የተማረ ድምጽ! Learned Voice Media!: Recent Episodes

Konso Scholars Forum

የተማረ ድምጽ በእንግሊዝኛው "Learned Voice Media" የኮንሶ ምሁራን ፎሬም ሚዲያ ሲሆን የኮንሶን ማህበረሰብ ለመለወጥ ምሁራዊ ውይይቶች፣ ትንታኔዎችና ሙግቶች የሚቀርቡበት ሚዲያ ነው::

መፈክራችን/Our motto! "የተማረ ድምጽ ለማህበረሰብ ለውጥ! Learned Voice for Social Change!"

View Details

በአሁኑ ጊዜ ኮሮና ቫይረስ የተሰኘ ተህዋስ ወይም ጀርም ከቻይና ውሃን ከተማ ተነስቶ በአለም ሁሉ በከፍተኛ ፍጥነት እየተሠራጨ ይገኛል:: በሽታው በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ደካማ የበሽታ መከላከል አቅም ያላቸውን በዕድሜ የገፉና ህጻናትን በመግደል ላይ ይገኛል:: በዚህ ፕሮግራም መምህር ያቬሎ ናታዬ ያታሣ ስለበሽታው ምንነት ስለምልክቶቹ ስለመተላለፊያ መንገዶቹና ሊደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄ በአፋ ኾንሶ ያቀርብልናል::

View Details

በአሁኑ ወቅት በኮንሶ ዞን የመንግሥት ሥልጣን ላይ ባሉ ግለሰቦች በዜጎችና በሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራርና አባላት ላይ እየደረሰ ያለን ጥቃት ወከባና እንግልት በተመለከተ ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ ይሆን ዘንድ በመምህር ታታሻ ታካዬ በአፋ ኾንሶ የቀረበ አጭር ቅኝትና ምክረ አሳብ::

View Details

በኮንሶ ዞን መጪው የመንግሥት ምርጫን በተመለከተ ለማህበረሰብ ግንዛቤ ይሆን ዘንድ በመምህር ታታሻ ታካዬ በአፋ ኾንሶ የቀረበ ትንታኔ::  ይህን መልዕክት የመስማት ዕድል ያላችሁ ዳዎንሎድ በማድረግ በማንኛውም መንገድ በማሠራጨት የማህበረሰባችንን የኑሮና የኢኮኖሚ ሁኔታ በማሻሻሉ ሂደት የበኩሎዎን እንዲወጡ በተማረ ድምጽ ሚዲያ ስም አደራ እንላለን::

መፈክራችን! "የተማረ ድምጽ ለማህበረሰብ ለውጥ!"/"Learned Voice for Societal Change!"

View Details

ከዚህ ቀጥሎ የምታደምጡት ዝግጅት በኮንሶ ምሁራን የመወያያ መድረክ የቀረበ ሲሆን "ትምህርት፣ ቴክኖሎጂና የማህበረሰብ ንቃተ ህሊና" በሚል ርዕስ የተደረጉ ውይይቶች ሁለተኛውና የውይይት ቀጣይ ክፍል የሚቀርብበት ነው:: በዚህ ክፍል "ኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂና ትምህርት" በሚል ንዑስ ርዕስ የቀረበውን ውይይት የመጨረሻ ክፍል ወደ እናንተ እናደርሳለን:: 

View Details

ከዚህ ቀጥሎ የምታደምጡት ዝግጅት በኮንሶ ምሁራን የመወያያ መድረክ የቀረበ ሲሆን "ትምህርት፣ ቴክኖሎጂና የማህበረሰብ ንቃተ ህሊና" በሚል ርዕስ የተደረጉ ውይይቶች ሁለተኛውና የውይይት ቀጣይ ክፍል የሚቀርብበት ነው:: በዚህ ክፍልና በቀጣይ ሌላ ክፍል "ኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂና ትምህርት" በሚል ንዑስ ርዕስ ውይይቶችን ወደ እናንተ እናደርሳለን:: በዚህም መሠረት ትምህርትና አይ ሲ ቲ ሁለተኛው ክፍል እነሆ:: 

View Details

ከዚህ ቀጥሎ የምታደምጡት ዝግጅት በኮንሶ ምሁራን የመወያያ መድረክ የቀረበ ሲሆን "ትምህርት፣ ቴክኖሎጂና የማህበረሰብ ንቃተ ህሊና" በሚል ርዕስ የተደረጉ ውይይቶች ሁለተኛውና የውይይት ርዕሱ የመግቢያ አሳብ የሚቀርብበት ነው:: በዚህ ክፍልና በሌሎች ቀጣይ ሁለት የፕሮግራሙ ክፍሎች "ኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂና ትምህርት" በሚል ንዑስ ርዕስ ውይይቶችን ወደ እናንተ እናደርሳለን:: በዚህም መሠረት ይህ ክፍል የውይይቱ መግቢያ አሳብ የሚቀርብበት ነው:: 

View Details

ከዚህ ቀጥሎ የምታደምጡት ዝግጅት በኮንሶ ምሁራን መወያያ መድረክ የቀረበ ሲሆን "ትምህርት፣ ቴክኖሎጂና የማህበረሰብ ንቃተ ህሊና" በሚል ዋና ርዕስ ላይ የተደረጉ ውይይቶች የመጀመሪያው አሳብ የሚቀርብበት ነው:: በዚህ ክፍልና በበቀደሙት ሁለት የፕሮግራሙ ክፍሎች "ኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂና ልማት" በሚል ንዑስ ርዕስ ውይይቶችን ወደ እናንተ እናደርሳለን:: በዚህም መሠረት ይህ ሦስተኛውና የመጨረሻው ክፍል ነው::

View Details

ከዚህ ቀጥሎ የምታደምጡት ዝግጅት በኮንሶ ምሁራን መወያያ መድረክ የቀረበ ሲሆን "ትምህርት፣ ቴክኖሎጂና የማህበረሰብ ንቃተ ህሊና" በሚል ዋና ርዕስ ላይ የተደረጉ ውይይቶች የመጀመሪያው አሳብ የሚቀርብበት ነው:: በዚህ ክፍልና በቀደመው የመጀመሪያው የፕሮግራሙ ክፍል "ኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂና ልማት" በሚል ንዑስ ርዕስ ውይይቶችን ወደ እናንተ እናደርሳለን:: በዚህም መሠረት ይህ ሁለተኛው ክፍል ነው::

View Details

ከዚህ ቀጥሎ የምታደምጡት ዝግጅት በኮንሶ ምሁራን መወያያ መድረክ የቀረበ ሲሆን "ትምህርት፣ ቴክኖሎጂና የማህበረሰብ ንቃተ ህሊና" በሚል ርዕስ የተደረጉ ውይይቶች የመጀመሪያውና የመግቢያ አሳብ የሚቀርብበት ነው:: በዚህ ክፍልና በሌሎች ቀጣይ ሁለት የፕሮግራሙ ክፍሎች "ኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂና ልማት" በሚል ንዑስ ርዕስ ውይይቶችን ወደ እናንተ እናደርሳለን:: 

View Details

ይህ ውይይት "የኮንሶ ምሁንራን የሚጠቀሟቸው ሚዲያዎች ተደራሽነታቸው ምን ይመስላል?" በሚል ርዕስ የተደረገ ውይይት ሁለተኛውና የመጨረሻው ክፍል ነው:: 

በዚህ በሁለተኛው ክፍል "የኮንሶ ምሁራንን ለመድረስ ጥቅም ላይ የዋሉ ሚዲያዎችን እንዴት የበለጠ ተደራሽ ማድረግ ይቻላል ምሁራንን ለመቀስቀስ ሌሎች አማራጮችስ አሉ ወይ?" በሚሉ ሁለት አሳቦች ዙሪያ የተደረገውን ውይይት የምናቀርብ ይሆናል:: 

View Details

ይህ ውይይት "የኮንሶ ምሁንራን የሚጠቀሟቸው ሚዲያዎች ተደራሽነታቸው ምን ይመስላል?" በሚል ርዕስ የተደረገ ውይይት የመጀመሪያ ክፍል ነው:: 

በዚህ በመጀመሪያው ክፍል "የኮንሶ ምሁራንን ለመድረስና የዚህ ራዕይ አካል ለማድረግ እስከ አሁን ጥቅም ላይ የዋሉ ሚዲያዎች ምን ያህል ተደራሽ ሆነዋል?" በሚለው አሳብ ዙሪያ የተደረገውን ውይይት የምናቀርብ ይሆናል:: 

View Details

በውይይት 1 ወቅት በመምህር ካሳሁን የቀረበ አስተያየት

View Details

ይህ የድምጽ መልዕክት ስለኮንሶ ምሁራን መድረክ አስፈላጊነት ውይይት በተደረገበት ወቅት በታደለ ኦርቡላ የቀረበ አስተያየት የሚደመጥበት ነው:: 

View Details

ይህ የድምጽ መልዕክት ስለኮንሶ ምሁራን መድረክ አስፈላጊነት ውይይት በተደረገበት ወቅት በአለሙ አ. አያኖ (ዶ/ር) የቀረበ አስተያየት የሚደመጥበት ነው::

View Details

ይህ አጭር የድምጽ ፋይል የኮንሶ ምሁራን መድረክ/Konso Scholars Forum ለማቋቋም መጀመሪያ አካባቢ የተደረጉ ውይይቶችን ለማቅረብ የተዘጋጀ መግቢያ ነው::

View Details

ይህ አጭር የድምጽ መልዕክት "የተማረ ድምጽ/Learned Voice Media" የመግቢያና የሰላምታ መልዕክት ነው::