎቹ ዕይታ/30፡6
ለ) የዳዊት ምላሽ/ 30፡7
ሐ) አምላካዊ መልስ/30፡7-8
321__ኢየሱስን ማወቅ ከትንሳኤ በፊት እና ቦኋላ // ወንድም ሰለሞን ጨልጌ _ከስዊድን (የእሁድ ፋሲካ ቀን ዝግጅት)
ሉቃስ 24:1-45
...ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤
ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር።...ሉቃስ 24:15-16
...የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።ኤፌ 1:17
320_በልምድ ሳይሆን በጌታ ቃል ይሁንላችሁ // ወንድም ሰለሞን ጨልጌ _ከስዊድን (የቅዳሜ ዝግጅት)
ሉቃስ 5 :1-11
...ነገሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ አለው። ስምዖንም መልሶ፦ አቤቱ፥ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ አለው። ሉቃስ 5 :4-5
319_የመስቀሉ ቃል// ወንድም ሰለሞን ጨልጌ _ከስዊድን
1ኛ ቆሮ 1:18 የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። የአርብ(ስቅለት) ቀን አገልግሎት)
የፋሲካ ኮንፈረንስ መሪ ቃል "አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል 1ኛ ቆሮ 15:20
"እግዚአብሔር ትልቅ ነው ግን ማንንም አይንቅም!" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ኢዮብ 36፡1-11
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ፊልጵ. 2፡1-12፣ ማቴ. 19፡16-22
"ከርግማን በርከትን፣ ከሞት ህይወትን እንምረጥ!" በሚል ርዕስ በ2 ክፍል የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ሁለተኛው ክፍል።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ 30
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ማር. 12፡29-30፣ ዮሐ. 14፡15-16፣ 1 ዮሐ. 2፡3-5፣ 1 ሳሙ. 12፡20-21፣ ዮሐ. 14፡4-6፣ ዘዳ. 13፡4፣ ዮሐ. 14፡21-24
"ከርግማን በርከትን፣ ከሞት ህይወትን እንምረጥ!" በሚል ርዕስ በ2 ክፍል የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ 27፣ 28 እና 29
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ገላ. 3፡13-14፣ ዘዳ. 21፡22-23፣ ዘፍ. 12፡3፣ ኢል. 2፡28፣ ሮሜ 6፡14-18፣ 8፡12-14
በማልሚ ሳሌም ኅብረት በቄስ ኢዮብ ድንቁ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፣
መነሻ የየመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ኤፌ. 6፡10-20
ለመንፈሳዊ ውጊያ የሚያስፈልጉ ነገሮች፦
1) ለመንፈሳዊ ውጊያ የሚያስፈልገን የጦር መሣሪያችን የእግዚአብሔር ቃል ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ለምን ልዩ ሆነ?
2) ሁለተኛ ለመንፈሳዊ ውጊያ የሚያስፈልገን የጦር መሣሪያችን ጸሎት ነው
3) ሦስተኛ ለመንፈሳዊ ውጊያ የሚያስፈልገን ነገር መጽናት መቻላችን ነው
ለመንፈሳዊ ውጊያ ዝግጅቱ ስንሆን እግዚአብሔር እንዴት ሊጠቀምብን ይችላል?
"አካልና ብልቶች!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 1 ቆሮ. 12፡12-30
"እኔም አሳርፋችኋለሁ!" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ማቴ. 11፡25-30
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዮሐ. 14፡26-27፣ ሮሜ 5፡1-11፣ ኤፌ. 6፡15፣ ሮሜ 14፡17-20
"ክርስቲያናዊ ትሕትና" የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት በወንድም ያቬሎ ናታዬ፣ ክፍል 2።
መነሻ ጥቅሶች፡ 1 ጴጥሮስ 5፡5፣ ፊል. 2፡1-11
ክርስቲያናዊ ትሕትና በክርስቲያን ህይወት የሚገለጥባቸው መንገዶች
1) ለራስ ትክክለኛ ዕይታ መኖር /ሮሜ 12፡3 /
2) ሌሎችን ማስቀደም /ፊል. 2፡3 /
3) ምህረት ማድረግን አለመቸገር / ኤፌ. 4፡32 /
"ክርስቲያናዊ ትሕትና" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት።
1) መግቢያ - ትሕትና ምንድን ነው? / መዝ. 86፡1፣ ማቴ. 5፡3/
2) ክርስቲያናዊ ትሕትና / ፊል. 2፡3፣ ኤፌ. 4፡2፣ 1 ጴጥ. 5፡5፣
3) ትሕትና በክርስቶስ ህይወት ምሳሌነት /ማቴ. 11፣ 29፣ ፊል. 2፡1-11/
"ለሁሉም ዘመን አለው - ዘመኑ የመገለጥ ነው" - የ2024 ዘመን መለወጫ ዋዜማ መርሃ ግብር ላይ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ መክ. 3፡1-8፣ 1 ነገ. 17፡1-4፣ 1 ነገ. 18፡1-2
"አሮጌ እርሾና አዲስ ሊጥ" - የ2024 ዘመን መለወጫ ዋዜማ መርሃ ግብር ላይ በፓስተር ዳንኤል ሳቡሬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 1 ቆሮ. 5፡7
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዘጸ. 12፡15፣ ዘጸ. 13፡7፣ ማቴ. 16፡6፣ ማር. 8፡15፣ ገላ. 5፡1-15
የእግዚአብሔር ሥጦታ - የኢየሱስ ክርስቶስን ጽንሰትና ውልደት በተመለከተ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ማቴ. 1፡18-25፣ ሉቃ. 1፡26-35፣ ሉቃ. 2፡8-12፣ 21-32፣ 2፡15-20፣ 41-51
"ፍለጋውን መከተል" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
በዚህ ክፍል የተነሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡- መዝ. 25፡4-7፣ ሩት 1፡1-18፣ ማቴ. 25፡1-13፣ ሆሴ. 6፡3፣ ዮሐ. 14፡1-6፣6-7
"ኢየሱስን መውደድ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ጌታ ኢየሱስ ሰዎችን ጥያቄ እየጠየቀ ያገለግላቸው ነበር።
ቁ. 15 "ከእነዚህ አብልጠህ ትወደኛለህን?"
ቁ. 16 "በእውነት ትወደኛለህን?"
ቁ. 17 "ትወደኛለህን?"
ኢየሱስን መውደድ ማለት ምን ማለት ነው?
ጴጥሮስ ለጌታ ጥያቄዎች መልስ ከሰጠ በኋላ በህይወቱ የታዩ ለውጦች፡-
"እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ሮሜ 9፡1-4፣ 10፡1-2
ሀ) በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ራሱ ሊያዝን እንደሚችል ተጽፏል፡ -
1) እግዚአብሔር ያዝናል - ዮናስ 4፡11
2) ጌታ ኢየሱስ ያዝናል - ሉቃ.19፡41፣ ዮሐ. 11፡33-34፣ ማር.6፡34
3) መንፈስ ቅዱስ ያዝናል - ኤፌ. 4
ለ) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ያልሆነ ሐዘን
1) በእግዚአብሔር ምህረት ላይ የሚያስቆጣ ነው - ዮናስ 4፡1-3
2) ወደ ኀጢአት የሚወስድ ነው - 2 ሳሙ. 13፡1- 19
3) ተስፋ እንዳይታየን የሚያደርግ ነው - 1 ተሰሎ. 4፡15-18
ሐ) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን
1) ሰዎችን ወደ ንስሐ የሚገፋ ነው - ሐዋ. 2፡37-38
2) እግዚአብሔር ሲገስጸን የሚሰማን ሐዘን ነው - 2 ቆሮ. 7፡8-11
3) ሌሎች ችግር ውስጥ ሲሆኑ የሚሰማን ሐዘን ነው - ሮሜ 9፡1-5፣ 10፡1
4) ወደ ጾምና ጸሎት የሚመራ ሐዘን ነው - ነህ. 1፡1-4
በአባቶች ቀን "የሁላችን አባት - አብርሃም" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ ጥቅስ፡ ሮሜ 4፡16-17
አብርሃም በእምነት ያደረጋቸው 5 ነገሮች፡ -
1) አብርሃም #በእምነት የታዘዘ ሆነ - ዕብ. 11፡8፣ ዘፍ. 12፡1
2) አብርሃም #በእምነት ተቀመጠ - ዕብ. 11፡9-10፣ ዕብ. 12፡22፣ 1 ጴጥ. 2፡11፣ ፊል. 3፡20
3) አብርሃም #በእምነት ተስፋ አደረገ - ሮሜ 4፡18፣ ዕብ. 11፡11፣ ዘፍ. 15
4) አብርሃም #በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ - ሮሜ 4፡19
5) አብርሃም #በእምነቱ በረታ/ጸና እንጂ አተጠራጠረም - ሮሜ 4፡20
እምነቱም ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት - 4፡22-23
"ጌታ ሊያድ'ሰን ይፈልጋል!" በሚል ርዕስ በወንድም አብርሃም ፈንተ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
1) እግዚአብሔር እንዲያድሰን፣ ትሑት መሆን ከእኛ ይጠበቃል። ኢሳ. 66፡2፣ መዝ. 51፡12፣
2) እግዚአብሔር እኛን የሚያድስበት ዓላማ / ለእውነተኛው አምላክ ምስክሮች እንድንሆን ነው።
3) የእግዚአብሔር ተልዕኮ ለእኛ
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ 1 ሳሙኤል 30፡1-> ፣ ዕብ. 3፡13፣ 1 ጴጥ. 5፡6፣ ዘሌ. 18፡15፣ ፊል. 2፡5-11፣ ሮሜ 1፡16፣ 1 ዮሐ. 1፡1፣
"እግዚአብሔር ለማዳን ሥራው ይፈልጋችኋል!" በሚል ርዕስ በፓስተር አለማየሁ ሙልጌታ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ርዕስ: እግዚአብሔር ለማዳን ሥራው ይፈልጋችኋል!
1) እግዚአብሔር ቀዳሚው አጀንዳው ሰዎችን ማዳን ነው/ መሳ. 3፣ 10፣ ኢሳ. 9፡6-7፣ ማቴ. 1፡20-21፣ ቲቶ 2፡10-11፣ ሮሜ 1፡16-17
2) ሰዎች ነፍሳቸው እንድትድንና ከክፋት እንዲጠበቁ እግዚአብሔር ይፈልጋል / ዮሐ. 17፡15
3) እግዚአብሔር በእኛ በኩል ሰዎችን ማዳን ይፈጋል
1) የዮሴፍ ታሪክ
2) የሶሪያዊው ንዕማን አገልጋይ ታሪክ
3) የአስቴር ታሪክ
"ቃሉ ያሸንፋል!" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ ፋሼ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ዮሐ. 1፡1-13፣ 1 ዮሐ. 1፡1-5፣ 2፡1-4፣ 3፡1-4፣ ራዕ. 22፡12-21
"ቅዱስ ጥበብ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ምሳሌ 1፡7፣ 1 ጴጥሮስ 1፡13-17፣ ሉቃስ 2፡32፣ ሮሜ 3፡11-12፣ 1 ዮሐ. 4፡13-21
በማልሚ ሳሌም በተዘጋጀው ኮንፍራንስ ላይ "ታምራትን ለማየት ወደፊት ቀጥል!" በሚል ርዕስ በፓስተር ሰሎሞን አምዴ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ዘጸዐት 14፡15-16
ሌሎች ክፍሎች፡ ዕብ. 10፡35-38፣ 1 ቆሮ. 11፡17
በማልሚ ሳሌም በተዘጋጀው ኮንፍራንስ ላይ "ሙሽራውን ለመቀበል የተዘጋጃችሁ ሁኑ!" በሚል ርዕስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ማቴ. 25፡1-13
በማልሚ ሳሌም በተዘጋጀው ኮንፍራንስ ላይ "እግዚአብሔር ህዝቡን መባረክ ይፈልጋል!" በሚል ርዕስ በፓስተር ሰሎሞን አምዴ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ትንቢተ ሐጌ ምዕራፍ 1 እና 2
"የጌታን መንገድ መከተል" ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 15፡ የጌታን መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - 5) በጸሎት መትጋት (1 ተሰሎንቄ 5፡16-18)
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡ -
ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ይዘትና ቅደም ተከተል (ማቴ. 6፡9-13)
4) የጸሎቱ መደምደሚያ
1) ዘላለማዊ መንግሥት የእግዚአብሔር ነው
2) ዘላለማዊ ኃይል የእግዚአብሔር ነው
3) ዘላለማዊ ክብር የእግዚአብሔር ነው
"የጌታን መንገድ መከተል" ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 15፡ የጌታን መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - 5) በጸሎት መትጋት (1 ተሰሎንቄ 5፡16-18)
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡ -
ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ይዘትና ቅደም ተከተል (ማቴ. 6፡9-13)
3) ምድራዊ ህይወታችንን የሚመለከተው የጸሎቱ ክፍል
ሀ) ዕለት በዕለት ስለሚያስፈልጉን ነገሮች መጸለይ አለብን፣ ማቴ. 6፡11፣ ማቴ. 6፡25፣ 31-32፣ ፊልጵስዩስ 4፡6፣
ለ) በሌሎች ሰዎችና በእኛ መካከል ስለሚኖረን ግንኙነት መጸለይ አለብን፣ ማቴ. 6፡12፣ ሉቃስ 11፡4፣ 1 ዮሐንስ 4፡8፣
ሐ) እግዚአብሔር ከፈተናና ከክፉው እንዲጠብቀን መጸለይ አለብን፣ ማቴ. 6፡13ሀ፣ ማቴ. 26፡41፣ ማቴ. 13፡37-39፣ 1 ጴጥሮስ 5፡5-8፣ 1 ተሰሎ. 3፡3
በማልሚ ሳሌም ኅብረት በነበረው ኮንፍራንስ ላይ በፓስተር ሳምሶን ስምዖን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፡ ፊልጵ. 1፡8-11
"ምን ይታይሃል/ይታይሻል/ይታያችኋል?'' በሚል ርዕስ በፓስተር ሚልክያስ ደገፉ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡- ማርቆስ 8፡22-25፣ ኤርሚያስ 1፡11-12
"የጌታን መንገድ መከተል" ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 12፡ የጌታን መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - 5) በጸሎት መትጋት (1 ተሰሎንቄ 5፡16-18)
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡ -
ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ይዘትና ቅደም ተከተል (ማቴ. 6፡9-13)
2) የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ የሚያተኩረው የጸሎት ክፍል (ማቴ. 6፡ 9ሐ - 10ለ)
ሀ) የእግዚአብሔርን ስም መቀደስ / ማቴ. 6፡9ሐ፣ ዘሌ. 11፡44፣ ኢሳያስ 8፡13/
ለ) የእግዚአብሔር መንግሥት እንድትመጣ መለመን /ማቴ. 6፡10ሀ፣ ሮሜ 14፡17፣ ማቴ. 5፡6፣ ማቴ. 6፡33/
ሐ) የእግዚአብሔር ፈቃድ በምድር እንዲሆን መለመን /ማቴ. 6፡10ለ፣ ሮሜ 8፡14፣ ሮሜ 12፡2
"የፍቅር ዕዳ አለብን!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ ጥቅስ፡ ሮሜ 13፡8
መግቢያ፡ ቆላ. 2፡14፣ ገላ. 3፡13፣ 1 ቆሮ. 6፡19-20
በክርስቶስ ነጻ የወጣን 3 ዓይነት ዕዳ አለብን፡ -
1) የወንጌል ዕዳ አለብን ሮሜ 1፡14-15፣ ሐዋ. 9፡1-19
2) ለጌታ ተለይተን በቅድስና ህይወት የመኖር ዕዳ አለብን ሮሜ 8፡12-13
3) ሌሎችን የመውደድ ዕዳ አለብን ሮሜ 13፡8፣ ሮሜ 15፡24-27
ማቴ. 18፡21-35
"ክቡር የሆነው እምነትና ተስፋችን!" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ /2 ጴጥሮስ 1፡1-11/
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ /1 ጴጥሮስ ከምዕራፍ 1-5፣ ዮሐ. 21፡15-22፣ ኤርሚያስ 32፡17-19፣ ምሳሌ 2፡6፣ ገላቲያ 5፡22-23/
"እግዚአብሔርን ፍራ/የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት። ክፍል 2
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ፡ መክብብ 12፡1 3-14
እግዚአብሔርን ስለመፍራት 10 ነጥቦች፡ -
1) እግዚአብሔርን ፍራ የሚለው ትዕዛዝ ለእግዚአብሔር ህዝብ የተሰጠ ነው /1 ጴጥሮስ 2፡17፣ ዘዳግም 6፡13፣ ዘዳግም 10፡20/
2) እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው /ምሳሌ 1፡7፣ መዝሙር 111፡10፣ 1 ቆሮንቶስ 1፡20-25/
3) እግዚአብሔርን መፍራት የምንማረውና የምናድግበት ነገር ነው /ዘዳግም 17፡19-20፣ ዘዳግም 31፡13/
4) እግዚአብሔርን መፍራት የሚታይ ነገር ነው /ዘፍጥረት 20፡9-11/
5) እግዚአብሔርን መፍራት ከኃጢአት መራቅ ነው /ኢዮብ 28፡28/
6) እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል /ምሳሌ 8፡13/
7) እግዚአብሔርን መፍራት በኃጢአተኛ አይቀናም /መዝሙር 73፡1-28፣ ምሳሌ 23፡17-18/
8) እግዚአብሔርን መፍራት የእግዚአብሔርን ቃል ያስቀድማል /ምሳሌ 1፡29-31/
9) እግዚአብሔርን መፍራት በደልና በሰው ፊት ማድላት የለውም /2ዜና 19፡6-9/
10) እግዚአብሔርን መፍራት ከህይወት ሊጠፋ ይችላል /ኢዮብ 15፡4/
"የነገሩን ፍጻሜ እንስማ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት።
መሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ መክብብ 12፡1-12
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች / 1 ነገሥት 11፡1-6፣ ሮሜ 10፡17፣ ዳንኤል 5፡1-31 /
"የጸሎታችን መልስ ለምን ይዘገያል?" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ ፋሼ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ማር. 5፡21-43
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች /ኢዮብ 40፡1-7፣ ያዕ. 4፡3
"ወንጌል ሲሠራ ጠላት አይወድም!" በእህት ሙሉ ወልደሚካኤል የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ሐዋ. 6፡7-15
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ / ሐዋ. 2፡40-43፣ 3፡4-6፣ 4፡4፣ 5፡14፣ 6፡7 /
"የጌታን መንገድ መከተል" ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 12፡ የጌታን መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - 5) በጸሎት መትጋት (1 ተሰሎንቄ 5፡16-18)
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡ -
ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ይዘትና ቅደም ተከተል (ማቴ. 6፡9-13)
1) የጸሎት መግቢያ (6፡ 9ሐ)
ሀ) የእግዚአብሔርን አድራሻ በመናገር ይጀምራል / መዝሙር 11፡4፣ 103፡19/
ለ) በእግዚአብሔርና በእኛ መካከል ያለውን ግንኙነት ይገልጻል / ዮሐ. 1፡12፣ ሮሜ 8፡15፣ ገላቲያ 4፡6፣ ማርቆስ 14፡36 /
"ነውርን መናቅ!" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ዕብ. 12፡1-2
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ፊልጵ. 3፡12-14፣ ማቴ. 15፡21-28፣ ዘፍ. 28፡10-17፣ 30፡1-3፣ 30፡27-32፣ 31፡4-14
"የእግዚአብሔር ማህተም!" በሚል ርዕስ በጌታ ራት ቀን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
በዚህ ክፍል የቀረቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ /ራዕይ 9፡4፣ ዘፍጥረት 4፡1-15፣ ኢያሱ 2፡1-19፣ ዘጸአት 12፡1-13/
"መቀጣትን ታገሱ!" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ ፋሼ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መሪ ጥቅስ፡ ዕብ. 12፡6-13
ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ 2 ጢሞቴዎስ 1፡6-7 / ምሳሌ 10፡17 / ምሳሌ 12፡1 / ምሳሌ 29፡17 /
"የጌታን መንገድ መከተል" ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 12፡ የጌታን መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - 5) በጸሎት መትጋት (1 ተሰሎንቄ 5፡16-18)
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡ -
1) አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውነታዎች ስለጸሎት / ማር. 11፡24፣ ዮሐ. 17፣ ዘፍ. 4፡26፣ 1 ተሰሎንቄ 5፡17/
2) የጸሎት ምንነት / ማቴ. 6፡6፣ /
3) የጸሎት አስፈላጊነት / ዮሐ. 15፡4፣ ማቴ. 26፡41፣ ማቴ. 7፡7-8/
"የጌታን መንገድ መከተል" ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 11፡ የጌታን መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - 4b) የእግዚአብሔርን ቃል መሞላት (ቆላ. 3፡16) ... ካለፈው የቀጠለ
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡ -
የእግዚአብሔርን ቃል የመሞላት ፋይዳዎች፡
4) እግዚአብሔር የሚመራን በቃሉ ነው / ኢሳያስ 48፡17-19፣ መዝምሙር 119፡105/
5) እግዚአብሔር ማንኛውንም ነገር በህይወታችን የሚሠራው በቃሉ ነው / ኢሳያስ 55፡10-11፣ መዝሙር 107፡19-20፣ 2 ጢሞቴዎስ 3፡16-17፣ 2 ሳሙኤል 7፡1-13፣ 1 ነገሥት 6፡11-12፣ ዘፍጥረት 15፡1/
6) መንፈሳዊ ኅብረታችን የሚገነባው በቃሉ ነው / ቆላስይስ 3፡16
273 || ምስክሮቼ ትሆናላችሁ || ዘገዬ መኮንን ወ/ዊ
የሐዋ 1:1-10 የአዲስኪዳን ቤተክርስቲያን በሃይል.በክብር እና በሞገስ ጀመረች
የሐዋ 8:1-5በበኢየሩሳሌም ባለች ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ሁሉም ከሐዋርያትም በቀር ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ አገሮች ተበተኑ።
የሐዋ 9:1 ለአህዛብ ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጌል ተሰበከላቸው :: በዚህም መልክ ወንጌል ከእስራኤልወደ አህዛብ ወጣ::
"ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሁለተኛው ክፍል።
መነሻ ጥቅስ፡ ሐዋ. 1፡1-11
"ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ክፍል ።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ሉቃስ 23፡1-5
ከኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ ጋር የተያያዙ ሰዎች ተግባርና ለእኛ የሚሰጠን ትምህርት፡ -
1) ይሁዳ፡ ሉቃ.22፡3/ ማቴ. 27፡3
2) ጴጥሮስ፡ ሉቃ. 23፡32፣34
3) ጲላጦስ፡ ማቴ. 27፡19 / 27፡24
4) የካህናት አለቆችና ህዝቡ፡ ማቴ. 26፡59-60 / ማቴ. 27፡17-18
5) በልብሱ ዕጣ የሚጣጣሉ ቁማርተኞች፡
6) ቆሞ የሚመለከት ህዝብ፡
7) መኳንንት፡
8) ጭፍራዎች/ወታደሮች፡
9) ከኢየሱስ ጋር ከተሰቀሉት ወንበዴዎች ተሳዳቢው፡ ሉቃ.23፡39
10) ከኢየሱስ ጋር ከተሰቀሉት ወንበዴዎች የተጸጸተው፡
1 1) የኢየሱስ መስቀል ሥር የነበረው ሮማዊ የመቶ አለቃ፡ ሉቃ. 23፡44-46
1 2) ደረታቸውን የደቁት ሰዎች፡ ሉቃ. 23፡48
1 3) ኢየሱስን የሚያውቁት ሴቶች፡ ሉቃ. 23፡55
የ2023 ፋሲካ ኮንፍራንስ 4ኛውና የመጨረሻው መርሃ ግብር
ርዕስ፡ የድል ኃይላችን!
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ 1 ቆሮ. 15፡3-4 / ኢሳ. 53፡5
የክርስቶስ፦ 1) ሞት፣ 2) ትንሳኤና 3) ዕርገት
ሀ) የኢየሱስ ሞት ለአማኝ የድል ኃይል ነው ስንል ምን ማለታችን ነው?
ለ) የኢየሱስ ትንሳኤ ለአማኝ ምንድን ነው?
ሐ) የኢየሱስ ዕርገት ፋይዳዎች
የ2023 ፋሲካ ኮንፍራንስ 2ኛው መርሃ ግብር
ርዕስ፡ በመጽሐፍ ዘመኑን ማስተዋል!
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዳንኤል ፡1-2, 20-23 / ሮሜ 13፡11
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ 1 ዜና 12፡32 / ኤር 29፡10 / ምሳሌ 28፡13 / ሉቃስ 17፡26-30 / ያዕቆብ 3፡13-18 / ምሳሌ 8፡14
የ2023 ፋሲካ ኮንፍራንስ 2ኛው መርሃ ግብር
ርዕስ፡ ወደ ሰው አትሩጡ፣ ወደ እግዚአብሔር ሩጡ!
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ 2 ሳሙኤል 21፡1 (ኢያሱ 9)፣ ማር. 5፡25-29 / ማር. 9፡17-27
የ2023 ፋሲካ ኮንፍራንስ የመጀመሪያው መርሃ ግብር
ርዕስ፡ ለእግዚአብሔር ሰው ሁን!
መነሻ የመጽሕፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ 1 ነገሥት 2፡1-4 / 1 ጢሞቴዎስ 6፡11
ለእግዚአብሔር ሰው የመሆን ምንነት፡ መዝ. 89፡20 / ሐዋ. 13፡22
ለእግዚአብሔር የተገኙ ሰዎች ልዩ መለያዎች፡ -
1) ቃሉን የመታዘዝ ህይወት ይታይባቸዋል - 1 ተሰሎንቄ 2፡13 / ኢሳያስ 66፡2
2) የእግዚአብሔር አብሮነት መለያቸው ነው - 2 ነገሥት 4፡9 / 1 ጢሞቴዎስ 6፡11
3) የእግዚአብሔር ባህሪ በግልጽ ይነበብባቸዋል - ኤፌሶን 4፡23-24 / ሮሜ 8፡29
4) የማያሻማና ግልጽ የሆነ መለኮታዊ ራዕይ አላቸው - ሐዋ. 26፡18-1
በሆሳና እሑድ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
በዚህ ክፍል የቀረቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ዘካ. 9፡9 / 1ጴጥ. 5፡6-7 / 1 ሳሙ. 17 / 2 ቆሮ. 2፡14-17
"ድል መንሳት ሆኖልናል!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ ጥቅስ፡ ራዕ. 12፡10-11
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ራዕ. 5፡1-5/ ዕብ. 12፡23 / 1 ዮሐ. 2፡1 /
"አምላካችን ልዑል ነው!" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ ጥቅስ፡ ኤር. 32፡17
በዚህ ክፍል የቀረቡ ሌሎች ጥቅሶች፡ ሐዋ. 5፡38-39/ ቆላ. 1፡16
"የጌታን መንገድ መከተል" ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 10፡ የጌታን መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - 4a) የእግዚአብሔርን ቃል መሞላት (ቆላ. 3፡16)
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡ -
0) ስለመሞላት አጭር መግቢያ
የእግዚአብሔርን ቃል የመሞላት ፋይዳዎች፡
1) አዲሱ ማንነታችን የሚገነባው በቃሉ ነው! ቆላ. 3፡10-11/
2) አሮጌው ማንነታችን የሚወገደው በቃሉ ነው! ማቴ. 12፡35/ 1 ጴጥ. 2፡1-3/ ኤፌ. 4፡22-24/ ቆላ. 3፡8-9/
3) ዲያብሎስን መቃወም የምንችለው በቃሉ ነው! ኤፌ. 6፡11፣ 17/ 2 ቆሮ. 2፡11/ ማቴ. 4፡1-12/
"ስሙኝ!" በሚል ርዕስ በእህት አሰገደች ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ ጥቅስ፡ ኢሳ 46፡3 "እናንት የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ቅሬታ ሁሉ፣ ከተፀነሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የያዝኋችሁ፣ ከተወለዳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የተሸከምኋችሁ ስሙኝ።"
መልዕክቱ የተመሠረተበት ክፍል፡ ዘፍጥረት ምዕራፍ 6
የመልዕክቱ ፍሬ ሐሳቦች/ እግዚአብሔርን ስለመስማት ከኖኅ ህይወት የምንማራቸው 4 ነጥቦች፡ -
"በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ መዳናችሁን ፈጽሙ!" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ፊል. 2፡12/ ፊል. 2፡ 1-5/ ኢሳ. 66፡2/ ምሳ. 1፡7/ 1 ዮሐ. 1፡8-9/ ዕብ. 12፡2/
"መንፈስ ቅዱስን መጠማት" በሚል ርዕስ በወንድም እምነት ካሣ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
በመልዕክቱ የጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች /ሐዋ. 1፡8፣ 2፡17-18፣ 2፡1-4፣ 3፡1-10፣ 4፡3፣ ሮሜ 8፡26፣ ኤፌ. 5፡18፣ መዝ. 42፡1-2/
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 9፡ የጌታን መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - 3) በአዕምሮ መታደስ (ሮሜ 12፡2)
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡ -
0) የቀደሙት 8 ክፍል አጭር ክለሳ
1) ማደስ/ዕድሳት ምንድን ነው?
2) አዕምሮ በመጽሐፍ ቅዱስ
1) የሐሳብና የውሳኔ ማዕከል ነው (መዝ. 36፡1-4፣ ዳን. 1፡8)
2) የመንፈሳዊ ውጊያ የጦር ሜዳ ነው (ዘፍ. 3፡4-6፣ 6፡10-11፣ ማቴ. 15፡18-20፣ ቆላ. 3፡1-2)
3) አዕምሮን ማደስ የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? (ሮሜ 12፡2፣ ኤፌ. 2፡10፣ ዘፍ. 1፡27፣ ኤፌ 4፡17-32)
4) አዕምሮን የማደሻ መንገዶች
1) የእግዚአብሔርን ቃል መሞላት (ቆላ. 3፡16)
2) በጸሎት መትጋት (ኤፌ. 6፡18፣ 1 ተሰሎ. 5፡16-18፣ 1 ጴጥ. 4፡7)
3) የራስን ሐሳብ መመርመር (መዝ. 4፡4)
"እጥፍ መንፈስ መቀበል!" በእህት እሳየሁ አበበ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 1 ነገ. 19፡19-21/2 ነገ. 2፡1-22
"ጸንታችሁ ቁሙ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ክፍል 2።
"ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ ዳግመኛም በባርነት ቀንበር አትጠመዱ።" (ገላ. 5፡1)
በዚህ ክፍል የሚከተሎት ርዕሰ ጉዳዮች ተዳሰዋል፡ -
1) በእምነት መጽናት ይገባናል! (ቆላ. 2፡5 ፣ ዕብ. 11፡27)
2) በፍቅር መጽናት ይገባናል! (1 ቆሮ. 13፡7 ፣ ኤፌ. 3፡16-17 ፣ ቲቶ 2፡2)
3) በትዕግሥት መጽናት ይገባናል! (ያዕ. 5፡11 ፣ 2 ጢሞ. 2፡24)
4) በመከራ መጽናት ይገባናል! (ዕብ. 12፡1-3 ፣ ያዕ. 1፡12)
5) በአገልግሎት መጽናት ይገባናል! (2 ጢሞ. 4፡2)
6) በጸጋ መጽናት ይገባናል! (ዕብ. 13፡9)
7) በጸሎት መጽናት ይገባናል! (ሮሜ 12፡12)
1) በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ (1 ሳሙ. 2፡1 ፣ መዝ. 37፡23 ፣ 1 ዜና 17፡14)
2) በእዚአብሔር ቃል ላይ ህይወታችንን በመመሥረት (ማቴ. 7፡ 24-27)
3) በጸሎት መትጋት (ማቴ. 24፡36-44)
4) በመልካም ምክር (ምሳ. 15፡22 ፣ 19፡21 ፣ 20፡18)
5) መንፈሳዊ ኅብረት ውስጥ በመሆን (1 ቆሮ. 12፡4-11 ፣ መዝ. 133፡1 >)
"ጸንታችሁ ቁሙ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ክፍል ።
"ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ ዳግመኛም በባርነት ቀንበር አትጠመዱ።" (ገላ. 5፡1)
በዚህ ክፍል ጥቅም ላይ የዋሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ገላ. 2፡11-13/ ገላ. 3 እና 4/ ማቴ. 10፡22/ ማቴ. 24፡13/ 1 ጢሞ. 4፡16/ ሉቃ. 8፡15/ ቆላ. 2፡5/ ዕብ. 11፡27/ 1 ቆሮ. 13፡11/ ቲቶ 2፡2/ 1 ቆሮ 13፡7
በኮንቱላ ኅብረት በተዘጋጀው የዘመን መለወጫ ኮንፍራንስ ላይ በፓስተር አሌክስ ደፋር የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ርዕስ፡ እግዚአብሔር ይሠራል!
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ኤር. 18፡1-6/መክ. 3፡11
በኮንቱላ ኅብረት በተዘጋጀው የዘመን መለወጫ ኮንፍራንስ ላይ በፓስተር አሌክስ ደፋር የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ርዕስ፡ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ነን?
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ሉቃ. 1፡5-13
በኮንቱላ ኅብረት በተደረገው የዘመን መለወጫ ፕሮግራም ላይ የቀረበ መልዕክት
"የእግዚአብሔርን ማዳን ታያላችሁ!" በሚል ርዕስ በፓስተር አሌክስ ደፋር የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ዘጸ. 14፡13-14
በግርግም አስተኛችው - በትንሹ ገና ቀን በእህት ርትቫ ኮንኮላ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
በክፍሉ የቀረቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ሉቃ. 2፡7 እና ማቴ. 25፡1-3
"ወንጌላችን ኢየሱስ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ የቀረበ ትምህርት ክፍል 3 እና የመጨረሻው።
በዚህ ክፍል የተነሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ሮሜ 1፡1-7/ ኢሳ. 6፡3/ ዳን. 5፡23/
"ወንጌላችን ኢየሱስ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ የቀረበ ትምህርት ክፍል 2።
በዚህ ክፍል የተነሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ሮሜ 1፡1-7/ ማቴ. 1፡1-17/ ዮሐ. 1፡14/ ዕብ. 2፡14-17/ ማቴ. 1፡18/ ሉቃ. 1፡26-35/ ማቴ. 28፡18-20
"ወንጌላችን ኢየሱስ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ የቀረበ ትምህርት ክፍል ።
በዚህ ክፍል የተነሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ሮሜ 1፡1-7/ ሐዋ. 9፡1-17/ ሉቃ. 24፡25-2፣ 45/ ገላ. 3፡8-9/ ገላ. 1፡11-17/ ሐዋ. 13፡1-3/
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 8፡ የጌታ መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - 2) በእግዚአብሔር ጸጋ መደገፍ
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡-
ጸጋ ምንድን ነው?
ደጋ በአማኝ ህይወት ያከናወናቸው 2 ነገሮች
ድነታችን የጸጋ ውጤት ነው
አሁን ያለን መንፈሳዊ አቋም የጸጋ ውጤት ነው
ክርስቶስን በመከተል ህይወት የጸጋ ሚና
መካድ የሚገባንን ያስክደናል
በኀጢአት መኖርን ያስክደናል
ዓለማዊ ምኞትን ያስክደናል
መማር የሚገባንን ያስተምረናል
ራስን መግዛትን ያስተምረናል
እውነተኛ መንፈሳዊ ህይወትን መኖር ያስተምረናል
የተሰጠንን አገልግሎት በትጋት እንድናገለግል ይረዳናል
ስለክርስቶስ መከራንና የሥጋ ድካምን እንድንቋቋም ይረዳናል
የተሟላና የሚካፈል ኑሮ እንዲኖረን ይረዳናል
በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ቲቶ 2፡11-12/ ኤፌ. 2፡8/ ሮሜ. 3፡23-24/ ሮሜ. 15፡1-2/ 1 ጢሞ. 6፡9-10/ 2 ጢሞ. 1፡7/ 1 ዮሐ. 2፡28-29/ 2 ጴጥ. 1፡3/1 ቆሮ. 15፡10/ 2 ቆሮ. 12፡9-10/ 2 ቆሮ. 9፡8/
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 7፡ የጌታ መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት ራስን ማስገዛት
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡-
የጌታን መንገድ በመከተል ሂደት የመንፈስ ቅዱስ ሚናዎች፡ -
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ሮሜ 8፡12-17/ ዮሐ. 3፡5-6/ ኤፌ. 1፡13/ ዮሐ. 14፡15-26/ ዮሐ. 16፡5-15/ ሐዋ. 1፡7-8/ ሐዋ. 8፡26-40/ ሮሜ 8፡26-27/
"እግዚአብሔር ለምን ጠራን?" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ራዕ. 5፡9-14/ 1 ጢሞ. 1፡5/ ዘጸ. 4፡10-17/ ሉቃ. 1፡55
"ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷል" በሚል ርዕስ የጌታን ራት አስመልክቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ - ዘጸ. 1 2፥1-51/ ሉቃ. 22፡7-20/ 1 ቆሮ. 5፡6-8/ ሮሜ 3፡23-26/ ሮሜ 5፡8-9/ ዕብ. 9፡14/ 1 ዮሐ. 1፡7/ ሉቃ. 22፡19/ ዕብ. 1፡1-3/ ዮሐ. 3፡16
242_ተስፋ አንቆርጥም በፍርዱ መሰረት(ቄስ)
(በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤ )2ቆሮ1:8
(… ተስፋ እንዳንቆርጥ ፣ቁጥር:13 … አመንኩ ስለዚህም ተናገርኩ ቁጥር 18 የሚታየው የጊዜው ነውና የማይታየው ግን የዘላለም ነው። )2ቆሮ4፡1-18
(እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ) ፊሊ 3:10-11
241_ ታናሽ መንጋ በተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)
ዳሩ ግን መንግሥቱን ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።ሉቃስ 12:31-32
እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም። ኤፌ 2:19
ነገር ግን አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ፥ አትፍራ፥ አንተም እስራኤል ሆይ፥ አትደንግጥ፤ እነሆ፥ አንተን ከሩቅ ዘርህንም ከተማረከባት ምድር አድናለሁ፤ ያዕቆብም ተመልሶ ያርፋል ተዘልሎም ይቀመጣል፥ ማንም አያስፈራውምም።ኤር 46:27
240_እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማነው? በዘገዬ መኮንን (ወንጌላዊ)
ዋና መነሻ ሃሳብ የመጽሃፍ ቅዱስ ምእራፍ ዘፍ 20:1-18 በሙሉ
እግዚአብሔርን መፍራት የምንማረው:የምናሳድገው እና የምንለማመደው ነው::
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል። መዝ 25:12
በጥሞና ሊሰሙት የሚገባ::
239_በአንደበታችን ሃይል ይህንን ዘመን እንለፍ በእምነት ካሳ(ወንድም)
ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ይበላል፤... ምሳሌ 13:2
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው፣መስማትም በእግዚአብሄር ቃል ነው። ሮሜ 10፡ 17
የእ/ርን ቃ እናውጅ ንግግር ወደ ሃሳብ ፤ሃሳብም ወደ ተግባር ያድጋልና፤..
ዮሐ 1:12 ዮሐ 3:16 ዮሐ 3:18 ሉቃ 10:19
ሮሜ 3:24 ሮሜ 8:1 ሮሜ 8:11 ሮሜ 8:17
ሮሜ 8:37 1ቆሮ 6:11 2ቆሮ 2:14
እግዚአብሄር ያላለውን የሚል :የሚፈጽምስ ማነው (ሲ/ር ለምለም ጌታቸው)
ሰቆ 3:25-37 ... ጌታ ያላዘዘውን የሚልና የሚፈጽም ማን ነው?
ዘፍ 38 :1-11...ይሁዳም ምራቱን ትዕማርን፦ ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወንድሞቹ እንዳይሞት ብሎአልና። ትዕማርም ሄዳ በአባትዋ ቤት ተቀመጠች።
1ሳሙ 16:1-13 ሳሙኤልም እሴይን፦ የቀረ ሌላ ልጅ አለህን? አለው
መዝ 27:10 አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ።
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 6፡ የጌታ መንገድ ባህሪያት፡ በመበተን መሰብሰብ
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡-
1) ልግስናና ዘላለማዊ ፋይዳው
2) ልግስናና እውነተኛ ኃይማኖት
3) 7 የልግስና መሠረታዊ ምክንያቶች
በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 13፡1-17/ መዝ. 112፡9/ ማቴ. 25፡34-36/ ያዕ. 2፡27/ 2 ቆሮ. 9፡6-12/ ማቴ. 19፡21/ 2 ቆሮ. 8፡1-5/
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 5፡ የጌታ መንገድ ባህሪያት፡ በክፉ ፈንታ መልካምን መመለስ
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡-
1) ክፉን በመልካም ስለመመለስ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
2) በክፉ ፈንታ መልካምን ስለመመለስ የጌታ ምሳሌነት
3) ክፉን በክፉ መመለስ የማይገባን ስለምንድን ነው?
በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 13፡1-17/ ሮሜ 12፡17-21 (ምሳሌ 25፡21-22)/ 1 ተሰ. 5፡15/ ሉቃ. 22፡63-65/ ሉቃ. 23፡34/ ማቴ. 5፡44 (ኢሳ. 53፡12)/ ማቴ. 5፡44-45ሀ/ 1 ጴጥ. 3፡9/ ኤፌ. 4፡31-32
በዚህ ጊዜ፡ ወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተ ክርስቲያንን ወክሎ አጠቃላይ መልዕክት አስተላልፎ ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፣ በዕለቱ የነበሩት ሽማግሌዎች ወንድም ያቬሎ ናታዬና ወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) በተሰጣቸው ጊዜ በራሳቸው አጭር መልዕክት አስተላልፈው ይቅርታ ጠይቀዋል።
"የጌታ ራት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ጌታ በሰጠን የመታሰቢያ ሥርዓት ውስጥ እንድናስተውል የሚፈለጉ 3 ነጥቦች።
1) መታሰቢያ መሆኑን እንድናስብ፡ ሉቃ. 22፡ 17-19፣ 1 ቆሮ. 11፡24-25፣
2) አዲስ ኪዳን መሆኑን እንድናስብ፡ ማቴ. 26፡28፣ ማር. 14፡24፣ ሉቃ. 22፡20፣ ሮሜ 3፡25፣ 1 ጴጥ. 1፡18-19፣ ራዕ. 12፡11
3) ስለመዋደድ፣ ስለአንድነትና ስለፍቅር እንድናስብ፡ ዮሐ. 13፡ 1-38
የጌታ ራት መውሰድ የማይገባው ማን ነው? 1 ቆሮ. 11፡27
"የእግዚአብሔር በግ ማን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዮሐ. 4፡7-26፣ ማቴ. 16፡24-26፣ ሮሜ 12፡19-20፣ ሉቃ. 9፡57፣ ማቴ. 5፡11-12፣ 43-45
እግዚአብሔርን በግ እንድንሆን የጠራን ለምንድን ነው? በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ መዝ. 23፡1-6፣ 2 ቆሮ. 2፡14-17፣ 1ቆሮ. 3፡18-20
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት 8ተኛውና የመጨረሻው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 3፡14-22
ይህ ክፍል ለሎዶቂያ ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል።
በክፍሉ ውስጥ የተመለከቱ 7 ነጥቦች፡
1) መግቢያ ስለ ሎዶቂያ ከተማ
2) ጌታ ራሱን የገለጠበት መንገድ (3፡14) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዮሐ. 1፡1-3፣ ምሳሌ 8፡22-31
3) የነቀፋ ቃል (3፡15,16)
4) የተግሳጽ ቃል (3፡17)
5) የምክር ቃል (3፡18) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ኢሳ.9፡6
6) የማበረታቻ መልዕክት (3፡19-20)
7) ድል ለመንሳት የቀረበ የጥሪ መልዕክት (3፡21-22) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል 2 ጢሞ. 4፡7
ቅዳሜ፣ ጁላይ 30 ቀን 2022 ዓ.ም በነበረው የኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ የሽብሽር ፕሮግራም ላይ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ አጭር የገጠመኝ ጽሐፍ።
ቅዳሜ፣ ጁላይ 30 ቀን 2022 ዓ.ም በነበረው የኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ የሽብሽር ፕሮግራም ላይ በእህት ሙሉ ወልደ ሚካኤል የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ዘፍ. 38
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት 7ተኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 3፡7-13
ይህ ክፍል ለፊላዴልፊያ ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል።
በክፍሉ ውስጥ የተመለከቱ 6 ነጥቦች፡
በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታ ለፊላዴልፊያ መልዓክ/አገልጋይ ያስተላለፈው መልዕክት ውስጥ የሚከተሉት 6 ነጥቦች እንመለከታለን።
1) መግቢያ ስለ ፊላዴልፊያ ከተማ
2) ጌታ ራሱን የገለጠበት መንገድ (3፡7)
3) የምሥጋና መልዕክት (3፡8)
4) ጌታ ሊያደርገው ያለው ዕቅድ (3፡9)
5) ስለጌታ ጥበቃ የተሰጠ መልዕክት (3፡10)
6) እስከ መጨረሻ ስለመጽናት የቀረበ ምክር (3፡11)
7) ድል ለመንሳት የቀረበ የጥሪ መልዕክት (3፡12-13)
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 4፡ የጌታ መንገድ ባህሪያት፡ ነፍስን በመተው ለዘላለም ህይወት መጠበቅ
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡-
1) ጌታ ስለሞቱ ዓላማ ከተናገረበት ክፍል 3 ነጥቦችን እንመልከት
2) ጠላትን በመውደድ ረገድ የጌታ ምሳሌነት
3) ህይወትን በመተው የመጠበቅ ቁልፍ
በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 13፡1-17/ ዮሐ. 12፡23-28/ ማቴ. 16፡24-27/ ዕብ. 12፡1-4/ ዮሐ. 10፡17-18/ ቆላ. 3፡1-2/1 ቆሮ. 12፡3
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 3፡ የጌታ መንገድ ባህሪያት፡ ጠላትን መውደድ
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡-
1) ጠላት ምንድን ነው?
2) ጠላትን በመውደድ የጌታ ምሳሌነት
3) ጠላትን የመውደድ 5 ምክንያቶች
4) የካሪ ቡም ታሪክ - ጠላትን ይቅር ብሎ ስለመደድ
በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 13፡1-17/ ሉቃ. 23፡13-25፣ 32-34/ ማቴ. 27፡24-25/ ማቴ. 5፡43-48/ ዘሌ. 19፡18/ ሮሜ 12፡21/
"ኢየሱስ ማን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም በእምነት ካሳ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ቆላ. 1፡13-18/ ዮሐ. 8፡58/ ማቴ. 1፡21-24/
በኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች መካከል የተደረገ ልዩና እግዚአብሔር የከበረበት የዕርቅ መርሃ ግብር።
“እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣ ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም። በዚያን ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ እንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤ በዚያን ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ። እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤ እኛም ደስ አለን።”
መዝሙር 126:1-3
"ከተኩላዎች ተጠበቁ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፣ ማቴ. 10፡16/ ዮሐ. 10፡27-29/ ማቴ. 25፡32-40/ ዮሐ. 10፡1-12/
"እግዚአብሔር እረኛዬ ነው" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፣ መዝ. 100፡2-3/ መዝ. 23፡1-6/ ማቴ. 11፡28/ ኢሳ. 53፡6 / ኢሳ. 40፡11/ ዮሐ. 10፡27-29/ ማቴ. 25፡32-40
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት 6ተኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 3፡1-6
ይህ ክፍል ለሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል።
መልዕክቱ ውስጥ ያሉ 6 ነጥቦች፡
በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታ ለትያጥሮን መልዓክ/አገልጋይ ያስተላለፈው መልዕክት ውስጥ የሚከተሉት 6 ነጥቦች እንመለከታለን።
1) መግቢያ ስለ ሰርዴስ ከተማ
2) ጌታ ራሱን የገለጠበት መንገድ (3፡1) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ራዕ. 4፡7
3) የተግሳጽ/የነቀፋ መልዕክት (3፡2) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 1ሳሙ. 17፡2፣ ማቴ. 25፡1
4) የምክር መልዕክት (3፡3ሀ) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 1 ቆሮ. 15፡1፣ ፊልጵ. 4፡19
5) የማስጠንቀቂያ መልዕክት (3፡3ለ)
5) የማበረታቻ መልዕክት (3፡4-5)
6) የጥሪ መልዕክት (3፡6)
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሁለተኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 2፡18-29
ይህ ክፍል ለትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል።
መልዕክቱ ውስጥ ያሉ 6 ነጥቦች፡
በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታ ለትያጥሮን መልዓክ/አገልጋይ ያስተላለፈው መልዕክት ውስጥ የሚከተሉት 6 ነጥቦች እንመለከታለን።
1) መግቢያ ስለ ትያጥሮን ከተማ (ሐዋ. 16፡14)
2) ጌታ ራሱን የገለጠበት መንገድ (2፡18)
3) የምሥጋና መልዕክት (2፡19)
4) የተግሳጽ/የነቀፋ መልዕክት (2፡20-21)
5) የማስጠንቀቂያ መልዕክት (2፡22-23)
5) የማበረታቻ መልዕክት (2፡24-28)
6) የጥሪ መልዕክት (2፡29)
"በመጠን ኑሩ" በሚል ርዕስ፣ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መሪ ጥቅስ፡ 1 ጴጥ. 4፡7-8
በመጠን ስንኖር ምን ይሆናል?
1) እንድንጸልይ ይረዳናል 1 ጴጥ. 4፡7-8
2) እንድንነቃ ይረዳናል 1 ተሰሎ. 5፡6-8
3) የጠላትን ሐሳብ እንድንገነዘብ ይረዳናል 1 ጴጥ. 5፡8
4) ሁሉም ነገር በጊዜ ውስጥ መሆኑን እንድንገነዘብ ይረዳናል መክ. 3፡11
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 2፡ የጌታ መንገድ ባህሪያት፡ አገልጋይነት
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡-
1) አገልጋይነት ምንድን ነው?
2) አገልጋይነት የብልጫና የከፍታ መንገድ ነው
3) አገልጋይነት የቀዳማይነት ወይም የፊተኛነት መንገድ ነው
4) አገልጋይነት የታላቅነትና የገዥነት መንገድ ነው
በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 13፡1-17/ ማቴ. 23፡1-12/ ማር. 9፡33-37/ ማር. 10፡42-45/ ሉቃ. 22፡24-27/
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 1፡ መሠረታዊ ሐሳቦች፣ ዓላማና ቅድመ ሁኔታ የጌታን መንገድ ለመከተል
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡-
1) መንገድ ምንድን ነው?
2) መከተል ምንድን ነው?
3) የጌታን መንገድ የመከተል ዋና ዓላማ
4) የጌታን መንገድ ለመከተል አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ
በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 13፡12-17/ መዝ. 119፡9/ ሐዋ. 11፡26/ ዮሐ. 14፡15/ ሆሴ. 6፡3ሀ/ 2ቆሮ. 5፡17ሀ/ ዕብ. 12፡1-2/ ቆላ. 3፡10/ 1 ቆሮ. 2፡14/ 1 ቆሮ. 2፡16/
"ጊዜ/አሁን" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ መክ. 3:1፣10-11/ ዮሐ. 2፡1-11/ ዮሐ. 11፡17-27/ መሳ. 13፡2-1
"እግዚአብሔርን የሚያስደስተው እምነታችን ነው/የእምነት አስፈላጊነት" በሚል ርዕስ በወንድም በእምነት ካሳ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
(ቅዱሳን፣ በመቅረጸ-ድምጹ ድንገት መሙላት ምክንያት መልዕክቱ ወደ መጨረሻው አካባቢ የተቋረጠ ይመስላል። ሙሉ ሀሳቡ አልተቀዳም። ለተፈጠረው ቴክኒካዊ ስህተት ይቅርታ እንጠቅይቃለን።)
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፣ ዕብ. 11፡6 / ሮሜ 10፡17 / ሮሜ 14፡1
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሦስተኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 2፡12-17
ይህ ክፍል ለጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል።
የ2022 የኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተክርስቲያን በፊንላንድ የፋሲካ ኮንፍረንስ
"የጠላታችሁ ሐሳብ ተቀይሯል!" በሚል ርዕስ እሑድ ኤፕሪል 17 ቀን 2022 በነቢይ መስፍን አለሙ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት!
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ሐዋ. 28፡1-6
የ2022 የኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተክርስቲያን በፊንላንድ የፋሲካ ኮንፍረንስ
"የእናንተ ቤት ይበረታል፣ የጠላት ቤት ይደክማል!" በሚል ርዕስ ቅዳሜ ኤፕሪል 16 ቀን 2022 በነቢይ መስፍን አለሙ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት!
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 2 ሳሙ. 3፡1
የ2022 የኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተክርስቲያን በፊንላንድ የፋሲካ ኮንፍረንስ
"ነገራችሁ አልተሰወረም!" በሚል ርዕስ ቅዳሜ ኤፕሪል 16 ቀን 2022 በነቢይት አስናቀች ባንጫ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት!
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ኢሳ. 40፡27-31
የ2022 የኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተክርስቲያን በፊንላንድ የፋሲካ ኮንፍረንስ
"ይሰበራል!" በሚል ርዕስ ዓርብ ኤፕሪል 15 ቀን 2022 በነቢይ መስፍን አለሙ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት!
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ሐዋ. 16፡16-34
"የጠበቃችሁትን ማየት ይሆንላችኋል!" በሚል ርዕስ ነቢይት አስናቀች ባንጫ የቀረበ የእግዚአብ ሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ሉቃስ 2፡ 25-31 የእስራኤልን መጽናናት ይጠባበቅ ነበር። ጻድቅ እና ትጉህም ነበር።
"እኔ ነኝ አትፍሩ!" በሚል ርዕስ በዮሐ. 6፡20 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ክፍል §1።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶ፣ ዘፍ. 15፡1-6
በጌታ ራት ወቅት ጌታ በትኩረት የተናገራቸው 3 ዋና ነገሮች፡ -
1) መታሰቢያ ነው
ሉቃ. 22፡19/ 1 ቆሮ. 11፡23-26
2) አዲስ ኪዳን ነው
ማቴ. 26፡28 / ማር. 14፡24 / ሮሜ 3፡25 / ሮሜ 5፡9 / ሐዋ. 20፡28 / ዕብ. 9፡14
3) እርስ በርስ የመዋደድ (የአንድነት) ምልክት ነው
ዮሐ. 13፡1-38 / 1 ቆሮ. 10፡ 16-17
የጌታን ራት የሚካፈለው ማን ነው?
1 ቆሮ. 11፡27-29
"ልባም ሰው ማን ነው? በሚል በማቴ. 7፡24-27 ባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንድም እምነት ካሳ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ኤር. 11፡6 / ዮሐ. 10፡1-5 / ሉቃ. 10፡38-42 /ያዕ. 1፡22
የመልዕክቱ ጭብጥ፡ ልባም ሰው የጌታን (የእግዚአብሔርን) ቃል ሰምቶ የሚደርግ ሰው ነው።
"በሌሎች ላይ ስለመፍረድ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአሔር ቃል መልዕክት ክፍል 2።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ - ማቴ. 18:15-20/1 ቆሮ. 5:9-13/ 1 ቆሮ. 6፡1-11
"በሌሎች ላይ ስለመፍረድ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአሔር ቃል መልዕክት ክፍል ።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ - ማቴ. 7፡1-5/ዮሐ. 7፡24/ ሮሜ 2፡1-4
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሦስተኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 2፡8-11
ይህ ክፍል ለሰምርኔስ ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል።
መልዕክቱ ውስጥ ያሉ 5 ነጥቦች፡
በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታ ለሰምርኔስ መልዓክ/አገልጋይ ያስተላለፈው መልዕክት ውስጥ የሚከተሉት 5 ነጥቦች እንመለከታለን።
1) የላኪው ማንነት (ቁ.8)
2) የመጽናናት መልዕክት (ቁ.9)
3) ልደርስባቸው ስላለ መከራ መልዕክት (ቁ.10ሀ፣ለ፣ሐ)
4) የማበረታቻ መልዕክት (ቁ. 10መ)
5) የጥሪ መልዕክት (ቁ. 1)
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሁለተኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 2፡1-7
ይህ ክፍል ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል።
መልዕክቱ ውስጥ ያሉ 6 ነጥቦች፡
በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታ ለኤፌሶን መልዓክ/አገልጋይ ያስተላለፈው መልዕክት ውስጥ የሚከተሉት 6 ነጥቦች እንመለከታለን።
1) የምሥጋና መልዕክት (ቁ.2-3)
2) የተግሳጽ መልዕክት (ቁ.4)
3) የምክር መልዕክት (ቁ.5ሀ)
4) የማስጠንቀቂያ መልዕክት (ቁ. 5ለ፣ሐ)
5) የማበረታቻ መልዕክት (ቁ. 6)
6) የጥሪ መልዕክት (ቁ. 7)
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 1 ሙሉ
ምዕራፍ 1 ውስጥ ልብ ማለት የሚገቡን 7 ነጥቦች፡-
1) የመልዕክቱ ባለቤት፡- እግዚአብሔር ራሱ ነው።
እግዚአብሔር > ኢየሱስ > መልዓክ > ዮሐንስ
2) የመልዕክክት ተቀባይ፦ ዮሐንስ ነው።
3) መልዕክቱን የተቀበለበት ቦታና ሁኔታ፦ ቦታው ፍጥሞ በተባለ ደሴት ሲሆን፣ በእሥር ላይ ሆነ ነበር መልዕቱን የተቀበለው።
4) የመልዕክቱ ዓላማ፦ ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እና የመልዕክቱ ተደራሲያን የሆኑ 7ቱ አቢያተ ክርስቲያናትን ለማንቃት ነው። በተጨማሪም በመጨረሻው ዘመን በዓለም ላይ ሊሆን ያለውን ለማመልከት ነው።
5) ሰባት ቁጥር በመጽሐፉ ውስጥ መደጋገሙ ራሱን የቻለ መልዕክት አለው። በተጨማሪም ብፁዓን የሚለው ቃል ራሱ 7 ጊዜ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ተደጋግሟል።
6) ኢየሱስ ለሐዋሪያው ዮሐንስ ከዚህ በፊት ባልተለመደ አቀራረብና መንገድ ራሱን ገልጧል። ለምሳሌ መልኩን ለመግለጽ ሐዋሪያው የተጠቀመባቸውን አገላለጾች ልብ ማለት ይቻላል።
7) ጌታ ወደ ዮሐንስ ሲመጣ ዮሐንስ የነበረበት ሁኔታ፦ ስለክርስቶስ መከራን እየተቀበለ ያለበት ሁኔታና በዚያ ችግር ውስጥም ቢሆን በጌታ ቀን በመሆን ከመሆን እንዳላገደው እንመለከታለን።
"በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ መኖር" በሚል ርዕስ በ1 ሳሙ. 1-3 ባሉት ምዕራፎች ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
"ራስንና የራስን ሚና ማወቅ" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፣ ዮሐ. 1፡19-28፣ 35-37
"እስከዚህ ያደረስከኝ እኔ ማን ነኝ?" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የአመት መጨረሻ መልዕክት።
ዳዊት እስከዚህ ያደረስከኝ እኔ ማን ነኝ ያለባቸው ምክንያቶች፡-
1) ለንግሥና መመረጡና መቀባቱን አስቦ ነው 1 ሳሙ. 16፡ 1፣13
2) የእግዚአብሔርን ምህረት እያሰበ ነው 2 ዜና 21፡1፣13
3) የእግዚአብሔርን ጥበቃ እያሰበ ነው መዝ. 23
4) የእግዚአብሔርን እርዳታ እያሰበ ነው
መጪው አመት የብርታት አመት ነው
1 ነገ. 2፡1-3
1) የእግዚአብሔርን ቃል በመታዘዝ እንበርታ
2) በእግዚአብሔር ጸጋ እንበርታ (ዕብ. ፡1)
"የዕንባቆም ክርክርና የእግዚአብሔር መልስ" በሚል ርዕስ በትንቢተ ዕንባቆም ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ ትምህርት ሁለተኛውና የመጨረሻ ክፍል።
"የዕንባቆም ክርክርና የእግዚአብሔር መልስ" በሚል ርዕስ በትንቢተ ዕንባቆም ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል።
"በእምነት ማደግ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ዮሐ.20፡1-8፣ መዝ. 119፡97-104፣ ማቴ. 6፡27-30
"በእምነት መራመድ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ማቴ. 14፡23-36/ ያዕ. 1፡2/ ዕብ. 12፡1-2
"ለሚያምን ሁሉ ይቻላል" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ማር. 9፥2-25፣ ዘፍ. 17፥1
1) ለሚያምን መዳን ይቻላል / ሉቃ. 18፥18-27፣ ማር. 16፥16
2) ለሚያምን ለእግዚአብሔር ካህን መሆን ይቻላል / ራዕ. 1፥5-6፣ 1 ጴጥ. 2፥9
3) ለሚያምን እባቡን እና ጊንጡን መርገጥ ይቻላል / ራዕ. 12፥9፣ ሉቃ. 10፥19
"የህይወት ስኬት ቁልፎች" በሚል ርዕስ በመዝ. 1፡1-3 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል።
"የህይወት ስኬት ቁልፎች" በሚል ርዕስ በመዝ. 1፡1-3 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል።
182_ቀናችንን እንዋጅ በእህት ለምለም ጌታቸው (ሲ/ር)
ዘመናችንን ለመዋጀት ስናስብ ቀናችንን እንዋጅ በ ኤፌ 5:8-17 በዘፍ 1:1-5 እና ፊል 4:9 ላይ የተመሰረተ የእ/ር ቃል መልእክት
"ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ ....
....እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤
ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።" ኤፌ 5:8-17
"በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።
እግዚአብሔርም። ብርሃን ይሁን ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ። እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።
እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።"ዘፍ 1:1-5
በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ፊል 4:9
181_መታዘዝ (ክፍል 2) ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር )
ለመታዘዝ ምሳሌያችን ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ::
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌ 2:10
ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን። ያዕ 1:18
ጋለሞታይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው ከማይታዘዙ ጋር በእምነት አልጠፋችም። ዕብ 11:31
180_መታዘዝ (ክፍል-1) ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር
በግላችን ለእግዚአብሄር በመታዘዝ ምን እንማራለን:: መታዘዝ የበረከትም መንገድ ነው
ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።ዮሐ14:15
እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ :- ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።ሮሜ 12.1
እንዲህም አለው፦ እግዚአብሔር፦ በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና
በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤
የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ፥ ቃሌን ሰምተሃልና።
ዘፍ 22:16-18
179_ ከእኔ ተማሩ (ክፍል 6) ዘገየ መኮንን (ወ/ዊ)
ክፍል 6 ከእኔ ተማሩ በዘገየ መኮንን (ወ/ዊ)
መንፈስ ቅዱስን ከጌታ እንማር
ሕፃኑም አደገ፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ። ሉቃ 2:40
በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥... ኤፌ 3:16
178_ ከእኔ ተማሩ (ክፍል 5) ዘገየ መኮንን (ወ/ዊ)
ክፍል 5 ከእኔ ተማሩ ዘገየ መኮንን (ወ/ዊ)
5-1 እግዚአብሄርን መታዘዝ
በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ፊሊጵ 2:8
(እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን። ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ...)1ዮሐ 5:3
5-2 ማገልገልን እንማር
(...የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ። በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥) ማቲ 20: 25-26
5-3 መጽናትን እንማር
"ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር።"ሉቃ 22:42
"ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።"ማቲ 7:24-25
177_ከ እኔ ተማሩ (ክፍል 4) ዘገዬ መኮንን (ወ/ዊ)
ከክርስቶስ ምህረት ማድረግን እንማር
እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤
ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። ማቲ 11:28-29
እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።
ማቲ 28:19-20
176_ከእኔ ተማሩ ክፍል 3 // ዘገየ መኮንን (ወ/ዊ)
እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤
ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። ማቲ 11:28-29
175_መንፈሳዊ ጽናት ክፍል_ 2 ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)
ለመጽናት ስልጠናና፣ልምምድ ውስጥ መግባት ያስፈልጋል።
ለመጽናት መለማመድ ያለብን
1) አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። ዘዳ6:5
2)አትበቀልም፥ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፥ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ ..ዘለዋ 19፡ 18
እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ፣ ወደ እኔ ኑ ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ ።
ቀንበሬንም በላያችሁ ተሸከሙ፣ ከእኔም ተማሩ ፣እኔ የዋህ በልቤ ትሁት ነኝና፣ ለነፍሳችሁ ዕረፍትን ታገኛላችሁ።
ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። ማቲ 11፡ 28-30
174_መንፈሳዊ ጽናት ተከለ ማርቆስ ዶ/ር
ሰው አለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል። ማር 8:36
ሰው አለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል። ማር 8:36
ሰው ለአላማው ሲል ይጸናል :: ነፍሴን አላጎድልም የሌሎችም ነፍስ ሲትጎድል አላይም ያለ ማለት ነው::
"ከኢየሱስ መማር" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ክፍል 2።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ማቴ. 11፡28
"የቃሉ ሙላት" በሚል ርዕስ በቆላ. 3፡16 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ክፍል 3 እና የመጨረሻው።
"ከእኔ ተማሩ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ክፍል 1።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ማቴ. 11፡28,29 / ሐዋ. 4፡13 / ማቴ. 17፡5 / ማር. 9፡7 / ሉቃ. 9፡35 / ሐዋ. 3፡22 / ሐዋ. 7፡37 / ሐዋ. 2፡41,42 / ቆላ. 2፡8 / 2 ዮሐ. 1፡9 / ዮሐ. 15፡13 / ሮሜ 5፡8 / ዮሐ. 13፡35 / ሮሜ 13፡10 / ሮሜ 14፤15 /
በመንፈስ መሠራት በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ ፋሼ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዮሐ. 1፡25-34 / 1 ነገ. 8፡25 / መዝ. 118፡22-24 / ሐዋ. 2 / ማቴ. 16፡18-21
"እግዚአብሔርን መጠየቅ" በሚል ርዕስ በወ/ዊ ዘገየ መኮንን ያቀረበው የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ 2 ሳሙ. 21፡1-14 / ኤር. 6፡16
ይቅርታ በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሁለተኛውና የመጨረሻው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ማቴ. 26፡26-28 / ሉቃ. 23፡32-34 / ማር. 11፡25-26 / ማቴ. 6፡14-15
ይቅርታ በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ማቴ. 26፡26-28 / ሉቃ. 23፡32-34 / ማር. 11፡25-26 / ማቴ. 6፡14-15
"የወንጌል እውነት ማሳሰቢያ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ ተከታታይ ትምህርት 4ኛውና የመጨረሻው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 1 ቆሮ. 15፡1-19
"የወንጌል እውነት ማሳሰቢያ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ ተከታታይ ትምህርት ተኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 1 ቆሮ. 15፡1-19
"የወንጌል እውነት ማሳሰቢያ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ ተከታታይ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 1 ቆሮ. 15፡1-19
"የወንጌል እውነት ማሳሰቢያ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ ተከታታይ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 1 ቆሮ. 15፡1-19
"ግብዝነትና የእግዚአብሔር ቤተሰብ አዲሱ የአገልግሎት ሥርዓት" በሚል ርዕስ በማቴ. 22 እና 23 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ማቴ. ምዕራፍ 22 እና 23 በአብዛኛው።
"እኔንስ ማን ይሉኛል? እናንተንስ?" በሚል ርዕስ በ እህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ማቴ 16፡13-18 / ዘኁ. 13፡16 / መሳ. 6፡32 / ዘፍ. 35፡ 18 / 1ዜና 4፡9 / ሮሜ 5፡ 6-11/
"የዘላለም ህይወት ያለው ማን ነው?" በሚል ርዕስ በዮሐ. 5፡24 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
"መንፈስ ቅዱስ - የእግዚአብሔር ህግ አስፈጻሚ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆሳ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ዮሐ. 14፡16-17 / ማቴ. 5:1-3, 44 / ሮሜ 12፡1 / 2 ጴጥ. 1፡18-21 /ማቴ. 5፡9-16
"መንፈሳዊ ትጥቅ" በሚል ርዕስ በኤፌ. 6፡10-18 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: / 2 ቆሮ. 10፡4-5/ 2 ተሰሎ. 3፡3 / 1ጴጥ. 5፡8 / ያዕ. 4፡7 / ዮሐ. 10፡10 /
"መሳካት፣ መከናወን ወይም መቃናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ ተከታታይ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሁለተኛውና የመጨረሻው ክፍል።
"መሳካት፣ መከናወን ወይም መቃናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ ተከታታይ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል።
"እናውቀው ዘንድ እንከተለው" በሚል ርዕስ በሆሴዕ 6:1-3 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
ተጨማሪ ጥቅሶች: ዮሐ. 21:1-14 / ሉቃ. 24:13-33
"በሁለንተናዊ መሰጠት ማገልገል" በሚል ርዕስ በዶ/ር ሙላቱ በላይነህ ለአገልጋዮች የተሰጠ ትምህርት የሁለተኛውና የመጨረሻው ክፍል የጥያቄና መልስ ጊዜ።
"በሁለንተናዊ መሰጠት ማገልገል" በሚል ርዕስ በዶ/ር ሙላቱ በላይነህ ለአገልጋዮች እየተሰጠ ያለ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል የጥያቄና መልስ ጊዜ።
"በመንፈስ መመላለስ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሁለተኛው ክፍል::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ሉቃ. 1፡35/ ሮሜ 8፡14/ ቲቶ 3:5-7/ 1ቆሮ. 6:19-20/
ጌታ እኮ ነው መልሶ ያቆማል! በሚል ርዕስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 21 ላይ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ጥናት ሁለተኛውና የመጨረሻው ክፍል።
"ጌታ እኮ ነው - መልሶ ያቆማል!" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 21 ጥናት የመጀመሪያው ክፍል::
ተጨማሪ ጥቅሶች: ዮሐ. 20፡30፣31 / ማቴ 4:18-20/ ማቴ 16:16, 22, 23/ ሉቃ. 22:33, 56-61
"ታማኝ ባሪያ" በሚል ርዕስ በማቴ. 25:14-30 ባለው ክፍል ላይ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ኤፌ 4፡6-8/ 1 ቆሮ. 12፡4-11/ ዕብ. 3፡2-6/ 1ቆሮ. 4፡17/ ኤፌ. 6፡21/ 1 ጴጥ. 5፡12/ 3ኛ ዮሐ. 1፡5
"በመንፈስ መመላላስ" በሚል ርዕስ ገላ. 5፡22 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል።
ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ሮሜ 8፡14/ ዮሐ. 15፡1-2፣ 14፡12-17 / 1 ቆሮ. 13:4-7/ ገላ. 4፡18-19/ ሮሜ 12:1-2፣ 8:4-27/ ኤፌ. 6:18፣ 5:17-20/
136_የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? በወንድም ያቬሎ ናታዬ
"እውነተኛ አምላክ ብቻየሆንክ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት::" ዮሐ17:3 ላይ የተመሰረተ የእለቱ ከ እግዚአብሔር ቃል መልእክት
ሰዎች የዘላለምን ሕይወት እንዴት ያገኛሉ?
ስለ እግዚአብሔር ማወቅ እና እግዚአብሔርን ማወቅ ይለያያልና::
መልእክተኛ የ እግዚአብሔር ልጅ እርሱ ኢየሱስ እንደሆነ ማወቅ
"እግዚአብሔር ምድራችንን ይፈውሳል!" በሚል ርዕስ በ2ኛ ዜና 7:11-14 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሦስተኛውና የመጨረሻው ክፍል::
"እግዚአብሔር ምድራችንን ይፈውሳል!" በሚል ርዕስ በ2ኛ ዜና 7:11-14 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሁለተኛው ክፍል::
ተጨማሪ ጥቅሶች: ምሳ. 1:20-33/ኢሳ. 58:1-14/1 ዮሐ. 1:7-9
"እግዚአብሔር ምድራችንን ይፈውሳል!" በሚል ርዕስ በ2ኛ ዜና 7:11-14 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
ርዕስ: ጌታ ቅርብ ነው || ክፍል 2
"ጌታ ቅርብ ነው" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) ፊል. 4:4-9 ባለው የእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
ጌታ ቅርብ ነው በተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)
በአባቶች ቀን ፕሮግራም ላይ በፊሊ 4:6 ላይ የተመሰረተ ከ እ/ር ቃል መልእክት የቀረበ
"ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።
አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።"ፊሊ 4:4-6
"እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።"ኤር 29:12-13
"እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፦ ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰው አልረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና፤ ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደ ገና አልመታም።"ዘፍ 8:21
"ኢየሱስ ግን፦ አንድ ሰው ዳስሶኛል፥ ኃይል ከእኔ እንደ ወጣ እኔ አውቃለሁና አለ። ሴቲቱም እንዳልተሰወረች ባየች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፥ በምን ምክንያትም እንደ ዳሰሰችው ፈጥናም እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት አወራች።"ሉቃ 8:46
ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት አምስተኛውና የመጨረሻው ክፍል ነው::
ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:-
ርዕስ: ሰው ምንድን ነው?
ክፍል 5: የሰው ዋጋ
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ አሳቦች: -
-–ሌሎች ሥልጣኔዎችና ባህሎች ስለሰው ዋጋ ያላቸው ዕይታ
–እስልምና ስለሰው ዋጋ ያላቸው ዕይታ
–ምዕራባዊያን ስለሰው ዋጋ ያላቸው ዕይታ
–መጽሐፍ ቅዱስ ስለሰው ዋጋ ምን ያስተምራል?
–መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ዕይታ መከተል ያሉት ክትለቶች (implications)
ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት አራተኛው ክፍል ነው::
ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:-
ርዕስ: ሰው ምንድን ነው?
ክፍል 4: "ሰው ሰው የሆነው ለምንድን ነው?/ሰው የተፈጠረበት ዓላማ ምንድን ነው?"
ሰው በዋናነት የተፈጠረው ለኅብረት የሚለው አሳብ በስፋት ይተነተናል::
1) ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው የወደ ላይ ኅብረት
2) ሰው ከሌሎች ሰዎችና ከተፈጥሮ ጋር ያለው ኅብረት
3) የክርስቶስ መስቀል ምሳሌነት ለሁለቱም የሰው የኅበረት አቅጣጫዎች
4) ፍቅር - ኅብረትን መተግበሪያ ዓይነተኛ መሣሪያ የሚሉ አሳቦች በስፋት ተዳስሰዋል::
የጌታ መንገድ በሚል ርዕስ በወንድም አስቻለው ወልዴ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች: ዮሐ. 14:6/ ማቴ. 18:21-35 / ገላ. 5:19-21
"የልብ መዝገብ ቢከፈት ምን ይወጣል?" በሚል ርዕስ በ2ኛ ዜና 5 ላይ ተመሥርቶ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመልዕክቱ ጭብጥ: ቁጣንና ጦርነትን የሚያስቀር የልብ መዝገብ አለ/በተቃራኒው ደግሞ ቁጣና ጦርነትን የሚቀሰቅስ የልብ መዝገብ አለ/ለፈውስ የሚሆን የልብ መዝገብ አለ/ለደዌ የሚዳርግ የልብ መዝገብ አለ::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: 2 ነገ. 5:1> /ምሳ. 20:21 /1 ነገ. 19:15-19 /ሉቃ. 6:43-45
"እግዚአብሔር ያያል" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ ፋሼ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱድስ ጥቅሶች: ዘፍ. 16:1-16/ኢዮብ 40:1-2/ኢዮብ 42:1-6/ሮሜ 5:3-4/
"የመጥምቁ ዮሃንስ ምስክርነት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
በዮሐ 1:20-30 እና በሉቃስ 1:76 ላይ ባለው የእግዚአብሄር ቃል ላይ የተመሰረተ መልእክት::
"የሚያስፈልገው ጥቂት ነው!" በሚል ርዕስ በሉቃ. 10:38-42 ባለው ክፍል ላይ ተምሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ሉቃ. 10:38-42/ኢየሱስ በነ ማርታና ማሪያም ቤት || 1 ነገ. 17:7-14/ነቢዩ ኤልያስና የሰራፕታዋ ባልቴት || ማቴ. 15:32-38/ኢየሱስ 4000+ ሰዎችን በሰባት እንጀራና በጥቂት ዓሣ መመገቡ || መዝ. 37:16 ||
ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት ሦስተኛው ክፍል ነው::
ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:-
ርዕስ: ሰው ምንድን ነው?
ክፍል 3: "ሰው መንፈስ ነው፤ ነፍስ አለው፤ በሥጋ ውስጥ ይኖራል!" ባዮች ስህተታቸው ምንድን ነው?
1) የቃል እምነት እንቅስቃሴ ስለሰው ምንነት ያላቸውን አመለካከት በጥልቀት እንመለከታለን
2) የሚጠቅሷቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችና እንዴት እንደተሳሳቱ እንመለከታለን::
3) ከስህተት ራሳችንን ለመጠበቅ ከእያንዳንዳችን ምን እንደሚጠበቅ እንመለከታለን::
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች / ዘፍ. 1:26-27 / መዝ. 82:1-8 / ዮሐ. 10:34-36 / ዮሐ. 3:1-6 / ዕብ. 4:12 / 1 ጢሞ. 4:12 / 2ጢሞ. 2:14 /
ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል ነው::
ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:-
ርዕስ: ሰው ምንድን ነው?
ክፍል 2: ትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሰው ምንነት ዕይታ
ሀ) ሰው በትክክል ምንድን ነው?
ለ) የሰው ማንነት ክፍሎች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: 1 ተሰ. 5:23/ዕብ. 4:12/ኢዮብ 32:8/ሉቃ. 9:56/ማር. 14:34/ሉቃ. 23:46/ሐዋ. 7:59/መክ. 12:7/ፊል. 3:20-21
ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል ነው::
ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:-
ርዕስ: ሰው ምንድን ነው?
ክፍል 1: ዓለም ለሰው ያላት ዕይታ
1) የማቴሪያሊዝም ንጽረተ ዓለም አራማጆች ስለሰው ምንነት ያላቸው ዕይታ
2) የአይዲያሊዝም ንጽረተ ዓለም አራማጆች ስለሰው ምንነት ያላቸው ዕይታ
3) ክርስቲያናዊ የሰው ምንነት ዕይታ
ይህ ትምህርት ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት በሚል ርዕስ፣ የቤተሰብና ጋብቻ አማካሪ በሆነው በዶ/ር ሙላቱ በላይነህ በፊንላንድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የቀረበ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል ነው:: በዚህ ክፍል የሚከተሉት ዋና ዋና አሳቦች ተዳስሰዋል: -
ርዕስ: ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን የግንኙነት ጤንነት መጠበቅ
1) መግቢያ
2) በልጆች ጉዳይ ወላጆች ላይ መሥራት የሚያስፈልግባቸው ምክንያቶች
3) በልጆችና ወላጆች መካከል ጤናማ ግንኙነት እንዳይኖር የሚያደርጉ ነገሮች
4) ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ጤንነት ለመጠበቅ የሚረዱ ነገሮች
ይህ ትምህርት ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት በሚል ርዕስ፣ የቤተሰብና ጋብቻ አማካሪ በሆነው በዶ/ር ሙላቱ በላይነህ በፊንላንድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የቀረበ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል ነው:: በዚህ ክፍል የሚከተሉት ዋና ዋና አሳቦች ተዳስሰዋል: -
ርዕስ: ባልና ሚስት እርስ በርስ ያላቸውን የግንኙነት ጤንነት መጠበቅ
1) የትምህርቱ ዓላማዎች
2) ግንኙነቶቻችንን ሊረብሹ የሚችሉ ሁለንተናዊ አሉታዊ ተጽዕኖዎች
3) የጤናማ ግንኙነት ወይም ትዳር (መኖር/አለመኖር) መለኪያ መስፈርቶች
4) ግንኙነቶቻችንን ሊረብሹ የሚችሉ የታወቁ ምክንያቶች
5) የትዳርና የቤተሰብ ግንኙነትን ጤንነት መጠበቅ የሚቻልባቸው መንገዶች
118_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 3 / በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን
በጊዜውም ያለጊዜውም ቢመችም ባይመችም ተዘጋጅቶ መኖር 2 ጢሞ4:2
እስከ መጨረሻው መጽናት ማቲ 10:22
እንድንፀና የሚረዱን 4 ነገሮች
1 . የእግዚአብሄር ቃል በመታዘዝ ማቲ 7:26 እና 1 ዜና 28:5-7
ፀሎት 1ጴጥ 5:10
የእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ሐዋ 1:8
ቅዱሳን ወንድሞች እና እህቶች ሉቃ 22:32
117_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 2 / በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ
እንድንጸናባቸው ከታዘዝንባቸው 6 ነገሮች የመጀመሪያዎቹ 4ቱ
በ 2ቆሮ 12: 9 እና ምዕ 8:1 ጀምሮ ላይ የተመሰረተ የእ/ር ቃል መልእክት በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ
6.በጸጋ መጽናት
7.በፍቅር መጽናት
8.በአገልግሎት መጽናት
9.በወንጌል እውነት መጽናት
116_ፅና ወይም ፅኑ በዘገዬ መኮነን/ወንጌላዊ/
ፅና ወይም ፅኑ በኢያሱ 1:6 እና በዘዳ 31:7 ላይ የተመሰረተ የእ/ር ቃል መልእክት
መፅናት በግል: በቤተሰብ: በሕብረት
መፅናት ለአማኞች የተሰጠ ትእዛዝ ነው::
ሀ.በመፅናት ምሳሌ የሆኑን :
ሐና: ዳዊት: አሳ
ለ.እንድንፀናባቸው የታዘዝንባቸው ነገሮች
1. በተስፋ መጽናት
2. በእምነት መጽናት
3. በጸሎት መጽናት
በፈተና መጽናት
በትእግስት መጽናት
115_ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግሮቻችን /ክፍል 2 / ያቬሎ ናታዬ
የንግግሮቻችን 7 መመዘኛዎች
1- እያንዳንዱን ሰው ታሳቢ ማድረግ አለበት :
2-አውዳዊ ስልትን የተከተለ መሆን አለበት
3-እውቀትን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት
4-ትክክለኛ መልእክት የያዘ መሆኑን መረጋገጥ አለበት
5-ሁልጊዜ ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን አለበት
6-ንግግራችን የተቀመመ መሆን መረጋገጥ አለበት
7-ጸጋን የተሞላ መሆን አለበት
በጠብ ሳይሆን በጥበብ ለመመላለስ ንግግራችን እነዚህን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል::
ቆላ 4:5-6 በተጻፈው በእግዚአብሔር ቃል መልእክት ላይ የተመሰረተ
114_ ራዕይ ምዕ 5 ቁ 1-10 ባለው ቃል ላይ የተመሰረተ መልእክት /በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን
መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።ራዕ 5:9-10
ጥቅልሉ መጽሐፍ ራዕ 5: 1-3
ከሽማግሌዎች አንዱ ራዕ 5: 4-7
ለበጉ ክብር የምስጋና ዝማሬ ራዕ 5: 8-10
113_ ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግራችን ተከታታይ ትምህርት :: በወንድም ያቬሎ ናታዬ
ዘመኑን እየዋጃችሁ: በውጪ ባሉት ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ ::
"ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመላለሱ እንደሚገባ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ :በጨው እንደ ተቀመመ :በጸጋ ይሁን"::ቆላ 4:5
ክፍል 1
1:1 ዘመኑ ምን አይነት መልክ አለው? የሚዋጅ ዘመን በኤፌ 5:15 እና 2ኛ ጢሞ3:1-5 ላይ የተመሰረተ ቃል::
1)ዘመኑ የሚዋጅ ነው 2) ዘመኑ ክፉ ነው 3)ዘመኑን ዋጁ
1-2 ዘመኑን የምንዋጀው እንዴት ነው? በውጪ ባሉት ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ:: ቆላ 4:5
1)ዘመኑን መልክ በመረዳት 2)የራሳችንን ሓላፊነት በሚገባ በመወጣት 3)ቃሉ በሚሰጠን መመሪያ መሰረት ወደ እርምጃ መግባት
1-3 ትእዛዙን ተፈጻሚ የምናደርገው በ እነማን ዘንድ ነው? የእግዚአብሔርን ፈቃድ በንግግራችን ውስጥ:: ኤፌ 5:17
በጥበብ መመላለስ
ከማያምኑት ጋር ባለን እለታዊ መስተጋብር
በስራ:በሰፈር...
112_እግዚአብሔር ተዋጊ ነው :: በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ/
1/ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው :: እግዚአብሔር ስሙን ከፍ ለማድረግ ይዋጋል:: ዘጸ 15:1-3
እግዚእብሔር ያለማንም ጣልቃ ገብነት ለህዝቡ ብቻውን ተዋግቶ : ድል ሲነሳ ስላዩ: ሙሴና የእስራኤል ህዝብ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው" አሉት::
2/ እግዚእብሔር የራሱን ህዝብ ከጠላቶቻቸው ጥቃት ለመታደግ 2ዜና 20: 14-15
3/ እግዚእብሔር ህዝቡን ወደ አሰበለት ስፍራ ለማስገባት:: ዘጸ 14: 14-23
111_እግዚአብሄር መሐሪ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮነን
የእግዚአብሄር መሐሪነት የገባው እግዚአብሄር የሚምር የሚራራ መሆኑንን የተረዳው አብርሃም ስለሌሎች ያደረገውን ጸሎት እና ልመና ላይ የተመሰረተ ቃል ነው:: እኛም የእግዚአብሄር ምህረት እንደገበው ሰው እግዚአብሄር ለብዙዎች ምህረትን እንዲያደርግ አጥብቀን እንጸልይ ዘንድ ያስፈልገናል::
"የፈርሃ እግዚአብሔር በረከቶች" በሚል ር ዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መል ዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: መዝ. 25:12-14/ሚል. 3:16-18
"ጥበብን አግኝ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ተከታታይ ትምህርት የመጨረሻው ክፍል::
ክፍል 3: ጥበብን እንዴት ማግኘት ይቻላል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ኤር. 8:8-12/2ጢሞ. 3:14-17/ምሳሌ 2:1-11
ያዕ. 1:1-5/ሉቃ. 21:14-15/1ዜና 22:12/2ዜና 1:10
"ጥበብን አግኝ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሁለተኛው ክፍል::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ምሳሌ 24:3፣ 1:7፣ 19:23፣ 2:5/ መዝ. 19:19/ሐዋ. 6:3
"ጥበብን አግኝ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ምሳሌ 4:7-8/ ኤፌ. 5:15 / 1ቆሮ. 1:18-21/ ያዕ. 3:17
"ጊዜን ማስተዋል/ማወቅ" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: 1 ዜና 12:32/ኤፌ. 5:15-17/1 ነገ. 15:1-32 /2 ነገ. 21:9/2 ዜና 34:1-7
"የእግዚአብሔር ክብር መንገድ" በሚል ርዕስ በማቴ. 17:1-8 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በፓስተር ፋሲል በለጠ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ: ማቴ. 17:1-8
አራት ነጥቦች ስለ እግዚአብሔር ክብር
1) እግዚአብሔር ክብሩን የሚገልጠው በድንገት ነው
2) ሰውን ወደ ክብሩ የሚያስገባው እግዚአብሔር ራሱ ነው
3) የእግዚአብሔር ክብር ጫፍ/መደምደሚያ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
4) የእግዚአብሔር ክብር ለሰው የሚገለጥ/ማየት የሚቻልና የማይቻል ደረጃዎች አሉት
የእግዚአብሔርን የክብር መንገድ ለመጓዝ የሰው ድርሻ
1) ኢየሱስን መከተል
2) ኢየሱስን ማየት
3) ኢየሱስን መስማት
"ንስሐ፣ ተስፋና ተሃድሶ" በሚል ርዕስ በዶ/ር ትዕግሥት ቸርነት የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል: ዕዝራ 10:1-10
"ጌታን በተግባር መከተል" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ ተከታታይ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ዮሐ. 13:1-17/ማቴ. 5:43-48
"ለጥሪው ምላሽ የምንሰጠው እንዴት ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
ለጥሪው ምላሽ የምንሰጠው እንዴት ነው? 1) ጥሪውን በመለየትና ጠሪውን በመከተል 2) ራስን በመካድና የራስን መስቀል በመሸከም 3) የነፍሳችንን ዋጋ በማወቅና ነፍሳችንን በማዳን ይሁን!
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ማር. 8:34-38/ ማቴ. 9:9/ ማር. 2:14/ ማር. 10:17-22/ 1ቆሮ. 1:26/ ኤፌ. 4:1-3/ ሮሜ 8:14/ 1ዮሐ. 2:15-16/ ሉቃ. 9:23/ ገላ. 5:16-18/ ሉቃ. 12:19-21
"ምን አደርግልህ ዘንድ ትወዳለህ?" በሚል ር ዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: 1ነገ. 3:1-15/ዮሐ. 5:1-9/1ጢሞ. 2:1-4
"መንፈሳዊ ነገሮችን ማወቅ" በሚል መሪ አሳብ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ ክፍል "እግዚአብሔርን ማወቅ" በሚል ርዕስ በተከታታይነት የቀረበው ትምህርት ክፍል ነው::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: 1ቆሮ. 12:1-7/ገላ. 5:22/1ቆሮ. 1:7/1ቆሮ. 14:12,26/1ቆሮ. 14:1, 39-40/ምሳሌ 15:22/ምሳሌ 19:21
090_እግዚአብሄርን ማወቅ ክፍል 3 (በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን)
ወዳጆች ሆይ፥ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1ኛ ዮሐ 4:7 እና ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም በሚለው ቃል በመመልከት ከ1ኛ ቆሮ13:1-7 ባለው ላይ ቃል ላይ ተመስርተን ራሳችንን እናይ ዘንድ የሚያግዝ መልእክት ነው::
"ወንጌልን እንዴት እናገልግል?" - መልካሙን ሥራ ለመሥራት ተፈጠርን በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ተከታታይ መልዕክት ቀጣይ ክፍል::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ሮሜ 10:5-14/ኤፌ. 5:14-20/ፊል. 1:15-18/ቲቶ 1:9-11
"አትለፈኝ" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ማር. 6:45-51/ዘፍ. 18:1-5/መዝ. 27:6-9
"ወንጌልን በመሥራት መልካሙን ሥራ ማድረግ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የወንጌልን ሥራ ለመሥራት የሚያስፈልጉ ነገሮች:
1) ጸሎት: ማቴ. 9:35-38
2) ልባምና የዋህ መሆን: ማቴ. 10:17
3) ፍርሃትን ማስወገድ: ማቴ. 10:24-28
4) መንፈስ ቅዱስን መታመን: ማቴ. 10:19-20/ ዮሐ. 20:21
5) ለመላክ መታዘዝና መሄድ: ማቴ. 10:16/ ማር. 16:15
6) መጽናት: ማቴ. 10:22-23
"ፍጻሜያችንን እናስብ/እንመልከት!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ራዕ. 7:9-17/መክ. 12:13/መክ. 7:3-4/
84_ጨምሩ ክፍል _4
በወንድም ያቬሎ ናታዬ
በመንፈሳዊ ህይወት ለመጨመር መለኮታዊ ባህርይን መላበስ
በ2ኛ ጴጥሮስ 1:1-11ባለው መልእክት ላይ የተመሰረተ
ሀ-የእድገት አለመኖር ውጤት እንደ መንፈሳዊ እውርነት እና የራስን ሃጢአት አለማስተዋል:
ለ-የመንፈሳዊ እድገት መኖር ውጤት ስራፈቶች እና ፍሬቢሶች እንዳንሆን ይረዳል::
ሐ-ወደ እ/ር መንግስት መግባት በሙላት እንዲሆንልን ይረዳል::
083_የሰው ስራ እና የእግዚአብሄር ስራ
በፓስተር ሳምሶን ስምኦን
አቤቱ ስራህን ሰርተህልናልና ሰላምን ትሰጠናለህ:: ኢሳ 26:12
ሰዎች የራሳቸውን ስራ የሚሰሩበት ጊዜ አለ እግዚአብሄር ደግሞ የራሱን ስራ የሚሰራበት ጊዜ አለ
በዘፍ 15:1 ጀምሮ ባለው ላይ የተመሰረተ ከእግዚአብሄር ቃል መልእክት
"እግዚአብሔርን ማወቅ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ቀጣይና የመጨረሻ ክፍል::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: /ለ) እግዚአብሔርን ማወቅ ራሱ ምንድን ነው? 1) የእግዚአብሔርን ህይወት መካፈል ነው መዝ. 46:10፣ ዮሐ. 4:10፣ ዮሐ. 14:27፣ 2) እግዚአብሔርን መታዘዝ ነው ኤር. 22:16 3) እውነተኛ አንድነት በቅዱሳን ኅብረት ማድረግ ነው ኤፌ. 4:13፣ 4) የህይወት ልምምድ ነው ኢዮ. 42:2-3፣ 2ጢሞ. 1:12 ሐ) እግዚአብሔርን አለመፈለግ የሚያመጣው ፍርድ ሮሜ 1:28፣ ዳን. 4:25 መ) ማጠቃለያ: ሆሴ. 6:3/
"እግዚአብሔርን ማወቅ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: መግቢያ/ኢሳ. 1:3፣ 1ሳሙ. 2:3፣ ፊል. 3:9-11፣ ኤፌ. 1:16-19/ ሀ) እግዚአብሔርን ማወቅ ለምን? የዘላለም ህይወት ነው: ዮሐ. 17:1-3፣ ለእግ/ር ህዝብ ዋና ነገር ስለሆነ: ዘዳ. 8:3፣ ሆሴዕ 6:6፣ እግዚአብሔርን ማወቅ ከስህተት ይጠብቃል: ማቴ. 22:29፣ እግዚአብሔርን ማወቅ የእግዚአብሔርን ቁጣ ያርቃል: ሆሴዕ 4:1፣ ከጥፋት ይከልላል. ሆሴዕ 4:6፣ ለ) እግዚአብሔርን ማወቅ ራሱ ምንድን ነው? ማስተዋልን ማግኘት ነው: ኢሳ. 6:1፣ ራዕ. 4:1፣ ማቴ 16:13-17፣ ሉቃ. 24:44-45/
"ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ" በሚል ርዕስ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደትን አስመልክቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል: /ሉቃ. 1:26-35/
078_ጨምሩ ክፍል 1 በወንድም ያቬሎ ናታዬ
በመንፈሳዊ ህይወት ለመጨመር መለኮታዊ ባህርይን መላበስ 2 ጴጥ 1:1-11 ላይ የተመሰረተ
0.መግቢያ መጽሃፉና መልእክቱ
1.እ/ርና የሰው መለኮታዊ ማንነት
2.የተሰጠን የመለኮት ሃይልና ተስፋ ምንድናቸው::
3.የመለኮቱ ሃይል እጅግ ታላቅና ክቡር የሆነው ተስፋ ለምን ተሰጠን::
4.የመለኮታዊ ባህርይና የመንፈሳዊ ህይወት መሰረቶች (1ኛ.የሰው ድርሻ እና 2ኛ. የእ/ር ድርሻ)
077_ለምንድነው ዘወትር መጸለይ የሚያስፈልገን
ወንድም ዶ/ር ተከለ ማርቆስ በእለቱ የቀረበ የእግዚአብሄር ቃል መልእክት: ሁልጊዜ ጸልዩ የሚለውን ቃል ላይ በመመስረት "ለምንድነው ዘወትር መጸለይ የሚያስፈልገን?" ለሚለው ምላሽ ይሆን ዘንድ በአስር ዋና ዋና ነጥቦች ከፋፍሎ የሚያስረዳ በትምህርት መልክ የቀረበ መልእክት:: ጥቅሶች በጥቂቱ . ከእ/ር ጋር ህብረት ለማድረግ መዝ 42:1,ጥበብን ለማግኘት ያእ1:5, ከክፋት ለመጠበቅ መዝ20:1,ከፍርሃት እና ከጭንቀት ለመወጣት ፊሊ 4:4, እና... መዝ 32:1,ሉቃ 22:40 ,ሮሜ10:14,ኤፌ 1:15 ሌሎችም
"ጸሎት የአምልኮ ዋና ክፍል" በሚል አሳብ ላይ ተመሥርቶ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
መልዕክቱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረውን ጸሎት መሠረት አድርጎ እኛም እንደ ክርስቶስ ተከታዮች ጸሎታችን ምላሽ ያለው እንዲሆን እንዴት መጸለይ እንደሚገባን ያስረዳል::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ማቴ. 21:22፣ 6:9-13/ሉቃ. 11:1-5/ዮሐ. 15:7/ያዕ. 4:3/ምሳ. 3:5
"የወንድሙ ጠባቂ ማን ነው? ቁምና ልብህን ፈትሽ ቅጥርህንም ጠብቅ!" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመልዕክቱ ማዕከላዊ ሐሳብ ልክ እንደ ቃየን የወንድሞቻችንን ክፋት (ሞት) የምንጠብቅ ሳንሆን ልክ እንደ ሙሴ እህት ወንድሞቻችንን ከክፋት (ከሞት) የምንጠብቅ እንድንሆንና በክርስቶስ የተሰጠንን አንድነትና ኅብረት አስበን በዓለም ውስጥ እንዳሉት የጥፋት መሣሪያ ላለመሆን ልባችንን እንድንጠብቅ ማሳሰብ ነው::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ዘፍ. 4:1-10/1ቆሮ 1:9-10/ዘጸ. 2:1-10/ምሳ. 18:19-21
"ንቁ" በሚል ርዕስ በፓስተር ሰሎሞን አምደ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመልዕክቱ ማዕከላዊ ሀሳብ ሰዎችን ከዘላለም ጥፋት ለማዳን ወንጌልን መመስከር የእያንዳንዱ አማኝ ደቀ መዝሙር ኃላፊነት መሆኑንና ለወንጌላዊያን ብቻ የሚተው ሥራ አለመሆኑን አጽንዖት ሰጥቶ መግለጽ ነው::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ማቴ. 28:18-20/ሐዋ. 1:8/ማቴ. 13:24-30
ማክሰኞ ምሽት (22.10.2019) "በውስጥህ/ሽ ወንዝ አለ!" በሚል ርዕስ በፓስተር ሰሎሞን አምዴ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመልዕክቱ ዋና ትኩረት ለኢየሱስ ክርስቶስ ህይወቱን የሰጠና መንፈስ ቅዱስን የተቀበለ ማንኛውም ሰው የሌሎችን ህይወት መለወጥ የሚችል እምቅ መንፈሳዊ አቅም (ወንዝ) በውስጡ እንዳለ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት መተንተንና ማስገንዘብ ነው::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ሕዝ. 47:1-12/ራዕ. 22:1-2/ዮሐ. 7:38
"ጌታ ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮነን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመልዕክቱም ዋና ጭብጥ "ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣት ማውቅ ለምን ያስፈልጋል?" የሚል ሲሆን 1) ተዘጋጅቶ ለመኖር 2) ከጌታ የተሰጠንን አደራ በትጋት ለመፈጸም እንዲረዳን እና 3) በህይወት ጎዳና መጽናኛችን ስለመሆኑ በመልዕክቱ በስፋት ተብራርቷል::
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች: ሐዋ 1:9-11/ ራዕይ 1:5-7፣ ራዕይ 22:12/ማቴ. 24:37-44, 45-51/ሉቃ. 12:35-40, 41-48/1 ተሰ. 4:13-18
"ጌታ እንዳስተማረን እንጸልይ!" በሚል ርዕስ በማቴ. 6:9-13 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መል ዕክት::
"የስኬታማ ጸሎት ቁልፎች" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 15:7/ መዝ. 37:4/ ማቴ. 6:33
068_በበጎ ስራና በቃል መጽናት
ዶ/ር ተከለ ማርቆስ
እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ። ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን ልባችሁን ያጽናኑት በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ ያጽኑአችሁ።2ኛ ተሰ 2:15-15 ላይ የተመሰረተ መልእክት::
067_ለአገልጋይ የተሰጠ ማበረታቻ :መመሪያ እንዲሁም ምክር
በወንጌላዊ ዘገዬ መኮነን
በ1ኛ ጢሞቲዎስ ከምእራፍ 1 እስከ ምእራፍ 6 ድረስ በአለው መልእክቱ ላይ ስለ አገልጋይ እውነተኛ ማንነት:እውነትን ስለማሳወቅ ባጠቃላይ እውነት ላይ አትኩሮት ሰጥቶ ሃዋርያው ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ በጻፈው መልእክት ላይ የተመሰረተ ነው::
066_እድል እና ምህረትን መስጠት የእ/ር ስጦታ ነው:: በእህት ለምለም ጌታቸው
"አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን ይህንን አደረገልኝ ::ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረት አገኘሁ" ሐዋ 1:13
ወደ ፊሊሞና 1:1-25 አናሲሞስ እና ሐዋ 9:1-21 ሳኦል(ጳውሎስ)
065_ዳዊትም የገባዖንን ሰዎች፦ የእግዚአብሔርን ርስት ትባርኩ ዘንድ ምን ላድርግላችሁ? ማስተስረያውስ ምንድር ነው? አላቸው። መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 21:3
በሉኪ በተደረገው የቤተ ክርስቲያን የሽርሽር ጊዜ ላይ "የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ" በሚል ርዕስ በ 1ቆሮ. 1:22-31 ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የተፈጠርንበትን መልካም ሥራ ለማድረግ "ለእግዚአብሔር መሰጠት" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) መዝ. 37:1-6 ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
መልካሙን ሥራ ለመሥራት በክርስቶስ ተፈጠርን በሚል ርዕስ በኤፌ. 2 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
"የእግዚአብሔር መልዕተኛ" በሚል ርዕስ በዮሐንስ ወንጌል ላይ በተጻፈው የመጥምቁ ዮሐንስ ህይወት (ዮሐ. 1:6) ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
"የቤተ ክርስቲያን ዋና - ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ መስበክ ነው!" በሚል ርዕስ በወንድም በፍርዱ መሠረት በ1 ተሰሎንቄ ምዕራድ 1 ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
በብርሃን በመመላለስ እንደ ብርሃን ልጆች እንኑር በሚል ርዕስ በኤፌ. 5:9-10 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት
"ሁሉንም በጌታ በኢየሱስ ስም በማድረግ እንኑር" በሚል ርዕስ በቆላስይስ 3:17 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው::
"ህይወትን ከሙታንና ዓለም ሰፈር አንፈልግ" በሚል ርዕስ በሉቃ. 24:1-35 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
"የጌታን ራት የሚካፈል ማን ነው?" በሚል ርዕስ በ1ቆሮ. 11:26-32 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
ይህ "የልብ ንጽህና" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለው ተከታታይ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት የመጨረሻው ክፍል ነው:: የዚህ ክፍል ዋና ትኩረት የልብ ንጽህና ፋይዳዎች የሚል ሲሆን ሁለት መሠረታዊ አሳቦች ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል:: 1) የልብ ንጽህና እግዚአብሔርን እንድናይ ይረዳናል:: 2) የልብ ንጽህና የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዳንስት ይረዳናል::
ይህ ትምህርት "የልብ ንጽህና" በሚል ርዕስ በማቴ. 5:8 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የሚቀበው ተከታታይ መልዕክት ሁለተኛው ክፍል ሲሆን ልብን እንዴት ንጹህ ማድረግ ይቻላል? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ክፍል ነው::
የልብ ንጽህና በሚል ርዕስ በማቴ. 5:8 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ የቀረበ ተከታታይ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል ነው::
ይህ ክፍለ ጊዜ "የልብ ንጽህና ምንድን ነው?" እና "ስለልብ ንጽህና ማሰብና መማር አስፈላጊ ነውን?" የሚሉ ጥያቄዎችን ይመልሳል::
ኢየሱስን መውደድ በሚል ርዕስ በሉቃ. 7:36-50 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት!
"አንተም እንዲሁ አድርግ" በሚል ርዕስ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ አሥር ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት በመዝሙር ምዕራፍ 73 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ማዕከላዊ አሳብ ዕይታችን በዙሪያችን ባሉ ሰዎችና ሁኔታዎች ላይ ስናደርግ ሳናውቀው ከመንፈሳዊ ከፍታችን እንንሸራተታለን ነገር ግን በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ስንሆንና እንደ እግዚአብሔር ዕይታ ነገሮችን ማየት ስንጀምር የነገሮች ሁሉ ፍጻሜ ግልጽ ይሆንልናል የሚል ነው::
"ጀግና አይታዘንለትም!" በሚል ርዕስ በሉቃ. 23:26-29 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በፓስተር ዮሴፍ ፈንታው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሲሆን የመልዕክቱ ዋና ጭብጥ ኢየሱስ ስለሰው ልጆች መከራን የተቀበለው እንዲናዝንለት ሳይሆን እንድናምንበት ነው:: ሊታዘንላቸው የተገባቸው የተደረገላቸውን ያልተረዱና ክርስቶስን ያልተቀበሉት ናቸው::
"ንጉሥ ለሚወደው እንዲህ ይደረግለታል!" በሚል ርዕስ በአስቴር ምዕራፍ 6 ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው:: የመልዕክቱ ማዕከላዊ አሳብ ንጉሥ ሲወድ በንጉሥ አቅም ልክ መሆኑን ለማስገንዘብና እኛም በእግዚአብሔር የተወደድነው ለመረዳት ከአቅም በላይ በሆነ የእግዚአብሔር ፍቅር መሆኑን ማስገንዘብ ነው::
"የእግዚአብሔር ክብር" በሚል ርዕስ በፓስተር ዮሴፍ ፈንታው በ2ኛ ዜና 7:1-10 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሲሆን በመልዕክቱም የእግዚአብሔር ክብር ሲመጣ የሚሆኑ 4 መሠረታዊ ነገሮች ተዳስሰዋል::
ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "ምርኮው ይመለሳል" በሚል ርዕስ በ1ሳሙኤል ምዕራፍ 30 ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ማዕከላዊ አሳብ "ነገራችን በጠላት ሲወሰድብንና የሚናደርገው ግራ ሲገባን 1) ልባችንን በእግዚአብሔር ማበርታት አለብን 2) ማድረግ የሚገባንን እንዲያሳውቀን እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ አለብን 3) ምርኮአችንን ለመመለስ እግዚአብሔር አድርጉ የሚለንን ማድረግ አለብን" የሚል ነው::
ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "ህዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል" በሚል ርዕስ የገና በዓልን አስመልክቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ዋና ማዕከላዊ ትኩረት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣበትን ዋና ዋና ዓላማዎች መተንተን ነው::
ይህ የእግዚአብሔር መልዕክት "ምንጭ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የካሌብ ሴት ልጅ በነበረችው በአክሳ ህይወት ላይ ተመሥርቶ የቀረበ ነው:: የመልዕክት ዋና መልዕክት ስለምንጭ አስፈላጊነት ነው [ኢያ. 15.16-19ና መሳ. 1:11-15]:: ምንጭ ለአንድ የእርሻ መሬት ፍሬያማነት አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ መንፈስ ቅዱስም በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ ላለ የእግዚአብሔር ጸጋ ፍሬያማነት እጅግ አስፍላጊ ነው::
ይህ መልዕክት "ምን አላችሁ? ምን ይዛችኋል?" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ ሲሆን የመልክቱ ማዕከል እግዚአብሔር ባልተጠበቀ ሁኔታ ወስጥ ባልተጠበቁ ሰዎች ሌሎችን መርዳት እንደምችል የሚያስረግጥ መልዕክት ነው:: ለምሳሌ: 1) አንድ ህጻን ልጅ በያዘው ዳቦና ዓሣ አምስት ሺህ ህዝብ መመገቡ 2) በሰታፕታ መንደር እፍኝ ዱቀት ብቻ በነበራት ባልተት ኤልያስን መመገቡና 3) ባዶ የሚመስል የዘይት ማድጋን ተጠቅሞ የነቢይ ሚስት የነበረችን ባልቴት ባለዕዳ ልጆቿን እንዳይወስድባት መርዳቱ::
ይህ "እግዚአብሔርን መከተል" በሚል ርዕስ በወ/ዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው:: መልዕክቱ በኦሪት ዘኁልቁ ምዕራፍ 13 ላይ የተመሠረተ ሲሆን ማዕከላዊ አሳቡም እግዚአብሔርን በመከተል ሂዴት ውስጥ ትኩረታችን መሆን ያለበት ዙሪያችን ላይ በሚታየው ላይ ሳይሆን እግዚአብሔር በሰጠን የተስፋ ቃል ላይ ነው የሚል ነው::
"የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻዎች" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የመልዕክቱ ጭብጥ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሥራ ለመሥራት የሚረዱ ቁልፎች 1) የእግዚአብሔር ቃል 2) የኢየሱስ ስም 3) ጸሎትና 4) መንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ማስገንዘብ ነው::
ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "የአካል መታነጽና መክበር" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ ነው:: የመልዕክቱም ዋና ጭብጥ እግዚአብሔር በቃሉና በመንፈሱ አማካይነት ቅዱሳንን ያንጻል የሚል ነው::
ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን እንደ አካል" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ ነው:: የመልዕክቱም ዋና ጭብጥ የአካል ብልቶች ሁሉ ለአካላቸው ህልውና መቀጠል ተግባብተውና ተሳስበው እንደሚሠሩ፣ በቤተ ክርስቲያን ያሉ አማኞችም የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ህያው ሆና ተግባሯን በሚገባ መፈጸም እንድትችል በመተሳሰብ አብረው ለአንድ ዓላማ ሊቆሙ ይገባል የሚል ነው::
ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት የመጨረሻው ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ባልንጀራችንን እንደራሳችን መውደድ ያለብን ለምንድን ነው? ባልንጀራችንስ ማን ነው? ባልንጀራችንስ እንደራስ መውደድ ይቻላል ወይ? ባልንጀራችንን እንደራስ መውደድ የሚገለጽባቸው መንገዶችስ ምን ምን ናቸው? የሚሉ ጥያቄዎችን መመለስ ነው::
ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት እግዚአብሔርን በሁለንተናችን መውደድ ያለብን ለምንድን ነው? የሰው ሁለንተናስ ምንድን ነው? እግዚአብሔርንስ በሁለንተናችን መውደድ የምንችለው እንዴት ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን መመለስ ነው::
ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት የመጀመሪያ ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት እግዚአብሔር በዘመናት መካከል ለህዝቡ የሰጣቸውን ህጎች መዳሰስ ነው:: እንደዚሁም በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ሥራ በተሻሩና ባልተሻሩ የእግዚአብሔር ህጎች መካከል መለየት ነው::
በዮሐንስ ወንጌል 21:15-19 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱ ዋና ጭብጥ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ሲታጠቅ በሥጋ ማንነቱ የሚፈራውን በመንፈስ ቅዱስ ሲታጠቅ እንደማይፈራና ለእግዚአብሔር ክብር እስከ ሞት ድረስ እደሚጨክን ያስረዳል:: በመንፈስ ቅዱስ መታጠቅ ፈሪን ደፋር ያደርጋል:: ለዚህም የጴጥሮስን ህይወት ልብ ይሏል::
"ይቅርታ" በሚል ርዕስ በሉቃ. 23:32-43 እና ማቴ 6:14-15 ባለው ክፍል ላይ የተመሠረተና በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
"ዘመኑን ማወቅ" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱ ዋና በዘመናት መካከል ህዝቡን አገሮችን እና ቤተሰቦችን በማስተዋልና በጥበብ ለመምራት እግዚአብሔር ሰዎችን እንደሚያስነሳ የሚያገነዝብ ነው:: በዘመናችንም ምልልሳችን በጥበብና በማስተዋል መሆን እንደሚገባና ጥበብንም ከእግዚአብሔር ዘንድ መጠየቅ እንደሚቻል ይመክራል::
"በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱ ዋና አሳብ የመንፈስ ቅዱስ እሳት በአማኝ ህይወት ውስጥ የሚያደርጋቸውን ለውጦች የሚያስረዳ ነው::
"የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት የመጨረሻ ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ምዕመናን መሪዎችን በመምረጥ ጉዳይ ልዩ ጥንቃቄ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው ማስገንዘብና ትክክለኛ መሪዎችን መለየት የሚችሉባቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመዘኛዎችን በተመለከተ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው::
"የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ለሰው የተሰጡ አራት የሥልጣን ደረጃዎችን መተንተንና ከሰው ሥልጣን ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ችግሮችን መጠቆም ነው::
"የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ከሰው በላይ የሆኑና የእግዚአብሔር ብቻ ስለሆኑ የሥልጣን ደረጃዎች ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው::
"ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት የተቀበልነውን የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታ መለየት የሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት ይሰጣል::
"ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ለቤተ ክርስቲያን የተሰጡ የጸጋ ሥጦታዎችን ማወቅና መለየት ነው::
"ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው::
"ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው::
"ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ቀጣይ ክፍል:: ይህ ቤተ ክርስቲያን በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው::
"እምነት" በሚል ርዕስ በዮሐ. 14:1 እና በዕብ. 11:23-27 ባለው ክፍል ላይ የተመሠረተና በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
"ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በቆላ. 1:15-23 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
ይህ መል ዕክት በዘፍ. 1:1-5 ባለው የእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረተና በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱም ማዕከላዊ ጭብጥ ምንም እንኳን ነገሮች ቅርጽ አልባ ዋጋ ቢስና ተስፋ ቢስ ቢሆኑ ሠራተኛው መንፈስ ቅዱስ ስላለ ከእግዚአብሔር ቃል ሲወጣ ሁሉም ለበጎ ይለወጣል የሚል ነው:: በጨለመው ነገራችን ላይ ሁሉንም የሚለውጠው እግዚአብሔር ብርሃንን ያዛል:: ብርሃን ሲሆን ደግሞ ልዩነት ይሆናል:: ብርሃን የሌሎች መልካም ነገሮች ሁሉ መነሻ ነው::
ይህ መልዕክት በዘፍ. 12:1-3 ላይ የተመሠረተና በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ጭብጥ "የእግዚአብሔር ጥሪ ወይም ድምጽ ሲመጣ መለየትን ያመጣል" የሚል ነው::
ይህ መልዕክት የተመሠረተው በ1ኛ ሳሙ. 2:3 ላይ ሲሆን በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ነው:: የመልዕክቱ ዋና ጭብጥ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብናልፍና ግራ ብንጋባ በፍጻሜው ይህ ሁሉ ለምን እንደሆነብን እግዚአብሔር ሊገልጽልን ይችላል:: ስለዚህ በጽናት መቆምና ማለፍ ይኖርብናል:: በህይወታችን ከሚሆኑ ከእያንዳንዱ ክስተቶች ጀርባ የእግዚአብሔር ልዑአላዊ አሳብና ፈቃድ እንዳለ መገንዘብ እንደሚኖርብን ለማስገንዘብ የቀረበ መልዕክት ነው::