Wazema Dossier - Wazemaradio: Recent Episodes

None

Wazema Radio

View Details

በኮልፌ ቀራንዮ የሊዝ ጨረታ ለአንድካሬ 41ሺ ብር ቀረበ ዋዜማ ራዲዮ- ትናንት ረቡዕና ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ፒያሳ ጊዮርጊስ በሚገኘው ማዘጋጃ ቤት ለመሬት በሚቀርብ ዋጋ ደምቆ ዉሏል፡፡፣ የቴአትርና ባሕል አዳራሽ ሎቢ ዉስጥ የሊዝ ጉድ መሰማት የጀመረው ገና ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ነበር፡፡ የማክሰኞና የረቡዕ ባለተራ የነበረው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ሲሆን ለሊዝ ያቀረባቸው 70 ቦታዎች ሁሉንም በዉድ […]

The post በአዲስ አበባ የመሬት ችብቻቦ ቀጥሏል appeared first on Wazemaradio.

View Details

(ይህ እስከ ጠዋቱ ሁለት ሰዓት ድረስ ያጠናቀርነው ነው፣ በከተማዋ ያለውን ሁኔታ ተከታትለን ተጨማሪ ዘገባ እንደደረስን እናቀርባለን) ዋዜማ ራዲዮ-በአዲስ አበባ  እሁድ ነሀሴ 15 (ዛሬ) ሊደረግ የታቀደውን ስልፍ ሊቀላቀሉ ይችላሉ ተብለው የተጠረጠሩ በርካታ ወጣቶች ሌሊቱን በፀጥታ ሀይሎች ሲታፈሱ አደሩ። በኮልፌ ቀራንዮ በአራዳ በቃሊቲ በልደታና በየካ ክፍለ ከተሞች በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ከቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ ከየመንገዱና ከመኖሪያ ቤታቸው ተፍሰው […]

The post ስልፍ ይወጣሉ ተብለው የተጠረጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ሌሊቱን ሲታፈሱ አደሩ appeared first on Wazemaradio.

View Details

የፈተና ወረቀቱ የተሰረቀበትን ቦታና ተሳታፊ ግለሰቦችን ለመለየት ሁለት አስቸኳይ ስብሰባዎች ተደረገዋል (ዋዜማ)-ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ በመላው ኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ የሚደግፉ አስተባባሪዎች እና አራማጆች ጉዳዩን ወደ ሌላ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እርምጃ በዛሬው ዕለት ወስደዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ተጀምሮ የነበረው እና ለቀጣዮቹ ሶስት ቀናት እንዲካሄድ መርሃ ግብር ወጥቶለት የነበረውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲቋረጥ ማድረግ ችለዋል፡፡ […]

The post “ፈተናዎቹን በእጃችን ያስገባነው ከሶስት ሳምንት በፊት ነበር” የኦሮሞ ተቃውሞ አስተባባሪዎች appeared first on Wazemaradio.

View Details

ከመካከለኛው ምስራቅና ከአፍሪካ ያለገደብ የሚፈሰው የስደተኛ ጎርፍ ያሳሰባቸው የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ችግሩን ለመፍታት ተገቢ ያልኾኑ ርምጃዎችንም ጭምር እየወሰዱ እንደኾነ እየተገለጸ ነው። ዓለም ካወገዛቸው አምባገነን መሪዎችና ጨቋኝ መንግስታት ጋር ምስጢራዊ ስምምነቶች መደረጋቸውም እየተጋለጠ ነው። መዝገቡ ሀይሉ በጉዳዩ ዙሪያ ያዘጋጀውን የድምፅ ዘገባ እዚህ ያድምጡ አልያም ንባብዎን ይቀጥሉ በአብዛኛው ሶርያን ከመሰሉ የጦርነት አውድማ ከኾኑና እስካሁንም ያለፈባቸው የጦርነት መገረን […]

The post አውሮፓና የአፍሪቃ አምባገነን መሪዎች በሰደተኞች ጉዳይ ላይ የምስጢር ስምምነት ማድረጋቸው ተጋለጠ appeared first on Wazemaradio.

View Details

ጌታው እንዴት ሰንብተዋል? ኤርሚያስን ያውቁታል? ይበሉ ይተዋወቁት! ሁነኛ ወዳጄ ነው፡፡ የአገሬ ሀብታሞች ከብዙ ብር ሌላ ምን አላቸው ይበሉኝ፡፡ ብዙ በሽታ! ብዙ ስኳር፣ ብዙ ደም ግፊት፣ ብዙ ሪህ…ብዙ ጭንቀት፡፡ ኤርመያስ ከብዙ ብር ሌላ ምን አለው ብለው ይጠይቁኝ፡፡ ኤርሜያስ ከብዙ ብር ሌላ ብዙ ዕውቀት፣ ብዙ ሕልም፣ ብዙ እቅድ፣ ብዙ ቅዠት…፡፡ የአገሬ ሐብታም ቁርጥ ካላንቆራጠጠው ሀብታም የሆነ አይመስለውም፡፡ […]

The post የፊንፊኔ ደላላ- የኤርምያስ ወድቆ መነሳትና ህልም appeared first on Wazemaradio.

View Details

ዋዜማ ራዲዮ- በአያት ፀበል ኮንዶሚንየም አቅራቢያ የሚገኘውን ሰፊ ገላጣ መሬት የአዲስ አበባ መስተዳደር በሊዝ ለባለሀብቶች ካስተላለፈ በኋላ ላለፉት አስራ ሁለት ወራት ባለሀብቶች ቦታውን መረከብ አልቻሉም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ መሬቱን ለዓመታት ሲያርሱ የኖሩት ገበሬዎች መሬታችንን አናስነካም በማለታቸው ነው፡፡ በ15ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ ተሸንሽነው ለባለሀብቶች የቀረቡት መሬቶች ብዛት ከአንድ መቶ ሀምሳ በላይ ሲሆኑ አሁን ችግሩ የተፈጠረበት አካባቢ የሚገኙት […]

The post የአያት ገበሬዎች ከባለሀብቶች ጋር ተፋጠዋል appeared first on Wazemaradio.

View Details

ለመሆኑ የኢትዮዽያውያን ተመራጭ የአማርኛ ቋንቋ መገናኛ ብዙሀን ማን ነው? ለምን? ይህ የህዝብ አስተያየት ነው። በሳይንሳዊ ዘዴ የተደገፈ ጥናት ባይሆንም የህዝቡን የልብ ትርታ ያሳያል። ዋዜማ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ታዳሚዎች ጋር ያደረገችው ቆይታ እንዲህ ተሰናድቷል። አድምጡት

The post ህዝቡ ምን ይላል? ለመሆኑ የኢትዮዽያውያን ተመራጭ የአማርኛ ቋንቋ መገናኛ ብዙሀን ማን ነው? appeared first on Wazemaradio.

View Details

(ዋዜማ)-የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ያለው ድርቅ ክፉኛ ያሳሰበው ይመስላል። ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ባለስልጣኖችን በአጭር ጊዜ ልዩነት እየላከ የጉዳቱን መጠን በአካል እንዲመለከቱ እና ሁኔታውን እንዲያጠኑ እያደረገ ይገኛል። ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያን ከጎበኙት ኮንግረስማን ማይክል ኮንዌይ ተከትሎ የአሜሪካን የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስ ኤይድ—USAID) ምክትል ኃላፊ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘዋል ። በዩኤስ ኤይድ የዲሞክራሲ፣ ግጭት እና ሰብዓዊ እርዳታ ቢሮ ረዳት አስተዳዳሪ የሆኑት […]

The post የዋዜማ ጠብታ- አሜሪካ የኢትዮዽያ ረሀብ አሳስቧታል- ተጨማሪ ዕርዳታ ልትሰጥ ነው appeared first on Wazemaradio.

View Details

(ዋዜማ ራዲዮ) የኬንያ መንግስት ወደ 11ሺህ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበትን ዳዳብ ካምፕ እስከሚቀጥለው ዓመት ጥር ድረስ ሙሉ ለሙሉ እንደሚዘጋ አስታወቀ። ለዳዳብ ካምፕ መዘጋት መንስኤ ነው የተባለው የፀጥታ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ነው። በናይሮቢ “ዌስት ጌት” የገበያ ማዕከል የደረሰውን ጥቃት ጨምሮ በኬንያ ላይ ያነጣጠሩ የሽብር ድርጊቶች “የሚጠነሰሱት” እና “የሚቀናበሩት” በስደተኛ ካምፖች እንደሆነ የሀገሪቱ መንግስት ይገልጻል። ለዚህም እማኝ የሚያደርገው “አሉኝ” […]

The post በኬን ያ 11 ሺ ኢትዮጵያውያን አደጋ አንዣቦባቸዋል appeared first on Wazemaradio.

View Details

(ዋዜማ ራዲዮ)- የኢትዮጵያን ቡና በዋነኛነት ይሸምታሉ ከሚባሉ ሀገራት መካከል አንዷ በሆነችው ጃፓን የቡና መጠጣት ባህል ባለፉት 40 ዓመታት በከፍተኛ ደረጃ እንዳደገ ይነገራል፡፡ “የሻይ አፍቃሪዎችናቸው” የሚባሉት ጃፓናውያን አሁን አሁን በሳምንት በነፍስ ወከፍ እስከ 11 ኩባያ ቡና የሚያጣጥሙ ሆነዋል፡፡ በጥራት ላይ ድርድር የማያውቁት ጃፓናውያን ከኢትዮጵያ በሚገዙት ቡና ላይቅሬታ ማቅረብ ከጀመሩ ሰነበቱ፡፡   ቻላቸው ታደሰ ቡና የገባበትን አለም […]

The post ቡናችን ድንግዝግዝ ውስጥ ገብቷል! appeared first on Wazemaradio.