VOA Amharic: Recent Episodes

VOA Amharic

Broadcasting to the Horn of Africa region since September 1982.

View Details

ኢትዮጵያዊው አትሌት ሙሌ ዋሲሁን በባርሴሎናው የጎዳና ሩጫ ውድድር የኮርሱን ሪኮርድ በማሻሻል ድል ተቀዳጅቷል።

View Details

በኦሮምያ ከተሞች ትናንት የተጀመረው የግብይት ዕቀባና ሥራ የማቆም አድማ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን የተለያዩ ምንጮች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

View Details

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

View Details

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌንና አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ከእስር ለመፈታት የግንቦት ሰባት አባል መሆናቸውን አምነው የይቅርታ ፎርም ላይ እንዲፈርሙ መጠየቃቸውንና ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። የአቶ ክንፈሚካኤል ደበበ እናት ወ/ሮ ብዕዓት ኃይለጊዮርጊስ፤ "እኛም ቤተሰቦቹ ሆነ እርሱ ብዙ መሰዋትነት ከፍለናል። ስለዚህ ይቅርታ ባለመጠየቃቸው በጣም ደስ ብሎኛል።" ብለዋል።

View Details

አቶ ጉርሜሳ አያኖን ጨምሮ የአራቱ የኦፌኮ አመራር አባላት እና ሌሎች ተከሳሾች ክስ እንዲቋረጥ መወሰኑን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

View Details

ከመንግሥት ሰራተኞችና ከሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች እያገኙት ያለው ድጋፍ የሕዝቡ ትግል አንድ እርምጃ ወደ ፊት መሄዱን እንደሚያሳይ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ተናግረዋል፡፡

View Details

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

View Details

በባሌ ዞን በመዳ ወላቡ ወረዳ "መዳ" በተባለች ቀበሌ የገበያ ቦታ ላይ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በተፈጠረ ግጭት የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ከሟቾቹ ውስጥም አንዲት የስምንት ልጆች እና አንዲት የሰባት ልጆች እናት ወተት በመሸጥ ላይ እያሉ በመከላከያ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

View Details

ፓርቲያቸው ከኦሮሚያ ገዥ ኦህዴድ ለመነጋገር መወሰኑን ዶ/ር መረራ ጉዲና አስታወቁ፡፡

View Details

በኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባርና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ለሦስት ቀናት ይቆያል የተባለ ውይይት ትናንት ዕሁድ ተጀምሯል። በኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና በኦብነግ መካከል ንግግሩ የተጀመረው ተለይቶ ባልተገለፀ የኬንያ ከተማ ነው።